TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ዓለም በኅዋ ሲዋኝ እና በረቂቅ ኅዋስ ውስጥ ገብቶ የተሰወረውን የሕይወት ምሥጢር ለመረዳት ሲታትር እኛ ከለመድንው #የእንፉቅቅ ጉዞ ጥቂት ፈቅ ለማለት በሞከርን ቁጥር ይኸ እማ አይሆንም! አይደረግም! ካልን በዚያው በኋላ ቀርነታችን አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀን ለመቅረት ለመወሰናችን #ማረጋገጫ ነው"

▪️▪️ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አሕመድ▪️▪️

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኮ/ሌ በዛብህ ጉዳይ...‼️

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

"ኮ/ል በዛብህ ጴጥሮስን ሰኔ ላይ ኤርትራ ውስጥ በአካል አግኝቻቸዋለሁ። በመጪው ሰኔ ላይ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ" -- ኢንጅነር #ታደሰ

"እኔ ምንም መረጃ የለኝም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ #ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው"-- ፕ/ር #በየነ_ጴጥሮስ
.
.
ኢንጅነር ታደሰ ይባላሉ። ባለፈው ሰኔ ወር ላይ ወደ ኤርትራ ተጉዘው እንደነበር እና በቆይታቸው ወቅትም በኢትዮ- ኤርትራ ጦርነት ወቅት የሚያበሩት ጀት ተመትቶ የተማረኩትን ኢትዮጵያዊውን ኮሎኔል በዛብህ ጴጥሮስን እንዳገኟቸው ለጋዜጠኛ #አልያስ_መሰረት ተናግረዋል፤ አክለውም "በአሁን ሰአት እንደ ሌሎች የጦር ምርኮኞች በቀይ መስቀል ስር ይገኛሉ። እኔም እዛ አግኝቻቸዋለሁ። ትንሽ ከእድሜ መግፋት ውጪ በጥሩ ጤንነት ላይ ይገኛሉ። ሰኔ ወር ሲመጣ እንደሚፈቱ መረጃ አለኝ። ዝርዝሩን የመንግስት ሰዎች ያውቃሉ" ብለዋል።

የኮ/ሌ በዛብህ ጴጥሮስ ታላቅ ወንድም ወደሆኑት ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ስለጉዳዩ በሰጡት ምላሽ፦ "እኛ ይህ መረጃ የለንም። እኚህ ያልካቸው ግለሰብ እንዴት access ሊኖራቸው እንደቻለ አላውቅም። በግሌ የተሻለ (more powerful) የሆኑ መንገዶችን ሄጄ ማረጋገጫ ያጣሁበት ጉዳይ ነው። ወንድሜ በህይወት አለ ወይስ የለም የሚለውን ለማረጋገጥ እንኳን ካደረግነው ጥረት አንፃር ሲታይ የዚህ ሰውዬ መረጃ በጣም extreme ነው። በኤርትራ በኩል ያለው ሁኔታ ሲጠቃለል በኮሎኔል በዛብህ ዙርያ መነጋገር አንፈልግም የሚል ነው። ከዚያም አልፎ ጉዳዩን sensitive አርጎ መናደድ አለ። እኛን አትጠይቁን አይነት ነገር ነው ያየነው። በህይወት ተይዞ የአስመራ መንገዶች ላይ parade የተደረገ ሰው ነው። የኛ አቋም ህይወቱ አልፏል ከተባለ ታውቃላችሁ እና አካሉ የት ነው እያልን ነው። ግን ይህንን ጉዳይ መወያየት አይፈልጉም። ከኢትዮጵያ መንግስት ወገን ደሞ አሁን የተጀመረውን ንግግር ያበላሽብናል የሚል ነገር አለ። ለማንኛውም ያልካቸውን ሰውዬ አገናኘኝ። ይህ ለኛ ትልቅ development ነው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
'ኮሮና ቫይረስ ጠፍቷል፤ ውጡና ጨፍሩ' - ፖል ማኮንዳ

(በቢቢሲ የአማርኛው አገልግሎት)

የታንዛኒያው ነባር ፖለቲከኛ 'የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጠፍቷል' ማለታቸውን ተከትሎ ከሃገሬው ሰው ወቀሳ እየዘነበባቸው ነው። ፖለቲከኛው ይባስ ብለው ታንዛኒያውያን እሁድ ዕለት ወደ አደባባይ ወጥታችሁ የኮሮና ቫይረስ መጥፋትን አክብሩ ብለዋል።

የዳሬሳላም ኮሚሽነር ፖል ማኮንዳ የታንዛኒያ ዜጎች አዲስ ልብስ ገዝተው ደስታቸውን ቢገልፁ በበሽታው ምክንያት የተጎዱ ሰዎችን ይደግፋሉ ብለዋል።

ታንዛኒያ ወስጥ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስለመጥፋቱ ምንም #ማረጋገጫ የለም። የታንዛኒያ ጤና ሚኒስቴር ስለ ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መግለጫ ከሰጠ አንድ (1) ወር አልፎታል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#የብድር_ገደብ

ብሔራዊ ባንክ የጣለው የብድር ገደብ በባንኮች እና ተበዳሪዎች ላይ ተግዳሮት መፍጠሩ ተነግሯል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ / #NBE ከጥቂት ወራት በፊት ያወጣው የገንዘብ ፖሊሲ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡

የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር ዋነኛ ዓላማ ያደረገው ይህ ፖሊሲ ፣ የባንኮች የብድር ምጣኔ ካለፈው ዓመት ከ14 በመቶ በላይ እንዳይበልጥ ገደብ የጣለ ነው፡፡

በተለይ ባንኮች የሚሰጡት ብድር በገንዘብ ፖሊሲው ከተጣለባቸው ገደብ ጋር ለማጣጣም በማሰብ ቀደም ብለው የፈቀዷቸውን ብድሮች ጭምር ከመልቀቅ እንዲቆጠቡ ወይም መሰል አሠራርን እንዲከተሉ እያደረጋቸው ስለመሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

ከመመርያው መውጣት ቀደም ብለው የተፈቀዱ ብድሮች ሊለቀቅላቸው እንዳልቻለ የተለያዩ ባለሀብቶችና የንግድ አንቀሳቃሾች ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ገልጸዋል።

በዚህም የተፈቀደላቸውን ብድር ታሳቢ በማድረግ የገቧቸው የቢዝነስ ስምምነቶች እየተፋረሱባቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ቤትና ተሽከርካሪ ግዥ ውሎች ሳይቀሩ በእንጥልጥል እንዲቆዩ ማድረጉንም ከተበዳሪዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡ 

ብድር እንዲለቀቅላቸው #ማረጋገጫ አግኝተው የነበሩት ተበዳሪዎች አሁን ላይ ብድሩን ማግኘት ለምን እንዳልቻሉ ለሚያቀርቡት ጥያቄ የሚያገኙት ምላሽ " አዲሱ የገንዘብ ፖሊሲ የጣለው የብድር ዕቀባ " መሆኑን ያስረዳሉ።

አንዳንዶቹም የተፈቀደላቸውን ብድር በትዕግሥት እንዲጠብቁ እንደተነገራቸው ያመለክታሉ፡፡

ቤት ለመግዛት ተዋውለው ከሚገለገሉበት ባንክ የፈቀደላቸውን ብድር እየተጠባበቁ የነበሩ አንድ ተበዳሪ ብድሩ እንደሚያገኙት በተገለጸላቸው ወቅት ሊለቀቅላቸው ባለመቻሉ የቤት ሽያጭ ውላቸው ሊፈርስባቸው እንደሆነ ገልጸዋል። እንዲህ ያለው ችግር በአብዛኛው በግል ባንኮች አካባቢ የሚስተዋል ነው፡፡

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Reporter-Newspaper-10-17

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በረሃብ የሰዎች ህይወት ስለማለፉ ማረጋገጫ የለንም " - አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም (ዶ/ር)

የፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) " በኢትዮጵያ በረሃብ ምክንያት የሰው ህይወት አልፏል የሚል ማረጋገጫ የለንም " አሉ።

ኮሚሽነሩ ይህንን ያሉት ከፋና ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው።

አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም (ዶ/ር) ምን አሉ ?

- መንግስት 11 ቢሊዮን ብር መድቦ እየሰራ ነው።

- በፌዴራል የሚደረገው ድጋፍ ክልሎችና ከታች ያሉ መዋቅሮቻቸው እንዲሁም ማህበረሰቡ በሚያደርገው ድጋፍ ላይ ተጨማሪ ነው።

- አንዳንድ አካባቢዎች ላይ የአህል ክምችት ቢኖረንም ትራንስፖርት ሰጪዎች በፀጥታው ምክንያት በፈለግነው ልክ ለማቅረብ አልቻልንም የሚሉት ነገር አለ። ይሄን ከሚመለከታቸው ጋር ተነጋግሮ ይስተካከላል።

- የድርቅ አደጋ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ መዋቅራዊ አደረጃጀታችን የሚፈቅል አይደለም። የቀበሌ፣ የወረዳ ፣ የዞን፣ የክልል መዋቅር አለን የሚችለውን የመደጋገፍ ስራ ይሰራል። ህይወትን የመታደግ ስራ ይሰራል። እዚህ ላይ የፌዴራልም ድጋፍ አለ።

- የድርቅ አደጋ በሚኖርበት ጊዜ የስነምግብ ሁኔታዎችን በመውሰድ ምናልባት በአካባቢው የሚፈጠሩ ወረርሽኝ እና የመሳሰሉት ነገሮች የተለያዩ ነገሮችን ፈጥረው የዜጎቻችንን በሽታን የመቋቋም አቅም አዳክመው በቀላሉ የመሸነፍ እና የመሳሳሉት ጉዳዮች ሊፈጥር ይችላል።

-ሰዎች እንደሚያነሱት ፤ አንዳንድ #ሚዲያዎች እንደሚያነሱት በእህል እጥረት  ፤ ድርቅ ወደ ረሃብ ተቀይሮ የሰውን ህይወት የሚያጠፋበት ደረጃ የራሱ የሆነ ጊዜ አለው የራሱ የሆነ ጊዜ ይወስዳል በዚህ ነው ሰው የሞተው ለማለት #ምርመራ ይፈልጋል። የሰው የሞት ምክንያት ምንድነው ? እንደምናውቀው ሰው በተለያዩ ምክንያቶች ህይወቱ ያልፋል የዛ ህይወቱ ያለፈው ሰው ምክንያቱ ምንድነው ? የሚለውን የመለየት እና የማረጋገጥ ስራ የራሱ የሆነ አካሄድና  መንገድ ይጠይቃል።

- በእኛ በኮሚሽናችን ግምገማ የተመጣጠነ የምግብ አቅርቦት አለመኖር የሚፈጥራቸው ተጋላጭነት ሊኖር እንደሚችል የምንገነዘብ ቢሆንም ግን በረሃብ ምክንያት ህይወቱ ያለፈ ሰው ስለመኖሩ #ማረጋገጫ_የለንም
.
.
በኢትዮጵያ በተለይም በትግራይ እና አማራ ክልሎች ያሉ ከታች ያሉ መዋቅሮች በረሃብ ምክንያት ሰዎች ህይወት እንዳለፈ በተደጋጋሚ መግለፃቸው ይታወሳል።

በትግራይ ክልል የላይኛው መዋቅርም 25 ህፃናትን ጨምሮ 400 ሰዎች በረሃብ ምክንያት ህይወታቸው እንደጠፋ ማሳወቁ አይዘነጋም።

በክልል ከታች እስከላይ ማዋቅር የሚሰጡት እና ነዋሪዎች የሚገልጹት የረሃብ ሁኔታ በፌዴራል አደጋ ስጋት አመራር ቅቡልነት የለውም። ኮሚሽኑ በረሃብ ምክንያት የጠፋ ህይወት ስለመኖሩም ማረጋገጫ የለኝም ብሏል።

ከዚህ ቀደም የፌዴራል አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን  " ክልሎች ትኩረት እና የተሻለ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ' ይህንን ያህል ሰዎች #ሞተውብኛል፣ ይህንን ያህል ተጎድተውብኛል ' የሚል መረጃ ያቀርባሉ " ማለቱ አየዝነጋም።

@tikvahethiopia
“ 12 የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ተገድለዋል ” - የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበር

“ እውነት ነው። እኔ እንደ ባለሙያ ሁለት ሰዎች የተመቱ አይቻለሁ ” - የዓይን እማኝ የጤና ባለሙያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን ሳርማሌ ወረዳ በትፋቴ ቀበሌ መንግሦት “ሸኔ” ብሎ የሚጠራቸው  ታጣቂዎች በድንገት አደረሱት በተባለ ጥቃት 12 የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻዎች መገደላቸውን የዞኑ ሆስፒታል ባለስልጣንና የሆስፒታሉ ጤና ባለሙያ፣ የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበርና የዓይን እማኞች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል።

የዓይን እማኞቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹት፣ 9ኙ ሚሊሻዎች እሬሳቸው ሆስፒታል አድሮ መሸኘቱን፣ 3ቱ ደግሞ በምዕራብ ጉጂ ዞን በጋላና አባያ ወረዳ ኤርጋንሳ ወይም ፃልቄ ቀበሌ መመለሳቸውን ነው።

ሚሊሻዎች ተገደሉ የሚባል መረጃ ደርሶናል እውነት ነው ? ሲል ቲክቫህ ኢትዮጵያ ላቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምለሽ በኮሬ ዞን የትፋቴ ቀበሌ ሊቀመንበር አቶ መሐመድ ኪታሞ በሰጡት ቃል፣ “እውነት ነው ሚሊሻዎች ተገድለዋል” ብለዋል።

“ፃልቄ የሚባል አካባቢ (በገዳና ፃልቄ መካከል) ላይ 12 የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ተገድለዋል” ያሉት ሊቀመንበሩ፣ ድርጊቱ የተፈጠረው “ሰኞ ዕለት (ጥር 13 ቀን 2016 ዓ/ም) ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው ፤ “ሌሎች ታካሚዎችም አሉ። እኔ ከእነርሱ ጋር አይደለም የቆጠርኩት። የሞቱ ብቻ 12 ናቸው” ብለዋል።

ጥቃቱን ያደረሱት የ “ሸኔ” ታጣቂዎች ናቸው እንዴ ? ተብለው ሲጠየቁም፣ “አዎ የኦሮሚያ ሚሊሻዎች ከሸኔ ጋ ተገናኝተው” ብለዋል።

ስለ ጉዳዩ #ማረጋገጫ እንዲሰጡን ተመሳሳይ ጥያቄ ያቀረብንላቸው የኬሌ ከተማ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ በለጠ በበኩላቸው ፤ “ እኛ ጋ በእርግጥ የህክምና አገልግሎት ለመቀበል የመጡ 2 በጥይት የተመቱ ነበሩ። ከዚያ ወጪ ዘጠኝ እሬሳ እንደመጣና በዚሁ እንዳለፈ ነው የምናውቀው” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

“ መረጃው የደረሰኝ ሁለቱ ተወግተው መጥተው አገልገሎት አግኝተው እንደሄዱና ዘጠኙ እሬሳ ግቢ ገብቶ (ለማሳደር ከምሽቱ 3 በኋላ ነው ያመጧቸው” ያሉት ሥራ አስኪያጁ፣ “አሁን ያሉበትን ደረጃ ባናውቅም ሁለቱ ታክመው ነው የሄዱት” ሲሉ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጡ ስለ ጉዳዩ ጥያቄ ያቀረበላቸው የሆስፒታሉ የጤና ባለሙያ አቶ ገዛኸኝ እንደሻ በበኩላቸው፣ “እውነት ነው። እኔ እንደ ባለሙያ ሁለት ሰዎች የተመቱ አይቻለሁ። ታክመው ለተጨማሪ ህክምና ሂደዋል ጠዋት። የእነርሱ አመራርሮችም (የታካሚዎቹ) መጥተው ነበር” ብለዋል።

አክለውም፣ “የእኛ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነው። የእነርሱ ደግሞ ኦሮሚያ ክልል ስለሆነ በአቅራቢያ በሚገኘው ዞን መጥተው ነበር ወደ እኛ፣ ሲታከሙ አድረው ሂደዋል። የተመቱት የኦሮሚያ ጉጂ ዞን ሚሊሻዎች ናቸው” ሲሉ አስረድተዋል።

ዘገባውን አዘጋጅቶ የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ነው።

@tikvahethiopia