TIKVAH-ETHIOPIA
ፍሬወይኒ መብርሃቱ... ታህሳስ 28 በሚሊየም አዳራሻ ሊደረግ የነበረው የ2019 የCNN የዓመቱ ጀግና ፍሬወይኒ መብርሃቱ የክብር አቀባበል እና የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ ስነ ስርዓት የቀን እና የቦታ ለውጥ ተድርጎ ዛሬ በኤሊያና ሆቴል እጅግ በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል። ቆይት ብለን ዝርዝር መረጃዎችን እንሰጣችኃለን! PHOTO : TIKVAH-ETH @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፍሬወይኒ መብሃቱ የክብር አቀባበል...

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በCNN በ2019 የአመቱ ጀግና ተብላ ለተመረጠችውን ፍሬወይኒ መብራሃቶም ደማቅ አቀባበል አድረጎላታል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዕድር መሪዎች የመንግስት ኃላፊዎች፣ የካቢኔ አባላትና የመነን አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የማህበረሰባቸውን ችግር ተመልክተው መፍትሔ በመስጠታቸውና በርካታ ሴት ታዳጊዎችን ችግር በመፍታታቸው ከተማ አስተዳደሩ የሁላችንም ጀግና ነሽ በማለት ለፍሬወይኒ መብርሃቶም የካባ ሽልማት ያበረከተላት ሲሆን በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ስም የምስጋና ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዝግጅቱ እንደተጠቀሰው ጀግናዋ ፍሬወይኒ የጀመረችውን ሥራ ከዘንዶሮ አመት ጀምሮ በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የከተማዋን ነዋሪዎች በማስተባበር እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለማዳረስ ያቀደ ሲሆን ይህ ተግባር ሙሉ ለሙሉ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ የሚከወን ይሆናልም ተብሏል፡፡

የአመቱ የCNN ጀግና ፍሬወይኒ መብራቶም በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና ሁሉ ከተማ አስተዳደሩንና ህዝቡን ያመሰገኑ ሲሆን ይህንን ተግባር ወደፊት እንቀጥላለን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ለዝግጅቱ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት የጀግኒት ቤተሰብ አባላት በተለይም ለአርቲስት ጸደኒያ ገብረማርቆስና ቤቲ ጂ ከዛም በተጨማሪ በከተማዋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በስፋት እየተሳተፈ ለሚገኘው ለአርቲስት ያሬድ ሹመቴና ለአርቲስት መሀመድ ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል፡፡

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia