TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH ETH FAMILY

"ትላንት ጠዋት 3 ሰአት አካባቢ ከአውቶቢስ ተራ አየር ጤና ታክሲ ውስጥ #samsung ሞባይል ጥሎ የወረደ ካለ ምልክት ተናግሮ መውሰድ ይችላል። ስልኩ ሲም ስለሌለው ባለቤቱን ማግኘት ስለከበደኝ ነው። አመሰግናለው!"

ስልኩ የጠፋበት ሰው ምልክቱን ተናግሮ መውሰድ ይችላል፦ 0912309040 /Hikmet Abdu/

ለሁላችንም ትምህርት የሚሆን ተግባር!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አፍሪፖል

እ.ኤ.አ በመጋቢት ወር 2019 ከአዲስ አበባ ወደ ኬንያ ናይሮቢ በረራዉን ሲያደርግ በነበረዉ ET 302 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዉሮፕላን ቢሾፍቱ ከተማ አቅራቢያ በመከስከሱ የ35 ሀገራት መንገደኞች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡ አደጋዉ ከደረሰ ከሁለት ቀናት በኃላ ኢትዮጵያ በጠየቀችዉ ጥያቄ መሰረት ኢንተርፖል ምላሽ ሰጪ ቡድን በመላክ ምርመራዉን ሲያከናዉን ቆይቷል፡፡ ለህልፈተ ህይወት የተዳረጉትን ለመለየት እንዲረዳዉም ኢንተርፖል የተጎጂ ቤተሰቦች ዲ ኤን ኤ በማሰባሰብ ምርመራ አድርጓል፡፡ ኢንተርፖል ለአደጋዉ ምላሽ ሰጪ ቡድን በማሰማራት ስሰራ የነበረዉን ተጎጂዎችን የመለየት ስራ ከ 6 ወራት በኃላ በተሳካ ሁነታ ማጠናቀቅ መቻሉን አፍሪፖል በድህረ ገፁ ባወጣዉ መረጃ አስነብቧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-04-2

Ethiopian Federal Police Commission

@tsegabwolde @tikvahethiopia
⬆️በDV 2021 ለማመልከት የታደሰ እና የሚያገለግል ፓስፖርት ሊኖሮት ይገባል! ግዴታ ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ከለገ ጣፎ ለገዳዲ ከተማ 50 ፈረሰኞችና በርካታ ፎሌዎች የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው የተለያየ የባህል ትርኢት ላይ ለመሳተፍ ወደ አዲስ አበባ እያቀኑ ነው፡፡

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ነገ መስከረም 24 በሆራ ፊንፊኔ በሚከበረው የኢሬቻ በዓል ላይ ለመሳተፍ ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የመጡ የባህል ቡድኖች አዲስ አበባ እየገቡ ነው፡፡

Via OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ምድረ_ገነት

በምእራብ ጎንደር ዞን በሁመራ በኩል ወደ ምድረ ገነት ከተማ በጭነት ተሸከርካሪ በድብቅ ተጭኖ ሊገባ የነበረ 20 ኩንታል ካናቢስ የተባለ አደንዛዥ ዕፅ መያዙን ፖሊስ ገለፀ ፡፡ የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር አባይ አሻግሬ እንደተናገሩት ትናንት ረፋድ ላይ ሃሺሹ ሊያዝ የቻለው በከተማው ኬላ ላይ በተደረገ ጥብቅ ፍተሻ ነው፡፡

የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3- 8173 አዲስ አበባ የሆነው አይሱዚ ተሸከርካሪ ከጫነው 30 ኩንታል ጥቅል ጎመን ስር አደንዛዥ ዕፁን በድብቅ ጭኖ መገኘቱን ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡ የጭነት ተሸከርካሪው ሃሺሹን ከሻሸመኔ በመጫን በአፋር አድርጎ መቀሌ ፣ ሁመራንና ማይካድራ ከተሞችን በማለፍ በዞኑ ምድረ ገነት ከተባለው ከተማ ሊያዝ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት የመኪናው አሽከርካሪ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ ዋና ኢንስፔክተሩ ተናግረዋል፡፡

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቺክቭ በድሬዳዋ በተከሰተው ወረርሽኝ የተያዙ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ ቢመጣም በሽታው ሙሉ በሙሉ ባለመጥፋቱ የመቆጣጠር ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን የከተማዋ የጤና ቢሮ አስታውቋል። ከወር በፊት “ችጉንጉኒያ” ተብሎ የሚጠራው የበሽታ ወረርሽኝ  በድሬደዋ መከሰቱ ይታወሳል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Baga nagaan Irreecha bara 2019 geessan!
እንኳን ለ2012 ኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!


#TIKVAH_ETHIOPIA
PHOTO: TRAVEL ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገራችን የመጀመሪያ የሆነውን ዳያስፖራ ቅርንጫፍ ከፈተ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ ብቻ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ልዩ ቅርንጫፍ በዛሬው ዕለት አስመረቀ፡፡ ቅርንጫፉን መርቀው የከፈቱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዝዳንትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና፤ ልዩ ቅርንጫፉ ለዳያስፖራው ማህበረሰብ የቤት መሥሪያና መግዣ የብድር አገልግሎት የሚመቻችበት፣ የውጭ ምንዛሪ አገልግሎት፣ ዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎቶች የሚሰጡበት፣ እንዲሁም ሌሎች ለዳያስፖራው የኢንቨስትመንት አማራጮች የሚቀርቡበት ነው ብለዋል፡፡

Via CBE
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጠርጣሪ አመራሮች እና ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ ነው!

በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ተከስቶ በነበረ የፀጥታ ችግር የተጠረጠሩ ግለሰቦችና አመራሮች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ ዋና አዛዥና የኮማንድ ፖስቱ አባል ምክትል ኮማንደር ምናሉ ታደሰ እንደገለጹት ባለፉት ወራት በዞኑ የተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረ ግጭት በሰው ሕይወትና በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በዋናነት በሸኮ ወረዳ በተፈጠረ ግጭት የሰባት ሰዎች ሕይወት ሲጠፋ በ25 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን አስታውሰዋል፡፡

“በግጭቱ ከ4ሺህ 500 በላይ ዜጎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን 322 ሰዎች ሙሉ በሙሉ ንብረታቸው ወድሞባቸዋል” ብለዋል ኮማንደር ምናሉ። በግጭቱ 178 የሳር ክዳንና የቆርቆሮ መኖሪያ ቤቶች ሲቃጠሉ ከ320 በላይ የጦር መሳሪያዎችም መዘረፋቸውን ተናግረዋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ግለሰቦች በወረዳው ተከስቶ በነበረ ግጭት ወንጀሎችን በመፈጸምና በማስፈፀም የተጠረጠሩ መሆናቸውን ኮማንደር ምናሉ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኢሬቻ2012

ነገ በሆራ ፊንፊኔ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ዋዜማ በተለያዩ ፕሮግራሞች እየተከበረ ይገኛል። በፕሮግራሙ ላይ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሰት ምክትል ፕሬዝደንት፣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት የስራ ሀላፊዎችና ሚኒስትሮች ተገኝተዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ ከ49 ኩንታል በሶና ከ3 ሺ 5 መቶ 35 ኪ.ግ ቅቤ የተሰራው 4 ሺህ ሜትር ጩኮ ለእይታ ቀርቧል፡፡

Via #OBN
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምደባችሁን ከ11:30 ጀምሮ ተመልከቱ!

ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ!

ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ምደባ ስለትከናወነ የተመደባችሁበትን ከፍተኛ ት/ት ተቋም ከዛሬ ማለትም 23/01/2012 አ.ም. ከ11: 30 ሰኣት ጀምሮ በአገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዌብ ሳይት ማየት የምትችሉ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ያስታውቃል።

Via Ministry Of Education
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመግቢያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ የዩኒቨርሲቲ ምደባ ስለተጠናቀቀ የተመደባችሁበትን ዩኒቨርስቲ ዛሬ ከ11: 30 ሰዓት ጀምሮ በአገር አቀፍ የት/ት ምዘናና ፈተናዎች ኤጄንሲ ዌብ ሳይት www.neaea.gov.et በመግባት ማየት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

መልካም የትምህርት ዘመን!

via የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🤔የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎች ምደባቸው እንዲመለከቱ መልርክት ካስተላለፈ ከ40 ደቂቃ በላይ ቢሆንም ምደባ መመልከቻው ዌብሳይት እየሰራ አይደለም።

ለሚመለከታችሁ አካላት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
👍የዩኒቨርሲቲ ምደባችሁን መመልከት ትችላላችሁ!

http://twelve.neaea.gov.et/Home/Placement

መልካም የትምህርት ዘመን!
- እኔ ለወገኔ ህይወት የሚሆነው ቀይ አሻራ አሳርፋለው እርሶስ?

#ቀይ_አሻራችንን_እናሳርፍ
#15ኛ_ዙር_የደም_ልገሳ
#ሙስተቅበል

እሁድ ስቴድየም ብሄራዊ የደም ባንክ ቅጥር ግቢ እንገናኝ!

"ቀይ አሻራችንን እናሳርፍ"