TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ህወሓት ስለኢህአዴግ መፍረስ...

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ለሁለት ቀን ያካሄደውን ጉባኤ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ኢህአዴግን "ተዋሐደ" ሳይሆን "በክህደት ፈረሰ" ብሎታል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ዘመቻ...

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን (ሞዴስ፣ ፓንት..ወዘተ) የማሰባሰብ ዘመቻ በይፋ ጀምሯል፡፡ በዚህ በመክፈቻ ሰነ-ሥርዓት ላይ ከክፍለ ከተሞች 55,000 እንዲሁም ዛሬ ተካሄዶ በነበረው የማስ ስፓርት ላይ ከተሳተፉ የስፓርት ቤተሰቦች 100,000 ሞዴስ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡

በ አዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ አቅም ለማይፈቅድላቸው ተማሪዎች በዘንድሮ አመት ሙሉ ለሙሉ የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ለማዳረስ ለታቀደው እቅድ ወደ 700,000 የሚጠጋ ሞዴስ ያስፈልጋልም ነው የተባለው፡፡

More👇
https://telegra.ph/TIKVAH-01-05

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፍሬወይኒ መብርሃቱ... ታህሳስ 28 በሚሊየም አዳራሻ ሊደረግ የነበረው የ2019 የCNN የዓመቱ ጀግና ፍሬወይኒ መብርሃቱ የክብር አቀባበል እና የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ ስነ ስርዓት የቀን እና የቦታ ለውጥ ተድርጎ ዛሬ በኤሊያና ሆቴል እጅግ በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል። ቆይት ብለን ዝርዝር መረጃዎችን እንሰጣችኃለን! PHOTO : TIKVAH-ETH @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፍሬወይኒ መብሃቱ የክብር አቀባበል...

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በCNN በ2019 የአመቱ ጀግና ተብላ ለተመረጠችውን ፍሬወይኒ መብራሃቶም ደማቅ አቀባበል አድረጎላታል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዕድር መሪዎች የመንግስት ኃላፊዎች፣ የካቢኔ አባላትና የመነን አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የማህበረሰባቸውን ችግር ተመልክተው መፍትሔ በመስጠታቸውና በርካታ ሴት ታዳጊዎችን ችግር በመፍታታቸው ከተማ አስተዳደሩ የሁላችንም ጀግና ነሽ በማለት ለፍሬወይኒ መብርሃቶም የካባ ሽልማት ያበረከተላት ሲሆን በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ስም የምስጋና ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዝግጅቱ እንደተጠቀሰው ጀግናዋ ፍሬወይኒ የጀመረችውን ሥራ ከዘንዶሮ አመት ጀምሮ በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የከተማዋን ነዋሪዎች በማስተባበር እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለማዳረስ ያቀደ ሲሆን ይህ ተግባር ሙሉ ለሙሉ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ የሚከወን ይሆናልም ተብሏል፡፡

የአመቱ የCNN ጀግና ፍሬወይኒ መብራቶም በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና ሁሉ ከተማ አስተዳደሩንና ህዝቡን ያመሰገኑ ሲሆን ይህንን ተግባር ወደፊት እንቀጥላለን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ለዝግጅቱ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት የጀግኒት ቤተሰብ አባላት በተለይም ለአርቲስት ጸደኒያ ገብረማርቆስና ቤቲ ጂ ከዛም በተጨማሪ በከተማዋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በስፋት እየተሳተፈ ለሚገኘው ለአርቲስት ያሬድ ሹመቴና ለአርቲስት መሀመድ ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል፡፡

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቲክቫህ ቤተሰቦች ስም...

በፍሬወይኒ መብርቶም የክብር አቀባበል ላይ ተገኝተን በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በተለይም የቤተሰባችን አባላት በሆኑ ወጣቶች ስም በገንዘብ ሲተመን 5,000 ብር የሚያወጣ ሞዴስ እገዛ አድርገናል። እገዛችን በጣም ትንሽ እንደሆነች ብናውቅም ለሌሎች ወጣቶች መነሳሳትን ለመፍጠር ያህል ነው።

- የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በተለያዩ በጎ ስራዎች ላይ ስንሳተፍ ለበርካቶች ማህበራዊ ሚዲያን ለመልካም ስራም መጠቀም እንደምንችል ለማስታወስ ያህል ነው!!

- በያላችሁበት ከግንዛቤ ጀምሮ እስከ ቁሳቁስ የምታበረክቱት አስተዋጽኦ የብዙዎችን ህይወት ይለውጣል ብለን እናምናለን፡፡

- በመላው ቤተሰቦቻችን ስም ለ2019 የCNN ጀግና ፍሬወይኒ መብርሃቱ በድጋሚ እንኳን ደስ አለሽ፤ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን!

በነገራችን ላይ...

UNESCO (ዩኔስኮ) ባጠናው ጥናት መሰረት በሀገራችን 75% የሚሆኑ ሴቶች በቂ ንጽህና መጠበቂያ አያገኙም 50% የሚሆኑ ተማሪዎች በዚሁ የተነሳ ከትምህርት ገበታቸው ይስተጓጎላሉ፡፡

ስለ ሴቶች የወር አበባ አሁንም ድረስ ማህበረሰባችን ካለው አመለካከት ላይ የኢኮኖሚ ጫናው ተደምሮ ለበርካታ ሴት እህቶቻችን ከትምህርት መስተጓጎል እስከማቋረጥ ምክንያት ሆኗል፡፡

እናተም በየክፍለ ከተማው በመገኘት አግዙ!

እያንዳንዳችን ለውጥ ማምጣት እንችላለን!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ዶ/ር አብይ አህመድ ያቤሎ ከተማ ገብተዋል...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቤሎ ሲደርሱ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በቆይታቸውም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

(EBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
99 በመቶ የሚሆነው ተማሪ የመማር ፍላጎት አለው...

- በ170 ተማሪዎች ላይ የአንድ ዓመት ቅጣትና እስከ መጨረሻው ከዩኒቨርሲቲዎች የማባረር እርምጃ ተወስዷል

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል እንዲሁም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች እየተከሰተ ያለውን ረብሻ ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራን ለማከናወን ለመላው የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ለወላጆች ጥሪ ቀርቧል፡፡

170 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች የረብሻ ድርጊት ላይ በመሳተፋቸው ለአንድ ዓመት በትምህርት ገበታ ላይ እንዳይሳተፉ ከመቅጣት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ከዩኒቨርሲቲዎች የማባረር እርምጃ መወሰዱም ተጠቁሟል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ትናንት መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ድኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እንደተናገሩት፤ 99 በመቶ የሚሆነው ተማሪ የመማር ፍላጎት አለው ብለዋል።

(EPA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአውስትራሊያ ዝናብ ጥሏል...

በሰደድ እሳት ነበልባል በነደደችው አውስትራሊያ ዝናብ መጣሉ ነዋሪዎችን አስፈንጥዟል፡፡ አውስትራሊያ ሰሞኑን በከባድ የሰደድ እሳት እየታመሰች ትገኛለች፡፡

የሀገሪቱ መንግስት እሳቱን ለመቆጣጠር ዘመናዊ የእሳት ማጥፍያ መሳርያዎችን ቢጠቀምም እስካሁን ድረስ እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ግን አልቻለም፡፡ በሰደድ እሳቱ ሳብያም ከ5 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን በርካቶችን ለስደት ዳርጓቸዋል፡፡

ዛሬ ላይ ከወደ አውስትራሊያ የተሰማው ወሬ ዜጎችን እረፍት የሰጠ ነገር ሆኗል፡፡ በሀገሪቱ ባንዳንድ ከተሞች በዋናነትም በሲድኒ እና በሜልቦርን ዝናብ በመጣሉ ምክንያት የሙቀት መጠኑም እንደቀነሰ ነው የተነገረው፡፡

ዝናብ መጣሉን ተከትሎ የሀገሪቱ ዜጎች ደስታቸውን ሲገልጹ ተስተውሏል፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ግን ሰደድ እሳቱ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያልተቻለ በመሆኑ አሁንም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሰስቧል፡፡ በሀገሪቱ ዝናብ ከጣለ በኃላም ምንም አይነት የእሳት አደጋ የማስጠንቀቂያ ድምጽ እንዳልተሰማ ነው ቢቢሲ ያተተው፡፡

(ምንጭ፦ ቢቢሲ -በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ ምርቶች...

ሰባት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በባዛሮች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ ምርቶችን ሲሸጡ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስምንት ዓይነት ያህል የባህላዊ መድኃኒቶች ጸጉርን ለማከምና ለማሳጅ ይረዳል በሚል ሲሸጡ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እነዚህ ምርቶች ያልተመዘገቡ፣ የማይታወቁ ፣ጥራትና ደህነንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ በድንገተኛ ቁጥጥሩ ወቅት የያዛቸው እና ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ያሳሰበው ምርቶችም የሚከተሉት ናቸው፦

- ካስቱሪር ሄርባል ሄር ( KASTURIR HERBALHAIR )
- ንላንባሪ ካስቱራ ሄርባል ( NEELAMBARI KASTURA HERBAL )
- ንላምባሪ ሄርባል ኦይል ( NEELAMBARI, HERBAL OIL )
- ካስቱሪ ሄርባል ሄር ኦይል ( KASTURI HERBAL HAIR OIL)
- ንላምባሪ ሄርባል ( NEELAMBARI, HERBAL)
- ኤች ኤች አይ ኤን ኬ ኤን አይ ( HHINKNI)
- ሳንጂቪን ሄርባል አዩስቸር ( SNNSEV,N HYREBALE Ayu)
- ንላምባሪ ሄርባል ማሳጅ ( NEELAMBARI,HERBAL MASSAGE)

(ኤፍቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት...

ብሪታኒያ በቀጠናው የሚስተዋለውን ውጥረት እንዲያረግቡ የኢራቅ ባለስልጣናትን አሳሰበች። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶሚኒክ ራዓብ ትላንት ከኢራቅ ባለስልጣናት ጋር በስልክ ተነጋግረዋል። ዶሚኒክ በንግግራቸው አል-ቁድስ የተሰኘው የኢራን የአብዮት ዘብ አዛዥ ቃሲም ሱሌይማኒ በአሜሪካ መገደላቸውን ተከትሎ በቀጠናው የተስተዋለውን ውጥረት እንዲያረግቡ ባለስልጣናቱን አሳስበዋል። በአሜሪካ ድርጊት ማዘናቸውን የገለፁት ዶሚኒክ ከኢራን አቻቸው ጋር ለመነጋገር ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።

#AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
1,000,000 ብር መልሶ ያስረከበው ወጣት...

ዘረፋ በተበራከተበት በአሁኑ ጊዜ፥ በስህተት ወደ አካውንቱ የገባውን አንድ ሚልዮን ብር መልሶ ያስረከበው ወጣት ደሳለኝ ብስራት።

(አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ብርሃኔ ንጉሴ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የዓለም የነዳጅና የወርቅ ዋጋ እያሻቀበ ነው...

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ አገራት ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያት የዓለም የነዳጅና የወርቅ ዋጋ ማሻቀቡ ተገለፀ፡፡ የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከ4 በመቶ በላይ ማሻቀቡ ተነግሯል፡፡

ከዚህ ባሻገር የሳዑዲ ዓረቢያ የነዳጅ ማከማቻ እና ማጣሪያ ተቋማት በኢራን ጦር የሚሳኤል ጥቃት ሊደርስበት እንደሚችል አሜሪካ አስጠንቅቃለች፡፡ ኢራን በበኩሏ አሜሪካ ከፍተኛ የጦር ጀነራሏን በመግደሏ ሳቢያ በአውሮፓዊያኑ 2015 የተፈረመውን የኒውክለር ስምምነት ውጪ እንደሆነች አስታውቃለች፡፡

የወርቅ ዋጋም የአውሮፓውናኑን አዲስ ዓመት 2020ን በከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ነው የተቀላቀለው፡፡ ወርቅ በዓለም አቀፉ ገበያ ከዚህ ቀደም ከነበረው ሁሉ በከፍተኛ ዋጋ እየተሸጠ መሆኑንም ነው አልጃዚራ የዘገበው፡፡

(አልጀዚራ፣ ኢቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቴህራን ዩኒቨርሲቲ...

የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ካሚኔይ በቴህራን ዩኒቨርሲቲ በጀነራል ቃሲም ሱሌይማኒ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ ተገኝተው ፀሎት አድርገዋል። በስፍራው የተገኙት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጀነራሉ ሞት የተሰማቸውን ሃዘን በመግለፅ ሲያለቅሱ ይታያል። ዝግጅቱ በበርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች በቀጥታ ሲሰራጭ ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ 3 አሜሪካዊያን ተገድለዋል...

ትናንት በኬኒያ ላሙ ዳርቻ የጦር ሰፈር በተፈፀመው ጥቃት 3 አሜሪካውያን መገደላቸው ተሰምቷል። አሜሪካና ኬንያ በጋራ በማጠቀሙት በላሙ የባህር ዳርቻ የጦር ሰፈር አል-ሸባብ በፈፀመው ጥቃት አንድ የአሜሪካ ወታደር አባል እና 2 ኮንትራክተሮች በድምሩ 3 አሜሪካዊያን ሲገደሉ ሌሎች 2 ግለሰቦች ደግሞ ቆስለዋል።

#AlAin #CNN #AssociatedPress
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE

ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ በትላንትናው ዕለት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ከተናገሩት የወሰድነው፦

- በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደቱ እንዲደፈርስ የሚያደርጉ አካላትን ከተማሪዎች፣ ከአገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በተደረገው ውይይት መለየት ተችሏል።

- የሰው ህይወት ያጠፉ፣ አካል ያጎደሉና ንብረት ያወደሙትን የመያዝ ተግባሩ እንደተጠበቀ ሆኖ ዩኒቨርስቲዎችም በራሳቸው አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስዱ እየተደረገ ነው።

- በአሁኑ ወቅት ጥፋተኛ ሆነው በተገኙ ተማሪዎች፣ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰድ ተጀምሯል። በዚህም መሰረት ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ችግር በተፈጠረባቸው ዩኒቨርስቲዎች ከ440 በላይ ተማሪዎች የአንድ አመት እገዳ፣ ማስጠንቀቂያና ሙሉ ለሙሉ ከትምህርታቸው እንዲታገዱ ቅጣት ተወስኖባቸዋል።

- ችግሩን በማባባስ ሚና አላቸው የተባሉ 10 መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች የስራ ውላቸው ተቋርጧል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ የደሞዝ እገዳና ሌሎች እርምጃዎች ተወስዶባቸዋል።

- ሰላማዊ የመማር ማስተማሩን ለማወክ በተሳተፉት ላይ የሚወሰደው እርምጃ የሚቀጥል ይሆናል። በድርጊቱ የተሳተፉ መሆናቸው የተረጋገጠባቸው ከፍተኛ ኃላፊዎችም በቅርቡ ከሃላፊነታቸው ይነሳሉ።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በያቤሎ...

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው የቦረና ዞን ከያቤሎ ከተማ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሄዱ። በንግግራቸውም ወቅት የከተማዋ ነዋሪዎች የፍቅርና ሰላም እሴቶችን በአንድነት አጽንተው፣ ለኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት መሠረት እንዲያደርጓቸው አሳስበዋል።

የማኅበረሰቡ ሽማግሌዎች ባለፉት ሁለት ዓመታት የታዩትን የሃይማኖትና ሌሎች ነጻነቶች ዋቢ አድርገው፣ ኢትዮጵያ እየተጓዘችበት የምትገኘውን የዴሞክራሲ ጎዳና አድንቀዋል። በተጨማሪም፣ የአካባቢውን የመሠረተ ልማት፣ የውኃ እና የኤሌክትሪክ አገልግሎት ፍላጎት እንዲሁም የአርብቶ አደሩን ማኅበረሰብ ፍላጎት ከማሟላት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አንሥተዋል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቡሌ ሆራ ገብተዋል...

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኦሮሚያ ክልል ቡሌ ሆራ ሲደርሱ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በቆይታቸውም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia