#መርዓዊ

ጠፍታ በፖሊስ ስትፈለግ የቆየችው ግለሰብ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ በመኖሪያ ቤቷ ውስጥ ተቀብራ ተገኘች፡፡

በምዕራብ ጎጃም ዞን በመርዓዊ ከተማ አስተዳደር 03 ቀበሌ በተለምዶው ሚካዔል ቁጥር 1 (150 ሰፈር) ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነዋሪ የሆነችው ወረቀት አደመ አመራ የተባለች ግለሰብ ግንቦት 02/2015 ዓ.ም እንደጠፋች ከሟች ዘመድ ለፖሊስ ጥቆማ ይደረሳል፡፡

ፖሊስ የደረሰውን ጥቆማ መሰረት በማድረግ ባደረገው ክትትል ግንቦት 06 ቀን 2015 ዓ/ም በቤቷ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድላ ተቀብራ ተገኝታለች፡፡

የሟች አስከሬን ቤተሰቦቿ ፤በአካባቢው ነዋሪዎችና በፖሊስ አባላት ተቆፍሮ ወጥቶ  መርዓዊ ከተማ የመጀመሪያ ሆስፒታል ምርመራ የተደረገ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹን ይዞ ለፍርድ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት የወንጀል ምርመራ ክፍል አስታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የመርዓዊ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia