TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መቐለ👆

የሰማእታት ቀን ለ31ኛ ጊዜ መቐለ በሚገኘው የሰማእታት ሃውልት ዛሬ ተከብሯል። በበዓሉ ከፍተኛ የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) አመራሮችና የከተማው ነዋሪዎች የተገኙ ሲሆን፣ አመራሮች፣ የሰማእታት ቤተሰቦች፣ ነባር ታጋዮችና አካል ጉዳተኞች ጨምሮ የተለያዩ አካላት በሃውልቱ ስር የጉንጉን አበባ አስቀምጠዋል።

"የሰማእታትን በዓል ስናከብር የወደቁለትን አላማ ከዳር ለማድረስ ቃላችንን በማደስ ሊሆን ይገባል’’ ም/ር/ መስተዳድር ደብረ ጽዮን
.
.
NB. በዛሬው ዕለት የሚታሰበው የሰማዕታት ቀን የደርግ መንግሥት ሰኔ 15 ቀን 1980 በሐውዜን ከተማ ገበያ ከ2ሺህ 500 በላይ ሰላማዊ ዜጎችን በጦር ሄሊኮፕተሮች ድብደባ የጨፈጨፈበት ቀን በመሆኑነው።

Via ኢዜአ
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ቤተሰቦች በደቡብ ኢትዮጵያ! በምስሉ ላይ የጋሞዎችን የባህል ልብስ “ዱንጉዛን” ለብሰው የምናያቸው ቀዳማዊት እመቤት ሳባ ሀይለ፤ አብርሃም ኢሳያስ አፈወርቂ፤ ብርሃነ ኢሳያስ አፈወርቂ እና ኤልሳ ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው። በቅርብ ሳምንታት በደቡብ ኢትዮጵያዊ ተገኝተው ጉብኝት አርገው ነበር።

Via Petros Ashenafi Kebede
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ሥራ አቆመ!

ሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ቴፒ ግቢ በመምህራንና ሰራተኞች ላይ የደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ሥራ አቁሟል፡፡ በመምህራን ላይ የመደፈር፣ ንብረት የመዘረፍና ከሥራ ገበታቸው የመባረር ጥቃት ተፈፅሞባቸዋል ነው የተባለው፡፡ የተለያዩ ሦስት ባንኮችም የዝርፊያ ሙከራ እንደተደረገባቸውና ጭንብል ያጠለቁ የተደራጁ ቡድን ከጥበቃዎች ላይ ማሳሪያ እየለቀመ መውሰዱም ተገልጿል፡፡

Via #VOA
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ማንኛውም ዓይነት ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የሚከለክለውን መመሪያ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። በሞተር ብስክሌት ከሚተዳደሩ ዜጎች የወጣት ጥላሁነ ታደሰ አጭር ታሪክ በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቷል።

Via #walta
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethipia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በምሽት እጄን ጠምዝዞ 6700 ብር የያዘ ቦርሳየን የቀማኝ ሞተር ሳይክል ታርጋ አልነበረውም - በምሽት በሞተር ብስክሌት ዘረፋ የተፈፀመባት ወጣት ታሪክ፤

Via #walta
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ከ100 በላይ የኦነግ ታጣቂዎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ማሕበረሱ መቀላቀላቸው ተገለፀ።

የምዕራብ ጎጂ ዞን አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ አበራ ቡኖ ታጣቂዎቹ ወደ ማሕበረሰቡ የተቀላቀሉት በባህላዊ ሥርዓት መሠረት መሆኑን ለቢቢሲ ገልፀዋል።

የዞኑ አስተዳዳሪ አክለውም የተያዙት ወደ 500 የሚጠጉ ታጣቂዎች መሆናቸውን ተናግረው "113 የሚሆኑት ወደ ማሕበረሰቡ ተቀላቅለዋል። አብዛኞቹ በሰላማዊ መንገድ ነው የተመለሱት" ብለዋል።

ቀሪዎቹ የቀድሞ ኦነግ አባላት በሕዝብ መያዛቸውን የገለፁት ኃላፊ "አንዳንዶቹ የኦነግ አባላት ትጥቅ ሳይኖራቸው" ወደ ጫካ መግባታቸውን ተናግረዋል።

"ከ500 ታጣቂዎች መካከል በወንጀል የተጠረጠሩት ወደ ሕግ ይላካሉ" ያሉት አቶ አበራ ቀሪዎቹ ደግሞ ሥልጠና እንደሚገቡ አስረድተዋል።

ሥልጠናው ታጥቀው ለነበሩት ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ይሰጣል ያሉት አስተዳዳሪው፤ ሕዝቡ ሰላሙን የሚያደፈርሱትን አጋልጦ የሰጣቸው ሰዎች ስለሆኑ 'እንደ እስረኞች አናያቸውም' ብለዋል።

ትጥቅ ባይኖራቸውም ግን በዝርፊያ፣ ግድያ፣ በመድፈር፣ የተጠረጠሩ ሰዎች ተጣርተው ለሕግ ይቀርባሉ ሲሉ ተናግረዋል።

Via #BBC
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የአሜሪካው ፐሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ወደ ጦርነት መግባት እንዳማይፈልጉ የገለፁ ሲሆን ግጭት ከተከሰተ ግን አውዳሚ ወደ ሆነ ሁኔታ እንደሚያመራ አስጠንቅቀዋል፡፡

“ወደ ጦርነት መግባት አልፈልግም፣ነገር ግን ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ አውዳሚ ይሆናል ይህ እንዲሆን ግን ፍላጎት የለኝም” ብለዋል ለኤን ቢሲ በሰጡት ቃለ መጠይቅ ፣ ትራምፕ ኢራን መታ ለጣለችው ድሮን የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድ የታሰበውን መሰረዛቸውንም ሲጂቲን በመረጃው አስፍሯል፡፡

እንደ ዘገባው የኢራን ከመሬት ወደ አየር የተወነጨፈ ሚሳኤል የአሜሪካን አለም አቀፍ የቅኝት ሰው አልባ አውሮፕላን መቶ መጣሉ የሚታወስ ሲሆን ኢራን “የአየር ክልሌን በመጣሱ መትቸዋለሁ “ ስትል አሜሪካን በበኩሏ የአየር ክልሉ አለም አቀፍ የአየር መተላለፊያ ነው ብላለች፡፡

ትራምፕ በቲውተር ገፃቸው ደጋግመው እንደገለፁት ኢራን ላይ የአፀፋ እርምጃ ለመውሰድና ኢራን የኒኩለር ማበልፀግና የሚሳኤል ፕሮግራሟን እንድታቋርጥ የተጣለው የኢኮኖሚ ማእቀብን ለማንሳት እንደማይቻኮሉ መግለፃቸውን ዘገባው አመላክቷል።

🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
2:30 ይጀመራል ተብሎ 5:30 የተጀመረው ስብሰባ...
-----------------------------------------------------------
መሪዎች የሰዓት #ቀጠሮን በማክበር #ለወጣቶች አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ ተቀዳሚ ሙፍቲ ዑመር እድሪስ ጠየቁ። ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ይህን ያሉት ሁለት ሰዓት ከሰላሳ ደቂቃ ይጀመራል ተብሎ ከረፋዱ አምስት ሰዓት በተጀመረው የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር ሰባተኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው። ለጋዜጠኞች የተሰጠው የመግቢያ ካርድ ላይ “ሰዓት ይከበር” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ሰፍሯል። ለዚህም ይመስላል ጋዜጠኞችና ተሳታፊዎች በሰዓቱ ታድመዋል፤ ይሁንና የክብር እንግዶቹ በወቅቱ ሊገኙ ባለመቻላቸው ጉባኤው በሰዓቱ ሊጀመር አልቻለም። የዘገየበትን ምክንያት የገለጸ፣ #ይቅርታ የጠየቀም ሆነ ኃላፊነት የወሰደ አካልም የለም። በጉባኤው የከተማዋ ምክትል ከንቲባና የሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትርን ጨምሮ ከፌዴራልና ከከተማ አስተዳደሩ የተወጣጡ እንግዶችና የማህበሩ አባላት ታድመዋል። ተቀዳሚ ሙፍቲ ዑመር በዚሁ ጊዜ በተለያዩ ቦታዎች የሚካሄዱ ስብሰባዎች በተባሉበት ጊዜ #እንደማይጀመሩ ነው የገለጹት። በተባለበት ሰዓት በመገኘት ቀጠሮ በማክበር መሪዎች ለወጣቶች አርአያ ሊሆኑ እንደሚገባ በመግለጽ አገር፣ ሰላምና አንድነት የጋራ በመሆኑ ወጣቶች አንድነትን በተግባር በማሳየት ሰላምን ሊጠብቁ እንደሚገባም ገልጸዋል።

Via #ENA
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ግብጽ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ14 የአፍሪካ ሀገራት ነጻ የጉበት በሽታ ህክምና ልታደርግ መሆኑ ተሰምቷል። ህክምናው ከመች ጀምሮ እንደሚሰጥ አልታወቀም።

🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Alert‼️

በባህር ዳር ከተማ ተደጋጋሚ የመሳሪያ ተኩስ ድምፅ እየተሰማ እንደሆነ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል። ድምፁ የሚሰማው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ቢሮ አካባቢ እንደሆነ ነው የተጠቆመው። ጉዳዩ ምን እንደሆነ አጣርቼ አሳውቃለሁ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከባህር ዳር...

"ፀግሽ ባህርዳር የርዕሰ መስተዳድሩ ቢሮ አካባባቢ ከፍተኛ #ተኩስ እየተሰማ ነው። መንገዱም ተዘግቷል። Becky ከባህርዳር"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ባህር_ዳር
/ከጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት/

"አሁን በባህር ዳር የሚገኝ ጋዜጠኛ በስልክ እንደነገረኝ "እየተከሰተ ያለው ነገር የከፋ ሳይሆን አይቀርም። ሰዎች በጥይት ተመተዋል እየተባለ ነው። ሁሉም በድንጋጤ ወደየቤቱ ለመግባት እየተሯሯጠ ነው"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሰበር_ዜና በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተደረገ። #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ባህር_ዳር

በፕሬዝደንቱ ጽህፈት ቤት፣ በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን እና በፈለገ ህይዎት ሆስፒታል አካባቢ የተኩስ ልውውጡ አሁንም እንዳለ ተሰምቷል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና #ባህር_ዳር

አካባቢያችሁን በንቃት ጠብቁ ተብሏል...

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉን የጠቅላይ ሚንስትር ፕሬስ ሴክሬተሪ ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን አስታወቁ፡፡ በክልሉ ዛሬ በተደራጀ ሁኔታ በመንግስት መዋቅር ላይ ጥቃት ለመሰንዘር መሞከሩን አቶ ንጉሱ ገልፀዋል፡፡

በክልሉ መፈንቅለ መንግስት በማካሄድ የመሪ ድርጅቱ አዴፓ እና የአማራ ክልል ህዝብ ያገኘውን ነፃነትና ሰላም ለመንጠቅ እንዲሁም በህዝቡና በመንግስት ላይ ጥቃት ለመፈፀም የተደራጀ እንቅስቃሴ መደረጉንም ነው አቶ ንጉሱ የገለፁት፡፡

የተደረገውን የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ የፌደራል መንግስት የፀጥታ መዋቅር ክልሉን በተለይም ባህርዳር ከተማና አካባቢውን በቁጥጥር ስር አውሎ በተግባሩ የተሳተፉት ላይ እርምጃ ለመውሰድ ትእዛዝ መሰጠቱም ተገልጿል፡፡ ህብረተሰቡም አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ጥሪም ቀርቧል፡፡

Via #etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Breaking #ባህር_ዳር

አልፎ አልፎ ከሚሰማ ተኩስ ውጭ፣ የተኩስ ልውውጡ ቆሟል። #elu

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰበር_ዜና #ባህር_ዳር

በአማራ ክልል የተሞከረው መፈንቅለ መንግስት #መክሸፉን አቶ ንጉሱ ጥላሁን ተናግረዋል። ይህንን ድርጊት በፈፀሙት ላይ #እርምጃ እንዲወሰድ ትእዛዝ ተሰጥቷል፤ እንቅስቃሴም ተጀምሯል ሲሉ ገልፀዋል።

Via #etv/#Elias_Meseret/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥንቃቄ #ባህር_ዳር

"ባህርዳር መንገዶች ተዘግተዋል። አሁንም የተኩስ ድምፅ ይሰማል። ሰላማዊ ሰዎች በዚህ የተኩስ ልውውጥ የጥቃቱ ሰለባ እንዳይሆኑ መደወል የምትችሉ ሰዎች ደውላችሁ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አድርጉ። ይህንን መልዕክት የደረሳችሁ ባህር ዳር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እላለሁ። ሰላም ለባህር ዳር!"

Via Seyum Argaw
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ላይ የተደረገው የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ የሀገሪቱን ሕገ መንግሥት የሚፃረር፣ የክልሉ ሕዝብና መንግሥት ለረጅም ጊዜ የታገሉለትን ሰላምና መረጋጋት ለመንጠቅ የተደራጀ በመሆኑ የፌደራል መንግሥት ሙሉ በሙሉ እንደሚያወግዘው የጠቅላይ ሚንስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ።

የፌደራል መንግሥት የጸጥታ መዋቅር የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥር ሥር አውሎ በፈጸሙት አካላት ላይ ተገቢውን ርምጃ እንዲወስድ ትእዛዝ ተቀብሎ ተፈጻሚ በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ጥቃት በመንግሥት መዋቅር ላይ ብቻ ሳይሆን በአማራ ሕዝብ ላይ የተቃጣ መሆኑን በመገንዘብ የክልሉ ሕዝብ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅና ተረጋግቶ ሁኔታዎችን እንዲመለከት ጥሪ ቀርቧል።

ይህን ሕገ ወጥ ሙከራ ክልሉ ብቻ ሳይሆን ማንኛውም ክልልና መላው ኢትዮጵያዊ ሊያወግዘው የሚገባ ሲሆን የፌደራል መንግሥት የታጠቁ ቡድኖችን ሕገ ወጥ እንቅስቃሴ የመቀልበስ፣ የመግታትና በቁጥጥር ሥር የማዋል ሙሉ ዐቅም ያለው መሆኑን ያረጋግጣል።

Via #PMOEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህር_ዳር

"አሁን ላይ ባህር ዳር ተኩሱ ቆሟል። መረጋጋት እየተፈጠረ ነው። የአማራ ልዩ ኃይል ሁኔታውን እያረጋጋ እንደሆነ ታውቋል።" #በላይ_ማናዬ

@tsegabwolde @tikvahethiopia