TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው ዓመት ጀምሮ የቅደመ ምረቃ ተማሪዎችን በውድድር ብቻ እንደሚቀበል ገለጸ። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከመጪው 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን የሚቀበለው በምደባ ሳይሆን #በውድድር መሆኑን አስታውቋል። ዩኒቨርስቲው ክፍያ የሚፈጽሙ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎችን " በልዩ " ሁኔታ ለማስተማር እንዳቀደም ገልጿል። አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ይህንን ያስታወቀው…
" ወጪያቸው በመንግሥት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጥተን እንቀበላለን " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ትምህርት ሚኒስቴር ከሚያስቀምጠው የመቁረጫ ነጥብ በላይ ያመጡ ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል መገለጹ ይታወቃል፡፡

በሀገሪቱ የመጀመሪያው ራስ ገዝ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም የሆነው ዩኒቨርሲቲው፣ በሚቀጥለው የትምህርት ዘመን ተማሪዎችን የሚቀበልበት መስፈርት ላይ ማብራሪያ አቅርቧል፡፡

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸው በመንግሥት የሚሸፈንላቸውን ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጥቶ ይቀበላል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በማታው ክፍለ ጊዜ (Extension) በግል እየተማሩ እንደሚገኙ ተማሪዎች፤ በመደበኛው ክፍለ ጊዜም (Regular) ተመሳሳይ ተማሪዎችን ተቀበሎ በመጠነኛ ክፍያ የሚያስተምር መሆኑን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ ማህበራዊ ገፆች ላይ " አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሀብታሞች መማሪያ ብቻ ይሆናል" ተብሎ የሚናፈሰው ወሬ ሐሰተኛና የህግ አግባብነት የሌለው ነው ብሏል።

ራስ ገዝ አስተዳደር መሆን ያስፈለገው የገንዘብ አቅም ያላቸው ተማሪዎችን ብቻ ተቀብሎ ለማስተማር እንዳልሆነ ባወጣው ማብራሪያ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው፤ "አንድ ተማሪ ወደ ተቋሙ ለመማር ሲመጣ እንደማንኛውም ተማሪ ከክፍያው በፊት የተቋሙን የትምህርት መመዘኛ መስፈርቶች ማግኘት ይጠበቅበታል" ብሏል፡፡

Via @tikvahuniversity
ቪድዮ ፦ ከሞስኮ ወደ ሴንት ፒተርስበርግ ይበር የነበረ የግል አውሮፕለን ተከስክሶ በውስጡ የነበሩ ሁሉም ተሳፋሪዎች መሞታቸውን የሩስያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

አውሮፕላኑ ሰባት ተሳፋሪዎች እንዲሁም ሦስት የበረራ ሠራተኞችን አሳፍሮ ነበር ተብሏል።

በዚህ አውሮፕላን ውስጥ " ቫግነር " የተሰኘው ቅጥረኛ ቡድን መሪ የቭጌኒ ፕሪጎዢን ተሳፍሮበት ነበር ተብሏል። ከሱ በተጨማሪ ድሚትሪ ዩትኪን የተባለው ከቡድኑ መስራች አንድ ውስጥ ነበረበት ተብሏል።

ከቅጥረኛ ቡድኑ ቫግነር ጋር ግንኙነት ያለውና " ግሬይ ዞን " የተሰኘ የቴሌግራም ቻናል ፕሪጎዢን ተሳፍሮበት የነበረው ጄት በአየር መከላከያ ተመትቶ ወድቋል ብሏል።

አውሮፕላኑ የተመታው በሰሜናዊ ሞስኮ ቴቨር ክልል ውስጥ ነው ሲል ገልጿል።

ፕሪጎዢን የተባለው ግለሰብ አለበት ተብሎ የታመነው አውሮፕላን ሲከሰከስ የሚያሳዩ ቪድዮዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች እየተሰራጩ ይገኛሉ።

ይኸው የቅጥረኛ ቡድኑ መሪ ከጥቂት ወራት በፊት በሩሲያ ጦር ላይ ያልተሳካ አመጽ መርቶ የነበረ ሲሆን በዚህም #የሀገር_ክህደት_ወንጀል ክስ ተመስርቶበት ነበር።

ከክሱ በኃላ ከፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ባደረገው ድርድር ክሱ ውድቅ ተደርጎለት ነበር።

ቫግነር ማነው ?

ይህ ቡድን እራሱን ‘የግል የጦር ኩባንያ’ ብሎ ይገልጻል። ነገር ግን ለሩሲያ መንግሥት ቅርበት ያለው ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን ነው።

መሥራቹ ደግመ የቀድሞው ወንጀለኛ የአሁኑ የቭላድሚር ፑቲን የቅርብ ወዳጅ የነበረው የቭጌኒ ፕሪጎዚን ነው።

የቡድኑ ዋና ተግባሩ ተቀጥሮ መዋጋት ሲሆን በዩክሬን ጦርነት ከሩሲያ ጎን በመሰለፍ ቁልፍ ሚና እንደተጫወተ ይነገራል።

በአፍሪካ ከ10 ባላነሱ አገራት ውስጥ ተሰማርቷል።

Via BBC / TSI
Video : Social Media

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ መሾማቸውን አስተዳደሩ አሳውቋል።

በተጨማሪ ለአዲስ ከተማ ፣ ለሚኩራ፣ አራዳ ፣ ጉለሌ ክፍለ ከተሞች አዳዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚዎች ተሹመዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሰጠ በለው ሹመት እና ሽግሽግ አቶ ሲሳይ ጌታቸው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል። በዚሁ ቦታ ላይ የነበሩት ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ተነስተዋል።

አቶ አውራሪስ ከበደ ደግሞ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ሆነው ተሹመዋል።

በሌላ በኩል ፤ አቶ ኦይዳ አወል የአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ አቶ አበበ ተቀባ የአራዳ ክ/ከተማ ፣ አቶ ወልዴ ወገሴ የጉለሌ ክ/ከተማ፣ አቶ ታረቀኝ ገመቹ የለሚኩራ ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው መሾማቸው ተነግሯል።

(ተጨማሪ የተሿሚ ዝርዝሮችን ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን ከ5000 ሜትር ወንዶች ተሳትፎ ጋር በተገናኘ ለውድድሩ ተመርጦ ወደ ስፍራው ያቀናው አትሌት ጥላሁን ኃይሌ ከውድድሩ መቀነሱን ገልጿል።

በምትኩ በ10,000 ሜትር አራተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው እና የርቀቱ የአመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት አትሌት በሪሁ አረጋዊ ፣ ከሀጎስ ገብረህይወት እና ዮሚፍ ቀጀልቻ ጋር በውድድሩ ሀገራችንን እንደሚወክሉ ትላንት የዓለም አትሌቲክስ ይፋ አድርጓል።

ትላንት ውሳኔውን ከተሰማ በኋላ አትሌት ጥላሁን ሀይሌ በከፍተኛ የሀዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ ቅሬታውን ለባህልና ስፖርት ሚንስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት የገለፀ ሲሆን በተጨማሪ በቪድዮ ተሰራብኝ ስላለው ግፍ ተናግሯል። ቪድዮዎችም በማህበራዊ ሚዲያዎች ተሰራጭተዋል።

በዚሁ ጉዳይ ከጥቂት ደቂቃ በኃላ በፌዴሬሽኑ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል። ይህን ጋዜጣዊ መግለጫ በስፍራው የሚገኘው የቲክቫህ ኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ በቀጥታ በድምፅ ያሰራጨዋል።

በመግለጫው ላይ ከአትሌቱ መቀነስ ጋር በተያያዘ ጥያቄዎች ይጠየቃሉ ተብሎ ይጠበቃል ፤ መግለጫው እንደተጠናቀቀ በሁለቱም በኩል ያሉትን ሃሳቦች የምናደርሳችሁ ይሆናል።

የ5000 ሜትር ወንዶች ማጣርያ ውድድር ዛሬ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል። አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዩሚፍ ቀጀልቻ፣ ሀጎስ ገ/ህይወት፣ በሪሁ አረጋዊ የማጣሪያ ውድድር ተካፋዮች ናቸው ብሏል።

መግለጫውን በ @tikvahethsport ይከታተሉ።

https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዜዳንት ደራርቱ ቱሉ ፤ አትሌት ጥላሁን ኃይሌን ይቅርታ ጠየቀች።

ደራርቱ ፤ " ጥላሁን ስላዘንክ ፤ ስለተበሳጨህ በጣም ይቅርታ " ያለች ሲሆን " ይቅርታ የምለው በጣም ስላለቀሰ ስላዘነ ነው ፤ ነገር ግን መብቱን አልነካንም ፤ እሱን አስወጥተን ማንንም አላስገባብም። ሁሉም ባላቸው ሰዓት እና በብቃታቸው ነው የገቡት " ብላለች።

ደራርቱ እንደ አመራር እና እንደ እናት በተፈጠረው ነገር አዝኛለሁ ፤ ይቅርታም እላለሁ ስትል ተናግራለች።

" የአትሌቱን መብት ነክተን አላስቀረነውም 4ኛ በመሆኑ ብቻ ነው ያስቀረነው " ስትልም አክላለች።

ውሳኔዎች ሲተላለፉ በኮሚቴ ተነጋግረን ለሀገር የሚበጀውን ነው ያለችው ደራርቱ እኔ ብቻዬን ማንም የማስገባትም ሆነ የማስወጣት መብት የለኝም ብላለች።

አትሌት ጥላሁን ኃይሌ በ5000 ሜትር ውድድር ተመርጦ ወደ ሀንጋሪ ከተጓዘ በኃላ ፤ ትላንት በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ እና በሱ ምትክ በሪሁ አረጋዊ መካተቱን ሊያውቅ ችሏል።

በዚህም እጅግ ሀዘን ውስጥ የገባ ሲሆን " የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዜዳንት ደራርቱ የሰራችብኝን ግፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደኝ " ብሏል።

" የሀገሬን ባንዲራ ከፍ ለማድረግ ብዙ ውጣ ውረድ ስለፋ ስደክም ቆይቼ የተሻለ ብቃት ኖሮኝ ፌዴሬሽኑ በሰራብኝ ግፍ ተቀንሻለሁ " ያለ ሲሆን " አሰልጣኝ ሁሴን ሽቦ ነው ፌዴሬሽኑን እየመራ ያለው ማለት ይቻላል ልጄ ይሮጥልኛል ብሎ በሪሁ አራተኛ ወጥቶ ገብቶ እንዲወዳደር ተደርጓል " ሲል ቅሬታው አቅርቧል።

" ቀን እና ማታ በአጥንት እስክቀር ድረስ የለፋሁበት እንጀራዬን እንዲህ መደረጉን ህዝቡ ይወቅልኝ ፤ ፌዴሬሽኑ ውስጥ የሚሰራውን ግፍ ህዝብ ይወቅልኝ " ብሏል።

" ፌዴሬሽኑን የሚመሩት አትሌት የነበሩ ናቸው እነሱ ሲመጡት ውስጥ ያለው አሰራር ይሻሻላል ቢባልም ጭራሽ በነሱ ባሰ፤ ስም አለም ሚዲያውን እንቆጣጠራለን ታዋቂ ነን ፤ ህዝቡን ማሳመን እንችላለን ብለው ይሄን ሁሉ ግፍ የሚያደርጉት እነሱ ናቸው " ሲል አክሏል።

ይህን የአትሌቱን ቅሬታ በተመለከተ ዛሬ መግለጫ የሰጡት የፌዴሬሽን አመራሮች ምርጫው ብቃትን መሰረት ያደረገ ሀገርንም ይጠቅማል በሚል እንጂ ማንንም አስወጥቶ የማስገባት ጉዳይ አይደለም፤ በሪሁ የተሻለ ሰዓት ስላለው ብቃቱም ጥሩ ስለሆነ ነው የገባው ብለዋል።

አትሌት ጥላሁን ኃይሌ የማይወዳደር ከሆነ ለምን እንዲሄድ እንደተደረገ ሲገልፁም ፤ ምናልባት በሪሁ የሆነ ነገር ቢሆን የሱ መኖር አስፈላጊ ነው ፤ ተጠባባቂ አትሌት ሁኔም ይኖራል ይህ ድሮም የነበረ አሰራር ነው ሲሉ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በ5 ሃገሮች (ብራዚል ፣ ህንድ  ፣ ቻይና ፣ ሩስያ ፣ ደቡብ አፍሪካ) የተመሠረተው የBRICS ቡድን መሪዎች ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ጉባኤያቸውን እያካሄዱ ይገኛሉ። በዚሁ የBRICS ጉባኤ ላይ ተካፋይ ለመሆን የአፍሪካ ሀገራት በተደረገላቸው ግብዣ ደቡብ አፍሪካ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ለዚሁ ስብሰባ ደቡብ አፍሪካ የገቡ ሲሆን የኤርትራው ፕሬዜዳንት ኢሳያስ…
#NewsAlert

ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ።

በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን በአዲስ አባልነት መቀበላቸውን ታውቋል።

BRICS በብራዚል፣ ሩስያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረው ቡድን ነው።

አሁን ላይ ይኸው ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘ የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል ’ የሚለውን መፍትሄ ለማበጀት እንቅስቃሴ ላይ እንደሆነ እየተነገረ ነው።

ይህንን ቡድን ለመቀላቀል በርካታ ሀገራት ጥያቄ ሲያቀርቡ የነበረ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያም አንዷ ጠያቂ ነበረች። BRICSም ኢትዮጵያን ጨምሮ ሌሎችን ሀገራት በይፋ ተቀብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት አገኘ። በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ያለው 15ኛው የብሪክስ አባል ሀገራት ጉባኤ ኢትዮጵያን ጨምሮ አርጀንቲና፣ ግብጽ፣ ኢራን፣ ሳዑዲ አረቢያን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶችን በአዲስ አባልነት መቀበላቸውን ታውቋል። BRICS በብራዚል፣ ሩስያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ቻይና፣ ህንድ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረው ቡድን ነው። አሁን…
#BRICS

BRICS ዛሬ አዳዲስ አባል ሀገራትን መቀበሉን አሳውቋል።

እነዚህም ፦

🇪🇹 #ኢትዮጵያ
🇦🇷 አርጀንቲና
🇪🇬 ግብፅ
🇮🇷 ኢራን
🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ናቸው።

አዳዲሶቹ አባል አገራት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀላቀሉ  የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ተናግረዋል፡፡

የሀገራችን ኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የBRICS ጉባኤ ኢትዮጵያን በአባልነት ተቀብሎ ማፅደቁን ተከትሎ ባስተላለፉት መልዕክት ፤ " ይህ ለሀገራችን ታሪካዊ ሁነት ነው " ብለዋል። " ኢትዮጵያ ሁሉን አካታች ለሚሆን የበለፀገ የዓለም ስርዓት መስፈን ከሁሉም ጋር ለመስራት ሁሌም ዝግጁ ናት " ሲሉም ገልጸዋል።

BRICS አዳዲስ አባል ሀገራትን መቀበሉን ተከትሎ አጠቃላይ አባላቱ አስራ አንድ (11) ይሆናሉ።

እነሱም ፦
🇧🇷 ብራዚል
🇷🇺 ሩስያ
🇮🇳 ህንድ
🇨🇳 ቻይና
🇿🇦 ደቡብ አፍሪካ
🇦🇷 አርጀንቲና
🇪🇬 ግብፅ
🇪🇹 ኢትዮጵያ
🇮🇷 ኢራን
🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ
🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ናቸው።

@tikvahethiopia