TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Attention

የአዋሽ-ኮምቦልቻ-ወልድያ/ሃራ ገበያ ባቡር ፕሮጀክት የኃይል አቅርቦት የመንግስትን ትኩረት ይሻል! #ENA #ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#CBE | የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ኘሬዝዳንት ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ኢድሪስ በትላንትናው ዕለት ከወለድ ነፃ የባንከ አገልግሎት የሚሰጠውን መካ ቅርንጫፍ መርቀው ከፍተዋል፡፡ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር ባንኩ የተሟላ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎትን የሚሰጥ ልዩ ቅርንጫፍ መክፈቱ ለህዝበ ሙስሊሙ ያለውን ከበሬታና የአገልጋይነት ስሜት የሚያሳይ በመሆኑ ሊመሰገን ይገባል ብለዋል፡፡

Via CBE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሀድያ ዞን ሻሾጎ ወረዳ ሰሞኑን የዘነበው ዝናብ ባስከተለው ከፍተኛ ጎርፍ በ14 ቀበሌያት የሚኖሩ 7 መቶ 54 ቤተሰቦች ቤትና ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት በማድረስ ማፈናቀሉን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት መምሪያ አሳወቀ፡፡ የጎርፍ አደጋው ከ 1ሺህ 7 መቶ 22 በላይ ሄክታር መሬት ማሳ የመኸር ሰብልን በማውደም ከ 3 መቶ 5 በላይ እንስሳትን መግደሉን መምሪያው ጨምሮ ገልጿል፡፡ የዞኑ አስተዳደር አደጋው ጉዳት ያደረሰባቸው ቀበሌያትን ተዟዙሮ በመመልከት ችግሩን በጊዜያዊነትና በዘላቂነት ለመፍታት ከሚመለከታቸው የመንግስት የበላይ አካለት ጋር በመነጋገር በየደረጃው ጥረት እየተደረገ እንደሆነ ጠቁሟል።

Via Sisay Yohannes
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
AudioLab
#Gaas_Ahmed

በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 "ልዩ መረጃ" ላይ የቀረበው መረጃ የተሳሳተ ስለሆነ ሊታርም ይገባል ሲሉ የአፋር የሰብዓዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH ተናግረዋል።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH በላኩት የድምፅ መልዕክት ተከታዩን ብለዋል፦

"በሬድዮ ጣቢያው የተሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም፤ ሶስቱ ከተማ የሚባሉት በሱማሌ ክልል ቁጥጥር ስር የነበሩ አልነበሩም፤ የconflict ዞኖች ሲመሰረቱ አመሰራረታቸው ከኮብትሮባንድ ጋር የተያያዘ ስልነበር በሁለቱም በኩል እንዳይተዳደሩና ውሳኔ እስከሚሰጥ ድረስ በራሱ የኮንትሮባንድ ከተማ ሆኖ የቆየ ነው። በኃላ ውሳኔ ሲሰጥ ወደአፋር የተካለሉ እንጂ በሱማሌ ክልል ስር ሆኖ ሲተዳደሩ ነበሩ አይደሉም። ሌላው ደግሞ የአፋር ኃይሎች የሱማሌ ክልልን ዘልቀው በመግባት ጥቃት ፈፅመዋል የሚለውም ከእውነት የራቀ ነው። ግጭቱ ያለበት አካባቢ እራሱ አፋር አካባቢ ነው፤ ቦታውም ከሱማሌ ክልል ወደ 300 ኪሎሜትር ወደአፋር ውስጥ ገብቶ ነው። ስለዚህ መረጃው የአንድ ወገን ብቻ በመሆኑ ሊታረም ይገባዋል። የአንድ ወገንን ድምፅ ብቻ ይዞ እንዲህ ያለ ፕሮፖጋንድ መስጠት ተገቢ አይደለም። ይሄ ለሁለቱም ህዝቦች መፍትሄ ሊሆን አይችልም።"

አቶ ጋአስ አህመድ ለTIKVAH-ETH ጨምረው እንደገለፁት በአፋር ክልል በሚገኙ አርብቶ አደሮች ላይ ጥቃት እየተፈፀመ ያለው ከተለያዩ አካላት ስለመሆኑ የቪድዮ መረጃ ጭምር አለን ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከተናገሩት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች፦

• የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ዝምድና ውክልና እስከመሰጣጠት የደረሰ ስለሆነ እንኳን ደስ አላችሁ!

• ባቀረብንላችሁ ጥሪ መሰረት የ5 ሚሊዮን ብሩን እራት የታደማችሁ ውድ ኢትዮጵያውያን እንኳን በሰላም መጣችሁ

• የ5 ሚሊዮን ብሩን እራት እንዲደገም በርካቶች ጥሪ ቢያቀርቡም እራቱ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ የተደረገ በመሆኑ እንደማይደገም አረጋግጠዋል

• በፕሮጀክቱ ቀን ከለሊት በመስራት ማጠናቀቅ የቻሉ ኢትዮጵያውያንም እንኳን ደስ አላችሁ ተብሏል

• እኛ ኢትዮጵያውያን ታሪክ አለን፣ እኛ ኢትዮጵያውያን ዱካችን በባህርም ሆነ በሰማይ ይታያል

• ስልጣኔ የተከማቸ የእውቀት ጥበብ ነው፣ ስልጣኔ ሳያቋርጥ እንደሚፈስ ጅረት ነው

• አባቶቻችን ጥፋት ቢሰሩም ከነሱ ጥፋት ተምረን አባቶቻችን አንድ አድርገው ያሳለፉልንን አገር አንድ አድርገን ማሻገር ግዴታ እንዳለብን ያሳያል

• ልጆቻችን ቤተመንግስት ፎቶ የማይነሳ የሚያስፈራ ስፍራ ሳይሆን፣ በመገዳደል ብቻ የሚገባበት ሳይሆን የሚጎበኝ ስፍራ መሆኑንም ለማሳየት የሚስችል ስፍራ ነው

• በአዲስ አበባ ከአፍሪካ ትልቁን ፓርክ እንገነባለን

• ይህንን ለማሳካት የሚያቆመን አንዳችም ሀይል የለም

• በዚህ ቤተመንህግስት ርካታ አስደናቂ ግብዣዎች ተደርገዋል በርካቶችም አድንቀውት አልፈዋል

• ዛሬ ለመላ ኢትዮጵያውያን መናገር የምፈልገው እኛ እንቀጥላለን ታሪክን ከዛሬ ጋር ለነገ በሚበጅ መልኩ አስተሳስረን እንቀጥላለን

• የሚያግዘን ካገኘን የወሩን በሳምንት የሳምንቱንም በእለት እንጨርሳለን

• ጨርሰን ሪባን እንቆርጣለን እንጂ ተስፋ አንቆርጥም

Via etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Nobel Peace Prize 2019

ዶክተር አብይ ከ16 አመቷ ታዳጊ ብርቱ ፉክክር ገጥሟቸዋል!

የዘንድሮው የአለም የሰላም ሽልማት(ኖቤል ሽልማት) አሸናፊ ማን ይሆን ? የሚለው ቅድመ ግምት የበርካታ ምእራባዊያን ሚዲያዎችን እና የቁመራ ድርጅቶችን እያነጋገር፣እና የውድድር ገበያቸውንም እያሟሟቀላቸው ይገኛል።

ታዲያ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት በሚጠበቀው አመታዊው የኖቤል ሽልማት ዋንኛ እጩ ተወዳዳሪዎች መካከል ከሰባ ሺህ በላይ ነፍሳት የጠፋበት እና ዳግም ውጥረት የነገሰበት የኢትዬ- ኤርትራ ወታደራዊ ፍጥጫን በሰላማዊ መንገድ እንዲቆም ግንባር ቀደም ሚና እንደተጫወቱ የሚነገርላቸው የኢትዮጵያው ጠ/ሚ/ር አብይ አሕመድ እንዱ ናቸው።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-10-4

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🔖እናስተዋዉቅዎ!
የጀ'ርባ ች-ግር አለቦት? ረጅም ሰአቶን ቢሮው ውስጥ በስራ ተቀምጠው ያሳልፋሉ? እንግዲህ መፍ-ትሄው በእጆት ነው፦
የጀ'ርባ መጉበጥ ች-ግርን የሚ-ቀርፍ
ቀጥያል እና ማራኪ ቁ'መና የሚ-ያላብስ
ሙሉ ለሙሉ በራስ መተመን
የጀ'ርባን ችግሮችን በአጭር ጊዜ መፍ-ትሔ የሚሰጥ
ከማንኛውም አለባበስ ጋር የሚሄድ
•ለቢሮ ሰራተኞች ፣ለአስፖርተኞች፣ከባድ ስራ ለምትሰሩ በጣም አስፈላጊ ነው
•በተመጣጣኝ ዋጋ የቀረበ ዋጋ 850 ብር
•ለክልል ከተሞች ወኪሎች ስላሉን ይደውሉልን 0922501644 or 0911659463 https://publielectoral.lat/joinchat/AAAAAEUWUXbqXP1bl7cfnA

☀️መልካም ቀን ይሁንላችሁ! #ETHIOPIA☀️
አንጋፋዋ ጋዜጠኛ አስካለ ተስፋዬ የ2012 ዓ.ም አርአያ ሰው ሽልማት አሸናፊ ሆነች!

ከ22 ዓመታት በላይ በጋዜጠኝነት ሙያ አገሯንና ህዝቧን እያገለገለች የምትገኘው ጋዜጠኛ አስካለ፣ እንደ አሁኑ መገናኛ ብዙሃን ብዙም ባልተስፋፉበት ጊዜ፣ አንድ ለእናቱ በነበረው የኢትዮጵያ ሬዲዮ ታቀርባቸው በነበሩ ፕሮግራሞች ተወዳጅ ለመሆን በቅታለች። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ በኢቲቪ መዝናኛ ቻናል በሚተላለፈው ዉሎ አዳር በተሰኘው ፕሮግራሟ ሌላ ተወዳጅነትን አግኝታለች።

የዉሎ አዳር ኘሮግራም የኛ የኢትዮጵያዊያንን አኗኗር በተለይም ሰፊውን የገጠሩን ህብረተሰብ አኗኗር ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ኘሮግራም ነው። በዚሁ ፕሮግራም ባሳየችው ሙያዊ ብቃት፣ መቀመጫውን አሜሪካ - ዳላስ ባደረገው አድዋ የባህልና ታሪክ ማህበር አዘጋጅነት የሚከናወነውን የ2012 አርአያ ሰው ሽልማት ለማሸነፍ በቅታለች ።

Via Kidus
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"በጣም ተማረናል" የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ከነጌሌ ቦረና!

"በጉጂ ዞን፤ ነጌሌ ቦረና ከተማ ህብረተሰቡ በከፍተኛ ደረጃ በኤሌትሪክ መቆራረጥ እየተቸገረ ይገኛል። የችግሩ ምክኒያት ደግሞ የከተማው መብራት ሃይል ጽ/ቤት ነው። በከተማው ለኤሌትሪክ መቆራረጥ መንስዔ የሆነውን የመስመር ፣ የትራንስፎርመርና የብሬከር ችግሮችን በአፈጣኝ ለመፍታት የፍላጎትና የአቅም ማጣት እንዲሁም ጽ/ቤቱ በውሳጣዊ አሰራሩ በመልካም አስተዳደር ችግር የተተበተበ በመሆኑ ነው። ህብረተሰቡ ስለሚቆራረጠው የኤሌትሪክ አገልግሎት መንስዔውን ጽ/ቤቱን በሚጠይቅበት ጌዜ የተሳሳተ ምክኒያት በመስጠት አንዳንዴም ለምላሽ ዳተኛ በመሆን ህብረተሰቡን ለከፍተኛ ችግር ዳርገዋል። የሚመለከታቸው አካላቶች አፋጣኝ የመፍትሄ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

የኬንያ ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በትላንትናው ዕለት በአንድነት ፓርክ የምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ማንኛውም ሀገር የራሱ ታሪክ ያለው መሆኑን ያነሱት ፕሬዚዳንት ኬያንታ፥ ለወደ ፊት የተሻለ ሀገር ግንባታም ካለፉት ታሪኮች ውስጥ ጥሩ ተሞክሮዎችን መውሰድ እንደሚገባ አንስተዋል።

ኬንያ እና ኢትዮጵያ በባህል፣በኢኮኖሚ እና በተለያዩ ዘርፎች ጥብቅ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን በመጥቀስ በቀጣይ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከርም በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት እያካሄደቸው ያለው ሁለንተናዊ ለውጥ የሚበረታታ መሆኑም ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ጠቁመዋል።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ምርቃቱን አስመልክተው ባደረጉት ንግግር ለኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ሁለንተናዊ ግንኙነት ያላት መሆኑን የገለጹት ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር፥ ለዚህም በደቡብ ሱዳን በተከሰተው የሰላም ችግር ወቅት ኢትዮጵያ በርካታ የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን በመቀበል ያደረገቸውን ከፍተኛ አስተዋፅኦ አንስተዋል። ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ተቀናቃኝ ሃይሎች መካከል ሰላም እንዲወርድ ያደረገችውን ከፍተኛ ጥረትም አድንቀዋል።

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ የተከናወነው የቤተ-መንግሥት ዕድሳት አስደናቂ መሆኑን በመግለፅ ለሀገሪቱ ቱሪዝም እንዲሁም የኢኮኖሚ ለውጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል። የአንድነት ፓርክ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ከማስፋፋት እና ቱሪዝምን በመሳብ ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለውና የሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UnityPark

የሱዳኑ ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ በፕሮግራም ላይ በመገኘታቸው ደስተኛ መሆናቸውን በመግለፅ ለኢዮጵያ መንግስትና ህዝብ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያ በሱዳን ተፈጥሮ የነበረውን ቀወስ ለመፍታት የነበራት ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት አብደላ ሃምዶክ፥ የአንድነት ፓርክ ለሀገሪቱ ታላቅ ስጦታ መሆኑን አንስተዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የከባድ ጭነት ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ማድረጉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት አጀንሲ አስታውቋል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ጅሬኛ ሂርጳ ትናንት በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ የከተማዋን ትራፊክ እንቅስቃሴ ለማሳለጥና አሁን ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ
ከግምት ውስጥ በማስገባት በከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች የእንቅስቃሴ ገደብ ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡ በተሻሻለው መመሪያ መሠረትም፤ ማንኛውም የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ከጠዋቱ 12፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት እና ከቀኑ ከ10፡00 ሰዓት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ካለው ጊዜ ውጪ መንቀሳቀስ የሚፈቅድ መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ፤ በዚህም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በከተማዋ ውስጥ መዘዋወርና ማንኛውንምአገልግሎት መስጠት እንደሚችሉ ጠቁመዋል፡፡

Via EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጎዳና ላይ ልብስ ነጋዴው የ10,000,000 ብር ዕድለኛ ሆነ። የድሬዳዋ ነዋሪው የ27 ዓመቱ ወጣት አንዳምላክ ባዴ ጳጉሜ 6 ቀን 2011 ዓ/ም በወጣው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ 1ኛ ዕጣ 10,000,000 ብር አሸናፊ ሆኗል።

ምንጭ፦ ብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የ2019 #NobelPeacePrize ከ25 ደቂቃ በኃላ ይፋ ይደረጋል። ጥሩ የኢንተርኔት ግንኙነት ካላችሁ ከታች ባለው የዩትዩብ ሊንክ ቀጥታ መከታተል እንደምትችሉ ልንጠቁማችሁ እንወዳለን! https://www.youtube.com/watch?v=7Vhj3N9HHj8

•የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ
•የኒውዚላንድ ጠ/ሚ ጃሲንዳ አርደርን
•የአሜሪካው ፕሬዝደንት ትረምፕ ሽልማቱን ሊያሸንፉ ይችላሉ ተብለው ከተገመቱ ሰዎች መካከል ይገኙበታል።

ነገር ግን...የአየር ለውጥ አክቲቪስቷ ስዊድናዊቷ የ16 ዓመት ታዳጊ ግሬታ ተንበርግ ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷታል። የዘንድሮ አሸናፊ ማን እንደሆነ ከ25 ደቂቃ በኃላ ይታወቃል!!

#ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
5 ደቂቃ የ2019 Nobel Peace Prize!
BREAKING NEWS:

The Norwegian Nobel Committee has decided to award the Nobel Peace Prize for 2019 to Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed Ali.#NobelPrize #NobelPeacePrize

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ2019 የኖቬል የሰላም ሽልማትን አሸነፉ!

የ2019ኙን የሰላም ኖቤል ሽልማት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አሸነፉ፡፡ በአውሮፓዊኑ የዘመን ቀመር 1901 የተጀመረው የኖቤል ሽልማት በተለያዩ ዘርፎች ግለሰብና ድርቶችን ሲሸልም ኖኗል፡፡

በሰላም ዘርፍም የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማትን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በዋናነትም ለኢትዮ-ኤርትራ እርቅ ላደረጉት አስተዋፅኦ በሚል እንዳሸነፉ ሸላሚው ድርጅት ይፋ አድርጓል፡፡

ከጠ/ሚንስትሩ ጋር የማሸነፍ ግምትን የ16 ዓመቷ ስዊድናዊት የአየር ንብረት ተማጋች ግሪታ ቱምበርግ፣ ብራዚላዊው የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ ራኦኒ ሜቱክተይር እና ‘’ሪፖርተርስ ዊዝአውት ቦርደርስ’’ የተባለው የመገናኛ ብዙኃን ዘርፍ ተማጋች ድርጅት የመጨረሻ እጩ ስለመሆናቸው ዓለም ዐቀፍ የመገናኛ ብዙኃን አውታሮች መረጃ አግኝተናል በማለት ሲዘግቡ ሰንብተውም ነበር፡፡ በኖርዊጂያን የኖቤል ኮሚቴ የሚሰጠው የኖቤል የሰላም ሽልማት ከሚያሰጠው ከፍ ያለ እውቅና ባሻገር 743 ሺሕ ፓወንድ እንደሚያሸልምም ይገለፃል፡፡

Via Ahadu TV
@tsegabwolde @tikvahethiopia