TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
የጀነራል ቃሲም ሱሊማኒ አስክሬን ሽኝት... የኢራን ብሔራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጄነራል ቃሲም ሱለይማኒ አስክሬን ከኢራቅ ወደ ኢራን እየተሸኘ ነው። የጀነራሉን አስክሬን ለመሸኘት በሺዎች የሚቆጠሩ ኢራቃዊያን አደባባይ የወጡ ሲሆን፤ ''ሞት ለአሜሪካ'' ሲሉም ድምጻቸውን አሰምተዋል። የጀነራሉ አስክሬን ወደ ኢራን ከተሸኘ በኋላ በተወለዱበት ከተማ ገብዓተ መሬታቸው የፊታችን ማክሰኞ ይፈጸማል…
የጀነራሉ አስክሬን ቅበላ...

በ100 ሺህዎች የሚቆጠሩ ኢራናዊያን በአሜሪካ የሰው አልባ ጥቃት የተገደሉትን ወታዳራዊ መሪያቸውን ቃሴም ሱለይማኒን አስክሬን አደባባይ በመውጣት ተቀብለዋል፡፡

ኢራናዊያኑ በአህቫዝ እና በማሽሃድ አደባባዮች በመውጣት አሜሪካ ኢራቅ ውስጥ በፈፀመችው የሰው አልባ አውሮፕላን ጥቃት የተገደሉትን የኢራን ብሄራዊ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዥ ጀኔራል ቃሴም ሶሊማኒን  አስክሬን ተቀብለዋል፡፡

አስክሬኑን በተቀበሉበት ወቅት ኢራናዊያኑ ሀዘናቸውን የገለፁ ሲሆን  ሞት ለአሜሪካ የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል፡፡ አብዮት ዘብ ጠባቂ ሃይል አዛዡ ቃሴም ሶሊማኒ አስክሬን ከተገደሉ ሁለት ቀናት በኋላ  ነው በ ደቡብ ምስራቅ ወደ ምትገኘው አህባዝ ከተማ በዛሬው ዕለት አቅንቷል፡፡

(አልጀዘራ,ቢቢሲ,ኤፍቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በትዊተር ገጻቸው...

- ኢራን በ ጄነራሉ ግድያ አጸፋ ለመስጠት "የአሜሪካ ንብረቶች ላይ ማነጣጠሯን በድፍረት እየተናገረች ትገኛለች" ብለዋል።

- አሜሪካ 52 የኢራን ተቋማት ላይ ማነጣጠሯን በመግለጽ ኢራን ጥቃት ከፈጸመች "አንዳንዶቹ ለኢራንና ለኢራናውያን ባሕል ትልቅ ቦታ ያላቸው ናቸው፤ በፍጥነትና በማያዳግም ሁኔታ ነው ምላሽ የምንሰጠው" ብለዋል። "አሜሪካ ሌላ ማስፈራሪያ አትፈልግም" ሲሉም አክለዋል።

- ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራን 52 ስፍራዎች የተመረጡት በአውሮፓውያኑ 1979 በኢራን በሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲ ታግተው የነበሩትን 52 አሜሪካውያንን ለማስታወስ መሆኑን ገልፀዋል። እነዚህ የኢምባሲው ሠራተኞች ለአንድ አመት ያህል ታግተው ቆይተው ነበር።

- ፕሬዝዳንት ትራምፕ ይህንን የትውተር መልዕክታቸውን ባሰፈሩ በጥቂት ደቂቃ ውስጥ የአሜሪካ መንግስት ተቋም የሆነ አንድ ድረገጽን "የኢራን ሳይበር ሰኪዩሪቲ ግሩፕ ሀከር" የተሰኘ የኮምፒዩተር ጠላፊ ቡድን እንዳይሰራ አድርጎታል።

(BBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመኪና አደጋ የ7 ሰዎች ሕይወት አለፈ...

በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን ድሬ ወረዳ በዛሬው ዕለት በደረሰ የመኪና አደጋ የሰባት ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡ አደጋው የደረሰው ወደ ዲሎ ገበያ ሰዎችን አሳፍሮ በመጓዝ ላይ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና በመገልበጡ ነው፡፡

(የድሬ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ፅህፈት ቤት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"...ጉባኤው በድል ተጠናቋል" - ህወሓት የህወሓት የአስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ፣ "ጉባኤ ፅናትና መኸተ" በድል ተጠናቋል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል። ዝርዝር ጉዳዮች ከደቂቃዎች በኃላ ለህዝብ እንደሚያሰራጭ ገልጿል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ /ህወሃት/ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር እንደማይዋሃድ አስታወቀ። ድርጅቱ ለሁለት ቀናት ያካሔደውን ጉባኤ ዛሬ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ከብልጽግና ፓርቲ ጋር የዓላማና የመስመር ልዩነት ስላለው እንደማይዋሃድ አስታውቋል።

ከፌዴራል መንግስት ጋር የሚኖረው ግንኙነትም ህግና ህገ-መንግስትን መሰረት ያደረገ እንደሚሆን ያመለከተው መግለጫው ከዚህ ውጭ የሚኖር እንቅስቃሴ ተቀባይነት እንደማይኖረው አመልክቷል።

ኢህአደግን የመሰረቱ የአራቱ ድርጅቶችን የጋራ ሀብት ህግና ስርአት በተከተለ መንገድ ድርሻውን እንደሚያስመልስም በአቋም መግለጫው አስታውቋል።

የኢህአዴግን መፍረስ ተከትሎ ህወሓት ከሌሎች ፈዴራላዊ ሀይሎች ጋር በፎረም፣ በጥምረትና በግንባር ደረጃ ስትራተጂካዊ ግንኙነት ለመመስረት መወሰኑንም ገልጿል።

(ENA)
@tikvahethiopiaBot @tikvaherhiopia
ህወሓት ብልፅግና ፓርቲን ህገወጥ ብሎታል...

ህወሓት ውሁዱ ፓርቲ ብልፅግናን 'አዲስ የተመሰረተ፣ ሕገወጥና ጥገኛ ፓርቲ' ሲል ገልፆታል፡፡ በቀጣይም ህወሓት ከሌሎች የኢትዮጵያ 'ፌደራሊስት' ሀይሎች ጋር ይሰራል ተብሏል፡፡

(ጋዜጠኛ ሚሊዮን ኃይለስላሴ ከDW)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቤንያሚን ኔታንያሁ...

እስራኤል የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ባለቤት መሆኗን ቤንያሚን ኔታንያሁ ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሃገራቸው በጥብቅ ይዛው የቆየችውን ሚስጥራዊ ጉዳይ የገለፁት ከካቢኒያቸው ጋር ተሰብስበው በነበረበት ወቅት ነው።

በስብሰባው በኢነርጂ ልማት ዙሪያ ከግሪክ እና ቆጵሮስ ጋር የተደረጉ ስምምነቶችን በተመከተ ለካቢኔያቸው ሲያስረዱ የነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ 'የዚህ ፕሮጀክት ፋይዳ እስራኤልን የኒውክሌር ባለቤት ማድረግ ነው' ሲሉ ተናግረዋል። ሮይተርስ አምልጧቸው ነው ያለውን ይህን ንግግር ኔታንያሁ ወዲያውኑ ቢያስተካክሉትም ብዙዎች ግን ተቀባብለውታል።

#AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢራቅ ፓርላማ ውሳኔ...

የኢራቅ ምክር ቤት በአገሪቱ የሰፈሩ 5,200 የአሜሪካ ወታደሮች ለቀው እንዲወጡ መንግሥትን የሚጠይቅ የውሳኔ ሐሳብ አጽድቋል። የምክር ቤቱ ውሳኔ ተግባራዊ እንዲሆን በመንግሥት መጽደቅ ይኖርበታል።

(DW)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ133 በላይ የዳስ ጥላ መማሪያ ክፍሎች እየተቀየሩ ነው...

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሚገኙ ከ133 በላይ የዳስ ጥላ መማሪያ ክፍሎችን ወደ ዘመናዊ ግንባታ ለመቀየር እየተሰራ መሆኑን የብሔረሰብ አስተዳደሩ ትምህርት መምሪያ አስታወቀ። የዳስ መማሪያ ክፍሎችን ወደቋሚ መማሪያ ህንጻዎች ለመቀየር እየተሰራ ያለው ከሰቆጣ ቃልኪዳን በተገኘ የበጀት ድጋፍ መሆኑ ታውቋል።

(ኢዜአ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ህወሓት ስለኢህአዴግ መፍረስ...

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ለሁለት ቀን ያካሄደውን ጉባኤ ሲያጠናቅቅ ባወጣው የአቋም መግለጫ ኢህአዴግን "ተዋሐደ" ሳይሆን "በክህደት ፈረሰ" ብሎታል።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን የማሰባሰብ ዘመቻ...

ዛሬ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቅም ለሌላቸው ሴት ተማሪዎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን (ሞዴስ፣ ፓንት..ወዘተ) የማሰባሰብ ዘመቻ በይፋ ጀምሯል፡፡ በዚህ በመክፈቻ ሰነ-ሥርዓት ላይ ከክፍለ ከተሞች 55,000 እንዲሁም ዛሬ ተካሄዶ በነበረው የማስ ስፓርት ላይ ከተሳተፉ የስፓርት ቤተሰቦች 100,000 ሞዴስ ማሰባሰብ ተችሏል፡፡

በ አዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ አቅም ለማይፈቅድላቸው ተማሪዎች በዘንድሮ አመት ሙሉ ለሙሉ የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ለማዳረስ ለታቀደው እቅድ ወደ 700,000 የሚጠጋ ሞዴስ ያስፈልጋልም ነው የተባለው፡፡

More👇
https://telegra.ph/TIKVAH-01-05

#TIKVAH_ETHIOPIA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፍሬወይኒ መብርሃቱ... ታህሳስ 28 በሚሊየም አዳራሻ ሊደረግ የነበረው የ2019 የCNN የዓመቱ ጀግና ፍሬወይኒ መብርሃቱ የክብር አቀባበል እና የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ ስነ ስርዓት የቀን እና የቦታ ለውጥ ተድርጎ ዛሬ በኤሊያና ሆቴል እጅግ በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል። ቆይት ብለን ዝርዝር መረጃዎችን እንሰጣችኃለን! PHOTO : TIKVAH-ETH @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፍሬወይኒ መብሃቱ የክብር አቀባበል...

የአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በCNN በ2019 የአመቱ ጀግና ተብላ ለተመረጠችውን ፍሬወይኒ መብራሃቶም ደማቅ አቀባበል አድረጎላታል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዕድር መሪዎች የመንግስት ኃላፊዎች፣ የካቢኔ አባላትና የመነን አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የማህበረሰባቸውን ችግር ተመልክተው መፍትሔ በመስጠታቸውና በርካታ ሴት ታዳጊዎችን ችግር በመፍታታቸው ከተማ አስተዳደሩ የሁላችንም ጀግና ነሽ በማለት ለፍሬወይኒ መብርሃቶም የካባ ሽልማት ያበረከተላት ሲሆን በተጨማሪም በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ስም የምስጋና ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡

በዝግጅቱ እንደተጠቀሰው ጀግናዋ ፍሬወይኒ የጀመረችውን ሥራ ከዘንዶሮ አመት ጀምሮ በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ሴት ተማሪዎች የከተማዋን ነዋሪዎች በማስተባበር እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ለማዳረስ ያቀደ ሲሆን ይህ ተግባር ሙሉ ለሙሉ ከሚቀጥለው አመት ጀምሮ በከተማ አስተዳደሩ የሚከወን ይሆናልም ተብሏል፡፡

የአመቱ የCNN ጀግና ፍሬወይኒ መብራቶም በበኩላቸው ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና ሁሉ ከተማ አስተዳደሩንና ህዝቡን ያመሰገኑ ሲሆን ይህንን ተግባር ወደፊት እንቀጥላለን በማለት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመጨረሻም ከተማ አስተዳደሩ ለዝግጅቱ መሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉት የጀግኒት ቤተሰብ አባላት በተለይም ለአርቲስት ጸደኒያ ገብረማርቆስና ቤቲ ጂ ከዛም በተጨማሪ በከተማዋ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ላይ በስፋት እየተሳተፈ ለሚገኘው ለአርቲስት ያሬድ ሹመቴና ለአርቲስት መሀመድ ከፍተኛ ምስጋና አቅርቧል፡፡

#ቲክቫህኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቲክቫህ ቤተሰቦች ስም...

በፍሬወይኒ መብርቶም የክብር አቀባበል ላይ ተገኝተን በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በተለይም የቤተሰባችን አባላት በሆኑ ወጣቶች ስም በገንዘብ ሲተመን 5,000 ብር የሚያወጣ ሞዴስ እገዛ አድርገናል። እገዛችን በጣም ትንሽ እንደሆነች ብናውቅም ለሌሎች ወጣቶች መነሳሳትን ለመፍጠር ያህል ነው።

- የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች በተለያዩ በጎ ስራዎች ላይ ስንሳተፍ ለበርካቶች ማህበራዊ ሚዲያን ለመልካም ስራም መጠቀም እንደምንችል ለማስታወስ ያህል ነው!!

- በያላችሁበት ከግንዛቤ ጀምሮ እስከ ቁሳቁስ የምታበረክቱት አስተዋጽኦ የብዙዎችን ህይወት ይለውጣል ብለን እናምናለን፡፡

- በመላው ቤተሰቦቻችን ስም ለ2019 የCNN ጀግና ፍሬወይኒ መብርሃቱ በድጋሚ እንኳን ደስ አለሽ፤ እንኳን ደስ አለን ለማለት እንወዳለን!

በነገራችን ላይ...

UNESCO (ዩኔስኮ) ባጠናው ጥናት መሰረት በሀገራችን 75% የሚሆኑ ሴቶች በቂ ንጽህና መጠበቂያ አያገኙም 50% የሚሆኑ ተማሪዎች በዚሁ የተነሳ ከትምህርት ገበታቸው ይስተጓጎላሉ፡፡

ስለ ሴቶች የወር አበባ አሁንም ድረስ ማህበረሰባችን ካለው አመለካከት ላይ የኢኮኖሚ ጫናው ተደምሮ ለበርካታ ሴት እህቶቻችን ከትምህርት መስተጓጎል እስከማቋረጥ ምክንያት ሆኗል፡፡

እናተም በየክፍለ ከተማው በመገኘት አግዙ!

እያንዳንዳችን ለውጥ ማምጣት እንችላለን!
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ዶ/ር አብይ አህመድ ያቤሎ ከተማ ገብተዋል...

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አሕመድ ቦረና ዞን ያቤሎ ከተማ ገብተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያቤሎ ሲደርሱ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በቆይታቸውም ከህብረተሰቡ ጋር ውይይት የሚያደርጉ ይሆናል፡፡

(EBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
99 በመቶ የሚሆነው ተማሪ የመማር ፍላጎት አለው...

- በ170 ተማሪዎች ላይ የአንድ ዓመት ቅጣትና እስከ መጨረሻው ከዩኒቨርሲቲዎች የማባረር እርምጃ ተወስዷል

በኦሮሚያ እና በአማራ ክልል እንዲሁም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲዎች እየተከሰተ ያለውን ረብሻ ሙሉ ለሙሉ ለማስቆም እና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥራን ለማከናወን ለመላው የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብና ለወላጆች ጥሪ ቀርቧል፡፡

170 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች የረብሻ ድርጊት ላይ በመሳተፋቸው ለአንድ ዓመት በትምህርት ገበታ ላይ እንዳይሳተፉ ከመቅጣት ጀምሮ እስከ መጨረሻው ከዩኒቨርሲቲዎች የማባረር እርምጃ መወሰዱም ተጠቁሟል፡፡

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን እና የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ ትናንት መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ድኤታው ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እንደተናገሩት፤ 99 በመቶ የሚሆነው ተማሪ የመማር ፍላጎት አለው ብለዋል።

(EPA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአውስትራሊያ ዝናብ ጥሏል...

በሰደድ እሳት ነበልባል በነደደችው አውስትራሊያ ዝናብ መጣሉ ነዋሪዎችን አስፈንጥዟል፡፡ አውስትራሊያ ሰሞኑን በከባድ የሰደድ እሳት እየታመሰች ትገኛለች፡፡

የሀገሪቱ መንግስት እሳቱን ለመቆጣጠር ዘመናዊ የእሳት ማጥፍያ መሳርያዎችን ቢጠቀምም እስካሁን ድረስ እሳቱን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ግን አልቻለም፡፡ በሰደድ እሳቱ ሳብያም ከ5 ሚሊየን በላይ እንስሳት የሞቱ ሲሆን በርካቶችን ለስደት ዳርጓቸዋል፡፡

ዛሬ ላይ ከወደ አውስትራሊያ የተሰማው ወሬ ዜጎችን እረፍት የሰጠ ነገር ሆኗል፡፡ በሀገሪቱ ባንዳንድ ከተሞች በዋናነትም በሲድኒ እና በሜልቦርን ዝናብ በመጣሉ ምክንያት የሙቀት መጠኑም እንደቀነሰ ነው የተነገረው፡፡

ዝናብ መጣሉን ተከትሎ የሀገሪቱ ዜጎች ደስታቸውን ሲገልጹ ተስተውሏል፡፡ የሀገሪቱ ባለስልጣናት ግን ሰደድ እሳቱ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ያልተቻለ በመሆኑ አሁንም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሰስቧል፡፡ በሀገሪቱ ዝናብ ከጣለ በኃላም ምንም አይነት የእሳት አደጋ የማስጠንቀቂያ ድምጽ እንዳልተሰማ ነው ቢቢሲ ያተተው፡፡

(ምንጭ፦ ቢቢሲ -በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ ምርቶች...

ሰባት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በባዛሮች ጥራታቸውና ፈዋሽነታቸው ያልተረጋገጡ ምርቶችን ሲሸጡ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ስምንት ዓይነት ያህል የባህላዊ መድኃኒቶች ጸጉርን ለማከምና ለማሳጅ ይረዳል በሚል ሲሸጡ በመገኘታቸው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተጠቁሟል፡፡

በባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እነዚህ ምርቶች ያልተመዘገቡ፣ የማይታወቁ ፣ጥራትና ደህነንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም አሳስቧል፡፡

ባለስልጣኑ በድንገተኛ ቁጥጥሩ ወቅት የያዛቸው እና ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ያሳሰበው ምርቶችም የሚከተሉት ናቸው፦

- ካስቱሪር ሄርባል ሄር ( KASTURIR HERBALHAIR )
- ንላንባሪ ካስቱራ ሄርባል ( NEELAMBARI KASTURA HERBAL )
- ንላምባሪ ሄርባል ኦይል ( NEELAMBARI, HERBAL OIL )
- ካስቱሪ ሄርባል ሄር ኦይል ( KASTURI HERBAL HAIR OIL)
- ንላምባሪ ሄርባል ( NEELAMBARI, HERBAL)
- ኤች ኤች አይ ኤን ኬ ኤን አይ ( HHINKNI)
- ሳንጂቪን ሄርባል አዩስቸር ( SNNSEV,N HYREBALE Ayu)
- ንላምባሪ ሄርባል ማሳጅ ( NEELAMBARI,HERBAL MASSAGE)

(ኤፍቢሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመካከለኛው ምስራቅ ውጥረት...

ብሪታኒያ በቀጠናው የሚስተዋለውን ውጥረት እንዲያረግቡ የኢራቅ ባለስልጣናትን አሳሰበች። ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ዶሚኒክ ራዓብ ትላንት ከኢራቅ ባለስልጣናት ጋር በስልክ ተነጋግረዋል። ዶሚኒክ በንግግራቸው አል-ቁድስ የተሰኘው የኢራን የአብዮት ዘብ አዛዥ ቃሲም ሱሌይማኒ በአሜሪካ መገደላቸውን ተከትሎ በቀጠናው የተስተዋለውን ውጥረት እንዲያረግቡ ባለስልጣናቱን አሳስበዋል። በአሜሪካ ድርጊት ማዘናቸውን የገለፁት ዶሚኒክ ከኢራን አቻቸው ጋር ለመነጋገር ማቀዳቸውን አስታውቀዋል።

#AlAin
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
1,000,000 ብር መልሶ ያስረከበው ወጣት...

ዘረፋ በተበራከተበት በአሁኑ ጊዜ፥ በስህተት ወደ አካውንቱ የገባውን አንድ ሚልዮን ብር መልሶ ያስረከበው ወጣት ደሳለኝ ብስራት።

(አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ፣ ብርሃኔ ንጉሴ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia