TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#CustomsCommission

" የጀመርነውን እርምጃ አጠናክረን እንቀጥላለን " - የጉምሩክ ኮሚሽን

የጉምሩክ ኮሚሽን ፥ የግል መገልገያ እቃዎችን በቦሌ አለም አቀፍ ኤርፖርት ለማስገባት ለመንገደኞች የተፈቀደውን መመሪያ ተገን አድርገው ከመመሪያው ውጭ በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተመላላሽ መንገደኞች በመንግስት ገቢ እና በንግድ ስርዓቱ ላይ ጫና እያደረሱ በመሆኑ የተጀመረው እርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

ኮሚሽነር ደበሌ ፥ የዓለም አቀፍ መንገደኞች ከውጭ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ይዘዋቸው ስለሚመጡ እና ከቀረጥ ነጻ ስለተፈቀዱ ብሎም ስላልተፈቀዱ የግል መገልገያ እቃዎችን ለመወሰን ከዚህ በፊት መመሪያ ቁጥር 51/2010 ጸድቆ ስራ ላይ መዋሉን ጠቅሰዋል፡፡

ኮሚሽኑ ባደረገው ጥናት መሰረት ከመመሪያው ዓላማ ውጭ አንዳንድ ተመላላሽ መንገደኞች በህገወጥ ንግድ ላይ ተሰማርተው በመገኘታቸው መንግስት በዘርፉ የሚያገኘውን ገቢ እንዲያጣ እና በንግድ ስርዓቱም ላይ ፍትሀዊ ውድድር እንዳይኖር እያደረጉ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

እነዚህ በህገወጥ ንግድ ላይ የተሰማሩ ተመላላሽ መንገደኞች የሚያደርጉት የገንዝብ ዝውውር በህጋዊ የፋይናንስ ተቋማት የሚከወን ባለመሆኑም ህገወጥ የገንዝብ ዝውውር እንዲስፋፋ፣ የኑሮ ውድነት እንዲባባስና የንግድ ስርዓቱ እንዲታወክ እያደረጉ መሆኑን ገልፀዋል።

መመሪያውን ተላልፈው የተገኙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ እና ወደ ህጋዊ የንግድ መረብ እንዲገቡ ኮሚሽኑ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርብም ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ አለመቻላቸውን ኮሚሽነር ደበሌ ገልጸው በእነዚህ አካላት ላይ የሚወሰደው እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እና ከሌሎች የጸጥታ አካላትም ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

@tikvahethiopia
#NBE #CustomsCommission #LC

የኢትዮጵያ ብሔራዊ  ባንክ፣ በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ጥያቄ መሠረት አስመጪና ላኪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ ከአንድ ጊዜ በላይ ምርት ወደ አገር ቤት እንዳያስገቡም ሆነ ወደ ውጪ እንዳይልኩ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ብሔራዊ ባንክ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም. ለሁሉም ባንኮች የጻፈው ደብዳቤ እንደሚለው ፤ ኮሚሽኑ በወሰነው ውሳኔ አንዳንድ ላኪዎችና አስመጪዎች በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያየ ጊዜ ምርቶችን መላክና ማስመጣት የሚፈቅደውን ሕግ፣ የአገርን ጥቅም በሚያሳጣና በሕገወጥ መንገድ እየተጠቀሙበት በመሆኑ አንድ LC (LETTER OF CREDIT) ለአንድ ምርት ብቻ እንዲሆን ሊያደረግ ነው።

ትዕዛዙ ተግባራዊ የሚሆነው ኅዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም. እነድሆነ ተገልጿል።

አስመጪና ላኪዎች ትዕዛዙ በአሁኑ ሰዓት በክፍልፋይ (Partial Shipment) መሠረት ስምምነት ያደረጉ ድርጅቶችን ያካተተ መሆን የለበትም ሲሉ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል ተናግረዋል።

እኚሁ አስመጪና ላኪዎች አንዳንድ ባንኮች ከደንበኞቻቸው ጋር ያሰሩትን ስምምነት መቀየር እንደማይችሉና ትዕዛዙ ተግባራዊ መሆን ያለበት አዲስ ስምምነት ለሚያደርጉ ድርጅቶች መሆን እንደሚገባ ለብሔራዊ ባንክ ደብዳቤ እየላኩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በባንኮች በኩል የሚከፈተው LC (LETTER OF CREDIT) በገዥና በአቅራቢ ድርጅት መካከል የሚደረግ ጠንካራ ስምምነት መሆኑ ይታወቃል፡፡

የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) ማለት ገዥውና አቅራቢ በስምምነታቸው መሠረት በአንድ ጊዜ ሁሉንም ምርት በተለያየ ምክንያት መላክ ስለማይቻል ከሥር ከሥር እየተመረተ ለመላክ የሚስማሙበት አካሄድ ነው፡፡

አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በኮንቴይነር እጥረት፣ ገዥው በቂ ማከማቻ ቦታ ከሌለው፣ የክፍልፋይ ስምምነት ይደረጋል፡፡ ይህ ስምምነት ጥሬ ዕቃዎቹ በወቅቱ እንዲገቡ ያደርጋል እንጂ አገርን የሚጎዳ አይደለም ሲሉ አስመጪ ድርጅቶች ተናግረዋል፡፡

የአስመጪዎች ትልቅ ሥጋት የሆነው የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) መሠረት የታዘዙት ዕቃዎች ጂቡቲ የሚደርሱት የጉምሩክ ኮሚሽን ውሳኔ ከሚጀመርበት ቀን በኋላ ነው፡፡

በአዲሱ ትዕዛዝ ቀድሞ ስምምነት የነበራቸውን በማካተቱ ምርቶቹ መጥተው ወደብ ላይ መዘግየት፣ የባንክ  ብድር መክፈል አለመቻል፣ የቀረጥ ክፍያ አለመስተናገድና ለተጨማሪ " ዴሜሬጅ " ክፍያ እንደሚያወጡ ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም ዕገዳው ቀድሞ ስምምነት የተደረገባቸውን ሳያካትት ከኅዳር 10 ቀን በኋላ ለሚደረግ አዲስ ስምምነት ፈቃድ መከልከል አለበት ብለዋል፡፡

በክፍልፋይ ጊዜ በአንድ የባንክ ፈቃድ በተለያዩ ወቅቶች ምርቶችን ማስገባት መፈቀዱ፣ አስመጪዎቹ ባንክ ከፈቀደላቸው የውጭ ምንዛሪ በላይ የሚያወጡ ምርቶችን የማስገባት ዕድሎችን እንደመፍጠሩ፣ በዚህም ባንኩ ከፈቀደላቸው ውጪ ጥቅም ላይ ያዋሉት ገንዘብ ከጥቁር ገበያ የተገኘ ነው የሚለውን ጥርጣሬ ከማሳደጉ ባለፈ፣ አሠራሩም ሕገወጥ ገበያን አበረታቷል በሚል የተላለፈ ትዕዛዝ ነው፡፡

በጉዳዩ ላይ  ማብራሪያ የሰጡት የዘርፉ ባለሙያ እንደሚሉት ከሆነ የክፍልፋይ ስምምነት (Partial Shipment) አገርን ችግር ውስጥ የሚከት አይደለም ብለዋል፡፡

ጉምሩክ ኮሚሽን ሕገወጥ ተግባርን ለመከላከል የሚፈልግ ከሆነ በቀላሉ ሕገወጦቹን በመለየት በሕግ መጠየቅ እንጂ በትክክለኛ አካሄድ የሚሠሩትንም በአንድ ላይ በማገድ መፍትሔ አይመጣም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የዚህ መረጃ ባለቤት ሪፖርተር ጋዜጣ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጉምሩክ

(አስመጪዎች)

" በኢንቮይስ ያልተከፈሉ አሉ። ብዙ እቃዎች ናቸው ያሉት። እቃዎቹ አንድ ላይ ጉምሩክ የገቡ ናቸው።

የነዛና የነዚህ ልዩነት በጣም ሰፊ ነው። ከ4 እስከ 5 ሚሊዮን በኮንቴነር ጭማሪ የሚያመጡ ናቸው።

እነዚህም አብረው የሚስተናገዱበት መንገድ መኖር አለበት።

እቃዎቹ ሰሞኑን የታሪፍ ፣ የቀረጥ ለውጥ ሁሉ ተደርጎባቸው ነበር። በአንድ አይተም እስከ 10 ዶላር ጭምር ተደርጎ ነበር ከሬት ውጭ እሱ ላይ ብዙ ቅሬታ አልነበረም ሁሉም አንድ ላይ ስለጨመረበት።

አሁን ላይ እቃው አብሮ ገብቷል። እነዚህ ኢንቮይስ ከፍለዋል። እኛ በኢንቮይስ አልከፈልንም። ተመሳሳይ እቃዎች ናቸው።

የእነሱ ይውጣ ፤ እናተ ደግሞ በአዲሱ ሬት ክፈሉ ብንባል በጣም ትልቅ ልዩነት ይኖራል። በአንድ ገበያ ላይ ተወዳድሮ ለመስራት የሚቻል አይደለም።

ጉምሩክ ይኔንም ስጋታችንን ቢይይልን።

ሁለት ቦታ ተከፍለናል ፤ በኢንቮይስ የከፈሉ አሉ በኢንቮይስ ያልከፈልን አለን። ልዩነቱ ብዙ ነው በሚሊዮኖች ነው።

አንድ ገበያ ላይ  ነው የምንሰራውና እኛንም ከገበያ እንዳያስወጣን ይሄም ይታይልን። "

#CustomsCommission

@tikvahethiopia