TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የዘንድሮው የኣሸንዳ ፣ ማርያ ዓይኒ ዋሪ በዓል እንዴት እየተከበረ ነው ?

የኣሸንዳ ፣ ማርያ ዓይኒ ዋሪ በዓል ካለፉት ዓመታት እጅግ በተሻለ ድምቀት በትግራይ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

በዓሉ በዋነኝነት ትግራይ ውስጥ እጅግ በደመቀ ሁኔታ በመከበር ላይ ነው።

ከእሁድ ነሃሴ 13/2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መከበር የጀመረው በዓሉ ፤ ነሃሴ 13 ና 14 / 2015 ዓ.ም በዓዲግራት ከተማ በይፋ የማርያ ስነ-ሰርዓት ተከብረዋል።

ነሃሴ 15/2015 ዓ.ም አመሻሽ በመቐለ የሐወልቲ ሰማእታት ቅጥር ግቢ በአሸንዳ ሴቶች የሻማ ማብራት ስነ-ሰርዓት ተከናውነዋል።

ነሃሴ 16 /2015 ዓ.ም አሸንዳ በተምቤን ዓብይ ዓዲ ተከብሯል።

በተጨማሪ ባዛው ዕለት ከሰአት በኋላ በመቐለ በተለመዶ " ባሎኒ ስቴድዮም " ተብሎ በሚጠራው ቦታ ይፋዊ የአሸንዳ ፣ ማርያ ፣ ዓይኒ ዋሪ በዓል አከባበር ተካሂዷል።

በመቐለ ሮማናት አደባባይ የበዓሉ መንፈሳዊ አመጣጥና ትርጉም የሚሳይ ፕሮግራም ተካሂዶ ነበር።

መቐለ በነበረ ይፋዊ የበዓሉ ስነስርዓት ላይ  ከኦሮሚያ ክልል የተወከሉ አባገዳዎችና ሃደ ስንቄዎች ተገኝተው የነበረ ሲሆን የኦሮምያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የ10 ሚሊዮን ብር  ድጋፍ ለትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር አድርጓል።

የ2015 ዓ.ም የአሸንዳ በዓል ምክንያት በማድረግ 23 ሰአሊዎች ያሳተፈ የስእል እግዚብሽንም በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በኤግዚብሽኑ የቀረቡ የቅብ ስእሎች አብዛኞቹ በትግራይ የተካሄደው አስከፊ ጦርነት ያስከተለው ምስቅልቅል ፣ አሸንዳና ውበት ፣ ከጦርነት በኋላ የሚካሄደው የመልሶ ግንባታና ተስፋው የሚያመላክቱ ስእሎች ያካተቱ ናቸው።

የስእል ኤግዚብሽኑ በመቐለ የሰማእታት ሃወልት ሙዚየም የቀረበ ሲሆን እስከ ነሃሴ 21/ 2015 ዓ.ም ይቆያል።

በዓሉን ምክንያት በማድረግ የአሸንዳ 2015 ዓ.ም የሞዴሎች ውድድር የተካሄደ ሲሆን ነሃሴ 18 10 ኪሎ ሜትር የሸፈነ የከተማ ታላቅ ሩጫ በመቐለ ተካሂዷል።

ዘንድሮ መቐለ ከተማ ከወትሮው በተለየ መልኩ ድምቃለች ተውባለች ዋና መንገዶችዋ በሰው ተጨናንቀዋል።

ከተማይቱ ፤ በባህላዊ አለባበስና የፀጉር አሰራርና አጋጌጥ በተዋቡ የአሸንዳ ሴቶች ተጨናንቀዋል።

በዘንድሮው በዓል ከትግራይ ውጭ የመጡ በርካታ እንግዶች ያሉ ሲሆን ከነሱ መካከል የውጭ ቱሪስቶች ይገኙባቸዋል። 

ነሃሴ 24 /2015 ዓ.ም በኣክሱም ከተማ የአሸንዳ ዓይኒዋሪ በዓል እንደሚካሄድ ከወጣው መርሃ ግብር ለመረዳት ችለናል።

መረጃውን አሰባስቦ ያደረሰን የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ነው።

ፎቶ ፦ ትግራይ ቴሌቪዥን / Mekelle Tikvah Family

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዘንድሮው የኣሸንዳ ፣ ማርያ ዓይኒ ዋሪ በዓል እንዴት እየተከበረ ነው ? የኣሸንዳ ፣ ማርያ ዓይኒ ዋሪ በዓል ካለፉት ዓመታት እጅግ በተሻለ ድምቀት በትግራይ እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል። በዓሉ በዋነኝነት ትግራይ ውስጥ እጅግ በደመቀ ሁኔታ በመከበር ላይ ነው። ከእሁድ ነሃሴ 13/2015 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መከበር የጀመረው በዓሉ ፤ ነሃሴ 13 ና 14 / 2015 ዓ.ም በዓዲግራት…
#ኣሸንዳ

የዘንድሮው የኣሸንዳ በዓል ወደ አለፍነው ጦርነት ያስገቡን ስህተቶች ላለመደግም ቃል የምንገባበት ነው ሲሉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ተናግረዋል።

" ባለፉት ሁለት ሶስት የጦርነት አመታት በትግራይ ሴቶች የደረሰው ግፍ አሰቃቂ ነው። " ያሉት አቶ ጌታቸው  " የትግራይ ሴቶች ሰላምና ስቃይ የትግራይ ህዝብ ሰላምና ስቃይ ነው። " ብለዋል።

" ከሶስት አመታት በፊት የአሸንዳ በዓል ከተጫወቱት ቆነጃጂት በጦርነት ምክንያት  አካላቸው የጎደሉ የተሰው አሉ " ያሉት ፕሬዜዳንቱ " ይህንን እንዳይደገም በሚደረገው ትግል የሴቶች ተሳትፎ ከፍተኛ ነው። " ሲሉ አስገንዝበዋል።

ሴቶች ተውበው የአሸንዳ በዓል ሲያከብሩ ኤችአይቪ ኤድስ የመሰሉ ተላላፊ በሽታዎች መዘንጋት እንደሌለባቸው አሳስበዋል።

" በዓሉ ተፋናቃይ ህዝባችን ወደ ቀድመው ቄየው የሚመለስበት ፣ ስቃይ ውስጥ የሚገኘው ህዝባችን ነፃ እንዲሚወጣ ገሃድ የሚሆንበት እንደሚሆን እንተማመናለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Amhara

ለአንድ ቀን ይቆያል የተባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በባሕር ዳር እየተካሄደ ይገኛል።

ጉባኤው በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ እየመከረ ነው ተብሏል።

የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊና የኮማንድፖስቱ አባል አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለምክር ቤቱ ንግግር አሰምተዋል።

በዚህም ንግግራቸው ፤ በክልሉ የተፈጠረው ወቅታዊ ግጭት " ድህረ ጦርነት የፈጠረው ልዩነት ነው " ብለዋል።

አቶ ደሳለኝ ችግሩን በሰላም ለመፍታት ጥረት ተደርጎ ነበር ያሉ ሲሆን " ካለፈው ጥር ወር መጨረሻ ጀምሮ እየተስተዋለ የመጣውን የክልሉን የሰላምና ጸጥታ ችግር በክልሉ አቅም ለመፍታት የታየው ዳተኝነት እና የአመራሩ የተዛነፈ እይታ ችግሩ ውሎ ሲያድር አቅም እንዲያገኝ እና ከክልሉ መንግሥት አቅም ውጭ እንዲሆን አድርጎታል " ብለዋል።

ግጭቱ ፦
- በክልሉ ውስጥ እየተስተዋለ የመጣው ዋልታረገጥ ልዩነት፣
- #የሕዝብ_ጥያቄዎች_አለመመለሳቸው_የፈጠረው_ብሶት
-  የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የፈጠረው የሥነ-ልቦና አለመረጋጋት የፈጠሩት ችግር እንደሆነ አቶ ደሳለኝ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

የሃሰት ፕሮፖጋንዳ የሚያመርቱ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት አቀጣጣይ ነበሩም ብለዋል።

ኮማንድፖስቱ ከታወጀ ማግስት ጀምሮ በክልሉ በርካታ አካባቢዎች ሰላም ታይቷል ያሉ ሲሆን አሁንም ቀሪ ሥራዎች በመኖራቸው የኦፕሬሽን ሥራዎች እየተሠሩ ነው ብለዋል።

አቶ ደሳለኝ ፤ በግጭቱ ተሳታፊ የሆኑ ኃይሎች የግጭት አማራጭን በመተው ለሰላማዊ ትግል እራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

" የሰላም አማራጮች አሁንም በሮቻቸው ዝግ አይደሉም " ያሉት አቶ ደሳለኝ " የሚፈለገው የሰላም አማራጭ ከተገፋ ግን ሕግን የማስከበር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል " ሲሉ ተደምጠዋል። #AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር አብርሃም በላይ ምን አሉ ? የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ በዛሬው እለት የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተረጋገጠ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ መልዕክት አስተለልፈዋል። በመልዕክታቸው ፤ " የአሸንዳ በዓል ለትግራይና ትግራዎት  ልዩ ትርጉም ያለው ሃይማኖታዊና ባህላዊ በአላችን ነው። " ብለዋል። " የዚህ አመት የአሸንዳ በዓል ህዝባችን ከደረሰበት ጉዳት ገና ባላገገመበት…
" በሚኒስትሩ የተላለፈው መልዕክት የአማራ ሕዝብ ከምድረ-ገፅ ፈፅሞ ሳይጠፋ የማይፈፀም የቀን ቅዥት ነው " - የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን

በትግራይ ጦርነት ከጀመረ በኃላ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን አስተዳደርን መዋቅርን በማፍረስ " የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን " በሚል የተቋቋመውና በአማራ ክልል ስር የሚገኘው አስተዳደር ከሰሞኑን የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ላወጡት መልዕክት ምላሽ የሚሰጥ መግለጫ አወጣ።

በዚሁ መግለጫው ፤ የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት አሳዛኝ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ነው ብሏል።

መክላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ የአሸንዳ በዓልን አስመልክቶ በትግርኛ ቋንቋ ያስተላለፉት መልዕክት የአማራ ክልል ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ የተላለፈ አደገኛ መልዕክት ነው ሲል ገልጿል።

" ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግስት ኃላፊነት ይዘው ሳለ ፍፁም ለአንድ ወገን ያደላ መልዕክት ማስተላለፋቸው ኃላፊነት የጎደለውና የአማራ ክልልን ወደለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ የተላለፈ መልዕክት ነው " ሲል ገልጾታል።

መልዕክቱ ፤ " የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር አማራ ክልልን ወደለየለት ብጥብጥና ግጭት እንዲያመራ ሆን ተብሎ የተረጨ መርዘኛ መልዕክት እንደሆነ እናምናለን " ያለው መግለጫው "  " ሚኒስትሩ ይህንን መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉበት ምንም ዓይነት ሕጋዊ ኃላፊነት ሳይኖራቸው እንዱን አካል ህገ-ወጥ ሌላውን ደግሞ ሕጋዊ ብሎ መፈረጅ ከፌዴራል ወርደው ለእንድ ክልል ለተወለዱበት ብሔር/ መወገን አመላካች ሆኖ አግኝተነዋል። " ብሏል።

" የአማራ ሕዝብን የእውነትና የፍትህ ጥያቄ የካደ ነው፡፡ " ሲልም አክሏል።

መግለጫው ፤ " በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የተቋቋመው መንግስታዊ መዋቅር በሰዎች በበጎፍቃድ የተቸረው ሳይሆን ለዘመናት በተከፈለው ውድ መስዋዕትነት የተገኘ መሆኑን ሚኒስትሩ የዘነጉት ይመስላል " ብሏል።

ሚኒስትሩ ፌዴራሉ መንግስት ከሰጣቸው ኃላፊነት ውጪ ተገቢ ያልሆነ መልዕክት በማስተላለፋቸው የአማራን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል ሲልም ገልጿል።

" የተላለፈው መልዕክት የአማራ ሕዝብ ከምድረ-ገፅ ፈፅሞ ሳይጠፋ የማይፈፀም የቀን ቅዥት ነው፡፡ " ብሏል።

የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ከሰሞኑን ኣሸንዳን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ በሚያከራክሩ የትግራይ ቦታዎች ነዋሪው የሚያነሳው ጥያቄ ካለው በህገ-መንግስት ብቻ የሚመለስበት ሁኔታ እንዲረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል።

" ህዝቡ በአጭር ጊዜ ወደ ቄየው ተመልሶ ህገ-መንግስታዊ መብቱ በሚያረጋግጥ መንገድ አስተዳደሩ ራሱ እንዲመሰርት ይደረጋል " ያሉት መከላከያ ሚኒስትሩ " በአከባቢዎቹ በነበረው ሁኔታ በመጠቀም ተፈጥሮ የቆየው አስተዳደር #እንዲፈርስና ከፌደራል የፀጥታ ሃይሎች ውጭ የታጠቀ ሃይል አንዳይኖር ፣ ይህ እንዲፈፀም የፌደራል የአገር መከላከያ ሰራዊት ሃላፊነት ወስዶ እንዲያስፈፅም ትእዛዝ ተሰጥቶ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ከዚህ ውጭ ከባለቤቱ በላይ ባለቤት ለመሆን የሚዳዳ ፤ ከባለ ጉዳይ በላይ ጉዳይ አለኝ የሚል ፤ ከህግና ስርአት ውጭ በጉልበት ለመንቀሳቀስ የሚሰራ አካል ካለ የፌደራል መንግስት በጀመረው መንገድ ህግና ህገ-መንግስታዊ ሰርአቱ እንዲረጋገጥ ይሰራል ሲሉ አሳስበዋል።

(ለመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ መልዕክት የተሰጠው ምላሽ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
በመቐለ ከተማ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ቦምብ ተወርውሮ የሞት አደጋው ያጋጠመው ነሃሴ 18 /2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰአት ነው።

የአይን እማኞች ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ እንደገለፁት ፤ የቦምብ አደጋው ያጋጠመው በከተማው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራው መጠጥ ቤት ነው። 

የአይን እማኞቹ አክለው እንደገለፁት ፤ በመጠጥ ቤቱ ሰዎች በብዛት እየተዘናኑ ሳለ ከቤቱ ውጭ ወደ መጠጥ ቤቱ የተወረወረው ቦምብ የአራት ስዎች ህይወት ወድያው ሲቀጠፍ ፤ የቤቱ ሰራተኞች የሚገኙባቸው በርካቶች ቆስለዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ቆየት ብሎ ከሆስፒታል ምንጭ ባገኘው መረጃ ተጨማሪ አንድ ሰው ህይወቱ በማለፉ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 5 መሆኑን ተረድቷል።

መቐለን ጭምሮ የበርካታ የትግራይ ከተሞች የፀጥታ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ፤ ቲክቫህ የመቐለ ከንቲባ አቶ ይትባረክ አምሃ ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል።

መቐለ ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች በሚገኙ መጠጥ ቤቶች መግብያ በር ' ተተኳሽና ስለታም ነገሮች ይዞ መግባት የተከለከለ ነው ' የሚሉ ፅሁፎች ማንበብ ከጦርነቱ በኋላ የተለመደ እንደሆነ የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በመቐለ ከተማ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ። ቦምብ ተወርውሮ የሞት አደጋው ያጋጠመው ነሃሴ 18 /2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰአት ነው። የአይን እማኞች ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ እንደገለፁት ፤ የቦምብ አደጋው ያጋጠመው በከተማው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራው መጠጥ ቤት ነው።  የአይን እማኞቹ አክለው እንደገለፁት ፤ በመጠጥ ቤቱ ሰዎች በብዛት…
#Mekelle

የመቐለ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ትላንት ለሊት 8 ሰዓት ላይ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " በሚባለው መጥጥ ቤት ቦንብ የተወረወረው " በቀድሞ ተሰናባች ታጋይ " በነበረ ግለሰብ መሆኑን ታውቋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ተጠርጣሪው እስካሁን አልተያዘም።

የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ኮማንደር ወልዳይ ማውጫ ፤ " ከአሸንዳ በዓል ጋር በተያያዘ በከተማዋ ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ሲደረግ ቆይቷል " ብለዋል።

" በበዓሉ መዝጊያ ቀን ትናንት ግን በከተማዋ ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ አሳዛኙ የቦንብ ጥቃት ተፈፅሞ ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ጥቃቱን የፈፀመው ግለሰብ ማንነቱ ተለይቷል " ያሉት ኮማንደር ወልዳይ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የተወረወረው ኤፍዋን የተባለ የእጅ ቦንብ መሆኑን ፖሊስ አረግጧል። የጥቃቱ አላማም " የግለሰቦች ጠብ " መሆኑን አስረድቷል።

ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በበኩሉ 20 በቦንብ ጥቃት የቆሰሉ ሰዎች ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ መቀበሉን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ትላንት ለሊት በተወረወረው ቦንብ 5 ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶችም መቁሰላቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆስፒታል ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
🪙የቁጠባ ትንሽ የለውም በቴሌብር ሳንዱቅ ለነገ ጥሪት ያኑሩ

🛍ገበያ ሲወጡ እጅ ቢያጥርዎ ቴሌብር እንደኪሴ የጎደለውን ሞልቶ ያሰቡትን ያሳካል

🫰ለህልምዎ ስኬት አንስተኛ ብድር ሲፈልጉ ቴሌብር መላ ዋስ፣ ምስክር፣ እወቁልኝ ሳያበዛ ገበና ሸፍኖ ያበድርዎታል

💰ደሞዝዎ በቴሌብር ሲከፈልዎ ደግሞ በመዳረሻ የደሞዝዎን 30% ብድር በፈጣን ቀላል ምቹ እና አስተማማኙ ቴሌብር ያገኛሉ!

#የፋይናንስ_አገልግሎት_ለሁሉም
#አብረንዎት_ነን
ኢትዮ ቴሌኮም ከዳሸን ባንክ ጋር በአጋርነት
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara ለአንድ ቀን ይቆያል የተባለው የአማራ ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤ በባሕር ዳር እየተካሄደ ይገኛል። ጉባኤው በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ችግሮች ዙሪያ እየመከረ ነው ተብሏል። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኅላፊና የኮማንድፖስቱ አባል አቶ ደሳለኝ ጣሰው ለምክር ቤቱ ንግግር አሰምተዋል። በዚህም ንግግራቸው ፤ በክልሉ የተፈጠረው ወቅታዊ ግጭት " ድህረ ጦርነት የፈጠረው ልዩነት ነው " ብለዋል።…
#NewsAlert

የአማራ ክልል ፕሬዜዳንት ዶክተር ይልቃል ከፋለ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውና ምክር ቤቱም እንደተቀበላቸው ተነግሯል።

ዶ/ር ይልቃል ከፋለ ፤ ለፖርቲያቸው ብልፅግና የመልቀቂያ ደብዳቤ ካስገቡ ከ8 ወራት በላይ እንደሆነ ገልጸው ፤ ወቅታዊ ሁኔታው እንዲቆዩ እንዳስገደዳቸው ጠቁመዋል፡፡

" በቀውስ ወቅት ወደ ሥልጣን መጥቶ በቀውስ ወቅት ኃላፊነትን መልቀቅ ህመሙን የማውቀው እኔ ብሆንም የምንችለውን ሁሉ ግን ሰጥቻለሁ ፤ጥያቄየንም ፓርቲዬ ተቀብሎኛል " ሲሉ ተናግረዋል።

የአማራ ክልል ምክር ቤትም የክልሉን ፕሬዜዳንት የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ መቀበሉ ተገልጿል።

@tikvahethiopia