TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
 
#USAID #OCHA

በትግራይ የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች ችግር ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመድረስ በሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች ላይ የሚገጥማቸው መሰናክል ተባብሷል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ (OCHA) አሳስቧል።

አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልገው 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ወዲህ ለመድረስ የተቻለው 1.8 ሚሊዮኑን ብቻ ነው ብሏል።

በክልሉ አሁን ካለው የከፋ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እንዳይከሰት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኦቻ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ እስከዚህ የአውሮፓ 2021 ማብቂያ ድረስ በቂ እርዳታ ለማቅረብ 853 ሚሊዮን ዶላር እስከፊታችን ሃምሌ መጨረሻ ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

በሌላ መረጃ ፦ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ወይም USAID/ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር የትግራይ ግጭት እጅግ የከበደ ረሃብ እያስከተለ እንደሆነ እና ከ5 ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን አሳስበዋል።

ሳምንታ ፓዎር "የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቅኝታችን አጣዳፊ የምግብ ችግር መኖሩን ይጠቁማል" ያሉ ሲሆን ችግሩ እጅግ አስከፊው ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

የኢትዮጲያ መንግሥት ግጭቱን ለማቆም እንዲሁም የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች የተቸገረውን ህዝብ ለመድረስ እንዲችሉ አሁኑኑ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ ገልፀዋል። #VOA

@tikvahethiopia
"... እስራኤል ራሷን ከጥቃት መከላከል መብቷ ነው " - አንቶኒ ብሊንከን

የኤሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እስራኤል እና ሃማስ ባለፈው ሳምንት ያደረጉትን የተኩስ አቁም ሥምምነት ለማጎልበት ወደመካከለኛው ምስራቅ ይገኛሉ።

ትላንት ማክሰኞ በእየሩሳሌም ጉብኝታቸው፣ እስራኤል ራሷን ከጥቃት መከላከል መብቷ መሆኑን አጥብቀው ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ብሊንከን ከእስራኤል ጠ/ሚር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ሆነው በሰጡት መግለጫ በውጊያው እስራኤልም ፍልስጥኤማውያንም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ለመጻኢው ጊዜ ተስፋ፣ መከባበር እና መተማመንን ለማስፈን ብዙ ሥራ መሰራት ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል።

ሰው ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ብዙውን ጊዜ በቁጥር ደረጃ ዝቅ ተደርገው የሚገለጹ ቢሆንም በእያንዳንዷ ቁጥር የሚገለጸው አባት፣ እናት፣ ልጅ፣ አያት፣ ጓደኛ ሰብዓዊ ፍጡር ነው።

ጥንታዊው የአይሁድ ሃይማኖታዊ ህግ እንደሚያስተምረውም፣ ህይወት ሲጠፋ የእስራኤላዊም ይሁን የፍልሥዔማዊ ህይወት መጥፋት ከመላው ዓለም መጥፋት የሚቆጠር ነው ብለዋል።

አሜሪካ ሃማስ በማይጠቀምበት መንገድ ጋዛን መልሶ ለመገንባት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ ትሰራለች ሲሉም ተደምጠዋል።

ብሊንከን ፥ በጋዛ እና በዌስት ባንክ ለሚኖሩ ፍልስጤማውያን የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለማጎልበት እንሰራለን ሲሉ ቃል የገቡንሲሆን እስራኤልንም ፍልስጥኤሞችንም የሚጠቅም የተረጋጋ ድባብ ሊያመጣ ይችላል ብለዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጤም ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስ እና ከጠ/ሚ ማሃማድ ሲታዬህ ጋር በራማላህ ተገናኝተው አሜሪካ የምታሰጠውን እርዳታ ይፋ አድርገዋል። #VOA

@tikvahethiopia
#Tigray

በአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ቤት የቨርሞንት ክፍለ ሃገር ሴኔተር ፓትሪክ ሌሂ በትግራይ ጉዳይ መግለጫ አውጥተዋል።

መግለጫው ሲጀምር "በ1984 እአአ በኢትዮጵያ በተራዘመ ድርቅ ሳቢያ በስፋት በተከሰተው የምግብ እጥረትና በመንግሥት አድላዊ ፖሊሲዎች የተነሳ የደረሰውን ከባድ ረሃብ በዚያም ምክንያት ብዙዎቹ የትግራይ ተወላጆች የሆኑ ሰውነታቸው በረሃብ ያለቀ ፤ 1 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የተሰደዱበትን የሚዘገንን ቸነፈር በደንብ አስታውሰዋለሁ"

ቆይቶ ዝናብ መጣል ጀመረ። ስደተኞቹም ወደቀያቸው ተመለሱ። ይሁን እንጂ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ሃገሪቱ በየጊዜው ግጭት እና የበቂ ምግብ ዕጦት ተለይቷት አያውቅም ሲሉም የዩናይትድ ስቴትሱ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት አባል አክለዋል።

ዛሬ የትግራይ ህዝብ ዘግናኝ በሆነ ደረጃ ጭካኔ የተመላበት የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥቃት እየተፈጸመበት ነው ያሉት ሴኔተር ሌሂ ህዝቡ በአጣዳፊነት የሚያስፈልገው የምግብ እርዳታ እንዳይደርሰው የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ወታደራዊ ኃይሎች እንዲሁም ሌሎች ታጣቂ ቡድኖች እየከለከሉ ናቸው" ብለዋል።

“የአሜሪካ እና ሌሎችም ከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ያደረጉ ቢሆንም የግጭቱ ተሳታፊ ወገኖች ግጭቱን አቁመው ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ የወሰዱት አንዳችም ትርጉም ያለው እርምጃ የለም" ሲሉ አክለዋል።

"ትግራይ ውስጥ የሚፈጸሙትን ግድያዎች፣ በግዴታ ከቀዬ ማፈናቀል፣ ወሲባዊ ጥቃቶች እና ሌሎችም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንዲሁም በውሃ አቅርቦት ስፍራዎችና በሆስፒታሎችና በመሰል የጤና ማዕከሎች ላይ የሚደርሰውን ውድመት የአሜሪካ መንግሥት አውግዟል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tigray-06-07 #VOA

@tikvahethiopia
ባለፉት ቀናት በሱዳን ጉብኝት ያደረጉት የUSAID ኃላፊ ሳማንታ ፖውር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ፖወር ወደኢትዮጵያ መግባታቸው በይፋ በሚዲያ ሳይታወቅ እና እሳቸው ሆነ ተቋማቸው ሳያሳውቁ ነው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው መግለጫ የሰጡት።

ለመሆኑ በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- ከሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና ከዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

- በትግራይ ክልል ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ የሰላም አማራጮች መታየት እንዳለባቸው ፣ ግጭት መቆም እንዳለበት ፣ ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ድርድር መምጣት እንዳለባቸው ከሰላም ሚኒስትር ጋር መነጋገራቸውን ገልፀዋል።

- የትግራይ ያለው የውጥ ግጭት ሊፈታ የሚችለው በሰላማዊ አማራጭ ብቻ መሆን እንዳለበት መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

- የአሜሪካ መንግስት ይሁን ሌሎች አካላት የሚሰጡት መገልጿቸው ሃሳቦች መፍትሄ ከማፈላለግ ሃሳብ ጋር የተያያዙ ናቸው ብለዋል።

- ለውጣዊ ግጭት ወታደራዊ አማራጭ መፍትሄ እንደማይሆን፣ ሁሉም አካላት ግጭቱን አስቸኳይ አቁመው ውይይት መጀመር እንዳለባቸው ተናግረዋል።

- ግጭቱ እየሰፋ መሄዱን ተናግረው ሰላማዊ መፍትሄ ካልተበጀለት ይበልጥ እየተስፋፋ በርካታ ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

- በአፋር እና አማራ ክልል ህወሃት በፈፀመው ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው አንስተዋል።

- ዓለም አቀፍ ህጎች መከበር እንዳለባቸው፣ ንፁሃን ለአላስፈላጊ ጉዳት መዳረግ እንደሌለባቸው ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኞች ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

- ከሰሞኑ የአሜሪካ መንግስት ይፋ ካደረገው 149 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት 45 ሚሊዮን ተጨማሪ በጀት ለኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ለኢትዮጵያ ይፋ አድርገዋል።

#VOA

@tikvahethiopia