TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#BRICS BRICS ዛሬ አዳዲስ አባል ሀገራትን መቀበሉን አሳውቋል። እነዚህም ፦ 🇪🇹 #ኢትዮጵያ 🇦🇷 አርጀንቲና 🇪🇬 ግብፅ 🇮🇷 ኢራን 🇸🇦 ሳዑዲ አረቢያ 🇦🇪 የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ናቸው። አዳዲሶቹ አባል አገራት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀላቀሉ  የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎዛ ተናግረዋል፡፡ የሀገራችን ኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የBRICS…
ስለ BRICS ምን ይታወቃል፤ ዓላማውስ ምንድነው ?

- BRICS አሁን ላይ አዳዲስ አባል ሀገራትን ሳይጨምር የተመሰረተው እኤአ 2001 ላይ በብራዚል፣ ሩስያ፣ ህንድ፣  ቻይና  ነው። በኃላም ደቡብ አፍሪካን አካቷል።

- የምዕራባውያን ተፅእኖን ለመገዳደር የተመሰረተ ስብሰብ ነው። በተጨማሪ እንደ IMF እና ዓለም ባንክ ያሉ የገንዘብ ተቋማትን አሰራር የማሻሻያ መንገዶችን ለመፈለግ፣ ለታዳጊ አገራት ምጣኔ ሃብት ድምጽ እና ውክልና ለመፍጠር ነው።

- አባል ሀገራቱ የቡድኑ አላማ ፍትህ እንደሆነ እና ብዝሃነት ያለው የዓለም ስርአት እንዲፈጠር መስራት መሆኑን ይናገራሉ። በምዕራባውያን የበላይነት የሚመራው የዓለም ስርአት እንዲያከትም ይፈልጋሉ።

- አሁን ይቀላቀለሉ የተባሉ አባል ሀገራትን ሳይጨምር አምስቱ ሀገራት ብቻቸውን 3.24 ቢሊዮን የህዝብ ብዛት አላቸው። ያላቸው ብሔራዊ ገቢም አንድ ላይ ሲሰላ 26 ትሪሊዮን ዶላር ይደርሳል። ይህ ከዓለም ምጣኔ ሃብት 26 በመቶውን የሚይዝ ነው።

- የBRICS አባል ሀገራት ለዓለም ንግድ #ከዶላር ውጪ ተጨማሪ መገበያያ ገንዘብ መኖር እንዳለበት ያምናሉ።

- ለዓለም ንግድ ዋነኛ መገበያያ ከሆነው ዶላር ተጨማሪ የመገበያያ ገንዘብ እንደሚያስፈልግ የሚያምኑት አባል ሀገራቱ ዓለም በጥቂት ሀገራት የበላይነት መመራቷ ማብቃት አለበት የሚል የፀና አቋም አላቸው።

- የኢኮኖሚ የበላይነቱ የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ብቻ መወሰኑ ብዙ ሀገራትን በጥቂቶች ጫና ስር እንዲወድቁ በማድረጉ ይህን ለማስተካከል እንደሚሰሩ አባል ሀገራቱ ይናገራሉ።

የብራዚል፣ ሩስያ፣ ሕንድ ፣ ቻይና እና ደ/አፍሪካ ስብስቡ BRICS " ልንቀላቀላችሁ እንፈልጋለን " ብለው ጥያቄ ካቀረቡለት ሀገራት መካከል በነዳጅ ሀብታም የሆኑትን ሳዑዲ አረቢያ ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስን ጨምሮ ኢራን፣ #ኢትዮጵያ፣ ግብፅ ፣ አርጀንቲናን በመጨመር እና አባል እንዲሆኑ በማፅደቅ አጠቃላይ የአባል ሀገራቱን ስብሰብ ወደ 11 አሳድጓል።

@tikvahethiopia
#ኩተሬ

በዛሬው ዕለት የዘገየው የኩተሬ የወረዳነት መዋቅር ጥያቄ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጠውና በአዲሱ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የስልጤ ህዝብ በተገቢው ኮታ እንዲወከል የኩተሬ ከተማና ዙሪያው ነዋሪዎች በሰላማዊ ሰልፍ ድምጻቸውን አሰሙ።

በሰልፉ ላይ ፤ የኩተሬ የወረዳነት ጥያቄ ከ1993 ጀምሮ ከስልጤ የማንነት ጥያቄ ጎን ለጎን ሲጠየቅ እንደነበር የተናገሩት ነዋሪዎች በተለይ ከለውጡ በኋላ በተደጋጋሚ ጊዜ ምላሽ ይሰጣል ቢባልም እስካሁን ምላሽ ባለማግኘታቸው ቅሬታቸውን ለማሰማት የአደባባይ ሰልፍ ለማድረግ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ፦

- ፍትህ ለኩተሬ፣
- ኩተሬ ወረዳነት ይገባታል፣
- ድምጻችን ይሰማ፣
- ህገ መንግስታዊ መብታችን ይከበር፣
- ጥያቄያችን የመልማት ነው ... የሚሉና ሌሎች መፈክሮች በሰልፉ ላይ ተሰምተዋል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የኩተሬ ከተማና የአጎራባች የገጠር ቀበሌያት ነዋሪዎች በነቂስ ወጥተው ድምፃቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን ከአሊቾ ውሪሮ ወረዳ የመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ በአካባቢው እየተነሳ ስላለው ጥያቄ ቤተሰቦቻችን ያነጋገረ ሲሆን ሰልፉ ፍፁም ሰላማዊ እንደነበር ገልጸዋል።

በሰልፉ ላይ ከወረዳው ጥያቄ ባለፈ በክልሉ ፍትሃዊ የተቋም ክፍፍል እንዲደረግ እና ፍትሃዊ የስልጣን ክፍፍል እንዲደረግ መጠየቁን አመልክተዋል።

የህዝቡን የመልማት ጥያቄዎች በፍጥነት ምላሽ እንዲሰጥም ተጠይቋል።

ፍፁም ሰላማዊ መንገድን በተከተለ ሁኔታ ህዝቡ ለጠየቀው ጥያቄ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጡ ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#VladimirPutin #NaredraModi

የሩስያው ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን ፤ ዛሬ BRICSን እንዲቀላቀሉ ውሳኔ ያገኙትን እና በመጪው አዲስ አመት ወደ ተግባር የሚገቡትን አዳዲሶቹ የቡድኑ አባል ሀገራት፦
- ኢትዮጵያ፣
- አርጀንቲና፣
- ኢራን፣
- የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ፣
- ሳዑዲ አረቢያን
- ግብፅን " እንኳን ደስ አላችሁ " ሲሉ የደስታ መልዕክት አስተላልፈውላቸዋል።

በሌላ በኩል ፤ ከBRICS መስራቾች አንዷ የሆነችው ሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትሯ ናሬድራ ሞዲ ከስብሰባው ጎን ለጎን ከኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር ውይይት ያደረጉ ሲሆን በዚሁ ወቅት በኢትዮጵያ የBRICS ቡድንን መቀላቀል" እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

ሞዲ እንደ ንግድ፣ መከላከያ፣ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቶችን ማሳደግ በሚቻልበት መንገድ ላይ ተወያይተናል ሲሉ ገልጸዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ፤ ኢትዮጵያ BRICSን እንድትቀላቀል ህንፍ ላደረገችው ድጋፍ አድናቆታቸውን ችረዋል።

በተመሳሳይ የቻይና መንግሥትም ለኢትዮጵያ " እንኳን ደስ እላችሁ " የሚል መልዕክት አስተላልፏል።

የBRICS ጉባኤ በደቡብ አፍሪካ እየተካሄደ ሲሆን የአዘጋጇ ሀገር ፕሬዜዳንት ሲሪል ራማፎሳ አዳዲሶቹ አባል አገራት ከጥር 1 ቀን 2024 ጀምሮ ቡድኑን ሙሉ በሙሉ እንደሚቀላቀሉ አሳውቀዋል።

(የፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን መልዕክት ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ።

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በ5000ሜ ይወክል የነበረው ጥላሁን ሀይሌ ዛሬ ከሰዓት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ታውቋል።

አትሌቱ ለወራት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ጋር ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ሃንጋሪ፣ ቡዳፔስት ቢያመራም ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል።

በዚህም ምክንያት አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ከአሰልጣኙ ጋር ከተማከረ በኃላ ዛሬ ከሰዓት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ታውቋል።

አትሌቱ ከዝርዝሩ ወጪ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በውሳኔው ማዘኑን እና ቅሬታውን በማህበራዊ ሚዲያ ካሰማ በኃላ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል።

ይሄም አትሌቱ ዜግነቱን #ይቀይራል የሚል ቢሆንም አትሌቱ ዜግነቱ መቀየር ሀሳቡም #እንደሌለው እና በቀጣይ ጠንክሮ በመስራት ኢትዮጵያን ወክሎ አቅሙን ማሳየት እንደሚፈልግ ለናሽናል ስፖርት ገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ዛሬ ምሽት በተደረገ የ5000ሜ ማጣሪያ ውድድር ሁሉም የኢትዮጵያ ተወካዮች (ዩሚፍ ቀጀልቻ፣ በሪሁ አረጋዊ፣ ሀጎስ ገ/ህይወት) ወደ ፍፃሜ ማለፋቸው ተረጋግጧል።

Via @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#TikTok #Kenya

በኬንያ ቲክቶክ ላይ የሚወጡ ቪዲዮች ቁጥጥር እንዲደረግባቸው ከኩባንያው ጋር መስማማቷን ሀገሪቱ ማስታወቋን ቪኦኤ ዘግቧል።

ስምምነቱ የተደረሰው " ቲክቶክ ያልተገቡ ቪዲዮዎችን ያሰራጫል " በሚል እንዲታገድ ከአንድ ግለሰብ ለሀገሪቱ ፓርላማ ከቀናት በፊት ጥያቄ መቅረቡን ተከትሎ ነው፡፡

የአጭር ቪዲዮ ማጋሪያው ኩባንያ ቲክቶክ፣ በመድረኩ ላይ የሚወጡትን ቪዲዮዎች መቆጣጠርን በተመለከተ ከኬንያ ጋር በጋራ ይሠራል ሲል የፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ጽ/ቤት አመልክቷል።

ይህን በተመለከተም ከኩባንያው ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሾ ዚ ችው ጋር መነጋገራቸውን ቢሮው ጨምሮ አስታውቋል።

በስምምነቱ መሠረት፣ " ያልተገቡ ናቸው " የሚባሉ ቪዲዮች ከመድረኩ እንደሚወገዱ ታውቋል።

በአፍሪካ በቲክቶክ ላይ የሚወጡትን የቪዲዮዎች ይዘት በተመለከተ ቁጥጥር ለማድረግ ኩባንያው በኬንያ ቢሮ እንደሚከፍት ዋና ሥራ አስፈጽሚው ሾ ዚ ችው ይፋ ማድረጋቸውም ታውቋል።

ቲክቶክ ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ ከቀረበ በኃላ የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዊታንጉላ ፤ " ቲክቶክ በኬንያውያን በወጣቶች ዘንድ ተዘውታሪ በመሆኑ ፦
- ግጭቶችን በማባባስ፣
- ልቅ ወሲብን በማስፋፋት፣
- የጥላቻ ንግግሮችን በማስፋፋት፣
- የብልግና ቃላትን በማስፋፋት፣
- አደገኛ ባሕሪያትን በማስፋፋት ለአገሪቱ ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ እሴቶች ጠንቅ እየሆነ ነው " ብለው ነበር።

በሌላ በኩል ፤ ሌላኛዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገር ሶማሊያ የአሸባሪዎች መፈንጫ ሆኗል ፤ ህዝቡንም እያሳሳተ ነው በሚል ቲክቶክ እንዲታገድ አዛለች። እግዱ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ ነው የሚጠበቀው። በተመሳሳይ ቴሌግራምም እንዲታገድ ውሳኔ ከተሰጠባቸው መተግበሪያዎች አንዱ ነው።

ሶማሊያ አሸባሪ ድርጅቶችና ቡድኖች አሰቃቂ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እንዲሁም ፎቶግራፎችን በማሰራጨት ሕብረተሰቡን ለማሳሳት ጥቅም ላይ ውሏል በሚል ነው እንዲታገዱ ያዘዘችው።

@tikvahethiopia