TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬆️

በአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ የአፍሪካ ንዑስ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኮንግረስማን #ክሪስ_ስሚዝ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው #ለውጥ አድናቆት ያላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር #ወርቅነህ _ገበየሁ በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ምክትል ጠ/ሚ ደመቀ⬆️

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ከረጅም ዓመታት የውጭ ሃገር ቆይታ በኋላ ወደ እናት ሃገሩ የተመለሰውን አርቲስት #ታማኝ_በየነን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡

አርቲስት ታማኝ ከረጅም ዓመታት የውጭ ሃገር ቆይታ በኋላ ሲመለስ . . . "ወደ ምትወዳት እናት ሃገርህ እንኳን ደህና መጣህ" ብለውታል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ፡፡

በሃገሪቱ የተጀመረው ለውጥ ውሃ-ልኩን ጠብቆ ለህዝብና ለሃገር የሚተርፍ ቁም-ነገር እንደዜጋ ለማበርከት መልካም መንፈስ እና ቀና ድጋፍ መኖሩን አቶ ደመቀ አውስተዋል፡፡

ከዚህ በኋላ ስለ እናት ሃገር እና ህዝቦቿ በርቀት በመብከንከን ሳይሆን፤ የዜግነት ግዴታን ለመወጣት እና ግላዊ አበርክቶን ለማኖር ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ገልጸዋል፡፡

አርቲስት ታማኝ በበኩሉ መንግስት ያደረገለትን ደማቅ አቀባበል እጅግ እንዳስደሰተው በመግለጽ፤ በሃገሪቱ የተጀመረው #ለውጥ ቀጣይነቱ
እንዲረጋገጥ እና ፍሬ እንዲያፈራ #የበኩሉን እንደሚወጣ ተናግሯል፡፡

"ሃገሬ #በምትፈልገኝ ቦታ ሁሉ በተግባር ለመገኘት ዝግጁ ነኝ!" በማለት አርቲስት ታማኝ ለምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ በውይይቱ ላይ አረጋግጧል፡፡

©Office of Deputy Prime Minister
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ⬇️

የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች መግቢያ ቀናትን እያራዘሙ እደሆነ ይታወቃል። ከዚህ ጋር ተያይዞ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀኑ ስለመራዘሙ የተማሪዎች ህብረት ተወካይን በስልክ አናግሬው ነበር የሰጠኝ ምላሽ፦ "እስካሁን የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀን ላይ ምንም #ለውጥ አልተደረገም። ዩኒቨርሲቲውም በዚህ ጉዳይ ምንም አላለም" ብሎኛል።

📌አዲስ እና የሚቀየር ነገር ካለ የማሳውቃችሁ ይሆናል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ዶ/ር #አብይ_አህመድ በመጨረሻ ሰአት በተደረገ የጉዞ #ለውጥ ምክንያት በሚቀጥለው ሳምንት የአለም መሪዎች ከሚገናኙበት የተ.መ.ድ ስብሰባ #መቅረታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያለው ግለሰብ ለAPው ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት ገልጿል። ዶ/ር አብይ በዘንድሮው ስብሰባ ከፍ ባለ ሁኔታ ከሚጠበቁት የአለም መሪዎች አንዱ እንደሚሆኑ ተገምቶ ነበር።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኤርትራ⬇️

አስር ያህል የኤርትራ ካቢኔ ሚንስትሮች ሀገራቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ጋር የተፈራረመቻቸውን ስምምነቶች አስመልክቶ #ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።

ሚንስትሮቹ ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በሌሎች ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ማብራሪያ እንዲስጧቸው ዛሬ አርብ ቀጠሮ ለመያዝ ሲሞክሩ ነበር።

ሚንስትሮቹ ከፕሬዝዳንት #ኢሳያስ ጋር ውይይት ማድረግ መጀመራቸውን ለስርዓቱ ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች እየገለፁ ነው።

በቅርቡ የሀገሪቱ የቀድሞ የፋይናንስ ሚንስትር ተይዞ #መታሰር፣ የህዝቡ የተሻለ መብት ጥያቄዎች ተደማምረው በርካታ ኤርትራውያን #ለውጥ እንዲኖር ፍላጎት አላቸው።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ታላቁ ሩጫ‼️

ህዳር 9 ቀን 2011 ዓመተ ምህረት የሚካሄደው የዘንደሮው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መነሻና መድረሻ ቦታ #ለውጥ  እንደተደረገበት ተገለፀ።

ለ18ኛ ጊዜ የሚዘጋጀው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ  ከዚህ በፊት  መነሻና መድረሻ ከነበረው  መስቀል አደባባይ  የቦታ ቅያሪ ማድረጉ ተጠቁሟል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ #ኤርሚያስ_አየለ ፥ ውድድሩ ይካሄዳል ተብሎ በተያዘበት እለት ከአፍሪካ ህብረት ልዩ የመሪዎች ጉባኤ ጋር በመገጣጠሙ ቦታው እንዲቀየር መደረጉን አስታውቀዋል።

ስራ አስኪያጁ ከሩጫው ቀን ይልቅ ሩጫው የሚካሄድበትን ቦታ መቀየር ቀላልና የተሻለው አማራጭ ሆኖ መገኘቱንም ጠቅሰዋል።

በመሆኑም ከመላው ዓለም የሚመጡትን ጨምሮ በጠቅላላው 44 ሺህ ህዝብ ይሳተፍበታል ተብሎ የሚጠበቀው የዘንድሮው ሩጫ መነሻና መድረሻ ቦታ ስድስት ኪሎ የሚገኘው የሰማእታት ሀውልት እንዲሆን ተወስኗል።

በዚህም መሰረት ሩጫው ከአደባባዩ በመነሳት በሚኒሊክ ሆስፒታል፣ እንግሊዝ ኤምባሲ በኩል ሾላ ገበያን በመዞር በአድዋ ደልድይ አደርጎ አራት ኪሎ ፓርላማን በማቋረጥ ስደስት ኪሎ ሰማእታት ሀውል ሲደረስ ያበቃል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዴፓ!!

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) #አዲሱን አርማውን በዛሬው እለት ይፋ አደረገ።

አዴፓ ባሳለፍነው መስከረም ወር ባካሄደው 12ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ላይ ነበር የአርማ #ለውጥ እንዲደረግ ውሳኔ ያሳለፈው።

ፓርቲው በድርጅታዊ ጉባዔው አዲሱ አርማ  መደቡ ከላይ አረንጓዴ መሃል ላይ ጎህ ሲቀድ የሚኖር ቀለም (ቢጫ) ሆኖ ከግርጌ ቀይ እንዲሆን መወሰኑ ይታወሳል።

እንዲሁም መሃሉ ላይ የስንዴ ዘለላ እና የኢንዱስትሪ ምልክት በግራ እና በቀኝ እንዲሆን የአባይ ወንዝ እና መጽሃፍም በአርማው መሃል ላይ እንዲካተት በውኖ ነበር።

በዚህም መሰረት የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) አዲሱ አርማውን በዛሬው እለት በፌስ ቡክ ገፁ ይፋ አድርጓል።

ምንጭ፦ ፋና
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሲኣን "የለውጥ ሀይሉ ከትክክለኛ #ለውጥ ፈላጊዎች ጋር ሊናበብ ይገባል" - አቶ ዱካሌ ላሚሶ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) ሊቀመንበር

ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/SID-07-11-2