TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ፤ ለተፈናቃዮች መቅረብ የጀመረው የምግብ ድጋፍ ተፈናቃዮች የሚገኙበትን አሳሳቢ ሁኔታ በሚመጥን ደረጃ ሊጠናከር ይገባል ብሏል ዛሬ በላከልን መግለጫ።
 
ኮሚሽኑ የምግብ ድጋፍ አቅርቦት ወቅቱን የጠበቀ፣ በቂ፣ ተደራሽ እና የሕፃናትን ፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ልዩ ፍላጎት ያገናዘበ ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝቧል።

(ከኢሰመኮ የተላከልን ዝርዝር መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

- " መንግሥት ኢሰመኮ ስለአማራ ክልል ያወጣውን ሪፖርት በተመለከተ ያወጣው መገለጫ ለሁሉም የሲቪክ ማኅበራት ማስፈራሪያ  ነው። ...የሲቪክ ማኅበራት ሪፓርት ማውጣት የሚፈሩበት ጊዜ ላይ ነው ያሉት " - ከኢትዮያ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ማዕከል (አቶ ያሬድ ኃይለማርያም)

- " አሁን ያለንበት ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ ነው፣ የመንግሥት አካላት በአስቸኳይ መፍትሄ መስጠት አለባቸው ካልሆነ የማንወጣበት አሮንቃ ውስጥ ነው የምንገባው። " -  ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) (አቶ ዳን ይርጋ)

- " ፍርድ ቤት ዋስትና የፈቀደለትን ሰው ወስዶ የሆነ ቦታ ማቆየት፣ ያለ ፍርድ ማሰር በተግባር የምናየው ቻሌንጅ ነው። ይህ ባለበት ሁኔታ ፓሊስ በተለይ የዜጎችን መብት በማክበርና በማስከበር በኩል ሁነኛ ተቋም ሆኖ እያለ በተግባር ያለው ግን ያ አይደለም " - ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ድርጅት ኅብረት (አቶ መሱድ)

- " 62 የፓለቲካ ፓርቲዎች አሉ ፤ እኛ ልንመርጣችሁ ወይስ እናንተ ልትመርጡን ነው ? እኛ የምንፈልገው 2፣ ቢበዛ ደግሞ 4 ነው። ለምን ወደዛ አትመጡም? የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚናፍቀው የባለስልጣናት ምርጫ አይደለም፣ የፓሊሲ ምርጫ ይፈልጋል። ለዚህስ ተዘጋጅታችኋል? "  - ከቪዢንና ኮይግረንስ ፎር ዴሞክራሲ  (አቶ ታደለ ደረሰ)

ቲክቫህ ኢትዮጵያ 75ኛውን የሰብዓዊ መብቶች በዓል በማስመልከት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከተባበሩት መንግሥትታት ጋር በመተባበር ጥቅምት 23 ቀን በሸራተን አዲስ ባዘጋጀው ፕሮግራም ላይ በመገኘት ሁነቱን ተከታትሏል ፤ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ኃላፊዎችንም አነጋግሯል።

(በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ተኩዬ ተዘጋጅቶ የቀረበ)

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-04-3

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እባክችሁ መፍትሄ ስጡን ፤ ጊዜው ያለ ትምህርት እየሄደብን ነው " - ተማሪዎች በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የሚማሩ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት እንዳልተመለሱ በመግለፅ ትምህርት ሚኒስቴር መፍትሄ እንዲፈልግላቸው ጥሪ አቀረቡ። መልዕክታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች እስካሁን የሚማሩባቸው ግቢዎች እንዳልጠሯቸው በማመልከት ያለ ትምህርት መቀመጣቸውን ገልጸዋል። በእነሱ እድሜና…
#Update

በአማራ ክልል የሚገኙ የ10 ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዜዳንቶች በቅርቡ ከክልሉ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አኳያ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠል ይቻል እንደሆነ ውይይት እንዳደረጉ ቪኦኤ ዘግቧል።

የክልሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ዋና ፀሀፊ ዶ/ር አስማረ ደጀን ለቪኦኤ ሬድዮ በሰጡት ቃል፤ የዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዜዳንቶች ባደረጉት ውይይት ወቅታዊው የክልሉ የፀጥታ ችግር በቅርቡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማስቀጠል የሚያስችል እንዳልሆነ የጋራ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል።

ዶ/ር አስማረ ደጀን፦

" ተማሪዎችን አስገብተን እንዲህ ያሉ ግጭቶች በሚመጡበት ጊዜ ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊነት አይወስዱም።

የፀጥታ አካሉ፣መንግሥት ነው ኃላፊነት የሚወስደው ምክንያቱም ፀጥታውን የሚያስከብረው መንግሥት ነው።

በተለይ የ12ኛ ክፍል ስናስፈትን የሁለተኛው ዙር ፈተና ሃምሌ አካባቢ ነበርና ተማሪዎች እንደነበሩ ግጭቱ ተጀመረ ተማሪዎችን የሚወስዳቸው ጠፋ ኃላፊነት የሚወስድ መቶ በመቶ ጠፋ ስለዚህ ዩኒቨርሲቲዎች ምንም ማድረግ አልቻሉም፤ የተለያዩ አካላትን ማግኘት አልቻሉም ተማሪዎችም የ200፣ የ120፣ የ100 ኪ/ሜ መንገድ በእግራቸው ተጉዘው ወደቤተሰቦቻቸው የሄዱበት ሁኔታ ነው ያለው፤በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በሚባልበት ደረጃ።

ዩኒቨርሲቲዎች አንደኛ ለ2016 የሚሆን የምግብ አቅርቦት ማዘጋጀት ነበረባቸው ነገር ግን አቅራቢዎቹ ከቦታ ቦታ ምርት ካለበት ቦታ ሄደው ተዘዋውረው መግዛት ስላልቻሉ የምግብ ግብአቶች በጠቅላላው ተማሪን ለመጥራት የሚያስችልበት ሁኔት አይደለም/ተማሪን ሊያስጠራ የሚችል ግብአት የለንም።

ተማሪ ይጠራ ቢባል ተማሪዎቻችን ከተለያዩ ክፍለ ሀገራት፣ ከክልሎች ነው የሚመጡት። "

ፎረሙ መንግስት የሚጠየቀውን ቅድመ ሁኔታ ማመቻቸት ከቻለ ዩኒቨርሲቲዎቹ ተማሪዎቹን ለመጥራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አሳውቋል።

ትምህርት ሚኒስቴር " ለ2016 ትምህርት በአሁን ሰዓት ተማሪዎችን ጥሩ እያለ ነው " የሚልው ፎረሙ ነገር ግን ለፀጥታው ኃላፊነት የሚወስድ አካል ከሌለ ይህን ማድረግ እንደሚያስቸግር አስገንዝቧል።

የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዜዳንት ዶ/ር ታፈረ መላኩ፤ ዘንድሮ በአካባቢው የቀጠለው አለመረጋጋት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ እንደማያስችል ከተስማሙት የፎረሙ አባላት እንደሆኑ አሳውቀዋል።

ዶ/ር ታፈረ " ያለው ሁኔታ ካልተሻሻለ
በስተቀር አሁን ባለው ሀገራዊ ሁኔታ ላይ ግቢ ውስጥ ተማሪ ማስገባት በእጅጉ ፈታኝ ነው የሚሆነው ለልጆችም ደህንነት በጣም አስጊ ነው " ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የምግብ አቅርቦት አስቸጋሪ እንደሆነ ገልጸዋል። ምግብ የሚቀርበው ከወረዳ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ጭምር ስለሆነ መንገዶች ደህንነታቸው ካልተጠበቀ በስተቀር አቅርቦቱን ማሟላት ከባድ እንደሆነ አክለዋል።

ቃላቸውን ለሬድዮ ጣቢያው የሰጡ ወላጆች የአካባቢው የደህንነት እና ሰላም ሁኔታ በአስተማማኝነት እስካልተረጋገጠ እና ለልጆቻቸው ደህንነት ዋስትና እስካላገኙ ድረስ ልጆቻቸውን ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደማይልኩ ገልጸዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ በአማራ ክልል ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ስለሚማሩ ተማሪዎች ተከታታይ መልዕክቶችን መላኩ ይታወቃል።

ተማሪዎች ያለ ትምህርት ረጅም ወራት መቀመጣቸውን በመግለፅ መንግስት ከተቻለ ወደ ተቋማቸው እንዲያስገባቸው ካልሆነም ወደ ሌሎች ተቋማት አስገብቶ እንዲያስተምራቸው ሲጠይቁ ከርመዋል።

በእነሱ ተመሳሳይ እድሜና የትምህርት ደረጃ ያሉና በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ወደ ተቋማቸው ገብተው ትምህርት መማር ከጀመሩ ሳምንታት ማለፉን በመግለፅም አስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግላቸው በተደጋጋሚ እየጠየቁ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በትግራይ ምን ያህል ተማሪ አለፈ ?

በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ሆኗል።

በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች በድረ-ገጽ eaes.et ላይ በመግባት የፈተና አዳራሽ መግቢያ መታወቂያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስማቸውን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

በተጨማሪም በቴሌግራም ቦት @eaesbot ላይ ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል።

ቅሬታ ያላቸው ተማሪዎች በተመሳሳይ ድረ-ገጽ ላይ እስከ ጥቅምት 29/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11:30 ድረስ ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ ፤ ምላሽም በተመሳሳይ መልኩ ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

በትግራይ ክልል በሚገኙ አራት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከመስከረም 29 እስከ ጥቅምት 02/2016 ዓ.ም የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከ9ሺህ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው ይታወሳል።

ምን ያህል ተማሪ 50 በመቶ እና በላይ አመጣ ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባሰራጩት ፅሁፍ የወጣውን የፈተና መስፈርት አሟልተው ብሔራዊ ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ፦
🔹73.09 በመቶ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች
🔸 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች

በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።

ዝርዝር ቁጥራዊ መረጃው በቀጣይ ይገለፃልም ብለዋል።

ዶ/ር ኪሮስ ውጤቱን ላስመዘገቡ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ ያሉ ሲሆን ይህ ውጤት እንዲመዘገብ የማይተካ ሚና ለተጫወቱት መምህራን፣ የትምህርት አመራሮች፣ ወላጆች ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።

የትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ደረጃውን የጠበቀ ፈተና በማዘጋጀት እና በመፈትን ውጤቱን በአጭር ጊዜ ለማሳወቅ ሌት ተቀን ላደረጉት ርብርብ የቢሮው ኃላፊ ምስጋና አቅርበውላቸዋል።

ተጨማሪ ቲክቫህ ትግርኛ @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ምን ያህል ተማሪ አለፈ ? በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ሆኗል። በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች በድረ-ገጽ eaes.et ላይ በመግባት የፈተና አዳራሽ መግቢያ መታወቂያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስማቸውን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በተጨማሪም…
#Tigray

657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።

በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል።

ይህንን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ ሙሴ ኪዳነ የሚባል ሲሆን የ " ቀላሚኖ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመመልከት ችሏል።

እንደ ትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ መረጃ አጠቃላይ መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች  73.09 በመቶ የሚሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች  እንዲሁም 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል።

በትግራይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኃላም በደም አፋሳሹ ጦርነት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው መቆየታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ቲክቫህ ትግርኛ @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia
ስኬታማ ምዕራፍ፤ ብሩህ ተስፋ!
****
ጥቅምት 18 ቀን 2006 ዓ.ም - በሀገራችን የባንክ ሥራ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የተከፈተበት ቀን፡፡
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት መስጠት በመጀመር እንደ ሁልጌዜው ሁሉ ፈር ቀዳጅነቱን አስመሰከረ፡፡
ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶችን በማለፍ የስኬት ታሪክ መፃፍም ተቻለ፡፡
ሲቢኢ ኑር 10 ዓመት ሞላው፡፡
በጉዟችን የገጠሙንን ተግዳሮቶች ያለፍንበትን መንገድ በመማማር፣
ከስኬቶቻችን ልምድ በማካፈል፣
አብረውን ለነበሩ ሁሉ ምስጋናን በማቅረብ፣
ለበለጠ ስኬትም ቃል በመግባት፣
10ኛ ዓመታችንን ከክቡራን ደንበኞቻችን ጋር በጋራ እንዘክራለን፡፡
ስኬታማ ምዕራፍ ነበረን፣ የወደፊቱም በብሩህ ተስፋ የተሞላ ነው፡፡

ትክክለኘውን የቴሌግራም ቻናል https://publielectoral.lat/combankethofficial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#SUNChips

መምጣቱ ላይቀር የሚያስጠብቀን የእረፍት ቀን ደርሷል! ዘና ፈታ እንበል! #መክሰስTime ደርሷል- ከ #ሰንቺፕስ 😋 ጋር #ሰኒሞመንትስ ☀️
Looking forward to snacking on the weekend with SUNChips. #SUNChips 😋 #SunnyMoments. ☀️
Facebook: https://www.facebook.com/sunchipsethiopia
Instagram: https://instagram.com/sunchipsethiopia 
#NBE #CustomsCommission #LC

የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ባንክ፣ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጥያቄ መሠረት አስመጪና ላኪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ወደ አገር ቤት እንዳያስገቡም ሆነ ወደ ውጪ እንዳይልኩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ እንደሚለው ፤ ኮሚሽኑ በወሰነው ውሳኔ አንዳንድ ላኪዎችና አስመጪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያየ ጊዜ ምርቶችን መላክና ማስመጣት የሚፈቅደውን ሕግ፣ የአገርን ጥቅም በሚያሳጣና በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀሙበት በመሆኑ አንድ LC (LETTER OF CREDIT) ለአንድ ምርት ብቻ እንዲሆን ሊያደረግ ነው።

ትዕዛዙ ተግባራዊ የሚሆነው ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. እነድሆነ ተገልጿል።

አስመጪና ላኪዎች ትዕዛዙ በአሁኑ ሰዓት በክፍልፋይ (Partial Shipment) መሠረት ስምምነት ያደረጉ ድርጅቶችን ያካተተ መሆን የለበትም ሲሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

እኚሁ አስመጪና ላኪዎች አንዳንድ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያሰሩትን ስምምነት መቀየር እንደማይችሉና ትዕዛዙ ተግባራዊ መሆን ያለበት አዲስ ስምምነት ለሚያደርጉ ድርጅቶች መሆን እንደሚገባ ለብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በባንኮች በኩል የሚከፈተው LC (LETTER OF CREDIT) በገዥና በአቅራቢ ድርጅት መካከል የሚደረግ ጠንካራ ስምምነት መሆኑ ይታወቃል፡፡

የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) ማለት ገዥውና አቅራቢ በስምምነታቸው መሠረት በአንድ ጊዜ ሁሉንም ምርት በተለያየ ምክንያት መላክ ስለማይቻል ከሥር ከሥር እየተመረተ ለመላክ የሚስማሙበት አካሄድ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በኮንቴይነር እጥረት፣ ገዥው በቂ ማከማቻ ቦታ ከሌለው፣ የክፍልፋይ ስምምነት ይደረጋል፡፡ ይህ ስምምነት ጥሬ ዕቃዎቹ በወቅቱ እንዲገቡ ያደርጋል እንጂ አገርን የሚጎዳ አይደለም ሲሉ አስመጪ ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡

የአስመጪዎች ትልቅ ሥጋት የሆነው የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) መሠረት የታዘዙት ዕቃዎች ጂቡቲ የሚደርሱት የጉምሩክ ኮሚሽን ውሳኔ ከሚጀመርበት ቀን በኋላ ነው፡፡

በአዲሱ ትዕዛዝ ቀድሞ ስምምነት የነበራቸውን በማካተቱ ምርቶቹ መጥተው ወደብ ላይ መዘግየት፣ የባንክ  ብድር መክፈል አለመቻል፣ የቀረጥ ክፍያ አለመስተናገድና ለተጨማሪ " ዴሜሬጅ " ክፍያ እንደሚያወጡ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ዕገዳው ቀድሞ ስምምነት የተደረገባቸውን ሳያካትት ከኅዳር 10 ቀን በኋላ ለሚደረግ አዲስ ስምምነት ፈቃድ መከልከል አለበት ብለዋል፡፡

በክፍልፋይ ጊዜ በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያዩ ወቅቶች ምርቶችን ማስገባት መፈቀዱ፣ አስመጪዎቹ ባንክ ከፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ በላይ የሚያወጡ ምርቶችን የማስገባት ዕድሎችን እንደመፍጠሩ፣ በዚህም ባንኩ ከፈቀደላቸው ውጪ ጥቅም ላይ ያዋሉት ገንዘብ ከጥቁር ገበያ የተገኘ ነው የሚለውን ጥርጣሬ ከማሳደጉ ባለፈ፣ አሠራሩም ሕገወጥ ገበያን አበረታቷል በሚል የተላለፈ ትዕዛዝ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ  ማብራሪያ የሰጡት የዘርፉ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነ የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) አገርን ችግር ውስጥ የሚከት አይደለም ብለዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን ሕገወጥ ተግባርን ለመከላከል የሚፈልግ ከሆነ በቀላሉ ሕገወጦቹን በመለየት በሕግ መጠየቅ እንጂ በትክክለኛ አካሄድ የሚሠሩትንም በአንድ ላይ በማገድ መፍትሔ አይመጣም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የዚህ መረጃ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
መምህራን ምን አሉ ? • " የመምህራን ደመወዝ ይቆረጣል የሚሰጠው ምክንያት ደግሞ አሳማኝ አይደለም " • " የፌዴራል መንግሥት የዓመቱን በጀት ወደ ክልሎች ቢልክም፣ ክልሎች ለወረዳዎች አይልኩም " • " አንዳንዴ ደመወዝ ለበርካታ ወራት ሳይከፈላቸው ይጠብቃሉ፤ ግማሽ ደመወዝ ብቻ የሚከፈልበት ጊዜም አለ " የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በጅግጅጋ ከተማ ባካሄደው 36ኛው ጉባዔ ላይ፣ በክልሎች የበርካታ…
#የኢትዮጵያ_መምህራን_ማህበር #ቲክቫህኢትዮጵያ

የመማሪያ መፅሀፍት ጉዳይ

" ቅሬታችንን መንግሥት ይወቅልን " ያሉ #ተማሪዎች ፣ የመማሪያ መፅሀፍት ሶፍት ኮፒ እንኳን ማግኘት ቢቻል ማንበቢያ ስልክ ያስፈልጋል ፣ ስማርት ስልክ ደግሞ የቤተሰቦቻችን ገቢ  ዝቅተኛ በመሆኑ ሊገዛልን አይችልም ሲሉ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አክለውም፣ በዚህ ሁኔታ እንዴት መማርና ውጤታማ መሆን እንችላለን ? ነው ወይስ ትምህርት መማር ያለባቸው የባለሃብት ልጆች ብቻ ናቸው ? ሲሉ ጠይቀዋል።

36ኛውን የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ምክር ቤት ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን በጅግጅጋ በነበረ ውይይት የተማሪዎችን የመጽሐፍ እና የሶፍት ኮፒ አለምግኘት ጨምሮ ሌሎች መምህራን የሚያነሷቸውን ቅሬታዎች በተመለከ ምን የመፍትሄ ሀሳብ እንደተቀመጠ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ጥያቄ አቅርቧል።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ " አንድ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት (ሳውላ ጎፋ አካባቢ) ፕሪንተርም፣ ፎቶ ኮፒም የለውም " ብለዋል።

" አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የማባዣ ቁሳቁስ እንኳን የሌላቸው አሉና ሶፍት ኮፒ ብቻ ልኮ ተማሪዎች መፅሐፍ አግኝተዋል ማለት አይቻልም " ያሉት የማኅበሩ ፕሬዝዳንት፣ " ሶፍት ኮፒ ደግሞ በሞባይል ነው የሚታየው፣ ሁሉም ተማሪ ደግሞ ለዛ የሚመጥን ስማርት ስልክ ላይኖረው ይችላል፣ አስቸኳይ መፍትሄ መስጠት ያስፈልጋል " ነው ያሉት።

" ተማሪዎች ሀርድ በእጃቸው ይዘው የሚያነቡት ሀርድ ኮፒ ያስፈልጋቸዋል " ያሉት ዮሐንስ (ዶ/ር)፣ ይህንን በተመለከተም በጅግጅጋ በነበረው የማኅበሩ ምክር ቤት ክልሎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መፅሐፍ እጥረት እንዳለ፣ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መፅሐፍ እንዳልደረሰ ተነግሯል ብለዋል።

የተነሱ ቅሬታዎችን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) " ወደ 40 ኮንቴነር ጂቡቲ ደርሷል፣ እንደውም ወደ መሀል አገርም እየተጓጓዘ ነው፣ በቅርቡ ወደ ትምህርት ቤቶች ይደርሳል " ማለታቸውን ይሐንስ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

የመምህራን ዝውውር ጉዳይ

ከዝውውር ጋር በተያያዘ መምህራን በተደጋጋሚ ቅሬታ ሲያነሱ የሚደመጥ ሲሆን፣ ችግሩን ለመቅረፍ ምን ውይይት እንደተደረገ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጥያቄ የቀረበላቸው የማኅበሩ ፕሬዚዳንት፣  መምህራን የሚዘዋውሩበት የዝውውር ስርዓት እንዳለ ገልጸው ተከታዩን አክለዋል።

" ዝውውር ለመምህራን እንደ #ትልቅ_የመብት_ጉዳይ የሚታይ ነው። " የተለያዩ የአፈፃፀም ጉድለቶች እንዳሉ ምክር ቤቱ በጅግጅጋ በነበረው ስብሰባ ገምግሟል። በየደረጃው ተስተካክሎ በመመሪያው መሠረት እንዲፈጸም ሰፊ ውይይት አድርገንበታል። "

ተፈናቃዮችን ያስጠለሉ ትምህርት ቤቶች ጉዳይ

" የተፈናቀሉ ዜጎች መጠለያ የሆኑ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ አይተናል። በዛ አካባቢ በተለይ ትምህርት ለመስጠት አስቸጋሪ ይሆናል " ሲሉ ዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር) አስረድተዋል።

ኢሰመኮ ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም ይፋ ባድረገው ሪፓርት በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቃዎች መካከል የተኩስ ልውውጥ በሚያገረሽበት አማራ ክልል ውስጥ ትምህርት ቤቶች የተፈናቃይ መጠለያ ካምፖች እንደሆኑ መረዳቱን ማስገንዘቡ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር በበኩሉ የተፈናቃይ መጠለያ በሆኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ መምህራን ማስተማር እንዳልቻሉ ፣ የትምህርት ተቋማትም ውድመት እንደሚደርስባቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የመምህራን ደመወዝ አለመከፈልና መቆረጥ ጉዳይ

መምህራን የሰሩበት ደመወዛቸው #ስለማይከፈላቸው እና የሚከፈላቸውም ስለሚቆረጥባቸው በተለይም ደቡብ ክልል ላይ የሥራ ማቆም አድማ እስከማድረግ የደረሱበትን ሁኔታ በተመለከተ ምን እንደታሰበም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመምህራን ማኅበሩ ፕሬዝዳንት ጥያቄ አቅርቧል።

ፕሬዝዳንቱ ለቲክቫህ በሰጡት ማብራሪያ ፤ " ቀደም ብሎ እዚያ አካባቢ ባጋጠመው ሁኔታ እኛም ለክልሉ መንግሥት ደብዳቤ ፅፈን ነበር፣ በዚያ መነሻ በወቅቱ ተከፍሎ ነበር። አሁን ኋላ ላይ ደግሞ ተመልሶ እንዳገረሸ ሰምተናል" ብለዋል።

" ምክንያቶቹ የተለያዩ ይሆናሉ። መምህራን የሰሩበትን በጊዜው ማግኘት አለባቸው " ያሉ ሲሆን " ደመወዙ የመምህራኑ ብቻ ሳይሆን የቤተሰቦቻቸውም፣ የልጆቻቸውም ጭምር ስለሆነ በየደረጃው ያለው መዋቅር ይህን ተከትሎ መፈጸም እንዳለበት ሁሌም እናሳስባለን " ሲሉ ገልጸዋል።

የደመወዝ አለመከፈልን በተመለከተ ለማኅበሩ ምን ያህል መምህራን ቅሬታ እንዳቀረቡ፣ ለስንቶቹ መፍትሄ እንደተሰጠ ማብራሪያ እንዲሰጡ ሲጠየቁም፣ በአብዛኛው ቅሬታ ያለው በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል፣ በጋምቤላ ክልል በተወሰነ መልኩ እንዲሁም በአፋርና በሌሎች አካባቢዎች እንድሆነ፣ ቅሬታው ከተለያዩ ወረዳዎች ስለሚመጣ ቁጥሩን ለመግለጽ እንደሚያስቸግር አስረድተዋል።

የማኅበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ በንቲ ፤ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በገለጹት መሠረት ፣ የ36ኛው የኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ምክር ቤት ምክንያት በማድረግ ሰሞኑን በጅግጅጋ በነበረው ፕሮግራም ውይይት ተደርጎባቸው የመፍትሄ ሀሳብ የተቀመጠላቸው ዋና ዋና አጀንዳዎች፡-
- የመምህራን ዝውውር
- የመምህራን ጥቅማጥቅም
- የመምህራን የትምህርት ዕድል
- የመኖሪያ ቤት አቅርቦት
- መልካም አስተዳደር
- የትምህርት ጥራት
- የተማሪዎችን የውጤት ቀውስ
-  የጸጥታ ችግር በትምህርት ላይ ያስከተለው ያለውን አሉታዊ ተጽዕኖ በተመለከተ ነው ብለዋል።

መረጃው በአዲስ አበባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተጠናቅሮ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#ትግራይ

" በተለያዩ ሚድያዎች ከሚሰማው በሬ ወለደ ወሬ በስተቀር ከኤርትራ በሚዋሰኑ የድንበር አከባቢዎች ከበፊቱ የተለየ ነገር የለም " - ኮማነደር ሙሉብርሃን

የድንበር የፀጥታ ጉዳይ የሚመለከት ሪፓርታጅ ! 

ኢትዮጵያ ከባህር በር ተጠቃሚነት ጋር አያይዛ ያነሳቸው ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ እንደነበር ይታወሳል።

ምንም እንኳን ስም ባትጠቅስም ጎረቤት አገር ኤርትራ በዜና ሚኒስተርዋ በኩል መግለጫ እስከማውጣትም ደርሳ ነበር።

ይህንን ተከትሎ ሁለቱ አገራት በሚያገናኘው ሰፊ የድንበር አከባቢ ፦
- ውጥረት እንዳለ ፣
- የሃገር መከላከያ ሰራዊት ከትግራይ ኃይል ጋር በጥምር ወደ ደንበር መጠጋታቸው ፣
- ከባባድ የጦር መሳሪያዎች እየተጓጓዙ እንደሚገኙ የሚያትቱ ምንጫቸው #ያልተረጋገረጠ የአገር ውስጥና የውጭ ሚድያ ዘገባዎች እንዲሁም የማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፅ ፅሁፎች ተደምጠዋል ተነበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል መሬት ላይ ያለውን ሁኔታ በአካል ለመመልከት ኢትዮጵያን በትግራይ በኩል ከሚያዋስኑ የምስራቃዊና የማእከላዊ ዞን አከባቢዎች ተጉዞ የሚከተለውን ሪፓርታጅ ልኳል።

የቲክቫህ ሪፖርተር እሁድ ጥቅምት 18/2016 ዓ.ም ከመቐለ ወደ ዓዲግራትና ፋፂ ተጓዘ ።

ዓዲግራት የምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ስትሆን ፣ ፋፂ የጉሎመኸዳ ወረዳ ዋና ከተማ ሆና ከኤርትራ ደንበር በ20 ኪሎ ሜትር ርቀት የምትገኝ ዛላኣምበሳ ከተማ ጨምሮ ከ5 በላይ ቀበሌዎችዋ እስከ አሁን በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ሰር የሚገኙባት ናት።

በተመሳሳይ በርካታ ቀበሌዎችዋ በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኙባት የኢሮብ ወረዳ የኮሙኒኬሽን ባለሞያ ልኡል አፅብሃ ፣ የዓዲግራት ከተማ ነዋሪ የሆኑት ነጋሲ መንገሻና አርአያ ሃይሉ ፣ የፋፂ ከተማ ነዋሪዎች የዕብዮ አለም ፣ ጠዓመ እና ልዋም የተባሉ የቲክቫህ ሪፓርተር አነጋግሮ የሰጡት መልስ በአከባቢያቸው ከበፊቱ የተለየ ነገር እንደሌለ በመግለፅ አሁንም በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ መንግስት በኤርትራ ሰራዊት ቁጥጥር ስር የሚገኙ አከባቢዎች እንዲያስለቅቅ ተማፅነዋል።

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ሪፓርተር የምስራቃዊ ዞን ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ሙሉብርሃን አነጋግሮም በተለያዩ ሚድያዎች ከሚሰሙት በሬ ወለደ ወሬ በስተቀር በዞኑ ከኤርትራ በሚዋሰኑ የድንበር አከባቢዎች ከበፊቱ የተለየ ነገር እንደሌለ አረጋግጠውለታል።

የቲክቫህ ሪፓርተር የማእከላይ ዞን ከተሞች ሆነው ለኤርትራ ድንበር የቀረቡት እንትጮ ፣ ድብድቦ ዓድዋና አክሱም ድረስ ተጉዟል።

ያለውን ሁኔታ በአይኑ ከመታዘብ በተጨማሪ የከተማዎቹ ነዋሪዎች አነጋግሮ በአከባቢያቸው ከበፊቱ የተለየ ነገር እንዳለዩ ነግረውታል።

ኣክሱም ድረስ በመጓዝ ያነጋገራቸው የማእከላይ ዞን ፓሊስ አዛዥ በለጠ ገ/የሱስም ከነዋሪዎቹ የተለየ አስተያየት እንደሌላቸው በመግለፅ ፣ ይሁን እንጂ ከኤርትራ ድንበር በጥቂት ኪሎ ሜትሮች ርቀት ከሚገኙት የራማና ከተማና አሕሳኣ ወረዳ የኤርትራ ሰራዊት አባላት ሾልከው በመግባት ሰዎች አፍነው የመውሰድ ሁኔታ እንዳለ ፣ የዚሁ ዋናው ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ የትግራይ ድንበር አከባቢ በቂ የሆነ የአገር መከላከያ ሰራዊት ባለመኖሩ መሆኑ ለቲክቫህ ሪፓርተር ገልጸዋል።

ያንብቡ ፦ https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-11-04-2

@tikvahethiopia
ከ60 በላይ የጤና ባለሙያዎች ፤ " ጤና ሚኒስቴር በሕግ የተወሰነልንን ልዩ አበል አልከፈለንም " አሉ።

የጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ እንደገለፁት፤ የኮቪድ - 19 ወረርሽኝ መጋቢት 8 ቀን 2012 ዓ / ም መከሰቱን ተከትሎ የጤና ማኒስቴር ባወጣው ጥሪ መሠረት የኢፌደሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ግንቦት 18 ቀን 2012 ዓ / ም ባወጣው መመሪያ የሕክምና አገልግሎት ለሚሰጡ ለመላው ሀኪሞች በቀን 1,050 ብር፣ ለየመጀመሪያ ድግሪ ባለሙያዎች 900 ብር ልዩ አበል እንዲከፈላቸው ተወስኖ ነበር።

በዚህ መሠረት ጤና ሚኒስቴር በኮቪድ - 19 ወቅት የአገልግሎት ሥራ ለሰሩት የተወሰኑ ወራት አበል እንደከፈላቸው ፣ ይሁን እንጂ ከዚያ በኃላ ክፍያውን እንዳቆመ ፣ ይህን ተከትሎም ቀሪው ልዩ አበል እንዲከፈላቸው በቃልና በደብዳቤ ቢጠይቁም ምላሽ እንዳላገኙ ፣ በመጨረሻም ክስ እንደመሰረቱ፣ በክሱ  መሠረትም ገንዘቡ እንዲከፈላቸው ቢወሰንም ጤና ሚኒስቴር ግን ከውሳኔው በኋላም ለመክፈል ፈቃደኛ እንዳሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አስረድተዋል።

በአጠቃላይ ቅሬታ አቅራቢዎቹ  በቁጥር 71 ሲሆኑ አንድ ሥማቸው እንዲጠቀስ ያልፈቀዱ ባለጉዳይ እና የጤና ባለሙያዎቹ ተወካይ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፦ " ጤና ሚኒስቴር ከተሰጠው ኃላፊነት አንፃር የጤና ሥርዓቱን ማዘመን፣ የጤና ባለሙያውን መብቶች፣ ጥቅሞች ማክበር፣ ለጤና ባለሙያዎች ምቹ ከባቢና የሥራ ዋስትና መፍጠር ነበር። ነገር ግን  መንግሥት ነኝ በማለት በማን አለብኝነት  በጤና ባለሙያዎች ላይ ከማሾፉም በላይ ጤና ባለሙያዎች ከአቅም በላይ ሲሆንባቸው መብታቸውን በፍትህ አካል ጠይቀው ተወስኖላቸው 'እንደውሳኔው ክፈል' ተብሎ ሲታዘዝ  'ያለውሳኔ ነው' በማለት ነገሮችን ማጣመም ተገቢና ከአንድ ሥሙ ትልቅ ከሆነ ተቋም የማይጠበቅ ነው " ሲሉ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ላይ ወቀሳ አቅርበዋል።

ጤና ባለሙያዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩት ማስረጃ ጤና ሚኒስቴር ፦
▪️ከ1ኛ - 14ኛ ተራ ቁጥር ላሉት የጤና ባለሙያዎች ከኅዳር 1 ቀን  2013 ዓ.ም እስከ ኅዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ለእያንዳንዳቸው 400 ሺሕ 050 ብር፣

▪️15ኛ ተራ ቁጥር ላይ ላሉ የጤና ባለሙያ ከሚያዚያ 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ኅዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ 242 ሺሕ 550 ብር፣

▪️ከ16ኛ - 66ኛ ተራ ቁጥር ላሉ የጤና ባለሙያዎች ደግሞ ከመስከረም 1 ቀን 2013 ዓ.ም ኅዳር 21 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ለእያንዳንዳቸው 396, 900 ብር በአጠቃላይ ከ1ኛ እስክ 66ኛ የጤና ባለሙያዎች የተጠቀሰው የኮቪድ - 19 ልዩ  አበል እንዲከፈላቸው አቤቱታ ማቅረባቸውን ያትታል።

ይህ የገንዘብ መጠን የጤና ባለሙያዎቹ ክስ ሲመሰርቱ ያካተቱት ሲሆን፣ በውሳኔ ግልባጩ ጤና ሚኒስቴር ለከሳሾች የልዩ አበሉን ከኀዳር 1 ቀን 2013 እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም እንዲከፈል ተብሎ ቢወሰንም የተጠቀሰ የልዩ አበል መጠን ግን የለም።

ቲክቫህ - ኢትዮጵያ የተመለከተው #የውሳኔ_ግልባጭ ፣ ጤና ሚኒስቴር (መልስ ሰጭ ተቋም) ለይግባኝ ባዮች ያቀረቧቸው ሁሉንም የመቃወሚያ ሀሳቦች ውድቅ አድርጎ ከኅዳር 1 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባሉት ወራት ውስጥ (የሚከፈልባቸው ወራት ከፋፍሎ አስቀምጦ) ፣ ጤና ሚኒስቴር ለ66ቱ የጤና ባለሙያዎች የጠየቁትን የኮቪድ - 19 ልዩ አበል እንዲከፍል ውሳኔ ማሳለፉን ያስረዳል።

የውሳኔ ግልባጩ " 15ኛ ይግባኝ ባይ አቶ ክንዳለም መኳንንት በኮቪድ - 19 ሥራ ላይ ያገለገሉበት ክፍያ አቤቱታቸውን ካቀረቡ በኋላ የተከፈላቸው መሆኑን የይግባኝ ባዮች ተወካይ በችሎት በማስረዳታቸው 15ኛ ይግባኝ ባይ ከክርክሩ ውጭ ሆኗል " ይላል።

ቲክቫህ የጤና ባለሙያዎቹ በሕግ የተወሰነላቸውን ልዩ አበል ያልከፈለበትን ምክንያት እንዲያስረዳ ጤና ሚኒስቴርን ጠይቋል።

በተቋሙ ኃላፊነት ተሰጥቷቸው የሚያገለግሉት አቶ ዮርዳኖስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት የፅሑፍ ምላሽ ፣ " ክልሎች ናቸው ጤና ባለሙያዎችን የሚቀጥሩት ስለሆነም የቀጠራቸው ክልል ጤና ቢሮ ማናገሩ ጥሩ ነው " ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስራ የሰሩበት አበል ሊከፍላቸው የሚገባው " የቀጠራቸው ክልል ነው " ስለተባለ የቀጠራቸው ተቋም ማን እንደሆነ ቅሬታ አቅራቢዎቹን ጠይቋል።

ይሁን እንጂ አንድ ቅሬታ አቅራቢ ለቲክቫህ በሰጡት ምላሽ ፣ "ጤና ባለሙያዎች የከሰስነው የቀጠረንን ተቋም ነው። ክልሎች ቀጥረውን እንዴት ጤና ሚኒስቴርን እንከሳለን ? ይህን እኮ እነሱም ያውቃሉ ውልም አለን። አሁን ከእነሱ ተቋም የለቀቅን ብዙዎች ነን እንጂ ከለቀቅን በኋላ ያለውን ደግሞ አልከሰስንም " ብለዋል።

እኚሁ ታማኝ ምንጭ በተጨማሪ ልዩ አበሉ ይከፈለን የሚሉች የጤና ባለሙያዎች የጤና ሚኒስቴር ሠራተኞች እንደነበሩ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ልከዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይበልጥ ይህንን ጉዳይ ለማጣራት የተመለከተው የውሳኔ ግልባጭ ፤ " መልስ ሰጭ መ/ቤት ይግባኝ ባዮች የልዩ አበል ክፍያ መጠየቅ ያለባቸው ተመድበው እየሰሩ ያሉበትን ተቋም ነው እንጂ ጤና ሚኒስቴርን አይደለም በማለት ያቀረበው መከራከሪያ ተቀባይነት የለውም " ሲል ውድቅ እንዳደረገው በግልጽ ያሳያል።

በመሆኑም አቶ ዮርዳኖስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ለምን " ክልሎች ናቸው ጤና ባለሙያዎችን የሚቀጥሩት ስለሆነም የቀጠራቸው ክልል ጤና ቢሮ ማናገሩ ጥሩ ነው " የሚል ምላሽ እንደሰጡ በድጋሚ ለመጠየቅ በፅሑፍና መልዕክትና በስልክ ጥሪ ቢሞክርም ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አልሆኑም።

በመጨረሻም ለጉዳዩ ምን አይነት ምላሽ እንዳላቸው ለመጠየቅ ለጤና  ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ስልክ ቢደወልም ባለማንሳታቸው ሀሳባቸውን ማካተት አልተቻለም።

የክሱን ሂደት በተመለከተም ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከሁነኛ አካላት ባደረገው ማጣራት የጤና ባለሙያዎቹ ልዩ አበሉ እንዲከፈላቸው መወሰኑን፣ አፈጻጸሙ ግን ገና እንዳልተቋጨ ለማወቅ ችሏል።

ይህ መረጃ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ኢዮብ ትኩዬ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia