TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ከምባታጠምባሮ የዱራሜ ከተማ የምክር ቤት አባላት በሙሉ እየተደራጀ በሚገኘው ክልል ያለውን የቢሮ ክፍፍል ተቃወሙ። አዲስ እየተደረጃ በሚገኘዉ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ የዞኑ ህዝብ ማግኘት የሚገባውን ቢሮ ያላስገኘ እና ፍትሐዊ ያልሆነ የቢሮ ክፍፍል በመሆኑ ሂደቱ ፍትሃዊ በሆነ አካሄድ እንዲደራጅ የዱራሜ ከተማ ምክር ቤት አባላት ጠይቀዋል። የምክር ቤት አባላቱ ጥያቄውን…
#Update

ነገ በዱራሜ ሊደረግ የነበረው ሰልፍ እንዲሰረዝ መደረጉን የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ገለፀ።

ከነባሩ ክልል / ስያሜውን " የማዕከላዊ ኢትዮጵያ " በሚል እየተደራጀ ከሚገኘው ክልል የተቋማት መቀመጫ እና ድልድል ጋር በተያያዘ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቅሬታዎች እንዳሉ ይታወቃል።

ነዋሪም ቅሬታውን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ሲሆን የዱራሜ ከተማ ምክር ቤትም የቢሮ ክፍፍሉ ፍትሃዊ አይደለም በሚል በሙሉ ድምፅ ተቃውሞ በማድረግ ማስተካከያ እንዲደረግ ጠይቋል።

ከዚሁ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ካለው ቅሬታ ጋር በተያያዘ ነገ በዱራሜ ከተማ ሰልፍ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነበር።

ሰልፉን ለማድረግ ሲያስተባብሩ የነበሩ አካላት " በከምባታ ጠምባሮ ዞን ላይ የሚፈፀምን ኢፍትሃዊ ድርጊትና የልማት ተጠቃሚነትን የሚጎትት ውሳኔ የዓለም ህዝብ እንዲያውቀው ለማድረግ ሰላማዊ ሰልፉ እንደተዘጋጀ " ገልጸው የነበረ ሲሆን በከተማው አስተዳደርም እውቅና አግኝቶ ነበር።

በከተማው አስተዳደር የተፈደቀው ሰልፍ ነገ ከጥዋት 3 እስከ 5 ሰዓት ድረስ ለማካሄድ እቅድ ተይዞ ነበር።

ነገር ግን በዛሬው ዕለት በከተማው ከንቲባ በተፃፈ ደብዳቤ " ሰልፉ መሰረዙ " ተገልጿል።

የከተማው አስተዳደር የሰልፉ መሰረዝ " በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በተለያዩ አከባቢዎች ያለዉን ግጭት ምክንያት በማድረግ ሰላማዊ ሰልፉን ወደ ብጥብጥ በመቀየር የሰዉ ህይወት እንዲያልፍና ንብረት እንድወድም ለማድረግ የተዘጋጁ ሀይሎች አንዳሉ የክልሉ ፀጥታ ቢሮ በጥልቀት የገመገመ በመሆኑ ነው " ብሏል።

ከዚህ ባለፈ ፤ የቢሮዎች ድልድል ፍትሃዊነትን በተመለከተ የክልሉ መንግስት ከዞን አመራር ጋር በመቀናጀት ምላሽ እንደሚሰጥ ከስምምነት ላይ የተደረሰ በመሆኑ ሰላማዊ ሰልፉ ተሰርዟል ሲል አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ " በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " የክላስተር ማዕከላት ከተሞች የቢሮዎች ድልድል ሒደት ለከምባታ ጠምባሮ ዞን የተደለደለው የቢሮ ቁጥር አነስተኛ መሆኑን በተመለከተ የዞኑ አመራር ባቀረበው ጥያቄ መነሻነት የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት ከደቡብ ክልል አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ነሐሴ 6 ቀን 2015 ዓ/ም በአካል ባደረጉት ውይይት ቢሮዎች እንዲጨመሩ ከስምምነት ደርሰዋል ሲል ዞኑ ገልጿል።

ለዱራሜ ከተማ እንዲጨመሩ የተወሰኑት ቢሮዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስፈፃሚ መ/ቤቶችን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በሚወጣው አዋጅ ተካትተው ከሌሎች የክላስተር ማዕከላት እኩል ሥራ እንዲጀምሩ እንደሚደረግም ዞኑ ገልጿል።

በዚህ መነሻነት የሀገሪቱ ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተካተቱ ክልከላዎችንና የአስቸኳይ ጊዜው አዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን ከግምት ውስጥ በማስገባት በዱራሜ ከተማ የሚካሔድ ሰልፍ እንደማይኖር ሊታወቅ ይገባል ብሏል።

የሰልፉ ዓላማ ከቢሮ ቁጥር ማነስ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ ከክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት አፋጣኝ ምላሽ በማግኘቱ ሁሉም የኅብረተሰብ ክፍል ወደ ልማት ሥራዎች ፊቱን እንዲያዞርና ጊዜውን በአግባቡ እንዲጠቀም የዞኑ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

የዞኑ አስተዳደር በሰጠው ማብራሪያ ምን ያህል ቢሮ እንደተጨመረ፣ የተጨመሩት ቢሮዎችስ የትኞቹ እንደሆኑ በግልፅ የሰጠው መረጃ የለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ከግንቦት እስከ ሐምሌ / 2015 ከትግራይ ወደ ኤርትራ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሻገሩ የነበሩ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል በድንበር አከባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ ወደ " ጉሎመኻዳ ወረዳ " አቅንቶ ነበር። የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ለቲክቫህ የመቐለ…
#ፋፂ

ከሰሞኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ዓዲግራት በ20 ኪሎ ሜትር ፤ ከኤርትራ ድንበር 15 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ፋፂ ከተማ ተገኝቶ ነበር።

" ፋፂ " የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳደር መቀመጫ ናት።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ስለ ህገ-ወጥ የመስረታዊ ሸቀጦች የኢንዱስትሪ እቃዎች ዝውውር እና በአጠቃላይ ስላለው ሁኔታ ጠይቀናቸዋል።

አቶ ሃፍቶም በራኺ ምን አሉ ?

አከባቢያቸው ከኤርትራ የሚዋሰን እና እስከአሁን ድረስ የወረዳው 6 ቀበሌዎች በኤርትራ ወታደሮች ስር መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም በርካታ ህገወጥ ተግባራት እንደሚፈፀሙ ጠቁመዋል።

ከነዚሁ ተግባራት አንዱ ህገወጥ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ይህንን ህገ ወጥ ተግባር የፀጥታ ሃይሉና
የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶች በመጠቀም ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚሁ ሂደት ፦
- የታሸጉና ያልታሸጉ ምግቦች ፣
- የኢንዱስትሪ መሳሪያዎች ፣
- የመብል ዘይት ፣
- ቴንዲኖ ፣
- የቤት ክዳን ቆርቆሮ ፣
- የተለያዩ ኬሚካሎች ፣
- የእርድ እንስሳት
- በተለይ ስሚንቶ በስፋትና በብዛት እንዲሁም ሌሎች እቃዎች ከህግ ውጪ ይንቀሳቀሳሉ ብለዋል።

በኤርትራ ወታደሮች ስር በሚገኙት በዛላኣምበሳ  ፣ በዳሞ ፣ በሰበያ ፣ በብዘት በሚባሉት መስመሮች በመኪና ፣ በጭነት እንስሳት እና በሰው ሸክም በኮንትሮባንድ መልክ በቀን እና በሌሊት እቃዎችን ለማስተላለፍ ይሞከራል ሲሉ ገልጸዋል።

" በተለይም የኤርትራ መንግስት በወረራ ከያዛቸው የትግራይ ኢትዮጵያ ግዛቶች ያለመውጣቱ ተያይዞ ፦ በርካታ የፀጥታ ችግሮች ያሉ መሆናቸው ፣ የህገ ወጥ የመተላለፊያ ቦታዎቹ መስፋት ለመቆጣጠር አዳጋች ቢሆንም ህዝብና የፀጥታ አካሉ በመቀናጀት የኮንትሮባንድና የፀጉረ ለወጥ እንቅስቃሴው በመከታተል ረገድ እጅግ አበረታች ስራ እየተሰራ ነው "  ብለዋል።

በተያያዘ መልኩ ከኤርትራ ወደ ትግራይ ኢትዮጵያ የሚደረገው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አልተቋረጠም ያሉ ሲሆን " ስደተኞቹ ተይዘው ህጋዊ ፎርማሊቲ ካሟሉ በኋላ ወደ ሚመለከተው አካል ተላልፈው ይሰጣሉ " ብለዋል።

አከባቢው ከባድ ጦርነት ያሰተናገደ ሰለሆነ ከተቀበሩና ከተጣሉ ፈንጅ ፣ የእጅ ቦምብ የመሳሰሉ የጦር መሳሪዎች ሙሉ በሙሉ የፀዳ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

የወዳደቁ ብረቶች ሰብስቦ ለመሸጥ ከመከፈለግ የተነሳ አንዳንድ ግለሰቦች ያልተተኮሱ የጦር መሳሪዎች ጭምር ሰብስበው ተሽከመው ሲንቀሳቀሱ በፀጥታ መዋቅሩ ተይዘው ከጉዳት የዳኑ እንዳሉ ጠቁመዋል።

" ህገወጥ ኮንትሮባንዲስቶች እና ህዝቡ ለአደጋ እንዳይጋለጡ አስፈላጊውን ትምህርት ይሰጣል " ያሉት አቶ ሃፍቶም " ከዚሁ ጎን ለጎን በፕሪቶሪያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጠናክሮ እንዲዘልቅ የሚያግዙ የተቀናጁ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

ህዝቡ ሰላሙ እየጠበቀ ከአከባቢው በህገ ወጥ መልክ ወደ ኤርትራ የሚተላለፉት መሰረታዊ ሸቀጦችና የኢንዳስትሪ መሳሪዎች በመከላከል ረገድ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፋፂ #ትግራይ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ነገ በዱራሜ ሊደረግ የነበረው ሰልፍ እንዲሰረዝ መደረጉን የዱራሜ ከተማ አስተዳደር ገለፀ። ከነባሩ ክልል / ስያሜውን " የማዕከላዊ ኢትዮጵያ " በሚል እየተደራጀ ከሚገኘው ክልል የተቋማት መቀመጫ እና ድልድል ጋር በተያያዘ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ቅሬታዎች እንዳሉ ይታወቃል። ነዋሪም ቅሬታውን በተለያየ መንገድ እየገለፀ ሲሆን የዱራሜ ከተማ ምክር ቤትም የቢሮ ክፍፍሉ ፍትሃዊ አይደለም በሚል…
#Update

" ሠልፉ የተከለከለው ለማፈን ሳይሆን የሕዝቡ ጥያቄ በውይይት በመፈታቱ ነው " - ኮማንድ ፖስት

በከምባታ ጠምባሮ ዞን በቡድን መንቀሳቀስና መሰብሰብን ጨምሮ ሌሎች ክልከላዎች ተጣሉ።

ማምሻውን የከምባታ ጠምባሮ ዞን ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት አስቸኳይ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫው በነገው እለት የሚካሄድ ምንም አይነት ሠላማዊ ሰልፍ የለም ብሏል።

" የሀገሪቱን ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ በተለይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተካተቱ ክልከላዎችንና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የተፈፃሚነት ወሰን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነገ በዱራሜ የሚካሔድ ሰልፍ እንደማይኖር ሊታወቅ ይገባል " ብሏል።

የሰልፉ ዓላማ ከቢሮ ቁጥር ማነስ ጋር የሚያያዝ ቢሆንም የዞኑ አስተባባሪ ኮሚቴ ከክልሉ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት አፋጣኝ ምላሽ እንዳገኘ በመግለጫው ጠቁሟል።

በዱራሜ ተፈቅዶ የነበረው ሠላማዊ ሠልፍ የተከለከለው " ለማፈን ሳይሆን የሕዝቡ ጥያቄ በውይይት በመፈታቱ ነው " ሲል የገለፀው የዞኑ ጊዜያዊ ኮመንድ ፖስት ከሰዓት ጀምሮ በዞኑ በሁሉም አካባቢዎች ተከልክለዋል ያላቸውን ተግባራት አሳውቋል።

- በቡድን መንቀሳቀስና መሰብሰብ ተገድቧል።

- ከሰልፉ ጋር በተያየዘ ቀስቃሽ መልዕክት የያዙ አልባሳት፣ ባነሮችና ጽሑፍፎችን መጠቀም ተከልክሏል።

- ከጀምሮ የባለ 2 እና ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ተገድቧል።

- በሁሉም አካባቢ ለአፍታም ቢሆን የንግድ ተቋማትና የመንግስት መሥሪያ ቤቶች መደበኛ ሥራ መቆም እንደሌለበት አሳስቧል።

በየአቅጣጫው በፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እንደሚደረግም ገልጿል።

በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለሚፈጠሩ ጥሰቶች መንግስትም ሆነ የፀጥታ ኃይል ኃላፊነት አይወስዱም ሲል ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ አሳስቧል።

በከምባታ ጠምባሮ ዞን፤ ከ ' ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ' የተቋማት ድልደላ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ቅሬታ አለ።

የቅሬታው ምንጭ፤ በክላስተር ቢሮ ክፍፍል ላይ ዞኑ ማግኘት የሚገባውን ተቋም አላገኘም፤ ሚዛናዊ ያልሆነ የቢሮዎች ክፍፍል ነው የተደረገው የሚል ነው።

ክፍልሉ እኩል የመልማት፣ የመበልፀግና የማደግ መብትን የሚገድብ በመሆኑ እንዲታረም ነው እየተጠየቀ ያለው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ለነገ ጥዋት ከ3 - 5 ድረስ የሚቆይ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቶ ነበር፤ ሰልፉም እየተፈፀመ ያለውን ኢፍትሐዊ አሰራር ለመቃወም ሲሆን፦
👉 ፍትሕ ለተጨቆነው የከምባታ ጠምባሮ ዞን ህዝብ
👉 12 ለ 1 የክላስተር ቢሮ ሽንሸናን እናወግዛለን
👉 የዞናችን ህዝብ ያነሳው የኢ-ፍትሃዊነት ጥያቄ ሳይመለስ በክልል ምስረታ ጉባኤ ላይ የሚሳተፉ አካላት ህዝባችንን አይወክሉም
👉 በከምባታ ጠምባሮ ዞን ላይ እየተፈፀመብንን ያለውን ኢፍትሃዊነት አጥብቀን እቃወማለን የሚሉና ሌሎችንም መልዕክቶች ለማስተላልፈ ዝግጅቶች ተደርገው ነበር።

ይህ ሰልፍ በከተማ አስተዳደሩ እውቅና አግኝቶ ዝግጅቶች ሲደረጉ ከቆዩ በኃላ ዛሬ ፍቃዱን የሰጠው የከተማው አስተዳደር ሰልፉ መሰረዙን ይፋ አድርጓል።

ዞኑ ባወጣው መግለጫ፤ የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር አስተባባሪ ኮሚቴ አካላት ከደቡብ ክልል አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ቢሮዎች እንዲጨመሩ ከስምምነት ደርሰዋል ሲል ገልጿል።

ለዱራሜ ከተማ እንዲጨመሩ የተወሰኑት ቢሮዎች የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አስፈፃሚ መ/ቤቶችን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በሚወጣው አዋጅ ተካትተው ከሌሎች የክላስተር ማዕከላት እኩል ሥራ እንዲጀምሩ እንደሚደረግም ነው ዞኑ ያሳወቀው።

በዚህም መነሻ ነገ ሰልፍ እንደማይደረግ ገልጿል።

የዞኑ አስተዳደር ባወጣው መግለጫ ምን ያህል ቢሮ እንደተጨመረ፣ የተጨመሩት ቢሮዎችስ የትኞቹ እንደሆኑ በግልፅ የሰጠው መረጃ የለም።

@tikvahethiopia
#Tigray

የትግራይ አስተዳደር በወቅታዊ ጉዳይ አቋሙ ምንድነው ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን ለማፍረስ ይቋምጣሉ " ያላቸውን በስም ያልጠቀሳቸውን ኃይሎች ዓላማ ለማክሸፍ ከፌዴራሉ መንግሥት ጋር ያለውን ግንኙነት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

ይህንን የገለፀው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ነው።

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በስም ያልገለፃቸውና በአማራ ክልል ውስጥ ይገኛሉ ያላቸው ' ፅንፈኛ ' ሲል የጠራቸው ኃይሎችና አጋሮቻቸው " ትግራይ ላይ አሰበዉት የነበረውን የጥፋት አላማ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዳከሸፈባቸው በአደባባይ የሚያማረሩበት ፤ ብሎም ከፌዴራል መንግስት ጋር ቀጥተኛ ጦርነት ውስጥ የገቡበት ሁኔታ ሲፈጠረ ፀረ ፕሪቶሪያና ፀረ ትግራይ አቋማቸውን በግልፅ በማራገብ ላይ ይገኛሉ " ብሏል።

" ይህን እንቅስቃሴ እንመራለን የሚሉ አመራሮችም ሆኑ አጋሮቻቸው እንዲሁም ያሰማሯቸው የሚድያ አፈቀላጤዎችና የርእዮተ አለም መሪዎች ፣ መከላከያ ሰራዊቱ በመውሰድ ላይ ያለውን እርምጃ ‘የህወሓት ቀጥተኛ ተሳትፎ አለበት’ በሚል በሬ ወለደ ጩኸት እየደረሰባቸው ላለው ሽንፈት የትግራይን ህዝብ ሰበብ ለማድረግ  ሲዳክሩ ይሰማሉ " ሲል ጊዜያዊ አስተዳደሩ ገልጿል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ " የፌዴራል መንግስት በነዚህ ሀይሎች ላይ እየወሰዳቸው ላሉ እርምጃዎች የትግራይንም ሆነ የሌላውን ወገን የተለየ ድጋፍ ያስፈልገዋል ብለን አናምንም " ያለ ሲሆን " ይሁንና ግን ፀረ ሰላም አቋማቸውን ለማራመድ እስኳሁን ሲረጩት የነበረውን መርዝ  አልበቃ ብሎ የትግራይን ህዝብ በትልቁ በትንሹ ቋሚ ስራ አድርገውት ይገኛሉ " ብሏል።

ይህ ዘመቻ በፍፁም አሸናፊ ሊያደርግ አይችልም ፤ በህዝቦች መካከል ሊኖር የሚገባውንም ሰላማዊ ግንኙነት በእጅጉ የሚጎዳ ነው ሲል አሳስቧል።

" አሁንም ቢሆን መላው የትግራይ ህዝብ ሁሉም ችግሮች #በሰላማዊ_መንገድ እንዲፈቱ ያለው ቁርጠኛ አቋም እንደተጠበቀ ነው " ያለው ጊዜያዉ አስተዳደሩ " የፕሪቶሪያውን ስምምነት ለማፍረስ የሚቋምጡ ፅንፈኛ ሀይሎችና የቅርብም የሩቅም አጋሮቻቸው በህዝባችን ላይ የሚያደርጉትን ዘመቻ ለማክሸፍ ከፌዴራል መንግስት እስካሁን ድረስ እያደረግነው የመጣነውን አበረታች ግንኙነት አጠናክረን የምንቀጥል ይሆናል " ሲል አቋሙን ገልጿል።

(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#State_of_Emergency ዛሬ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በ " አማራ ክልል " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነገግ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል። አመሻሹን ደግሞ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዴት ተግባራዊ እንደሚደረግ እንዲሁም የሚወሰዱ እርምጃዎች እና ተከለከሉ ተግባራት ዝርዝር ይፋ ተደርጓል። በዚህም ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅም በብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዳይሬከተር ጄነራል የሚመራ…
#State_of_Emergency

ነገ በአማራ ክልል እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የሕዝብ ተወካዮች በሚሰጡት ድምፅ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኛል።

ምክር ቤቱ፤ ከቀናት በፊት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ለነገ ሰኞ 8 ሰዓት ለምክር ቤት አባላት አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ ያቀረበ ሲሆን በዚሁ መሰረት አባላት ተሰብስበው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ሕጉ ምን ይላል ?

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ በ48 ሰዓታት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንደሚቀርብ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘ ወዲያውኑ እንደሚሻር የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ ሁለት (ሀ) ይደነግጋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሥራ ላይ ባልሆነበት ወቅት የታወጀ እንደሆነ በአሥራ አምስት ቀናት ውስጥ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ እንዳለበት፣ የምክር ቤቱን ሁለት ሦስተኛ ድምፅ ተቀባይነት ካላገኘም ወዲያውኑ እንደሚሻር የሕገ መንግሥቱ ቀጣይ አንቀጽ ይደነግጋል።

6ኛው ዙር ምርጫ በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቶ በነበረ ግጭትና አለመረጋጋት ሳቢያ በተሟላ ሁኔታ ባለመከናወኑ፣ በሥራ ላይ የሚገኘው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ካሉት 547 ወንበሮች መካከል የተወሰኑት የተጓደሉ ናቸው።

በአጠቃላይ አሁን በሥራ ላይ በሚገኘው ምክር ቤት መቀመጫ የያዙ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ብዛት 427 መሆኑን ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ መረዳት ይቻላል።

በመሆኑም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ም/ ቤቱ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ማፅደቅ ይኖርበታል በሚለው ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊፀና የሚችለው ከአጠቃላይ የምክር ቤቱ አባላት ማለትም በስድስተኛው ዙር ተመርጠው በምክር ቤቱ መቀመጫ ከያዙት 427 ተወካዮች መካከል 285 የሚሆኑት የድጋፍ ድምፅ ከሰጡ ነው።

ከተጠቀሱት 427 ተመራጮች ውስጥ 142 የምክር ቤት አባላት የተቃውሞ ድምፅ ከሰጡ ግን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቀሪ ሊሆን ይችላል። 

በም/ቤቱ ወንበር ካገኙ አጠቃላይ 427 አባላት ወስጥ 410 የሚሆኑት በገዢው ፓርቲ ብልፅግና አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ የሕዝብ ተወካዮች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ውስጥ ደግሞ 125 ያህሉ በአማራ ብልፅግና ፓርቲ አቅራቢነት የተወዳደሩና የክልሉን ሕዝብ የሚወክሉ ናቸው።

ከብልፅግና ፓርቲ ውጪ በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ አምስት የሕዝብ ተወካዮች ሲኖሩ፣ በኢዜማ አቅራቢነት ተወዳድረው የተመረጡ ሌሎች አራት የሕዝብ ተወካዮች እንደሚገኙም ይታወቃል።

ይሁን እንጂ ከዚህ ቀደም ለምክር ቤቱ በቀረቡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጆች ላይ ለተሰጠው ድምፅ ሥሌት የተደረገው በዕለቱ የነበረውን የምክር ቤቱ ምልዓተ ጉባዔ መሠረት አድርጎ በመሆኑ፣ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለምክር ቤት በሚቀርብበት ወቅት የሚኖረው የድምፅ አሰጣጥ ሥሌት በዕለቱ የሚኖረውን ምልዓተ ጉባዔ ታሳቢ የሚያደርግ ይሆናል።

በመሆኑም የሁለት ሦስተኛ ድምፅ ሥሌቱ ከላይ የምክር ቤቱን ጠቅላላ አባላት መሠረት በማድረግ ከተገለጸው ውጤት ያነሰ የድጋፍ እና ተቃውሞ ድምፅ የመከሰት ዕድሉ ሰፊ ነው።

(የሕግ ጉዳይ ማብራሪያ ከሪፖርተር ጋዜጣ)

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተለያዩ የሥራ መደቦች ሰልጣኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

✓ ሰልጣኝ አብራሪ/ፓይለት (Trainee Pilot)

✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ቴክኒሽያን
(Trainee Aircraft Maintenance Technician)

✓ ሰልጣኝ የአውሮፕላን ሜካኒክ (Trainee Aircraft Mechanic)

✓ ሰልጣኝ የበረራ አስተናጋጅ (Trainee Cabin Cors)

✓ ሰልጣኝ የመንገደኛ አገልግሎት ኢጀንት (Trainee Customer Service Agent)

አመልካቾች ለምዝገባ ሊያሟሉ የሚገባቸው፦

የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውንና ኮፒው፣ የ8ኛ ክፍል ሚኒስትሪ ካርድ፣ የልደት ካርድ፣ የታደሰ የቀበሌ የነዋሪነት ማረጋገጫ ካርድ እና አንድ ጉርድ ፎቶግራፍ

አመልካቾች ከተዘረዘሩት የሥራ መደቦች ውስጥ ማመልከት የሚችሉት በአንዱ ብቻ ነው።

የምዝገባ ጊዜ፦

ከነሐሴ 15 እስከ 19/2015 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፡-

➤ አዲስ አበባ በኦንላይን፣
➤ አምቦ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ደብረ ማርቆስኦኒቨርሲቲ፣
➤ ወሎ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ጅማ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ መቐለ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ሮቤ ቲቺንግ ኮሌጅ፣
➤ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ፣
➤ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ

(ዕድሜ ፣ ቁመት እና ሌሎች ተያያዥ መረጀዎችን ከላይ በተያያዘው የተቋሙ ማስታወቂያ ይመልከቱ)

@tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
አስቸኳይ_ጊዜ_አዋጅ_ቁጥር_6_2015_በተመለከተ_ከኢትዮጵያ_ሰብአዊ_መብቶች_ኮሚሽን_ኢሰመኮ_የተሰጠ_ምክረ.pdf
ኢሰመኮ በአማራ ክልል ጉዳይ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአማራ ክልል ከግጭቱ ጋር በተያያዘ ከሰብዓዊ መብት ጋር በተያያዘ እያደረገ ያለውን ክትትል በተመለከተ መግለጫ ልኮልናል።

በመግለጫው ምን አለ ?

- በሀገር መከላከያ ሰራዊት እና በፋኖ መካከል በአማራ ክልል የተቀሰቀሰውን ግጭት ፤ ግጭቱም ተከትሎ በሰብአዊ መብት አያያዝ ላይ እያደረሰ ያለውን ጉዳት እየተከታተለ እንደሚገኝ ጠቁሟል።

- በአማራ ክልል በከተሞች እና በከተሞች ዙሪያ ከባድ ውጊያዎች ተደርገው እንደነበር እነዚህም ውጊያዎች ንፁሀንን ለሞትና ጉዳት የዳረጉ፤ ንብረትንም ያወደሙ ከባድ መሳሪያዎች ጥቅም ላይ የዋሉባቸው መሆናቸውን አመልክቷል።

- መንገዶችን ለመዝጋት የሞከሩ ሲቪሎችን ጨምሮ ተቃዋሚዎች የተገደሉባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ።

- በክልሉ የሚገኙ ማረሚያ ቤቶች እና ፖሊስ ጣቢያዎች ተሰብረዋል፤ መሳሪያ እና ጥይቶች ተዘርፈዋል፣ ከፍርድ በፊት የታሰሩ እና ሌሎች እስረኞችም ከእስር አምልጠዋል።

- በተለያዩ እርከኖች ላይ የሚገኙ የአማራ ክልል ባለስልጣናት የጥቃት ኢላማ ሆነዋል። በዚህም በተለያዩ አካባቢዎች በጊዜያዊነት መንግሥታዊ መዋቅር እንዲፈርስ እና የመንግስት ባለስልጣናትም እንዲገደሉ ሆናል።

- በግጭቱ ምክንያት የመብራት፣ የውሃ፣ የባንክ አገልግሎት፣ ሆስፒታሎች፣ ትምህርት ቤቶች፣ የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ጨምሮ የመሠረታዊ አገልግሎቶች ተደራሽነት በብዙ አካባቢዎች እንዲቋረጡ ሆኗል።

- በግጭቱ ሱቆችም የተዘጉ ሲሆን ግጭቱ ነዋሪዎችን በመኖሪያ ቤታቸው እንዲቆዩና እና የእለት ተእለት ተግባራቸውን እንዳይፈፅሙ አድርጓል።

- በአማራ ክልል ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚሰጠው ሰብዓዊ እርዳታ በግጭቱና በመንገድ መዘጋቱ እንዲቋረጥ ሆኗል።

- በደብረ ብርሃን ከተማ ነሐሴ 6 እና 7 /2023 ብዙ ህዝብ በሚኖርባቸው 4 ቀበሌዎች ውስጥ በተካሄደ ከባድ ውጊያ በሆስፒታል፣ በቤተክርስቲያንና በትምህርት ቤት የሚገኙ ሰላማዊ ዜጎች ጨምሮ በአካባቢያቸው የነበሩ ነዋሪዎች እና በስራ ቦታቸው ላይ የነበሩ ሰራተኞች በተፈጠረው ግጭት በከባድ መሳሪያ ወይም በተኩስ ልውውጥ ሕይወታቸው አልፏል።

- በደብረ ብርሃን፣ ፍኖተሰላም  እና ቡሬ በተፈፀሙ ጥቃቶች በርካታ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጉዳት ስለመድረሱ፣ በመኖሪያ አካባቢዎች እና በህዝባዊ ቦታዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የሚገልጹ ተዓማኒነት ያላቸው ሪፖርቶች እንደደረሱት አሳውቋል።

- በባህር ዳር ከተማ በበርካታ አካባቢዎች ሰላማዊ ዜጎች በመንገድ ላይ ወይም ከቤታቸው ውጭ የተገደሉ ሲሆን አንዳንድ ወጣቶች ደግሞ በተለይ ተፈልገው ለድብደባ እና ግድያ ዒላማ ተደርገዋል።

- በጎንደር የተለያዩ አካባቢዎች የበርካታ ሰላማዊ ዜጎች ጉዳት እና የንብረት ውድመት እንዲሁም በሸዋ ሮቢት ከህግ አግባብ ውጪ በጸጥታ ሃይሎች ግድያ መፈጸሙ የሚገልጹ ተአማኒነት ያላቸው ሪፖርቶች እንደደረሱት አሳውቋል።

- በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአማራ ተወላጆች የሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ላይ በስፋት እስራት መፈፀሙና ከኤርትራ የመጡ ስደተኞችም በስፋት መታሰራቸውን ገልጿል ፤ ከእነዚህ ኤርትራውያን ውስጥ ጥቂቶቹ በኢትዮጵያ ጥገኝነት ጠያቄዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ አመልክቷል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በላከልን መግለጫ ፤ ተፋላሚ ወገኖች ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህግ ጥሰቶችን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ ፤ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ በመስማማት ግጭቶችን ወዲያውኑ እንዲያቆሙ ፤ ለውይይት እና ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቦታ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba በአዲስ አበባ የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ለአጭር ቀን ታገደ። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፤ የመሬት አገልግሎት አሰጣጥ ለአጭር ቀን የታገደ መሆኑን አሳውቋል። እገዳው ፤ ከሐምሌ 28/2ዐ15 ዓ.ም እስከ ነሐሴ 5/2ዐ15 ዓ/ም ድረስ ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ከቢሮ ሪፎርም ሥራ ጋር በተገናኝ የሚስተካከሉ ስራዎች ስላሉ ነው ተብሏል። በተጠቀሰው ጊዜ…
#Update

የመሬት አገልግሎት ዕግድ ተነሳ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፤ ከቢሮ ሪፎርም ስራ ጋር በተገናኘ በቀን 28/11/2015 ዓ/ም ለሁሉም ክፍለ ከተሞች የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት በላከው ደብዳቤ የመሬት አገልግሎት መታገዱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የዕገዳው መነሳት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከዛሬ ነሐሴ 8/2015 ዓ.ም ጀምሮ ዕግዱ የተነሳ መሆኑን በዶ/ር ቀነዓ ያደታ (የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ) ተፈርሞ ለሁሉም ክ/ከተሞች የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የተላከ ደብዳቤ ያሳያል።

ኃላፊው ፤ አገልግሎቶቹ ሕጋዊ አሰራሮችን በመከተል እንዲሰጡ አሳስበዋል።

(ደብዳቤው ከአዲስ አበባ ከተማ የመሬት መረጃ አገልግሎት የተገኘ ነው)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#State_of_Emergency ነገ በአማራ ክልል እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የሀገሪቱ አካባቢ ላይ ተግባራዊ እንዲደረግ በሚኒስትሮች ም/ቤት የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የሕዝብ ተወካዮች በሚሰጡት ድምፅ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኛል። ምክር ቤቱ፤ ከቀናት በፊት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ላይ መርምሮ ውሳኔ ለማሳለፍ ለነገ ሰኞ 8 ሰዓት ለምክር ቤት አባላት አስቸኳይ የስብሰባ…
#Update

ምክር ቤቱ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ስብሰባው ፤ የሚንስትሮች ምክር ቤት ሐምሌ 28 ቀን 2ዐ15 ዓ/ም ባካሄደው 23ኛ መደበኛ ስብሰባ በደነገገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ውይይት የሚያደርግ ይሆናል፡፡

Via HoPR

@tikvahethiopia