TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ⬆️ለከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እየተሰጠ የሚገኘው የ2 ቀን ስልጠና እንደቀጠለ ይገኛል።

ፎቶ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የባለስልጣናት ሀብት⬇️

የፌደራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በመጀመሪያ ዙር የ450 የመንግሥት ባለስልጣናትና ሠራተኞችን ሃብት ለህዝብ -ክፍት ለማድረግ የሶፍትዌር #ሙከራ ላይ መሆኑን አሳውቋል።

የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር አቶ አየልኝ ሙሉዓለም እስካሁን የ150 ሺህ ባለስልጣናት እና የመንግስት ሠራተኞች ሃብት በመመዝገብ ለህዝብ ክፍት የማድረጊያ ሶፍትዌር ከህንድ ኩባንያ ጋር በመተባበር ወደ ትግበራ መግባቱን ገልጸዋል።

የሶፍትዌር ትግበራው ለሙስና የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ የሆኑ ተቋማት ሃላፊዎችንና ሠራተኞችን ሀብት ይፋ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

እስካሁን የ80 ግለሰቦች የሀብት መረጃ ወደ ሶፍትዌሩ መመዝገባቸውን የገለጹት ኮሚሽነሩ የማሻሻያ ስራዎች ከተጠናቀቁ በኋላ ለህዝብ ክፍት እንደሚሆን ተናግረዋል።

ሙከራው ሲጠናቀቅ ማንኛውም ግለሰብ የሚፈልገውን የሀብት ምዝገባ መረጃ በስነምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ቢሮዎች በአካል ቀርቦ መመልከት እንደሚችልም ነው የጠቀሱት።

የሀብት ምዝገባ መረጃው ለህዝብ ክፍት የሚሆንበት ጊዜ ባይጠቀስም በቅርቡ እንደሚጀመር ግን ኮሚሽነር አቶ #አየልኝ ጠቁመዋል።

የሀብት ምዝገባ መረጃዎች እስከዛሬ ለህዝብ ክፍት ያልተደረገው ከስራው ውስብስብነትና በሶፍትዌሩ አለመጠናቀቅ መሆኑን ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ኮሚሽኑ ላለፉት ዓመታት በሰው ሃይል እጥረት፣ በስራው ውስብስብነትና አቅም ማነስ ምክንያት የሀብት ማጣራት ስራ እንዳልሰራም ነው ኮሚሽነሩ ያነሱት።

አቶ አየልኝ በዘንድሮው በጀት ዓመት የ80 ግለሰቦች ሀብት እየተጣራ እንደሚገኝ ገልጸው ከዚህም ውስጥ የ23ቱ በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UpdateSport ኢትዮጵያ ቡና የ2011 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።

ኢትዮጵያ ቡና 4-1 ባህር ዳር ከተማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኒይዎርክ⬇️

የአሜሪካዋ ኒይዎርክ ከተማ በ25 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ለአንድ ሳምንት #በተኩስ ሰው #ሳይሞት ማሳለፏ ተገለጸ፡፡

ባለፈው ሳምንት አንድም የተኩስ ሪፖርት ለከተማው ፖሊስ አለመድረሱንና ይህም በሃያ አምስት ዓመት ግዜ ውስጥ ሆኖ እንደማያውቅ የተናገረው የከተማው ፖሊስ ነው፡፡

የኒዎርክ ከተማ ከንቲባ ቢል ዲ ብላሶ በከተማው ምንም አይነት ተኩስ አለመሰማቱና በተኩስ ሰው አለመሞቱ በጣም የሚገርምና አስደናቂ ሲሉ ገልጸውታል፡፡

ስምንት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ኒይዎርክ ላይ አንድም የጥይት ተኩስ አለመሰማቱ የከተማው ፖሊስ የስራ ውጤት በመሆኑ ትልቅ ምስጋና ይገበዋል ብለዋል፡፡

የኒዩርክ የንዩፒዲ ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዋና ሃላፊ ሎሊፕሎክ እንደተናገሩት በከተማው በጥይት የሚደርስ ግድያ በየግዜው እየቀነሰ የመጣ ሲሆን በመሰከረም ወር ደግሞ በታሪክ ዝቅተኛው ግድያ የተፈጸመበት እንደሆነ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በከተማው ለተገኘው ከፍተኛ ውጤት የማህበረሰብ አቀፍ ፖለስ አገልግሎት ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱ መሆኑን የፖሊስ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ ፡-ሲኤንኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ሂዩማን ራይትስ ዎች⬇️

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሂዩማን ራይትስ ዎች ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የአፈና ስልቶችን #እንዲያስቆሙ ጠየቀ። በኢትዮጵያ በቅርቡ የተካሄዱት የጅምላ እስሮች እና "አመለካከትን የመቀየር ስልጠናዎች" ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጀመሯቸውን ፖለቲካዊ #ማሻሻያዎች አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው ብሏል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተሃድሶ ስልጠና የሚሰጥባቸውን ካምፖች #እንዲዘጉ እና የዘፈቀደ እስርንም በማስቆም ቁርጠኝነታቸውን እንዲያሳዩም አሳስቧል።

ምንጭ፦ DW የአማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር #ሬድዋን_ሁሴን የሹመት ደብዳቤያቸውን ለኤርትራው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኦስማን ሳልህ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ ነገ ጥዋት 2:00 ወደ እናት ሀገሩ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አቶ #ጌታቸው_ኣሰፋ የትግራይ ክልል ር/መስተዳደር የጸጥታ እና የደህንነት #አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።

ምንጭ፦ Getu Temesegen
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ ኢትዮጵያ- አዲስ አበባ ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሐረር⬆️ሐረር ከተማ ላለፉት ስድስት ወራት #ውሃ ተጠምታለች፣ በቆሻሻም ታፍናለች - የዚህ ምክንያቱ በአጎራባች አካባቢዎች ያሉ ወጣቶች በ5 ቀን ውስጥ 10 ሚሊየን ብር እንዲከፈላቸው በመጠየቅ የውሃ መስመሩን በመስበራቸውና ቆሻሻም አናስደፋም በማለታቸው ነው። እስካሁን ድረስ ከምሰራቅ ኦሮሚያ የሥራ ሃላፊዎች፣ አባገዳዎች፣ የሐይማኖት አባቶች እና ቄሮዎች ጋር ምክክር ቢደረግም መፍትሄ አልተገኘም። ወጣቶቹ ከውሃ ማጣሪያ ጣቢያ ሰራተኛው ቁልፉን #ነጥቀው ወስደዋል፣ ሞተሮቹን አጥፍተዋል፣ የውሃ መስመሩንም ሰብረው ውሃው በከንቱ እየፈሰሰ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር 102.1
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በሰለም ገብቷል⬆️አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ ወደ ኢትዮጵያ በሰላም ገብቷል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አትሌት #ፈይሳ_ሌሊሳ አዲስ አበባ ገብቷል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia