TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ አጎና (የጎተራ ኮንዶሚኒየም መግቢያ) በሚገኝ ህንፃ ላይ ምሽቱን የእሳት አደጋ መነሳቱን የአካባቢው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

የእሳት ደጋው ከተነሳ ከአንድ ሰዓት በላይ እንዳለፈውና የእሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እሳቱ ተጨማሪ ጥፋት እንዳያደርስ በቁጥጥር ስር ለማዋል ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ።

እስካሁን በህንፃውን አንደኛው ጎን ውስጥ የነበሩ ንብረቶች እየወደሙ ይገኛሉ።

ተጨማሪ መረጃዎችን ተከታትለን እናሳውቃለን።

#TikvahFamilyAA

@tikvahethiopia
" በተለያየ ሶሻል ሚዲያ ' አስቸኳይ ፓስፖርት እናወጣለን ' ከሚሉ ህገወጦች ራሳችሁን ጠብቁ ፤ ... በኦንላይ ምንም አይነት አስቸኳይ ፓስፖርት አይሰጥም " - የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት ምን ያስፈልጋል / ለምን ምን ጉዳዮች ይሰጣል አለ ?

- የህክምና ማስረጃ
- የትምህርት ዕድል ማስረጃ
- ለመንግስት ስራ ጉዳይ ለስብሰባ፣ ለወርክሾኘ
- ጊዜው ያላለፈ የመኖሪያ ፈቃድ ያለው ለባል/ለሚስት/ለልጅ
- ለአስመጭና ላኪ /ከፍተኛ ግብር ከፋይ/
- ፓስፖርት ላይ ጊዜው ያላለፈ የተመታ ቪዛ ካለ /ለማሳደስ/

ከእነዚህ ሰነዶች በአንዱ ዋናው ቢሮ በአካል በመገኘት ብቻ የተሟላ ማስረጃ በመያዝ በአስቸኳይ መስተናገድ ይቻላል ሲል አሳውቋል።

ክፍያ የሚከፈለው በቢሮ ብቻ መሆኑን አስገንዝቧል።

ዜጎች በተለያየ ሶሻል ሚዲያ " አስቸኳይ ፓስፖርት እናወጣለን " ከሚሉ ህገወጦች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

በኦን ላይን ምንም አይነት አስቸኳይ ፓስፖርት የማይሰጥ መሆኑንም ገልጾ ዜጎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመውጫ ፈተና ከየካቲት 6 እስከ የካቲት 11 ቀን 2016 ድረስ ይሰጣል። የ2016 ዓ/ም የአመቱ አጋማሽ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከነገ ረቡዕ የካቲት 6 ጀምሮ መሰጠት ይጀምራል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ዩኒቨርሲቲዎች ከትምህርት ሚኒስቴር ተልኮልናል ብለው ያጋሩትን የተሻሻለ የፈተና መርሃ ግብር የተመለከተ ሲሆን በዚህ መርሀ ግብር ሀገር አቀፉ የመውጫ ፈተና እስካ የካቲት 11 /2016 ዓ/ም ድረስ ይሰጣል።…
የመውጫ ፈተና ዛሬ በጤና ትምህርት ፕሮግራሞች  መሰጠት ጀምሯል።

ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛው ዙር የመውጫ ፈተና ከዛሬ ካቲት 6/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሰጠት እንደተጀመረ ገልጿል።

በዛሬው እለት በጤና ፕሮግራሞች በተጀመረው ፈተና ጠዋት 15,440 ተማሪዎች በ23 የጤና ፕሮግራሞች የተፈተኑ ሲሆን ከሰዓት 14,807 ተማሪዎች በ13 ፕሮግራሞች ተፈትነዋል።

ፈተናው በሁሉም የፈተና ማዕከላት ከተማ እየተሰጠ ሲሆን የመውጫ ፈተና አሰጣጡ ፍትሃዊነትና ተአማኒነት ለማስጠበቅና አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ የተመደቡ ታዛቢዎች በየተመደቡበት ተቋማት በመገኘት ስራ መጀመራቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

የሁለተኛ ዙር ፈተናው ፦
- በ47 የመንግስት ተቋማት
- በ84 የፈተና ማዕከላት የሚሰጥ ሲሆን በመንግስትና ግል ተቋማት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑትን ጨምሮ 149,145  ተፈታኞች በ204 የፈተና ፕሮግራሞች ይፈተናሉ።

ፈተናው የካቲት 11/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል ሲል ትምህርት ሚኒስቴር አመላክቷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

በአዱስ አበባ አጎና የተነሳው እሳት መጀመሪያ ላይ ከነበረበት የወደ መጥፋት ደረጃ ቢቀንስም እሳቱ ሙሉ በሙሉ አልጠፋም።

በስፍራው የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እና ተሽከርካሪዎች የሚገኙ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስም አጋዥ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስፍራው በመላክ እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል።

የእሳት አደጋ በተነሳበት ህንፃ ላይ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚገኙበት ነው።

የአደጋው መንስኤ እና ሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ይኖር እንደሆነ እስካሁን በውል አልታወቀም።

መረጃውን የላኩት በስፍራው የሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መርዓዊ

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን ነው የተከላከለው ፤ ... የመከላከያ ኃይል የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረግም " - መንግሥት

መንግሥት በመርዓዊ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ጉዳይ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ መንግሥት በመርዓዊ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን የ45 (ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ይላል) ሰላማዊ ሰዎች ግድያ አስተባብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ቢያንስ 45 ሲቪሎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መገደላቸውን ፤  " የፋኖ አባላት ናቸው " በሚል ተጠርጥረው የተያዙ እና ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሰዎች በተመሳሳይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን ማሳወቁ ይታወሳል።

የንፁሃን ግድያን እንዲሁም የኢሰመኮን ሪፖርት በተመለከተ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ድርጊቱን አስተባብለዋል።

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፤ በመርዓዊ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር አረጋግጠዋል።

" ታጣቂዎቹ በተለያዩ አቅጣጫዎች መከላከያ ሠራዊቱ የሰፈረበትን ካምፕ በአራት አቅጣጫ በማፈን መሣሪያ እና ሎጂስቲኩን ለመዝረፍ በመንቀሳቀሳቸው ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ ነው እርምጃ ወስዷል " ሲሉ ተናግረዋል።  

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ እርምጃ ሲወስድ እነዚህ ኃይሎች ተመልሰው ወደ ግለሰቦች ቤት ነው የገቡት " ያሉት ዶ/ር ለገሰ " ወደ ግለሰቦች ቤት በሚገቡበት ጊዜ በሕጉ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አሰሳ ሲያደርግ መልሰው ተኩስ ከፈቱበት " ብለዋል።

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን ነው የተከላከለው " ያሉት ዶ/ር ለገሰ ፤ " የመከላከያ ኃይል የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረግም " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች መግለጫ ያወጡ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በመንግሥት የፀጥታ ኃይላት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰዎች መካከል ከቤት እየተወሰዱ የተገደሉ መኖራቸውን መግለፃቸው ይታወቃል።

ይህንን በተመለከተ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ፤ " እንደዚያ አይነት እርምጃ ስለመወሰዱ ተረጋግጦ የመጣ መረጃ የለም " ብለዋል።

አክለውም " ሲቪል ይቅርና ታጣቂ እንኳን ለማጥቃት ሄዶ እጅ እስከሰጠ ድረስ የሚገደልበት ሥርዓት የለም። ሊሆንም አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" እንዲህ ሆኖ ከሆነም ራሱ መከላከያ ተቋሙ እርምጃ ይወስዳል" ሲሉ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የመርዓዊን ግድያ በተመለከተ በኢትዮጵያ የካናዳ ኤምባሲ " እጅግ ያሳስበኛል " ብሏል።

ተፈጽሟል የተባለውን ግድያ " የሚረብሽ ነው " ያለው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ በበኩሉ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ መንግሥት በበኩላቸው ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ይህ ጉዳይ የሚመለከተው በአማራ ክልል የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ እንደሆነ አሳውቀዋል።

" በጉዳዩ ላይ ምርመራ የሚያደርግ ሌላ አካል አይኖርም " ሲሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ለገሰ ጥሪውን ያቀረቡት የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ መንግሥት " ስለ ኢትዮጵያ ሁሌ እንዳሳሰባቸው ነው። ነገር ግን ይኸ ነው የሚባል የሚደረግ ነገር የለም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። 

" የራሳችን ተቋሞች አሉ። ተቋሞቻችን ለሕዝብ ተጠያቂ ናቸው የትኛውም አካል ጥፋት ካጠፋ፤ የትኛውም አካል ጉዳት ካደረሰ ሕጉ እና አሠራሩ በሚፈቅደው መሠረት እርምጃ ይወሰዳል " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ከ37ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ እና 44ኛው የሚኒስትሮች ስራ አስፈፃሚ ም/ቤት ስብሰባ ጋር በተያያዘ አሽከርካሪዎች ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ጉባኤው ተጀምሮ እስከሚጠናቀ ፦

ከፓርላማ መብራት-በውጭ ጉዳይ ሚ/ር - መስቀል አደባባይ ፍላሚንጎ - ኦምሎፒያ - ወሎ ሰፈር - ጃፓን ኤምባሲ - ፍሬንድ ሺፕ -ቦሌ ቀለበት መንገድ - ኤርፖርት

ከፓርላማ መብራት በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር -በብሔራዊ ቤተ - መንግስት -በፍልውሃ - በብሔራዊ ቴአትር- ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት አዳራሽ ዙሪያ

ከፓርላማ መብራት -ብሔራዊ ቤተ-መንግስት - ወዳጅነት ፓርክ - ንግድ ማተሚያ ቤት - ሞናርክ ሆቴል-ቴዎድሮስ አደባባይ-ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል- ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን- ብሔራዊ ቴአትር - ሜክሲኮ አደባባይ - አፍሪካ ህብረት መንገዶቹ እንግዶች ሲያልፉ አሽከርካሪዎችም ሆኑ እግረኞች ለእንግዶቹ ቅድሚያ በመስጠት ተባባሪ እንዲሆኑና ሌሎች ተለዋጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ መልዕክት ተላልፏል።

ከዚህ ባለፈ ፦

ከፓርላማ መብራት-በሸራተን ሆቴል ቁልቁለቱን-ፍልውሃና አምባሳደር ቴአትር ዙሪያውን

ከንግድ ም/ቤት ጀምሮ በሱዳን ኤምባሲ-አፍሪካ ህብረት ዋናው በር-ሳርቤት ድረስ በሁለቱም አቅጣጫዎች ከነገ ሐሙስ የካቲት 7 ቀን / 2016 ዓ/ም ጀምሮ እንግዶች ተጠቃለው እስኪመለሱ ድረስ ግራና ቀኝ በሁለቱም አቅጣጫ ለአጭርም ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
የውሃ ሽታ

እጁ ላይ ባለው የማስታወሻ ፅሁፍ ብቻ ፀሎትን በደንብ አወቃት። የበለጠ ሊያውቃትም ፈለገ ሊያገኛት ግን አይችልም። በህይወት ያለን ገዳይ ፍለጋ ውስጥ በህይወት ከሌለችው ፀሎት ጋር በፍቅር….
እንዴት? ለምን? የፀሎት የውሃ ሽታ መሆን ሮቤልን አወዛገበው።

ዛሬ ምሽት በ3:00 ሰዓት

እርስዎ ባልተጠበቀ መንገድ የሞተ ሰው ማስታወሻ ቢያገኙ ምን ያደርጋሉ?

በ አቦል ቲቪ 465

ፓኬጅ: ሜዳ

የዲኤስቲቪ ዲኮደር በ1,199 ብር ከ1 ወር ነፃ ሜዳ ፓኬጅ ጋር ያገኛሉ።

የዲኤስቲቪ የተለያዩ አገልግሎቶችን ለማግኘት ከታች  ያለውን የMyDStv Telegram ሊንክ ይጫኑ!
👇
https://bit.ly/2WDuBLk

#ሁሉምያለውእኛጋርነው #DStvEthiopia #YewehaSheta #የውሃሽታ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአዱስ አበባ አጎና የተነሳው እሳት መጀመሪያ ላይ ከነበረበት የወደ መጥፋት ደረጃ ቢቀንስም እሳቱ ሙሉ በሙሉ አልጠፋም። በስፍራው የአዲስ አበባ እሳት አደጋ ተቆጣጣሪዎች እና ተሽከርካሪዎች የሚገኙ ሲሆን የፌዴራል ፖሊስም አጋዥ ተሽከርካሪዎችን ወደ ስፍራው በመላክ እሳቱን ሙሉ በሙሉ ለማጥፋት ርብርብ እየተደረገ ይገኛል። የእሳት አደጋ በተነሳበት ህንፃ ላይ የተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች…
" ቃጠሎ በደረሰበት ህንፃ ላይ ምንም አይነት የቤተክርስቲያን አገልግሎት አይሰጥም ፤ ይሄንን አረጋግጠናል ! " - አቶ ንጋቱ ማሞ

ትላንት ምሽት በአ/አ በቀድሞ አጎና ሲኒማ ህንፃ ላይ የተነሳው እሳት ለመቆጣጠር እጅግ ፈታኝ እንደነበር የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ አሳውቋል።

እሳቱን መቆጣጠር ከባድ ያደረገው በፍጥነት በመስፋፋቱ ነው ተብሏል።

በእሳት አደጋው የህንፃው አንደኛ እና ሁለተኛ ወለሎች ከነሙሉ ንብረታቸው ወድመዋል።

ህንፃው ላይ የነበረው የውጭ የትርጉም ፊልም የሚያቀርበው " ያ " የተሰኘ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሙሉ በሙሉ ንብረቱ የታቀጠለ ሲሆን ቤተክርስቲያን ላይ ጉዳት ደረሰ ተብሎ የተወራው ግን የተሳሳተ መረጃ ነው።

የእስት እና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ባለሞያው አቶ ንጋቱ ማሞ ምን አሉ ?

- አደጋው በቀድሞ የአጎና ሲኒማ ህንፃ ላይ ነው የደረሰው።

- በአደጋው ምክንያት አንደኛ እና ሁለተኛ ፎቆ ላይ ያሉ ንብረቶችን ጨምሮ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

- ከባድ ጉዳት ከገጠማቸው መካከል ያ የቴሌቪዥን ስቱዲዮ የፕሮዳክሽን ስራ የሚሰሩበት ተጠቃሽ ነው።

- እሳቱ እኛ ከመድረሳችን አስቀድሞ የተስፋፋ ስለነበር በቀላሉ ለመቆጣጠር ችግር ነበር።

- ለስቱዲዮ ሳውንድፕሩፍ ተብሎ አገልግሎት ላይ የዋለ ስፖንጅ እና የመሳሰለው ቁሳቁስ ለእሳቱ መስፋፋት አስተዋጽኦ አድርጓል። ለጊዜው ያላወቅነው በርካታ የፕላስቲክ ወንበሮች አንደኛ ፎቅ ላይ ነበሩ እነሱም ተደማምረው እሳቱ ሰፍቷል።

- በእኛ በኩል እሳቱ ተስፋፍቶ ሌሎች ቦታዎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ማድረግ ተችሏል። ይህ ሂደት 5 ሰዓት ከ40 ደቂቃ ፈጅቷል።

- አደጋው ለመቆጣጠር ከተሰማሩት ሰራተኞች አንዱ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል።

ከዚሁ ከእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ውድመት ከደረሰባቸው ውስጥ በአንደኛ ፎቅ ላይ የሚገኝ " ቤተክርስቲያን ይገኝበታል " በሚል የሚሰራጨውን መረጃ በተመለከተ ፤ " የተሳሳተ መረጃ ነው " ብለዋል።

" እስካሁን ማረጋገጥ የተቻለው ያ የቴሌቪዥን ስቱዲያውን ነው " ያሉት ባለሞያው " ሌሎች ህንፃው ላይ የነበሩ የንግድ እና አገልግሎት ሰጪዎችን እያጣራን ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

አቶ ንጋቱ ፤ " ከቤተክርስቲያን ጋር ተያይዞ በዚህ ቃጠሎ በደረሰበት ህንፃ ላይ ምንም አይነት የቤተክርስቲያን አገልግሎት የሚሰጥበት አይደለም። ይሄን አረጋግጠናል። ከእምነት ተቋም ጋር ተያይዞ ምንም አይነት አደጋ አላጋጠመም ይሄን አረጋግጠናል። " ሲሉ አሳውቀዋል።

አጠቃላይ በአደጋው ስለደረሰው ጉዳት እና መንስኤ እስካሁን አልታወቀም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ መረጃውን ከሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ጣቢያ ነው ያገኘው።

@tikvahethiopia
10 ዓመት ?

የ13 ዓመት ልጃቸውን አስገድደው የደፈሩት አባት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን (በቀድሞው አማሮ ልዩ ወረዳ) ኬሌ 01 ቀበሌ በተለምዶ " ማክሰኞ ሰፈር " ተብሎ በሚጠራዎ አካባቢ አንድ አባት በመጋቢት ወር 2015 ዓ/ም ልጃቸውን አስገድደው የደፈሩት አባትበእስራት እንደተቀጡ የዞኑ ፎትህ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ወንጀሉን የፈጸሙት አቶ ስንታየሁ ከተማ መኮንን የተባሉ የ42 ዓመት አባት የአብራካቸው ክፋይ የ13 ዓመት 8ኛ ክፍል ተማሪ ልጃቸው ላይ ነበር።

በለበሰችው ሻርፕ አፏን አስሮ ኃይል ተጠቅሞ ደፍሯታል።

ልጅቷ በተደረገባት ድርጊት ማሕጸኗን ሕመም ሲሰማትና መቋቋም ባለመቻሏ የዐቃቢ ሕግ 2ኛ ምስክር ለሆነች ጎረቤቷ እያለቀሰችና እያነከሰች ሂዳ የተፈጸመባትን በዝርዝር ተናግራ ጎረቤቷም ወደ ሕክምና ተቋም አብረዋት ሂደው አስመርምረዋታል።

በምርመራውም በሕፃኗ ላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የመደፈር ወንጀል መፈጸሙንና የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በደሟ መገኘቱን በሕክምናው ተረጋግጧል።

የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጉዳዩን ሰምተውት የወንጀል ምርመራ አድርገዋል።

የኮሬ ዞን ከፍተኛ አቃቢ ሕግ ክስ በመመስረት ጉዳዩን በወቅቱ ለነበረው የአማሮ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሹም ወንጀል ስለመፈጸማቸው በችሎት ተጠይቀው ‘አልፈጸምኩም’ ብለው ክደው ተከራክረዋል።

በክርክሩ ልጅቷ የ13 ዓመት ታዳጊ በመሆኗ ከ5-20 ዓመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑና በልጅቷ ላይ ዛቻና እንግልት በመፈጸማቸው አባት ዋስትናቸው ተነፍጎ በፓሊስ እጅ ሆነው እንዲከራከሩ ተደርገዋል።

ፍርድ ቤት የልጅቷን፣ የዐቃቢ ሕግ ቃል ሰምቶ ምክሮችም እንደ ዐቃቢ ሕግ ክስ በዝርዝር ወንጀል ስለመፈጸሙ አስረድተው፣ የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮችም አባት ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ ለማስተባበል ቢሞክሩም በግልጽ ያስረዱት ነገር እንደሌለ ተመላክቷል።

በዚህም ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኝ የምስክር አመሰካከር፣ የቀረቡ የሕክምና ሰነዶች ከተገቢ ሕጎች ጋር አይቶ ግለሰቡም ጥፋተኛ ብሎ በሙሉ ድምፅ ፍርድ ሰጥቷል።

ዐቃቢ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ሲጠየቅ በሕጉ በራሱ ከብዶ የተዘረዘረ ስለሆነ የለኝም ያለ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቃ ፤ ቀደም ሲል ደንበኛቸው በወንጀል ተፈርዶበት የማያውቅ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ፣ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መድኃኒት ተጠቃሚ ስለሆነ ለፍርድ ቤቱ 3 ማቅለያዎችን አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኝ ተመልክቶ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ እንደወስነበት የዞኑ ፍትህ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ ያቀረበው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

@tikvahethiopia
 
#ከጠቀማችሁ

ከላይ በፎቶው የምትመለከቷቸው ተሽከርካሪዎች የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በጨረታ ለመሸጥ ያቀረባቸው ናቸው።

የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የተለያዩ ፦
- ያገለገሉ ቀላል ተሽከርካሪዎች
- ያገለገሉ ከባድ ተሽክርካሪዎች ፤
- ቁርጥራጭ የመኪና አካላት (ስክራፕ) እና የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (ስክራፕ) ንብረቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ እስከ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ከጠዋቱ 03:00 እስክ 10:00 ሰዓት ድረስ አዲስ አበባ በሚገኘው የመከላከያ ሠራዊት መኮንኖች ከበብ በመገኘት የተሽከርካሪ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረት (ስክራፕ) ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

ተጫራቾች እስከ የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ/ም ባሉት ቀናቶች የሚሸጡትን ተሽከርካሪዎች ለማየት ኮፈን ተከፍቶ ስለሚቆይ ዘውትር በስራ ሰዓት ከጥዋቱ 3:09 እስከ 10:00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን ቢሾፍቱ በሚገኘው አውቶሞቲቭ ካምፕ ጀርባ በመሄድ ሞያተኛ ይዞ መመልከት ይችላሉ።

ጨረታው የካቲት 18/2016 ከጥዋቱ 4:00 ሰዓት የሚዘጋ ሲሆን  በዚያው ቀን 4:30 ይከፈታል። የሁሉም ተሽከርካሪዎች ጨረታ የሚከፈተው በመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ክበብ ነው።

አሸናፊዎች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው ከከፈሉ በኃላ ተሽከርካሪዎቹን በ30 የስራ ቀናት ውስጥ ማንሳት ግዴታ አለባቸው።

ለስም ማዞሪያ ወጪ እና ብረታ ብረቶችን ከቦታው ለማንሳት የሚያስፈልግ ወጪ  ሙሉ በሙሉ በገዢዎቹ ነው የሚሸፈነው።

ቁርጥራጭ ብረቶችን ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ብረታ ብርት የማቅለጥ ፍቃድ የተሰጠው ብቻ ነው ተብሏል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ምናልባት ለስራም ሆነ ለግል ጉዳያችሁ ከጠቀመ በሚል ነው ይህን መረጃ ያጋራው።

@tikvahethiopia