TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢሬቻ 2011/2018⬇️

የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ #ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልክእት አስተላለፉ።

ርእሰ መስተዳድር አቶ #ለማ_መገርሳ በመልክታቸው፥ በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ስፍራ ለሚሰጠው የኢሬቻ በዓል እንኳን አደረሳችሁ ብለዋል።

ዘንድሮ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል በተቀናጀ እና አስገራሚ በሆነ መልኩ እንዲከበር ሁሉም የህብረተሰብ አካላት የበኩሉን እንዲወጣም ጥሪ አስተላልፈዋል።

አባ ገዳዎች፣ ወጣቶች እና ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሙሉ ባህልን በሚያፅባርቅ መልኩ የኢሬቻን በዓል አንዲያከብሩም ጠይቀዋል።

የ2010 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በተቀናጀ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ የተከበረ መሆኑን ያስታወሱት አቶ ለማ፥ የዘንድሮውም ከአምናው በተሻለ መልኩ ሰላማዊ እና ባህላችንን ለዓለም በምናስተዋውቅበት መልኩ ሊከበር ይገባል ብለዋል።

የኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት ነፀብራቅ በመሆኑ ልክ እንደ ገዳ ስርዓት ሁሉ የኢሬቻ በዓልንም በዩኔስኮ በዓለም ቅርሰነት ለማስመዝገብ እየተሰራ መሆኑን አቶ ለማ አንስተዋል።

ስለዚህ በዓሉን ለማክበር ወደ ስፍራው የሚሄዱ በሙሉ ከፖለቲካ ፓርቲ አርማ፣ ባንዲራ እና ዘፈኖች ራሳቸውን እንዲቆጥቡም ጠይቀዋል።

የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲጠናቀቅ መንግስት ከአባ ገዳዎች ህብረት እና ከወጣቶች ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑንም ርእሰ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ አንስተዋል።

ከጤና ጋር ተያይዞ ችግር ካጋጠመም የጤና ባለሙያዎች ከወዲሁ ዝግጅት እያደረጉ መሆኑን መግለፃቸውን ከኦሮሚያ ክለል የመንግሰት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

©fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2011

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ #ለኢሬቻ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኦሮሞ ህዝቦች እንኳን በፍቅርና #በአንድነት ለሚከበር የኢሬቻ በዓል አደረሳችሁ፤ አደረሰን ብለዋል፡፡

ኢሬቻ የገዳ ስርዓት አካልና የምስጋና የሰላም ቀን ነው፣ የኦሮሞ ምኞት ፍቅር፣ ብልጽግና፣ ባህሉ ደግሞ አብሮነት ነው፤ ኦሮሞ ለምለም ይዞ ለፈጣሪ #ምስጋና ያቀርባል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

የኦሮሞ ህዝብ የሚተዳደርበት #የገዳ ስርዓት ለዘመናዊ ዴሞክራሲ መሰረት የሆነና ታናሽ ታላቅን አክብሮ ከተላቅ የሚመር፣ ታላቅ ደግሞ ታናሽን በማብቃት ስርዓትን የሚያስቀጥል ስርዓት መሆንም ዶ/ር ዐቢይ ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮን የኢሬቻ በትግል የተገኘውን ለውጥ የሚናስቀጥልበት፣ በፍቅር፣ በአንድነትና በእኩልነት አገር የሚንመራበትና የገዳ ልምዶችን የሚንቀስምበት ጊዜ በመሆኑ ደስታችንን ድርብ ያደርገዋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ዐቢይ የዘንድሮ ኢሬቻ ባህላችንንና አንድነታችንን የምናጠናክርበት፣ የአባገዳዎች መልዕክት #የምንሰማበትና የምንተገብርበት ይሆናል የሚል ተስፋም አለን ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል በፖለቲካ አለላካከት #ልዩነቶቻቸን ሳይገድቡን በፍቅርና በአንድነት አብሮ ለመስራት የሚንመራረቅበት እንደሚሆን ተስፋ እንዳላቸውም ገልጸዋል፡፡

አሸናፊ ሀሳብ በመያዝ አንድነታችንን አጠንክረን፣ ለሰላም፣ የሕግ የበላይነትን ለማስከበር፣ ለፌዴራሊዝምና ለዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ አብረን መስራት አለብን ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

ሰላማችንን ማስጠበቅ በእጃችን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ሰላማችንንና ባህላቸን በመጠበቅና በማስጠበቅ አገርን መገንባት አለብን፤ በኢሬቻ በዓል ላይ ሰላማችንን በማስጠበቅ ለዓለም ምሳሌ መሆን አለብንም ብለዋል፡፡

ዘመኑ በፍቅርን አቅፈን ጥላቻን የምናሸንፍበት ዘመን እንዲሆንልን እመኛለሁ ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia