TIKVAH-ETHIOPIA
1.47M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንድታውቁት

" መኪና አቁሞ መሄድ ፍጹም የተከለከለ ነው " - ፖሊስ

የኮሪደር ልማት ስራዎቻቸው ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት መንገዶች ላይ ተሸከርካሪዎችን አቁሞ መሄድ ክልክል መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ከ5ቱ የኮሪደር ልማት ስራዎች ውስጥ ፦

➡️ ከአራት ኪሎ እስከ ቅ/ማሪያም ቤ/ክርስቲያን መታጠፊያ
➡️ ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መሐሙድ ሙዚቃ ቤት እንዲሁም
➡️ ከቀይ ባህር ኮንዶሚኒየም በደጎል አደባባይ እስከ ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን አቅጣጫ መንገዱ ትላንት ተከፍቶ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ፤ ለአገልግሎት ክፍት በተደረጉት መንገዶች ላይ ተሸከርካሪዎችን አቁሞ መሔድ ፍጹም ክልክል መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ነገ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆነዋል።

የ1445ኛው የኢድ አል አድሃ (አረፋ) በዓል ነገ ይከበራል።

የኢድል አል አድሃ (አረፋ) በዓል ሶላት ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅም ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

የሶላት ስነስርዓቱ የሚካሄደው በአዲስ አበባ ስታዲዮምና በዙሪያው በሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ላይ ነው።

ይህ ተከትሎ ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ የሶላት ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

በዚህም መሰረት ፦

- ከፒያሳ በቸርችል ጎዳና ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ቴዎድሮስ አደባባይ ላይ

- ከጎተራ ማሳለጫ ወደ ስታዲዮም የሚወስደው አጎና ሲኒማ ላይ

- ከሜክሲኮ ወደ ለገሃር የሚወስደው መንገድ ሜክሲኮ አደባባይ ላይ

- ከብሔራዊ ቤተመንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ፓርላማ መብራት ላይ

- ከኦሎሚፒያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመገናኛ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን የሚወስደው መንገድ 22 መስቀለኛ መንገዱ አካባቢ

- ከጥቁር አንበሳ ሼል ወደ ለገሀር የሚወስደው መንገድ ጥቁር አንበሳ ሼል አጠገብ

- ከሲግናል እና ከአቧሬ ወደ ካዛንቺስ የሚመጣው መንገድ አቧሬ ሴቶች አደባባይ ላይ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ መስቀል አደባባይ የሚመጣው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከቄራ በአዲሱ መንገድ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን የሚወስደው መንገድ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን መገንጠያ ላይ

- ከጌጃ ሰፈር በሰንጋተራ ወደ ለገሐር ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ሰንጋ ተራ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት አካባቢ

- ከአብነት በጌጃ ሰፈር ወደ ብሔራዊ ቴአትር የሚወስደው መንገድ ጎማ ቁጠባ አጠገብ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በሜትሮሎጂ ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሜትሮሎጂ መ/ቤት ላይ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የኋላ በር ወደ ብሔራዊ ቴአትር ለሚሄዱ ጥቁር አንበሳ ሼል ድሬንስ አካባቢ

- ከተክለ ሐይማኖት አካባቢ በጎላ ሚካኤል ውስጥ ለውስጥ ወደ ለገሐር ለሚሄዱ ጎላ ሚካኤል መስቀለኛው ላይ ይለፍ ለሌላቸው ተሽከርካሪዎች ከለሊቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ዝግጅቱ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ ይሆናሉ።

ህብረተሰቡ ይህንን ተገንዝቦ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም ጥሪ ቀርቧል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከኮሪደር ስራው ጋር በተያያዘ ከመገናኛ ወደ ቦሌ የሚወስደው መንገድ ከሃያት ሆስፒታል በኋላ ከነገ ሰኔ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት ሙሉ ቀንና ምሽትን ጨምሮ ለማንኛውም አይነት ተሽከርካሪ ዝግ እንደሚደረግ ተገልጿል።

አሽከርካሪዎች ሃያት ሆስፒታል ጋር ሳይደርሱ በፊት እና ከሆስፒታሉ አጠገብ ያሉትን የቀኝ መታጠፊያዎችን እንዲጠቀሙ የአ/አ ከተማ የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ጥሪ አቅርቧል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

ነገ ለስራ ይሁን ዘመድ ጥየቃ ወይም ደግሞ ለተለያየ ፕሮግራም ከቤት የምትወጡ ካላችሁ የሚዘጉ መንገዶች ይኖራሉ።

መንገዶች የሚዘጉት  80ኛውን የመቻል ስፖርት ቡድን ምስረታን ምክንያት በማድረግ በሚካሄድ የጎዳና ላይ ሩጫ ነው።

ሩጫው 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ሲሆን መነሻ እና መድረሻውን መስቀል አደባባይ ነው።

በዚህም ፦

- ከብሔራዊ ቤተመንግሥት ወደ መስቀል አደባባይ

- ከካዛንቺስ ወደ ባምቢስ

- ከኦሎምፒያ አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ

- ከጥላሁን አደባባይ ወደ ሳንጆሴፍ መብራት

- ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ

- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ከንጋቱ 11:00 ሰዓት ጀምሮ ሩጫው እስከሚጠናቀቅ ለተሽከርካሪ ዝግ አንደሚሆኑ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት  #አዲስአበባ

ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች ይኖራሉ።

ስለሆነም ነገ ለስራ፣ ለቤተሰብ ለጓደኛ ጥየቃ ለሌላም ጉዳዮች ፕሮግራም የያዛችሁ ፕሮግራማችሁን ከልሱ።

መንገድ የሚዘጋው " ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም " በሚል የጎዳና ላይ ሩጫ ስለሚካሄድ ነው።

ሩጫው መነሻውን መስቀል አደባባይ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

ከዛም በባምቢስ፣ ዑራኤል አደባባይ ወደ ቀኝ፣ ፒኮክ መናፈሻ ፣ ሰላም መንገድ ፣ በወሎ ሰፈር ፣ ደንበል ፣ ፍላሚንጎ በማድረግ መስቀል አደባባይ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡

በዚህም  ፦
- ከ22 ወደ ዘሪሁን ህንፃ
- ከዘሪሁን ህንፃ ወደ ዑራኤል አደባባይ
- ከአትላስ መብራት ወደ ዑራኤል አደባባይ
- ከቦሌ ሩዋንዳ መታጠፊያ ወደ ወሎ ሠፈር
- ከወሎ ሠፈር ጀምሮ እስከ ጋዜቦ አደባባይ ውስጥ ውስጡን ወደ ዋናው መንገድ የሚያስወጡት መንገዶች
- ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ኦሎምፒያ አደባባይ
- ከኤግዚብሽን ወደ ፊላሚንጎ
- ከጥላሁን አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ
- ከለገሃር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከቴሌ ማቋረጫ (ክቡ) ባንክ ወደ ስታድየም
- ከሀራምቤ መብራት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ
- ከካዛንቺስ ሼል (ኢንተር ኮንትኔታል ሆቴል) ወደ ባምቢስ
- ከዑራኤል አደባባይ ላይ እና ታች ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ መንገዶች ከንጋቱ 11:30 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ከዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ጀምሮ ደግሞ በተጠቀሱ መንገዶች ላይ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ተከልክሏል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት #አዲስአበባ

በኮሪደር ስራ ምክንያት ፦

➡️ ከፊጋ መስመር ወደ ቀኝ ታጥፎ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

➡️ ከጃክሮስ መስመር በኩል መብራቱን ተሻግሮ ወደ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

➡️ ከኢፌዴሪ የማዕድን ሚኒስቴር ጫፍ ታጥፎ ወደ ሰዓሊተ ምህረት አደባባይ

ከዛሬ ጀምሮ ላልተወሰኑ ቀናት ከጠዋቱ 12:00 ሰዓት አንስቶ ሙሉ ቀን እና ምሽት ለማንኛውም ተሽከርካሪ ዝግ እንደሆኑ ተገልጿል።

ሌላው ፤ ከአያት ወደ መገናኛ እና ከመገናኛ ወደ አያት ቀጥታ ማለፍ እንጂ አደባባዩን መዞርም ሆነ ማቋረጥ የተከለከለ ነው ተብሏል።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙም መልዕክት ተላልፏል።

መረጃው ከአ/አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ነው የተገኘው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ ከተማ ደንብ ማስከበር ባለስልጣን የተሻሻሉ የቅጣት እርከኖች ፦

🗑 ለማንኛውም ግለሰብ/ድርጅት

- ደረቅ ቆሻሻ በግቢው ውስጥ በአግባቡ አለመያዝ፤ በዓይነት አለመለየት፤ ማዝረክረክ፤ ለጤናና የአካባቢ ገጽታ በሚጎዳ መልኩ ማከማቸት፤ ለግለሰብ 2 ሺ ብር ለድርጅት 50 ሺ ብር ቅጣት

- የሲጋራ ቁርጥራጭ፣ የሶፍት ወረቀት፣ ፌስታል የመሳሰሉት ጥቃቅን ደረቅ ቆሻሻን ባልተፈቀደ ቦታ ወይም በፓርኮች፣ በአረንጓዴ ቦታ፣ በኮሪደር ከጣለ 2 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከመኖሪያ ቤት ወይም ከድርጅት ግቢ ውጭ ያለውን የአካባቢ ንጹህና አረንጓዴ አድርጎ አለመጠበቅ ከመኖሪያ ቤት አጥር ግቢ ውጭ እስከ 5 ሜትር ርቀት አለማጽዳት፤ 20 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከድርጅት/ተቋም አጥር ግቢ ውጭ እስከ 10 ሜትር አለማጽዳት፤ 100 ሺ ብር ቅጣት

- ወቅታዊና ልዩ ዝግጅት አከናውኖ በዓሉ ሲጠናቀቅ በዕለቱና ወዲያው ዝግጅቱ የተከናወነበትን አካባቢ ከቆሻሻ ያላጸዳ የፕሮግራሙ አዘጋጅ፤ 50 ሺ ብር ቅጣት

- ዓመታዊ፤ ወርሃዊና ሳምንታዊ የእምነት በዓላት ሲከናወኑ ዝግጅቱ ሲጠናቀቅ የዝግጅቱ ባለቤት በዕለቱና ወዲያው አካባቢውን ካላጸዳ፤ 20 ሺ ብር ቅጣት ይጣልባቸዋል።

🗑 ለጽዳት አገልግሎት ሰጭ ድርጅት/ማኅበራት፦

- ማኅበሩ ደረቅ ቆሻሻ ሲሰበስብ ገጽታ ካበላሸ 25 ሺ ብር ቅጣት፤

- ከጽዳት አስተዳደር ኤጀንሲ እውቅና ውጭ የአገልግሎት ክፍያ ከደንበኛው ከተቀበለ  50 ሺ ብር ቅጣት፤

- ጊዜያዊ የደረቅ ቆሻሻ ማስቀመጫ ቦታዎችን እስከ 5 ሜትር ዙሪያ ድረስ ጽዱ ካላደረገ 50 ሺ ብር ቅጣት ይጣልበታል።

Credit ➡️ @tikvahethmagzine

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት

" ከዛሬ ጀምሮ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ የተቃራኒ ጉዞ ተከልክሏል " - የትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ

በአዲስ አበባ፣ ከአያት አደባባይ ወደ መገናኛ ፤ ከመገናኛ ወደ አያት አደባባይ ድረስ በስራ የመውጫ እና የመግቢያ ሰዓቶች ላይ ይፈጠር የነበረውን የትራፊክ መጨናነቅ ለመቀነስ በሚል በጊዜያዊ መፍትሄነት ከአያት አደባባይ እስከ ሴንቸሪ ሞል በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ ተፈቅዶ ነበር።

ነገር ግን መጨናነቁን ይፈጥር የነበረው የሳዕሊተ ምህረት አደባባይ በመቀየሩ ከዛሬ ነሐሴ 6 ቀን 2016 ዓ/ም ጀምሮ በሁለቱም መስመሮች የተቃራኒ ጉዞ መከልከሉን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

አሽከርካሪዎች ይሄን ተገንዝበው የመደበኛ የጉዞ መስመሮችን ብቻ እንዲጠቀሙ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

#AddisAbaba #TMA

#TikvahEthiopia
@TikvahEthiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#እንድታውቁት🚨

በአዲስ አበባ የጭነት ፣ ማሽነሪዎችን እና መሰል ተሸከርካሪዎችን እንቅስቃሴ ለመወሰን የወጣ መመሪያ ቁጥር 149/2016 ምን ይላል ?

- መመሪያው ወደ አዲስ አበባ ከተማ ክልል በሚገቡና በከተማ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ እንዲሁም ከተማዋን አቋርጠው በሚያልፉ የመጫን አቅማቸው ከ1 ቶን ወይም ከ1ዐ ኩንታል በላይ የሆኑ የተለያዩ የፈሳሽና የደረቅ ጭነት ተሽከርካሪዎች እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡

- ማንኛውም የጭነት ማመላለሻ ተሽከርካሪ እና የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ከጠዋቱ 1፡00 እስከ 3፡00 ሰዓት ከሰዓት በኃላ ከቀኑ 10፡30 እስከ ምሽቱ 1፡ዐዐ ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ፣ ጭነት መጫንም ሆነ ማራገፍ እንዲሁም በዋና ዋና የትራፊክ ፍሰት በሚበዛባቸው መንገዶች ላይ መቆም የተከለከለ ነው፡፡

- በዚህ መመሪያ መሠረት ወደ ከተማ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ የተከለከለ የጭነት ተሽከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ወደ ከተማ ለመግባት በእንቅስቃሴ ላይ እያለ የሰዓት ገደቡ ቢደርስበት በከተማዋ መግቢያ በሮች ላይ ከዋና መንገድ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቦታ ላይ የአካባቢውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማያውክ መልኩ በመቆም የሰዓት ገደቡ እስኪያልፍ መጠበቅ አለበት።

- ማንኛውም የጭነት ተሽከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ በከተማ ውስጥ በእንቅስቃሴ ላይ እያለ በዚህ መመሪያ የተደነገገው የጊዜ ገደብ ቢደርስበት የአካባቢውን የትራፊክ እንቅስቃሴ በማያውክ መልኩ ከመንገድ በመውጣት መቆም አለበት።

- በዚህ መመሪያ የተደነገገው የሰዓት ገደብ #እሁድ እና #የበዓል_ቀናት ላይ ተግባራዊ የማይደረግ በመሆኑ ማናቸውም የጭነት ተሸከርካሪ ወይም የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ወደ ከተማ ውስጥ መግባትም ሆነ በከተማ ውስጥ መንቀሳቀስ፣ ጭነት መጫን ሆነ ማራገፍ ይችላል፡፡

የሰዓት ገደብ የማይመለከታቸው ተሽከርካሪዎች የትኞቹ ናቸው ?

1. ሰሌዳቸው በሀገር መከላከያ ወይም በፖሊስ የተመዘገቡ የሀገር መከላከያ እና ሌሎች የፀጥታ ስራዎችን የሚያከናወኑ ከባድና ቀላል የጭነት ተሽከርካሪዎች፤

2. በህግ መሠረት የድንገተኛ አደጋ ተሸከርካሪዎች ተብለው የተለዩ የድንገተኛ አደጋ የሚሰሩ ቀላልና ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች፤

3. ነዳጅ የሚያመላልሱ ቦቴዎች

አስተዳደራዊ ቅጣቱ ምን ይመስላል ?

🔵 በተከለከለ ሰዓት ወደ ከተማ ውስጥ በመግባትና በዋና ዋና መንገዶች ላይ የቆመ ብር 10,000 (አስር ሺህ ) ይቀጣል፡፡

🔵 በዋና ዋና መንገድ ላይ የተንቀሳቀሰም ሆነ የጭነት መጫንና ማውረድ ተግባር የፈፀመ ወይም የኮንስትራክሽን ስራ የሰራ ብር 20,000 (ሃያ ሺህ) ይቀጣል፡፡

🔵 በመመሪያው ላይ የተደነገገወን የሰዓት ገደብ በመተላለፍ ከተቀጣ በኃላ ለሁለተኛ ጊዜ ጥፋቱን በመድገም የተገኘ ማንኛውም ሰው ከላይ የተገለፀውን ቅጣት በእጥፍ ይከፍላል፡፡

NB. በተከለከለው ሰዓት በከተማው ውስጥ ሲንቀሳቃስ በመገኘቱ ቅጣት የተጣለበት አሸከርካሪ ሰዓቱ ሳይደርስ የቅጣት ወረቀት ይዞ በተከለከለው ሰዓት እንዲንቀሳቀስ አይፈቀድለትም። የትራፊክ ተቆጣጣሪው ፍሰት በማያሰናክል ቦታ ላይ ተሸከርካሪው እንዲቆም በማድረግ ቅጣቱን እንዲከፍል ማድረግ አለበት፡፡

🗓 ይህ መመሪያ ከመስከረም 2 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

#TikvahEthiopiaFamilyAA

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ውስጥ ከነገ ማለዳ 12 ሠዓት እስከ ዓርብ ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር ተከለከለ።

የከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ፥ " ለመስቀል ደመራ በዓል አከባበር የመንገድ ትራንስፖርት ደህንነት ሲባል ከመስከረም 16 እና 17 ቀን 2017 ዓ.ም ማለዳ 12 ሠዓት ድረስ በመዲናዋ የሞተር ብስክሌት የትራንስፖርት አገልግሎት ተከልክሏል " ሲል አሳውቋል።

የትራንስፖርትና የትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እና የትራፊክ ፖሊሶች አፈፃፀሙን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ በአዲስ አበባ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ተደርገዋል።

መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ በሚከበረው የመስቀል ደመራ በዓል ምክንያት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳውቋል።

መስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5:00 ሰአት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ለተሽከርካሪዎች ዝግ የሚደረጉ መንገዶችን የሚከተሉት ናቸው።

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ

- ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ

- ከሃራምቤ መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ መብራት ላይ

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ብሔራዊ ቤተ መንግስት አጠገብ

- ከዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ የሚወስደው መንገድ ከዛንቺስ ሼል አጠገብ

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወሰደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ ከመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ መርሀ ግብሩ ፍፃሜ ድረስ ይዘጋል።

በተጨማሪም በተገለፁት መስመሮች ላይ ተሽከርካሪዎችን ለአጭርም ይሁን ለረዥም ጊዜ ማቆም የተከለከለ ነው።

አሽከርካሪዎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ጥሪ ቀርቧል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ይችላል።

#AddisAbaba

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት🚨

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡

መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡

በዚህም ይህን መድኃኒት የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት እና በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ባለስልጣኑ አሳስቧል፡፡

መድኃኒቱ ' ሻይንፋርም ' በተባለ የቻይና የመድሃኒት አምራች የተመረተ ሲሆን፤ አርቲሜተር (Artemether 80mg/1ml) የሚል ስያሜ ያለው እና በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ነው።

(የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት🚨 የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን " አርቲሜተር " የተባለውን በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት ጥቅም ላይ እንዳይውል አግዷል፡፡ መ/ቤቱ ተደርጓል ባለው የገበያ ቅኝት መድኃኒቱ መገኘቱን ፣ በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ናሙናው ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሽ አርቲሜተር (Artemether) የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን ገልጿል፡፡ በዚህም ይህን መድኃኒት…
#እንድታውቁት🚨

የትኛው የወባ መድኃኒት ነው አትጠቀሙት የተባለው ?

አርቲሜተር የተባለ በመርፌ የሚሰጥ የወባ መድኃኒት /Arthemeter 80 mg/ml injection, Batch No. 231104SPF, manufacture Date; 11/2023 supplied by Shinepharm, China በተደረገ የገበያ ላይ ቅኝት የተገኘ እና በባለስልጣኑ ያልተመዘገበ እንዲሁም ከገበያም ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ ሲፈተሸ Arthemeter የተባለው ንጥረ ነገር በውስጡ አለመገኘቱ መረጋገጡን የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳውቋል።

ይህን መድኃኒት ነው የጤና ባለሙያዎች እንዳይጠቀሙት በተጨማሪም በየደረጃው ያሉ የክልል ተቆጣጣሪዎች በየአካባቢያቸው ጥብቅ ክትትል በማድረግ እርምጃዎች እንዲወስዱ ማሳሰቢያ የተላለፈው።

@tikvahethiopia