በመቐለ ከተማ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ቦምብ ተወርውሮ የሞት አደጋው ያጋጠመው ነሃሴ 18 /2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰአት ነው።

የአይን እማኞች ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ እንደገለፁት ፤ የቦምብ አደጋው ያጋጠመው በከተማው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራው መጠጥ ቤት ነው። 

የአይን እማኞቹ አክለው እንደገለፁት ፤ በመጠጥ ቤቱ ሰዎች በብዛት እየተዘናኑ ሳለ ከቤቱ ውጭ ወደ መጠጥ ቤቱ የተወረወረው ቦምብ የአራት ስዎች ህይወት ወድያው ሲቀጠፍ ፤ የቤቱ ሰራተኞች የሚገኙባቸው በርካቶች ቆስለዋል።

የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ቆየት ብሎ ከሆስፒታል ምንጭ ባገኘው መረጃ ተጨማሪ አንድ ሰው ህይወቱ በማለፉ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 5 መሆኑን ተረድቷል።

መቐለን ጭምሮ የበርካታ የትግራይ ከተሞች የፀጥታ ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ደረጃ መድረሱ፤ ቲክቫህ የመቐለ ከንቲባ አቶ ይትባረክ አምሃ ዋቢ በማድረግ መዘገቡ ይታወሳል።

መቐለ ጨምሮ በሌሎችም ከተሞች በሚገኙ መጠጥ ቤቶች መግብያ በር ' ተተኳሽና ስለታም ነገሮች ይዞ መግባት የተከለከለ ነው ' የሚሉ ፅሁፎች ማንበብ ከጦርነቱ በኋላ የተለመደ እንደሆነ የመቐለ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ዘግቧል።

@tikvahethiopia