TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሀያትን መታደግ መታደል ነው⬆️
-----------------------------------

በመጀመርያ ስለ ሀያት ኑሩ ትንሽ እንበላቹ ፦

ሀያት 20 አመቷን ከያዘች ሳምንታትን አስቆጥራለች በዚህ በኖረችባቸው አመታት ደስተኛ የሆነችባቸው እልፍ አእላፍ ቀናቶች አለፈዋል ሲከፋትም ፈጣሪዋን አመስግና ትኖራለች። ዛሬ ዛሬ ግን የማንኛችንም የሰው ልጆች የወንጀል መጥረግያ የሆነው ህመም ከወደ ሀያት ቤት ሰተት ብሎ ከገባ 4 አመታት ተቆጥረዋል። ከምትማርበት ዳግማዊ ብርሃን የመጀመር ደረጃ ት/ቤት ነው አዞሮ የመጣል ነገር በተደጋጋሚ አጋጠማት ደረጃዎችን በአሰቃቂ ሁኔታም ትንከባለላቸው ነበር በዚያም ሰውነቷ አላንቀሳቅስ ይላታል ይህን ግዜ የአጥንት ህክምና ቦታዎችን ባህላዊውንም እምነታዊዉንም ካዳነኝ ብላ ሁለት አመት ሙሉ ያለምንም መፍትሄ ተንከራተተች በስተመጨረሻም አንድ የአጥንት ስፔሻሊስቶች ወደ ሚገኙበት ሆስፒታል ታቀናለች ያልጠበቀችው ያላሰበችው ሁለተኛ አስከፊ በሽታ እንዳለባት ይነገራታል አንደኛዉ ኩላሊቷ ሙሉ በሙሉ ከጥቅም ውጪ እንደሆነና አንደኛው ደግሞ የጉዳቱ ሰለባ ስለሆነ ዲያሊስ እንድትጀምር ይነገራታል ሀያትና ቤተሰቧ የተረበሽ ስሜት ላይ ናቸው በእንደዚህ አይነት በሽታ ሚጠቁ ታማሚዎች ሲያስቡት የተስፋ መቁረጥ ስሜት ሲታይባቸው ፈጣሪን ግን በመለመን ላይ አሁንም አልቦዘኑም ዲያሊስ ከጀመረች 8 ወር ሆኗታል ለ 1 ዲያለስ 1400 እየከፈለች ትገኛለች ከባድ ህመም ሀኪሞች ተፈተነዋል የአጥንት ህክምናውን ወይስ የኩላሊቱን የቱን ለማስቀድም ግራ ገብቷቸዋል ማደንዘዣ የሀያት ሰውነት አድክሞታል ላያት ማያለቅስ ማያዝን ከየት መጥቶ የነገ ተስፋችን ሀያት ትምህርቷን ካቋረጠች 4 አመት ሞላት ታናናሿቿ ፍልቅልቅ እያሉ አብሽሪ እህቴ ትድኛለሽ የሚል አይነት ፊት ይስተዋልባቸዋል ቤተሰብ ህይወቷን ለመታደግ ይሯሯጣሉ እናት እያለቀስች ታወጋለች ልጄ ንቅለ ተከላዋን ታደርጋለች ኩላሊት ምለግሳት እኔ እናቷ ነኝ ዋናው ነገር ትዳንልኝ ብቻ እያለች ስታወራ አይኖቿ እንባ አቅረዋል ድህነት ፣ ማጣት በሽታ አስከፊ ነው።

ወገኖቼ አቅሙ ያላቹ ባለሀብቶች ፣ ግለሰቦች ፣ ድርጅቶች ፣ አርቲስቶች ወዘተ……ሀያትን ለመርዳት ፦
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000230747648 በእናቷ ሰአዳ እንድሪስ ያስገቡ።

በተጨማሪም ሀያትን ለመርዳት መሀተም ያለበት ትኬቶች ከ25 ብር እስከ 200 ብር የያዙ በአስተባባሪዎች አማካኝትነት እየተሸጠ ይገኛል። ትኬቱንም በመግዛት እንድትተባበሩን በአክብሮት እንጠይቃለን።

ሀያት ኑሩሁሴንን ለማግኘት 0967 992096

ሀያት 100% ትድኝያለሽ!

የኢትዮጵያ ቡና የስፖርት ክለብ ዳጋፊዎች
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለሚመለከተው አካል‼️

"ሰላም ፀግሽ የአዲግራት ዩኒቨርሲቲ 6ኞ አመት የህክምና ተማሪ ነኝ በጣም ከምነግርህ በላይ እያንገላቱን ነው።ከዚህ በፊት ላንተም አሳውቀንሃል ግን አደለም ችግሩ ሊፈታ ቀርቶ ትምሀርት አቁመናል።በተደጋጋሚ department ክፍሉን administrative ክፋሉን ብናሳውቅም መፍትሄ ልናገኝ አልቻልንም።መምህራኖችም ደሞዝ በግማሽ ቀንሰን ነው የምንሰራው ከሌላ ግቢ ለሚመጡ መምህራንን እይከፈለልንም ቡለውናል። general hospital 4ኛ አመት ተማርዎች practical year(clinical year) ሰለጀመሩ ማስተናገድ ከሚችለው በላይ ስለሆነ እኞ ትምህርተ እንድናቆም ተገደናል ። ከሌሎች ግቢዎች ቢንስ በ 6 ወር ዘግይተናል።ግቢው ምንም ችግራችን ሊፈታልን አልቻለም ከአቅማችን በላይ ነው ብሎናል እኛም ጊዜአችንን ገንዘባችንን በከቱ እየተፋ ነው ከባድ የ moral ውድቀት ደርሶብናል ባክህን ወደ በሚመለከተው አካል አድርስልን ስሜ እንዳይተቀስ።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
AAU⬇️

"The office of registeral confirmed me that, the registration of 2nd year and Above Addis Ababa University regular students scheduled for October 11 and 12. (ጥቅምት 1 እና 2) አዲስ ተማሪዎችን በሚመለከት የተባለ ነገር የለም፡፡ Please Convey the massage for all. Thank you for usual cooperations! Juhar s."

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ETV Zena Live! ዶክተር ዐብይ የመክፈቻ ንግግር በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነቀምት⬆️

በርቱልን! #የነቀምት ወጣቶች! በርቱልን!
.
.
ፈጣሪ እድሜ እና ጤና ይስጣችሁ ሌላ ምን እላለሁ!
#ETHIOPIA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ዐብይ በአሁን ሰዓት እያደረጉ ካለው ንግግር የተወሰደ!

©ሶፊ ከሀዋሳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የፓሪሱ ጥቃት⬇️

ፈረንሳይ በመዲናዋ በሰኔ ወር የፈነዳውን ቦምብ #ያቀነባበረው የኢራን የደህንነት
መስሪያ ቤት መሆኑን አረጋግጫለው አለች፡፡

በወቅቱ በፓሪስ ጎዳና ላይ ከኢራን የተሰደዱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ሰላማዊ ሰልፍ ላይ እንደነበሩ ተነግሯል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ፈረንሳይ የሁለት #ኢራናውያንን እና ከሀገሪቱ የደህንነት መስሪያ ቤት ጋር የተያያዙ የባንክ አካውንቶችን አግዳለች፡፡

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘም ረዥም ጊዜ የፈጀ ምርመራ ካካሄደች በኋላ ነው ይፋ ማድረጓን ያስታወቀችው፡፡

የኢራን የደህንነት መስሪያ ቤት ኃላፊ የሆኑት ሰይድ ሐሺም #በቀጥታ ትዕዛዙን እንደሰጡ ተገልጿል፡፡

የደህንነት መስሪያ ቤቱ ቃልአቀባይ ፓሪስ የደረሰችበትን ምርመራ ተቀባይነት የለውም ያሉ ሲሆን በጀርመን ተያዙ ተያዙ የተባሉ ዲፕሎማታቸውንም እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም ጥቃቱ የተፈጸመው የሁለቱ ሀገራትን የረዥም ጊዜ ወዳጅነት በማይፈልጉ ሴረኞች የተቀነባበረ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ሲጂቲኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዶክተር ዐብይ በአሁን ሰዓት እያደረጉ ካለው ንግግር የተወሰደ!

©ሶፊ ከሀዋሳ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አስቸኳይ መረጃ‼️

ከቤኒሻንጉል ጉሙዝና ከምስራቅ ወለጋ ዞን አጎራባች ወረዳዎች #የተፈናቀሉ ዜጎችን #በገንዘብ ለመርዳት የምትፈልጉ፦

በኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ
937719

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000259030138

በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ
1000072131111

#ሼር

ምንጭ፦ ኦሮሚያ ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updateሀዋሳ⬆️የኢህአዴግ 11ኛው ድርጅታዊ ጉባኤ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ ባደረጉት ንግግር በይፋ ተከፍቷል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ዓለም በኅዋ ሲዋኝ እና በረቂቅ ኅዋስ ውስጥ ገብቶ የተሰወረውን የሕይወት ምሥጢር ለመረዳት ሲታትር እኛ ከለመድንው #የእንፉቅቅ ጉዞ ጥቂት ፈቅ ለማለት በሞከርን ቁጥር ይኸ እማ አይሆንም! አይደረግም! ካልን በዚያው በኋላ ቀርነታችን አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀን ለመቅረት ለመወሰናችን #ማረጋገጫ ነው"

▪️▪️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አሕመድ▪️▪️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update በኢህአዴግ 11ኛው ጉባኤ ላይ ተሳታፊ ከሆኑት የተፎካካሪ ድርጅት መሪዎች መካከል ፕሮፌሰር #ብርሀኑ_ነጋ አንዳኛው ናቸው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#updateሀዋሳ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ዶ/ር #ዐቢይ_አህመድ በ11ኛው የግንባሩ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ካደረጉት ንግግር የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች ፡-

• 11ኛው የኢህአዴግ ጉባኤ በለውጥ ምሁዋር ውስጥ በገባንበት ወቅት መካሄዱ ታሪካዊ ያደርገዋል፡፡

• ኢህአዴግ ከዚህ ቀደም የሚያጋጥሙትን ፈተናዎች እያሸነፈ እንደመጣው ሁሉ የሚገጥሙትን ችግሮች እየፈታ የለውጡ ሞተር ሆኖ አገር መምራቱን ይቀጥላል፡፡

• ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ነገዋን በመፈለግ ላይ ያለች፣ በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገች አገር ናት፡፡

• የሽግግር ሂደቱን የአገራችን አርሶአደር “የበሬውን ብልሃት እና የወይፈኑን ጉልበት አቀናጅቶ” …እንደሚለው ሁሉ በእኛም ዘንድ ተተኪዎችን በጎ ልምድ ካላቸው በማስተሳሰር አገራዊ ለውጡን ለማሳካት ኢህአዴግ ይታትራል፡፡

• አገር የምታድገው በቅብብሎሽ ነው፡፡

• ያለትላንት ዛሬ አልተገኘምና የትናቱን ትውልድ ማመስገን ያስፈልጋል፡፡ እኛም በተራችን በተተኪ ትውልድ መተካታችን አይዘነጋምና፡፡

• መተካካት የታቀደ ሂደት እንጂ ድንገተኛ ሆኖ እልቂት እንዳያመጣ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

• ይህ ትውልድ ስልጣንን በእጁ አስገብቶ ቀድሞ የነበረውን ነገር በማስፍረስ የተጠመደ መሆን አይገባውም፡፡

• ትላንት እና ዛሬን ያጣጣመች ኢትዮጵያን ለመገንባት ተግቶ መስራት ያስፈልጋል፡፡

• ኢትዮጵያ በላቀ ተግበራቸው ያገነኗት መሪዎች እንደነበሯት ሁሉ፣ ውድቀት የዳረጓትም ነበሩ፡፡ ለጠላቶቿ የሰጧት መሪዎችም ነበሩ፡፡

• ያለመተማማን በማስፋት፣ በጠብና በጦርነት ሊተላለቁ የነበሩ ልጆቿን አስታርቀው ወደ ልዩ ምዕራፍ ያስገቧት ነበሩ፡፡

• በአሁኑ ጊዜ ያለው አመራርስ የትኛውን ታሪክ ይደግማል? የሚለው ጥያቄ ለእኛ ቀርቧል፡፡

• የአገራችን እጣ ፈንታ አሁን እድሉን ባገኙት ፖለቲከኞች እንዲሁም በህዝቧ እጅ ነው፡፡

• ዘመናዊና ስልጡን አገር ለመፍጠር ህዝብን የስልጣን ልዕልና መገለጫ አድርጎ የሚቀበል ስርዓት መፍጥር ሲሳካልን ነው፡፡

• ህዝብ የሚያምናቸውና የሚከተላቸው ልዩ ልዩ የማህበረሰብ መሪዎችን ካገኘን በእምነት፣ በባህል፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፖለቲካ፣ በጦር አመራር፣ በምህንድስና፣ በስፖርትና ኪነጥበብብ፣ በሌሎች ዘርፎችም ጭምር ከተዋጣልን አገር የተሳካ ጉዞ አድርጋ በከፍታ ጉዞ ላይ ትደርሳለች፡፡

• የምንፈልጋትን አገር መምሰልና መሆን የሚገባን እኛው ራሳችን ነን፡፡

• የበለፀገች የጋራ ቤታችንን ለጋራ ልጆቻችን ማድረስ የምንፈልግ ከሆነ ዝርፊያውንነና መጠላለፉን ትተን በጋራ መስራት አለብን፡፡

• ዘርና ሀይማኖትን መሰረት አድርገን ሌሎችን ከመቆስቆስ ይልቅ ለጋራ ጥቅምና ድል እንስራ፡፡

• ከመካከላችን ማንም እስከተጎዳ ድረስ ሁላችንም እንጎዳለን፤ ስለዚህ ለሁላችንም የምትሆን አገር በመደመር መገንባት ግድ ይለናል፡፡

• ኢትዮጵያ በሁላችንም ላብና ደም የተሰራች አገር በመሆኗ ባለቤቶቿ ሁላችንም ነን፡፡ አዲሲቷንም ኢትዮጵያ በጋራ ልንገነባ ይገባል፡፡

• ኢህአዴግ ከዳር እሰከዳር የሚሳተፉበት ድርጅት እንዲሆን መስራት ያስፈለጋል፡፡

• ኢህአዴግ አጋር ፓርቲዎችን ወደ ግንባሩ ለማስገባት አቅዶ ቢንቀሳቀስም በአገራዊ ሁኔታው በጥናት እንዲመለስ የቀረበውን ጥናት ማድረስ ባመቻሉ፣ ይህን ምላሽ እንዲያገኝ የሚያስችል ውሳኔ ላይ ይደረሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

• የተጀመረውን የፖለቲካ ምህዳር የማስፋቱ ሂደት የይስሙላ ባለመሆኑ በሁሉም መስክ ተጠናክሮ ይገፋበታል፡፡

• የተፎካካሪዎቻችን ሀሳብ ላይሳማማን ይችላል፣ ነገር ግን የነሱን ሀሳብ በመገደብ ሳይሆን የነሱን ሀሳብ የሚያሸነፍ ሀሳብ ይዘን በመቅረብ ብቻ እንዲሆን እንሰራለን፡፡

• ዛሬ ላይ ሁነን የትላንትናውን ሁነታችንን መቀየር አንችልም፣ ይሁን እንጂ የነገዋን ኢትዮጵያ ተስማምተን መገንባት እንችላለን፡፡

• አዲስ ታሪክ ለመፃፍና ለመስራት በሚያስችል የዘመን አካፋይ አንጓ ላይ እንገኛለን፡፡

• ክልላዊ አስተዳደርን ከብሄር ማንነት ጋር ሳናምታታ ፌደራሊዝሙን ከተገበርነው ለአኛ አውድ ተመራጭነቱ አያጠያይቅም፡፡

• ሰዎች በየትኛው የአገሪቱ ክፍል ተንቀሳቅሰው የመስራት መብታቸው ተረጋግጦ ኢትዮጵያ ህብረ ብሄራዊ የምትሆንበት ገፅታም ሊረጋገጥ ይገባል፡፡

• እስካሁን የብሄር ማንነት እና ኢትዮጵያዊ ማንነት ሚዛን ጠብቀው የመጡ ባለመሆናቸው የህዝብ ለህዝብ መድረኮች፣ የባህል መድረኮችና ሌሎች መድረኮችን በማዘጋጀት ከፍ ከፍ የሚያርገንን ስራ መስራት ያስፈልገናል፡፡

• መደመር ሁሉም የየራሱን ጥንካሬ ይዞ ከሆነ እምቅና አዲስ ታሪክ መፃፍ ያስችለናል፡፡

• አገራችን የገጠማት ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያው ቀውስ መስኤው ከግብርገብነት ቀውስ የሚመነጭ ነው፡፡

• በሞራልና ግብረገብ የወደቀ ማህበረሰብ ውስጥ ሆነን ሰላም፣ ፍትህ፣ ብልፅግናን ማረጋገጥ ከባድ ነው፡፡

• በሞራል ልዕልና፣ በስነ ምግባር ምሳሌ በመሆን የሀይማኖት ፣ የጎሳና ማህበረሰብ መሪዎች መሪ በመሆን አርዓያነትን በማሳየት ከችግራችን እንዲንወጣ ያስፈልጋል፡፡

• ዜጎች የሚገጥማቻውን መሰረታዊ አገልግሎት የመልካም አስተዳደር ችግር ብሎ መግለፅ አይመጥነውም፡፡

• ስራ አጥነት መቀነስ፣ የዜች የኑሮ ደረጃን ማሳደግ፣ የህግ የበላይነት ማረጋገጥ ላይ ትኩረት የሰጠ ጉባኤ ሆኖ እንደሚቀጥል እምነቴ ነው፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia