TIKVAH-ETHIOPIA
በትግራይ ምን ያህል ተማሪ አለፈ ? በትግራይ ክልል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ከምሽቱ 3 ሰዓት ጀምሮ ይፋ ሆኗል። በክልሉ የተሰጠውን የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች በድረ-ገጽ eaes.et ላይ በመግባት የፈተና አዳራሽ መግቢያ መታወቂያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስማቸውን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። በተጨማሪም…
#Tigray

657 ከፍተኛው ውጤት ሆኖ ተመዝግቧል።

በትግራይ ክልል በተሰጠው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል 657 ከፍተኛው ሆኖ መመዝገቡ ታውቋል።

ይህንን ከፍተኛ ውጤት ያመጣው ተማሪ ሙሴ ኪዳነ የሚባል ሲሆን የ " ቀላሚኖ " የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለመመልከት ችሏል።

እንደ ትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዑሽ መረጃ አጠቃላይ መስፈርቱን አሟልተው ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች  73.09 በመቶ የሚሆኑ የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች  እንዲሁም 51.38 በመቶ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በአጠቃላይ 66.96 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ ውጤት በማምጣት የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ አግኝተዋል።

በትግራይ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በኃላም በደም አፋሳሹ ጦርነት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው መቆየታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

ቲክቫህ ትግርኛ @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia