ዳግም የሀገራችንን ስም በዓለም ከፍ ያደሩጉት ወጣቶች !

ላለፉት 6 ተከታታይ ቀናት በኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሲካሄድ ሰንብቷል።

በዚችም ሀገራችን በ19 አትሌቶች በሁለቱም ፆታ በ10 የውድድር ተግባራት ብቻ ተሳትፋለች።

የአትሌቲክስ ቡድናችን በሻምፒዮናው ፦

🥇6 ወርቅ፣
🥈5 ብር
🥉1 ነሃስ በድምሩ በ12 ሜዳልያዎች በማግኘት ከዓለም ሃገራት አሜሪካንን እና ጃማይካን በመከተል 3ኛ ደረጃን ይዘን አጠናቀናል።

የተመዘገበው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪካችን ዘንድሮ #ከፍተኛው ውጤት ነው።

ከተሳተፍንበት ውስን የውድድር ተግባራት አንፃር እጅግ የሚያኮራ ውጤት ነው።

ሜዳሊያ ያስመዘገቡ የነገዎቹ የሀገር ተስፋዎች እነማን ናቸው ?

#ወርቅ

🥇ኤርሚያስ ግርማ (800 ሜትር)
🥇መልክነህ አዘዘ (3000 ሜትር)
🥇አዲሱ ይሁኔ (5000 ሜትር)
🥇ሳሙኤል ዱጉና (3000 ሜትር መሰናክል)
🥇 ብርቄ ሀየሎም (1500 ሜትር)
🥇መዲና ኢሳ (5000 ሜትር)

#ብር

🥈ኤርሚያስ ግርማ (1500 ሜትር)
🥈ሳሙኤል ፍሬው (3000 ሜትር መሰናክል)
🥈ፅዮን አበበ (3000 ሜትር)
🥈መልክናት ውዱ (5000 ሜትር)
🥈ሲምቦ አለማየሁ (3000 ሜትር መሰናክል)

#ብር

🥉መሰረት የሻነህ (3000 ሜትር መሰናክል)

እንኳን ደስ አለን አላችሁ !

ይቀላቀሉ : @tikvahethsport
https: //publielectoral.lat/s/+VvwzStMNcNHmhK0x

@tikvahethiopia