ባለፉት ቀናት በሱዳን ጉብኝት ያደረጉት የUSAID ኃላፊ ሳማንታ ፖውር ኢትዮጵያ ይገኛሉ።

ፖወር ወደኢትዮጵያ መግባታቸው በይፋ በሚዲያ ሳይታወቅ እና እሳቸው ሆነ ተቋማቸው ሳያሳውቁ ነው ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነው መግለጫ የሰጡት።

ለመሆኑ በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- ከሰላም ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እና ከዶ/ር ሊያ ታደሰ ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

- በትግራይ ክልል ካለው ግጭት ጋር በተያያዘ የሰላም አማራጮች መታየት እንዳለባቸው ፣ ግጭት መቆም እንዳለበት ፣ ሁሉም ተፋላሚ ኃይሎች ወደ ድርድር መምጣት እንዳለባቸው ከሰላም ሚኒስትር ጋር መነጋገራቸውን ገልፀዋል።

- የትግራይ ያለው የውጥ ግጭት ሊፈታ የሚችለው በሰላማዊ አማራጭ ብቻ መሆን እንዳለበት መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

- የአሜሪካ መንግስት ይሁን ሌሎች አካላት የሚሰጡት መገልጿቸው ሃሳቦች መፍትሄ ከማፈላለግ ሃሳብ ጋር የተያያዙ ናቸው ብለዋል።

- ለውጣዊ ግጭት ወታደራዊ አማራጭ መፍትሄ እንደማይሆን፣ ሁሉም አካላት ግጭቱን አስቸኳይ አቁመው ውይይት መጀመር እንዳለባቸው ተናግረዋል።

- ግጭቱ እየሰፋ መሄዱን ተናግረው ሰላማዊ መፍትሄ ካልተበጀለት ይበልጥ እየተስፋፋ በርካታ ሰዎች ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

- በአፋር እና አማራ ክልል ህወሃት በፈፀመው ጥቃት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸው አንስተዋል።

- ዓለም አቀፍ ህጎች መከበር እንዳለባቸው፣ ንፁሃን ለአላስፈላጊ ጉዳት መዳረግ እንደሌለባቸው ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኞች ጥበቃ ሊደረግላቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።

- ከሰሞኑ የአሜሪካ መንግስት ይፋ ካደረገው 149 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ድጋፍ በተጨማሪ በዛሬው ዕለት 45 ሚሊዮን ተጨማሪ በጀት ለኮቪድ ወረርሽኝ ለመከላከል ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ለኢትዮጵያ ይፋ አድርገዋል።

#VOA

@tikvahethiopia