TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር አብርሃም በላይ ምን አሉ ? የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ በዛሬው እለት የአሸንዳ በዓልን ምክንያት በማድረግ በተረጋገጠ የማህበራዊ ሚዲያ ገፃቸው ላይ መልዕክት አስተለልፈዋል። በመልዕክታቸው ፤ " የአሸንዳ በዓል ለትግራይና ትግራዎት  ልዩ ትርጉም ያለው ሃይማኖታዊና ባህላዊ በአላችን ነው። " ብለዋል። " የዚህ አመት የአሸንዳ በዓል ህዝባችን ከደረሰበት ጉዳት ገና ባላገገመበት…
" በሚኒስትሩ የተላለፈው መልዕክት የአማራ ሕዝብ ከምድረ-ገፅ ፈፅሞ ሳይጠፋ የማይፈፀም የቀን ቅዥት ነው " - የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን

በትግራይ ጦርነት ከጀመረ በኃላ የትግራይ ምዕራባዊ ዞን አስተዳደርን መዋቅርን በማፍረስ " የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን " በሚል የተቋቋመውና በአማራ ክልል ስር የሚገኘው አስተዳደር ከሰሞኑን የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር አብርሃም በላይ ላወጡት መልዕክት ምላሽ የሚሰጥ መግለጫ አወጣ።

በዚሁ መግለጫው ፤ የሀገር መከላከያ ሚኒስትሩ ያስተላለፉት መልዕክት አሳዛኝ ፍጹም ኃላፊነት የጎደለው ነው ብሏል።

መክላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ የአሸንዳ በዓልን አስመልክቶ በትግርኛ ቋንቋ ያስተላለፉት መልዕክት የአማራ ክልል ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ አድርጎ የተላለፈ አደገኛ መልዕክት ነው ሲል ገልጿል።

" ሚኒስትሩ የፌዴራል መንግስት ኃላፊነት ይዘው ሳለ ፍፁም ለአንድ ወገን ያደላ መልዕክት ማስተላለፋቸው ኃላፊነት የጎደለውና የአማራ ክልልን ወደለየለት ግጭት ለማስገባት ሆን ተብሎ የተላለፈ መልዕክት ነው " ሲል ገልጾታል።

መልዕክቱ ፤ " የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አስተዳደር አማራ ክልልን ወደለየለት ብጥብጥና ግጭት እንዲያመራ ሆን ተብሎ የተረጨ መርዘኛ መልዕክት እንደሆነ እናምናለን " ያለው መግለጫው "  " ሚኒስትሩ ይህንን መልዕክት ማስተላለፍ የሚችሉበት ምንም ዓይነት ሕጋዊ ኃላፊነት ሳይኖራቸው እንዱን አካል ህገ-ወጥ ሌላውን ደግሞ ሕጋዊ ብሎ መፈረጅ ከፌዴራል ወርደው ለእንድ ክልል ለተወለዱበት ብሔር/ መወገን አመላካች ሆኖ አግኝተነዋል። " ብሏል።

" የአማራ ሕዝብን የእውነትና የፍትህ ጥያቄ የካደ ነው፡፡ " ሲልም አክሏል።

መግለጫው ፤ " በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን የተቋቋመው መንግስታዊ መዋቅር በሰዎች በበጎፍቃድ የተቸረው ሳይሆን ለዘመናት በተከፈለው ውድ መስዋዕትነት የተገኘ መሆኑን ሚኒስትሩ የዘነጉት ይመስላል " ብሏል።

ሚኒስትሩ ፌዴራሉ መንግስት ከሰጣቸው ኃላፊነት ውጪ ተገቢ ያልሆነ መልዕክት በማስተላለፋቸው የአማራን ሕዝብ ይቅርታ ሊጠይቁ ይገባል ሲልም ገልጿል።

" የተላለፈው መልዕክት የአማራ ሕዝብ ከምድረ-ገፅ ፈፅሞ ሳይጠፋ የማይፈፀም የቀን ቅዥት ነው፡፡ " ብሏል።

የሀገር መከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ ከሰሞኑን ኣሸንዳን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ በሚያከራክሩ የትግራይ ቦታዎች ነዋሪው የሚያነሳው ጥያቄ ካለው በህገ-መንግስት ብቻ የሚመለስበት ሁኔታ እንዲረጋገጥ እየተሰራ ነው ብለዋል።

" ህዝቡ በአጭር ጊዜ ወደ ቄየው ተመልሶ ህገ-መንግስታዊ መብቱ በሚያረጋግጥ መንገድ አስተዳደሩ ራሱ እንዲመሰርት ይደረጋል " ያሉት መከላከያ ሚኒስትሩ " በአከባቢዎቹ በነበረው ሁኔታ በመጠቀም ተፈጥሮ የቆየው አስተዳደር #እንዲፈርስና ከፌደራል የፀጥታ ሃይሎች ውጭ የታጠቀ ሃይል አንዳይኖር ፣ ይህ እንዲፈፀም የፌደራል የአገር መከላከያ ሰራዊት ሃላፊነት ወስዶ እንዲያስፈፅም ትእዛዝ ተሰጥቶ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ " ሲሉ አሳውቀዋል።

ከዚህ ውጭ ከባለቤቱ በላይ ባለቤት ለመሆን የሚዳዳ ፤ ከባለ ጉዳይ በላይ ጉዳይ አለኝ የሚል ፤ ከህግና ስርአት ውጭ በጉልበት ለመንቀሳቀስ የሚሰራ አካል ካለ የፌደራል መንግስት በጀመረው መንገድ ህግና ህገ-መንግስታዊ ሰርአቱ እንዲረጋገጥ ይሰራል ሲሉ አሳስበዋል።

(ለመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ መልዕክት የተሰጠው ምላሽ ሙሉ መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia