TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች🔝በትላንት ዕለት በተካሄደው #ታላቁ_ሩጫ_በኢትዮጵያ ላይ ከታዩት የፍትህ ጥያቄዎች አንዱ ነው። "ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሶሳ🔝

የአማራ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤቶች የጋራ #ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ በአጎራባች ወረዳዎች ዘላቂ ሰላም ለመፈጠር፣ ችግሮች ሲያጋጥሙ በዴሞክራሲያዊ መንገድ ለመፍታት እና በፖለቲካዊ ዘርፎችም በጋራ ለመሥራት ስምምነቱ ተፈርሟል ነው የተባለው።

ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ የልምድ ልውውጥ ለማድረግ፣ አሠራሮችን በማሻሻል ለወከሉት ሕዝብ በግልጽነትና በተጠያቂነት ለማገልገል፣ የተጀመረውን ለውጥም አጠናክሮ ለማስቀጠል ነው ስምምነቱን የአማራና ቤኒሻንጉል ክልል ምክር ቤቶች ትላንት የተፈራረሙት፡፡

የጋራ መድረክ በመመሥረትም በዓመት ሁለት ጊዜ እየተገናኙ ለመምከር ምክር ቤቶቹ ስምምነት አድርገዋል፡፡ ስምምነቱ አንድ የጋራ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ማኅበረሰብ ለመገንባት የሚደረገውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት መሆኑም ተነግሯል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Deleted Account
Forwarded from Deleted Account
🇪🇹| ወደ ኢትዮጵያ በቀላሉና በርካሽ ዋጋ መደወል ይፈልጋሉ?

የRingAround Appን በስልካችሁ ላይ ጫኑ!
ዛሬውኑ ሲጭኑት
በሰሜን አሜሪካ $2 የመደወያ ዶላርን በነፃ እንሰጣለን!
በአውሮፓና በአውስትራልያ $1 የመደወያ ዶላርን በነፃ እንሰጣለን!

ለመጫን --> https://ringaround.lpages.co/et-tikvah-downloadringaroundapp
ዋሽንግቶን ዲሲ🔝በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ደብረ ሃይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን፣ በዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮዽያ አምባሳደር ካሳ ተክለብርሃን "ለቤተክርስቲያን አንድነት ላደረጉት ጥረት" #ዕውቅና ሰጥቷል።

ምንጭ:- ኢትዮጵያ ላይቭ ሀፕዴት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ወላይታ🕊ሲዳማ!

ትናንት "ፍቅር በደልን አይቆጥርም " በሚል መርህ በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር ለማጠናከር የሚያግዝ የዕርቅና
የሰላም ኮንፈረንስ በሀዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል አዳራሽ ተካሂዷል።

በኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የደኢህዴን ሊቀ መንበርና የኢፌደሪ የሠላም ሚኒስቴር ሚኒስትሯ ወይዘሮ #ሙፈሪሀት_ካሚል፥ በሲዳማና በወላይታ ሕዝቦች መካከል ሰላም ሰፍኖ ዕርቅና የሠላም ኮንፈረንስ እንዲካሄድ ትልቅ አስተዋፅኦ የነበራቸውን አባቶች አመስግነዋል፡፡

ሰላም በእያንዳንዳችን ልቦና እና ቤት የሚገኝ በኛው ጥበቃ የሚጎለብት በመሆኑ ልንጠብቀው ይገባል ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ወጣቶች ሰላምን ከሚያደፈርሱ ቆስቋሽ ድርጊቶች እንዲጠበቁም አሳስበዋል፡፡

በዕርቁ ሥነ ሥርዓት ላይ ከሲዳማና ወላይታ ዞን የተወጣጡ የኃይማኖት መሪዎችና አባቶች፣ ከሁለቱም ዞኖች የተወጣጡ የባህል ሽማግሌዎችና ወጣቶች፣ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የኦሮሞ አባ ገዳዎች እና ጥሪ የተደረገላቸዉ ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ምንጭ፦ arts tv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ባህር ዳር🔝

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ላይነር በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ላይነር በባሕር ዳር ጉብኝት እያደረጉ ነው፡፡

አምባሳደሩ ከባሕር ዳር ከንቲባ ከሙሉቀን አየሁ ጋር ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይታቸውም ሶስት አበይት ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ፣በጣና ላይ የተጋረጠው እንቦጭ እና በግንባታው ዘርፍ ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ እንዲመጡ ምን መደረግ እንዳለበት ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ማይክል የወጣቶች ስራ እድል ፈጠራ፣በክልሉ መስህቦች ላይ በተጋረጡ ጉዳዮች እና ባለሀብቶች ወደ ከተማዋ እንዲመጡ ከአቻ አሜሪካ ከተሞች ጋር በጋራ እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡ ቅርሶች ላይ አሜሪካ እየሰራች ነው፡፡ በቀጣይም እቅዷን ይፋ እንደምታደርግም ገልጸዋል፡፡

አምባሳደር ማይክል ራይነር ዛሬ ከሰዓተ በኋላ ደግሞ በባሕር ዳር የሚገኘውን የገነሜ ቤተመጽሀፍትን ይጎበኛሉ፡፡ቤተመጽሀፍቱም በኢምባሲው ወጪ እድሳት ይደረግለታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

አምባሳደር ማይክል ራይነር ዛሬ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳርጋቸው ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ማይክል ራይነር አምባሳደር ሆነው ከተሾሙ በኋላ የመጀመሪያ ጉብኝት ያደረጉት ባሕር ዳር መሆኑ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegawolde @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶክተር ዐብይ🔝

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር #ዐቢይ_አህመድ የተባባሩት መንግሥታት ድርጅት የኤች አይቪ ኤይድስ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሓፊ የሆኑት ሚሼል ሲዲቤን ዛሬ ጠዋት አነጋገሩ፡፡

በመካሄድ ላይ ባለው የማሻሻያ እንቅስቃሴ አማካኝነት አፍሪካንና ኢትዮጵያን በተመለከተ ያለውን ትርክት ለመለወጥ ያላቸውን ቁርጠኝነት አጽንኦት በመስጠት የተናገሩት ዶ/ር ዐቢይ ሕዝብን ማዕከል ያደረገ የጤና ልማት ጥረትን ለማጠናከር ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር ተስማምተዋል፡፡

ምንጭ፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኮንጎ‼️

የዓለም ጤና ድርጅት ሰራተኞቹን ከምስራቃዊ ኮንጎ #አሸሸ። የድርጅቱ ሰራተኞች #የኢቮላ_ወረረሽኝ በተስፋፋባት ቤኒ በሽተኞችን እየረዱ በነበሩበት ወቅት በአማፂያንና በሰላም አስከባሪዎች መካከል በተፈጠረ ግጭት ሳቢያ ነው አካባቢውን ለቀው የወጡት፡፡

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው የጤና ባለሞያዎቹ የሚኖሩበት ህንጻ በተኩስ ልውውጡ ወቅት በመሳሪያ ተመቷል፡፡

ሰራተኞቹ ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም የዓለም ጤና ድርጅት በቤኒ ግዛት የኢቮላ ወረርሽን ከተከሰተ ወዲህ የስጋቱ መጠን በማየሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የጤና ባለሞያቹን ለማሸሽ ተገዷል፡፡

የዲሞክራቲክ ኮንጎ የጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በግጭቱ ምክንያት ኢቮላን የመከላከሉ ተግባር በመስተጓጎሉ የበርካቶች ህይዎች አደጋ ላይ ነው፡፡

ባለፈው ሳምንት ስድስት የማላዊ ዜግነት ያላቸው የሰላም አስከባሪ ወታደሮች በአማፂዎቹ መገደላቸው ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ አርትስ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ ክልል‼️

በደቡብ ክልል ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ ሊሻገሩ ነበር የተባሉ 25 ኤርትራውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። ወጣቶቹ በኬንያ አቋርጠው #ኡጋንዳ የመግባት እቅድ እንደነበራቸው ፖሊስ ገልጿል።

ኤርትራውያኑ ሐሙስ ዕለት የተያዙት በክልሉ በደቡብ ኦሞ ዞን፤ ሐመር ወረዳ ውስጥ ቱርሚ በተባለች አነስተኛ የጠረፍ ከተማ ላይ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር #ካሳ_ካውዛ ለDW ተናግረዋል፡፡ ኤርትራውያኑ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ
መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

“የተያዙበት ምክንያት ባልተለመደ ሁኔታ ወደዚያ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከደረሱ በኋላ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ወደ ጭነት መኪና ተዛውረው ሊጓዙ ሲሉ በፖሊስ ጥርጣሬ ተይዘዋል። ሲታዩ ያው በኬንያ በኩል ወደ ኡጋንዳ ካምፓላ መድረስ እንፈልጋለን የሚሉ ወጣቶች
ነበሩ። ወጣቶቹ እነርሱ እንደሚሉት የኤርትራ ዜጎች ነን ነው። በእጃቸው ላይ የያዙት አንዳንድ መታወቂያዎችም ከኤርትራ ትምህርት ቤት የተነሱ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። አሁን ወደ ዞናችን ፖሊስ መምሪያ አስመጥተን ወጣቶቹን በዚያው በዞናችን ፖሊስ መምሪያ ግቢ ውስጥ ይገኛሉ” ሲሉ የዞኑ የፖሊስ ኃላፊ ወጣቶቹ እንዴት ሊያዙ እንደቻሉ አስረድተዋል።

ዋና ኢንስፔክተር ካሳ ወጣቶቹን በተመለከተ በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከክልሉ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ እስከአሁን በፖሊስ እጅ በሚገኙት ኤርትራዊያን ጉዳይ ላይ ያለው ነገር አለመኖሩን ተዘግቧል።

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia