TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መርዓዊ

ጠፍታ በፖሊስ ስትፈለግ የቆየችው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ተቀብራ ተገኘች፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ በተለምዶው ሚካዔል ቁጥር 1 (150 ሰፈር) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወረቀት አደመ አመራ የተባለች ግለሰብ ግንቦት 02/2015 ዓ.ም እንደጠፋች ከሟች ዘመድ ለፖሊስ ጥቆማ ይደረሳል፡፡

ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ግንቦት 06 ቀን 2015 ዓ/ም በቤቷ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ተቀብራ ተገኝታለች፡፡

የሟች አስከሬን ቤተሰቦቿ ፤በአካባቢው ነዋሪዎችና በፖሊስ አባላት ተቆፍሮ ወጥቶ  መርዓዊ ከተማ የመጀመሪያ ሆስፒታል ምርመራ የተደረገ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹን ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የመርዓዊ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መርዓዊ

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን ነው የተከላከለው ፤ ... የመከላከያ ኃይል የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረግም " - መንግሥት

መንግሥት በመርዓዊ የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ጉዳይ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ መንግሥት በመርዓዊ ከተማ ተፈጽሟል የተባለውን የ45 (ቁጥሩ ከዚህም ከፍ ይላል) ሰላማዊ ሰዎች ግድያ አስተባብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ቢያንስ 45 ሲቪሎች በመንግሥት የፀጥታ ኃይል መገደላቸውን ፤  " የፋኖ አባላት ናቸው " በሚል ተጠርጥረው የተያዙ እና ለጊዜው ብዛታቸውን ለማረጋገጥ ያልተቻለ ሰዎች በተመሳሳይ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች ከሕግ ውጭ መገደላቸውን ማሳወቁ ይታወሳል።

የንፁሃን ግድያን እንዲሁም የኢሰመኮን ሪፖርት በተመለከተ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ቃላቸውን የሰጡት የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ድርጊቱን አስተባብለዋል።

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ፤ በመርዓዊ በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር አረጋግጠዋል።

" ታጣቂዎቹ በተለያዩ አቅጣጫዎች መከላከያ ሠራዊቱ የሰፈረበትን ካምፕ በአራት አቅጣጫ በማፈን መሣሪያ እና ሎጂስቲኩን ለመዝረፍ በመንቀሳቀሳቸው ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ ነው እርምጃ ወስዷል " ሲሉ ተናግረዋል።  

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን የመከላከል መብቱን ተጠቅሞ እርምጃ ሲወስድ እነዚህ ኃይሎች ተመልሰው ወደ ግለሰቦች ቤት ነው የገቡት " ያሉት ዶ/ር ለገሰ " ወደ ግለሰቦች ቤት በሚገቡበት ጊዜ በሕጉ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት አሰሳ ሲያደርግ መልሰው ተኩስ ከፈቱበት " ብለዋል።

" መከላከያ ሠራዊት ራሱን ነው የተከላከለው " ያሉት ዶ/ር ለገሰ ፤ " የመከላከያ ኃይል የትኛውንም ዐይነት ሲቪል ዒላማ አላደረግም " ብለዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንን ጨምሮ ሌሎች መግለጫ ያወጡ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች በመንግሥት የፀጥታ ኃይላት እርምጃ ከተወሰደባቸው ሰዎች መካከል ከቤት እየተወሰዱ የተገደሉ መኖራቸውን መግለፃቸው ይታወቃል።

ይህንን በተመለከተ የተጠየቁት ሚኒስትሩ ፤ " እንደዚያ አይነት እርምጃ ስለመወሰዱ ተረጋግጦ የመጣ መረጃ የለም " ብለዋል።

አክለውም " ሲቪል ይቅርና ታጣቂ እንኳን ለማጥቃት ሄዶ እጅ እስከሰጠ ድረስ የሚገደልበት ሥርዓት የለም። ሊሆንም አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" እንዲህ ሆኖ ከሆነም ራሱ መከላከያ ተቋሙ እርምጃ ይወስዳል" ሲሉ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል ፤ የመርዓዊን ግድያ በተመለከተ በኢትዮጵያ የካናዳ ኤምባሲ " እጅግ ያሳስበኛል " ብሏል።

ተፈጽሟል የተባለውን ግድያ " የሚረብሽ ነው " ያለው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ኪንግደም ኤምባሲ በበኩሉ ሙሉ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ መንግሥት በበኩላቸው ገለልተኛ ምርመራ እንዲደረግ ጥሪ አስተላልፈዋል።

ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ይህ ጉዳይ የሚመለከተው በአማራ ክልል የተደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቦርድ እንደሆነ አሳውቀዋል።

" በጉዳዩ ላይ ምርመራ የሚያደርግ ሌላ አካል አይኖርም " ሲሉ ገልጸዋል።

ዶ/ር ለገሰ ጥሪውን ያቀረቡት የአውሮፓ ኅብረት እና የአሜሪካ መንግሥት " ስለ ኢትዮጵያ ሁሌ እንዳሳሰባቸው ነው። ነገር ግን ይኸ ነው የሚባል የሚደረግ ነገር የለም " ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። 

" የራሳችን ተቋሞች አሉ። ተቋሞቻችን ለሕዝብ ተጠያቂ ናቸው የትኛውም አካል ጥፋት ካጠፋ፤ የትኛውም አካል ጉዳት ካደረሰ ሕጉ እና አሠራሩ በሚፈቅደው መሠረት እርምጃ ይወሰዳል " ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia