TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Attention

ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ በሚወስደው መንገድ ልዩ ቦታው ጎሃ ፅዮን አካባቢ መንገድ ተዘግቷል። ለመንገዱ መዘጋት ምክንያቱ ምን እንደሆነ አላወቅንም የሚሉት የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ወደመጣንበት እንድንመለስ ተነግሮናል፤ አንዳንድ መኪኖችም እየተመለሱ ይገኛሉ ብለዋል። በርካታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ተማሪዎች በጉዞ ላይ ስለሚገኙ የሚመለከታቸው አካላት ችግሩ የሚፈታበትን መንገድ እንዲፈልጉ ጥሪ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ጥሪ አቅርበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#PMOEthiopia

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ያገኙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ለሰላም የተሰጠ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታወቀ። ፅህፈት ቤቱ ባወጣው መግለጫ ይህ ለሰላም የተሰጠ ሽልማት በመሆኑም መላው ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች ለሰላም እንዲቆሙ ጥሪ አቅርቧል።

የዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማትም የኢትዮጵያውያን የጋራ ድል መሆኑንም አስታውቋል። ኢትዮጵያን አዲሲቷ የተስፋ አድማስ በማድረግ የበለፀገች እንድትሆን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የማንቂያ ጥሪ መሆኑንም ነው ያመለከተው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ተሸላሚ በመሆን በዘርፉ 100ኛው ተሸላሚ ሆነዋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የመንግስታቱ ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን ተከትሎ ባስተላለፉት የደስታ መግለጫ መልዕክት፣ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አመራር ለአፍሪካና ለሌች አገራት ምሳሌ ነው ብለዋል፡፡ ዋና ጸሓፊው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ራዕይ በኤርትራና ኢትዮጵያ መካከል ታሪካዊ መቀራረብን ፈጥሯል ብለዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
WORLD EXCLUSIVE: Listen to the call between Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed Ali and Olav Njølstad, Secretary of the Norwegian Nobel Committee, recorded shortly after the announcement of the 2019 Nobel Peace Prize.

Via Nobel Prize
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ለጠ/ሚ አብይ የእንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላፉ!

ግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ በመሆናቸው የአንኳን ደስ አልዎት መልዕክት አስተላለፉ፡፡ ፕሬዚዳንቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ወንድም የኢትዮጵያ ህዝቦች የ2019 የኖቤል ሽልማት ዶክተር አብይ አህመድ በማሸናፈቸው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከአዲስ አበባ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ "ዘመን ባስ" ተገልብጦ በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል። የደረሰውን ጉዳት አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃዎች ሲደርሱን እናጋራለን።

Via ANANIYA/TIKVAH ETH FAMILY/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

በነአቶ በረከት ስምዖን የክስ መዝገብ ዛሬ ከሰዓት በኋላ የተሰየመው ችሎት ዐቃቤ ሕግ ያቀረበውን ተጨማሪ ሰነድ መርምሮ የሰነዱ አካል እንዲሆን ብይን ሰጥቷል፡፡ ከፍርድ በፊት የሚቀርብ ማንኛውም ማስረጃ መርምሮ ትክክለኛ ብይን ለመስጠት አጋዥ ስለሚሆን ዐቃቤ ሕግ እንዲያዝለት ያቀረበውን 141 ገፅ ማስረጃ ከዚህ ቀደም የቀረበው የሰነድ ማስረጃ አካል እንዲሆን ሊያያዝ ይገባል ብሏል ፍርድ ቤቱ፡፡ ፍርድ ቤቱ ሰነዱን መርምሮ ብይን ለመስጠትም ለጥቅምት 21 ቀን 2012 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረ "ዘመን ባስ" ተገልብጦ በደረሰው አደጋ የ4 ሰው ህይወት ማለፉን ተመልክቻለሁ ሲል አንድ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል ገልጾልናል። በሰዓቱ ወደ ሀረር እየተጓዝኩ ነበር ያለን የቤተሰባችን አባል እኔ እያለሁ አራት ሰው መሞቱን አይቻለሁ ብሏል። ተጨማሪ የፎቶ መረጃዎችን አጋርቶናል።

Via Cheery/TIKVAH ETH FAMILY/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
መንገዱ እንደተዘጋ ነው!

አዲስ አበባን ከባህርዳርና ጎንደር የሚያገናኘው መንገድ ጎሃ ጺዮን ከተማ ላይ እንደተዘጋ ነው። በርከት ያሉ ተሽከርካሪዎችም ወደመጡበት እንዲመለሱ ተነግሯቸው ወደመጡበት መመለሳቸውን በስፍራው የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት ገልፀዋል። ለምን ግድ መዘጋት ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማጣራት ጥረት እናደርጋለን።

Via Muhamedanwar Seid/TIKVAH-ETH/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"One Small Step to Pave a Way"
ጥቆማ!
አንተም አንቺም እኔም ያገባናል!
•በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ስለመጣው የፍቺ ቁጥር
•በትዳር ውስጥ እየታየ ስላለው እርካታና ደስታ ማጣት
•በፍቅር ህይወት የነበሩ መተሳሰቦች እና ሌሎችም በጋብቻ ውስጥ አለመቀጠል
ሁላችንንም ያገባናል!!
እነዚህና መሰል ሀሳቦች የፊታችን ቅዳሜ በ 8:00 ሰአት 6ኪሎ በሚገኘው የስብሰባ ማእከል(አሴምብሊ) ይዳሰሳሉ።

ሰላማዊ አለም እንዲኖረን ሰላማዊ ቤተሰብ እንፍጠር!

ፍኖተ-ጋብቻ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቢሾፍቱ ከተማ/ኡኬ ደንካካ የሚባለው አካባቢ በደረሰው የጦር አውሮፕላን መከስከስ አደጋ የሁለት አብራሪዎች ህይወት እንዳለፈ ለጉዳዩ ቅርብ ነኝ ያሉ የቤተሰባችን አባል ከቢሾፍቱ መረጃ ሰጥተዋል።

Via DIN/TIKVAH ETH FAMILY/
VIDEO: ሮብኤል/TIKVAH ETH FAMILY/


ተጨማሪ መረጃዎች ይፋ ሲደረጉ እናቀርባለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ልዑል አልጋ ወራሽ መሐመድ ቢን ዛይድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸውን ተከትሎ “ጓደኛዬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ሽልማትን በማሸነፉ የተሰማኝን ደስታና ጥልቅ ስሜት ለመግለፅ እወዳለሁ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀጠናው ላመጣው ሰላምና ተስፋ ሽልማቱ ይገባዋል” ብለዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BEDESA

ከትናንት በስቲያ እኩለ ቀን ላይ በምዕራብ ሃረርጌ ዞን በዴሳ ከተማ ውሃ ለመቅዳት የውሃ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ የቀረውን የ13 ዓመት ታደጊ ህይወት ለማትረፍ የሞከሩ 4 ሰዎችን ጨምሮ አምስት ሰዎች ህይወታቸው አለፈ። የዓይን እማኞች እና የአከባቢው መስተዳደሮች ለቢቢሲ እንደተናገሩት በቅድሚያ እስከ 22 ሜትር ጥልቀት ያለው እና ከኮንክሪት ወደ ተሰራው ጉድጓድ ውስጥ የ13 ዓመት ታዳጊው ከገባ በኋላ የእርሱን ህይወት ለማዳን በተደረጉ ጥረቶች ነው የተቀሩት የአራቱ ሰዎች ህይወት ያለፈው።

Via BBC አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጥቅምት2

የአዲስ አበባ ባላደራ ምክር ቤት ለዕሁድ ስለጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ ለአስተዳደሩ ስለ ሰልፉ ብናሳውቅም፣ እስካሁን ምላሽ አልተሰጠንም- ብሏል የባላደራው ሰብሳቢ እስክንድር ነጋ፡፡ ሆኖም በሕጉ መሠረት፣ ዝምታው ዕውቅና እንደመስጠት ስለሚቆጠር ፖሊስ ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ ሰልፉ ለሀገራዊ ዲሞክራሲ ነው፤ እናም ሕዝቡ ለሰልፉ ይውጣ ሲል ጥሪ አድርጓል፡፡ ሰልፉ ከተደናቀፈ ባላደራው ወደሚቀጥለው የትግል ምዕራፍ ይሄዳል፡፡ መግለጫው በተሰጠበት ግቢ አቅራቢያ ወጣቶች ባላደራው ላይ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡

Via #wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የ2019 የሰላም የኖቤል ሽልማት በማሸነፋቸው የእንኳን ደስ አልዎት መልእክት አስተላልፏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተሸለሙት የኖቤል የሰላም ሽልማት ሀገሪቱ የጀመረችው የሰላም ጉዞን አጠናክሮ ለመቀጠል እንደሚያስችል እምነቱን ገልጿል።

Via ትግራይ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

ከባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ተሽከርካሪዎች ጎሃፅዮን ላይ መንገድ በመዘጋቱ እንዳናልፍ ተደርገናል ሲሉ ለአሐዱ ተናገሩ፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በበኩሉ እሁድ በአዲስ አበባ ይደረጋል በተባለው ሰልፍ ስጋት መንገዱ መዘጋቱን ገልጿል፡፡

አርብ ከማለዳ 3 ሰዓት ጀምሮ በኦሮሚያ ፀጥታ አካላት ከባሕር ዳር መስመር የሚመጡ ተሽከርካሪዎች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ ጎሃፅዮን ላይ መታገዳቸውን አሽከርካሪዎች ለአሐዱ ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ በተከለከሉት ተሽከርካሪዎቹ ውስጥ ወደ ተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚሄዱ በርካታ ተማሪዎች መኖራቸውን የገለፁት አሽከርካሪዎቹ፤ መንገድ በመዘጋቱ ምክንያት ወደ መጡበት ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል፡፡

አሐዱ ቴሌቪዥን መረጃ የጠየቃቸው የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ደረጀ ፈጠነ መንገዱ እሁድ በአዲስ አበባ ከተማ የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት ስጋቶች በመኖራቸው መዘጋቱን ገልፀዋል፡፡ መንገዱን ዘግቷል የተባለው የወረጃርሶ ፖሊስ በኬላው ላይ በሚደረግ ፍተሻ በተፈጠረ መጨናነቅ እንጂ የተዘጋ መንገድ የለም ሲል አስተባብሏል፡፡

ፖሊስ የፀጥታ ስጋት በአካባቢው አለ መባሉን ተከትሎ ፍተሻ እያደረገ መሆኑን የወረጃርሶ ፖሊስ ኃላፊ ኢንስፔክተር መንግሥት ከተማ ገልፀዋል፡፡ ይሁንና ተጓዦች ለተለያዩ እንግልቶች መዳረጋቸውን በመግለጽ ፌደራሉ መንግሥት ጣልቃ እንዲገባ ጠይቀዋል፡፡

ምንጭ፦ አሃዱ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AddisAbeba

የቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በከተማዋ አዲስ በሚጀመሩ ቤቶች ግንባታ ዙሪያ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰቷዋል፡፡ የቢሮው ኃላፊ ኢ/ር ሰናይት ዳምጠው የከተማ አስተዳደሩ በ2012 ቀደም ሲል ከነበሩ ዲዛይኖች ላይ መጠነኛ ማሻሻያ በማድረግ 500ሺ መኖሪያ ቤቶችን በከተማው ለማስገንባት በተለያዩ የግንባታ አማራጮችን ይዞ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ገልፀዋል፡፡

በዚህም ፦

1. በመንግስት የሚገነቡ 150 ሺ ቤቶችን በ20/80 እና 40/60 ፕሮግራም ተመዝግበው ለሚገኙ የሚነገቡ ይሆናል፡፡

2. በ75 ሄክታር መሬት ላይ 25 ሺ ኪራይ ቤቶች ግንባታ፡፡ ለዚህኛው በተለየ መልኩ በ10ሩም ክፍለ ከተሞች መታደስ እና መቀየር የሚገባቸውን የቀበሌ ቤቶች የሚገኙበትን ይዞታ በመጠቀም የሚገነባ ይሆናል፡፡ በዚህም መሠረት የፓይለት ስራው በሁለት ክፍለ ከተሞች ተጀምሯል፡፡

3. የከተማዋ ኪስ ቦታዎች በመጠቀም የ175 ሺ የማህበር ቤቶች ግንባታ በማካሄድ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ ማድረግ

4. ባለሃብቶችን በማሳተፍ አቅም ላላቸው ነዋሪዎች የአፓርታማዎችን ግንባታ ማከናወን፡፡ ከተለያዩ የሃገር ውስጥ እና የውጪ ሃገር ባለሃብቶች ጋር በመሆን በተያዘው ዓመት 25 ሺ ቤቶችን ለመገንባት ዕቅድ ተይዟል፡፡

5. ከሪል ስቴት አልሚዎች ጋር በመሆን 75 ሺ ቤቶች ግንባታ ይጀመራል፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የግንባታ አማራጮችን በ2012 ዓ.ም በመጀመር በዓመቱ መጨረሻ የግንባታዎቹን 30% ለማጠናቀቅ ይሰራል፡፡ በተጨማሪም በግንባታ ላይ የሚገኙ 139 ሺ በላይ ቤቶች ግንባታቸውን በማጠናቀቅ ለነዋሪዎች የሚተላለፉ ይሆናል፡፡ ከ90 ሺ በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ወጣቶች በግንባታው የስራ ዕድል ያገኛሉ፡፡

Via Mayor Office AA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NobelPeacePrize

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ክብርት ወይዘሮ ፅዮን ተክሉ ለTIKVAH-ETH በላኩት መልዕክት ክቡር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ መሆናቸውን በማስመልከት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር እና በ "እኛ ለእኛ" የኢትዮጵያውያን በጎ ፍቃደኞች መርሃ ግብር ስም የእንኳን ደስ ያልዎት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia