10 ዓመት ?

የ13 ዓመት ልጃቸውን አስገድደው የደፈሩት አባት በ10 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጡ።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን (በቀድሞው አማሮ ልዩ ወረዳ) ኬሌ 01 ቀበሌ በተለምዶ " ማክሰኞ ሰፈር " ተብሎ በሚጠራዎ አካባቢ አንድ አባት በመጋቢት ወር 2015 ዓ/ም ልጃቸውን አስገድደው የደፈሩት አባትበእስራት እንደተቀጡ የዞኑ ፎትህ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ወንጀሉን የፈጸሙት አቶ ስንታየሁ ከተማ መኮንን የተባሉ የ42 ዓመት አባት የአብራካቸው ክፋይ የ13 ዓመት 8ኛ ክፍል ተማሪ ልጃቸው ላይ ነበር።

በለበሰችው ሻርፕ አፏን አስሮ ኃይል ተጠቅሞ ደፍሯታል።

ልጅቷ በተደረገባት ድርጊት ማሕጸኗን ሕመም ሲሰማትና መቋቋም ባለመቻሏ የዐቃቢ ሕግ 2ኛ ምስክር ለሆነች ጎረቤቷ እያለቀሰችና እያነከሰች ሂዳ የተፈጸመባትን በዝርዝር ተናግራ ጎረቤቷም ወደ ሕክምና ተቋም አብረዋት ሂደው አስመርምረዋታል።

በምርመራውም በሕፃኗ ላይ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የመደፈር ወንጀል መፈጸሙንና የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቫይረስ በደሟ መገኘቱን በሕክምናው ተረጋግጧል።

የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ጉዳዩን ሰምተውት የወንጀል ምርመራ አድርገዋል።

የኮሬ ዞን ከፍተኛ አቃቢ ሕግ ክስ በመመስረት ጉዳዩን በወቅቱ ለነበረው የአማሮ ልዩ ወረዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሹም ወንጀል ስለመፈጸማቸው በችሎት ተጠይቀው ‘አልፈጸምኩም’ ብለው ክደው ተከራክረዋል።

በክርክሩ ልጅቷ የ13 ዓመት ታዳጊ በመሆኗ ከ5-20 ዓመት ሊደርስ በሚችል ጽኑ እስራት የሚያስቀጣ በመሆኑና በልጅቷ ላይ ዛቻና እንግልት በመፈጸማቸው አባት ዋስትናቸው ተነፍጎ በፓሊስ እጅ ሆነው እንዲከራከሩ ተደርገዋል።

ፍርድ ቤት የልጅቷን፣ የዐቃቢ ሕግ ቃል ሰምቶ ምክሮችም እንደ ዐቃቢ ሕግ ክስ በዝርዝር ወንጀል ስለመፈጸሙ አስረድተው፣ የተከሳሽ መከላከያ ምስክሮችም አባት ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ ለማስተባበል ቢሞክሩም በግልጽ ያስረዱት ነገር እንደሌለ ተመላክቷል።

በዚህም ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኝ የምስክር አመሰካከር፣ የቀረቡ የሕክምና ሰነዶች ከተገቢ ሕጎች ጋር አይቶ ግለሰቡም ጥፋተኛ ብሎ በሙሉ ድምፅ ፍርድ ሰጥቷል።

ዐቃቢ ሕግ የቅጣት ማክበጃ ሲጠየቅ በሕጉ በራሱ ከብዶ የተዘረዘረ ስለሆነ የለኝም ያለ ሲሆን የተከሳሽ ጠበቃ ፤ ቀደም ሲል ደንበኛቸው በወንጀል ተፈርዶበት የማያውቅ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪ ፣ የኤች.አይ.ቪ ኤድስ መድኃኒት ተጠቃሚ ስለሆነ ለፍርድ ቤቱ 3 ማቅለያዎችን አቅርበዋል።

ፍርድ ቤቱ ግራ ቀኝ ተመልክቶ በ10 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ እንደወስነበት የዞኑ ፍትህ ቢሮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

መረጃውን አዘጋጅቶ ያቀረበው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ነው።

@tikvahethiopia