#update ኒይዎርክ⬇️

የአሜሪካዋ ኒይዎርክ ከተማ በ25 ዓመት ጊዜ ውስጥ ለመጀመሪያ ግዜ ለአንድ ሳምንት #በተኩስ ሰው #ሳይሞት ማሳለፏ ተገለጸ፡፡

ባለፈው ሳምንት አንድም የተኩስ ሪፖርት ለከተማው ፖሊስ አለመድረሱንና ይህም በሃያ አምስት ዓመት ግዜ ውስጥ ሆኖ እንደማያውቅ የተናገረው የከተማው ፖሊስ ነው፡፡

የኒዎርክ ከተማ ከንቲባ ቢል ዲ ብላሶ በከተማው ምንም አይነት ተኩስ አለመሰማቱና በተኩስ ሰው አለመሞቱ በጣም የሚገርምና አስደናቂ ሲሉ ገልጸውታል፡፡

ስምንት ነጥብ ስድስት ሚሊዮን ሰዎች የሚኖሩባት ከተማ ኒይዎርክ ላይ አንድም የጥይት ተኩስ አለመሰማቱ የከተማው ፖሊስ የስራ ውጤት በመሆኑ ትልቅ ምስጋና ይገበዋል ብለዋል፡፡

የኒዩርክ የንዩፒዲ ፖሊስ የወንጀል መከላከል ዋና ሃላፊ ሎሊፕሎክ እንደተናገሩት በከተማው በጥይት የሚደርስ ግድያ በየግዜው እየቀነሰ የመጣ ሲሆን በመሰከረም ወር ደግሞ በታሪክ ዝቅተኛው ግድያ የተፈጸመበት እንደሆነ ጨምረው ተናግረዋል፡፡

በከተማው ለተገኘው ከፍተኛ ውጤት የማህበረሰብ አቀፍ ፖለስ አገልግሎት ላይ ትኩረት ተደርጎ መሰራቱ መሆኑን የፖሊስ ሃላፊው ተናግረዋል፡፡

ምንጭ ፡-ሲኤንኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia