TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Tigray ከግንቦት እስከ ሐምሌ / 2015 ከትግራይ ወደ ኤርትራ በህገ-ወጥ መንገድ ሊሻገሩ የነበሩ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል። የቲክቫህ መቐለ ቤተሰብ አባል በድንበር አከባቢ ያለውን ሁኔታ በሚመለከት የሚመለከታቸውን አካላት ለመጠየቅ ወደ " ጉሎመኻዳ ወረዳ " አቅንቶ ነበር። የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ለቲክቫህ የመቐለ…
#ፋፂ

ከሰሞኑን የቲክቫህ ኢትዮጵያ መቐለ ቤተሰብ አባል ከትግራይ ምስራቃዊ ዞን ዋና ከተማ ዓዲግራት በ20 ኪሎ ሜትር ፤ ከኤርትራ ድንበር 15 ኪሎ ሜትር በምትርቀው ፋፂ ከተማ ተገኝቶ ነበር።

" ፋፂ " የጉሎመኻዳ ወረዳ አስተዳደር መቀመጫ ናት።

የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቶም ባራኺ ስለ ህገ-ወጥ የመስረታዊ ሸቀጦች የኢንዱስትሪ እቃዎች ዝውውር እና በአጠቃላይ ስላለው ሁኔታ ጠይቀናቸዋል።

አቶ ሃፍቶም በራኺ ምን አሉ ?

አከባቢያቸው ከኤርትራ የሚዋሰን እና እስከአሁን ድረስ የወረዳው 6 ቀበሌዎች በኤርትራ ወታደሮች ስር መሆናቸውን ገልጸዋል። በዚህም በርካታ ህገወጥ ተግባራት እንደሚፈፀሙ ጠቁመዋል።

ከነዚሁ ተግባራት አንዱ ህገወጥ የኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ነው፡፡

ይህንን ህገ ወጥ ተግባር የፀጥታ ሃይሉና
የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶች በመጠቀም ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

በዚሁ ሂደት ፦
- የታሸጉና ያልታሸጉ ምግቦች ፣
- የኢንዱስትሪ መሳሪያዎች ፣
- የመብል ዘይት ፣
- ቴንዲኖ ፣
- የቤት ክዳን ቆርቆሮ ፣
- የተለያዩ ኬሚካሎች ፣
- የእርድ እንስሳት
- በተለይ ስሚንቶ በስፋትና በብዛት እንዲሁም ሌሎች እቃዎች ከህግ ውጪ ይንቀሳቀሳሉ ብለዋል።

በኤርትራ ወታደሮች ስር በሚገኙት በዛላኣምበሳ  ፣ በዳሞ ፣ በሰበያ ፣ በብዘት በሚባሉት መስመሮች በመኪና ፣ በጭነት እንስሳት እና በሰው ሸክም በኮንትሮባንድ መልክ በቀን እና በሌሊት እቃዎችን ለማስተላለፍ ይሞከራል ሲሉ ገልጸዋል።

" በተለይም የኤርትራ መንግስት በወረራ ከያዛቸው የትግራይ ኢትዮጵያ ግዛቶች ያለመውጣቱ ተያይዞ ፦ በርካታ የፀጥታ ችግሮች ያሉ መሆናቸው ፣ የህገ ወጥ የመተላለፊያ ቦታዎቹ መስፋት ለመቆጣጠር አዳጋች ቢሆንም ህዝብና የፀጥታ አካሉ በመቀናጀት የኮንትሮባንድና የፀጉረ ለወጥ እንቅስቃሴው በመከታተል ረገድ እጅግ አበረታች ስራ እየተሰራ ነው "  ብለዋል።

በተያያዘ መልኩ ከኤርትራ ወደ ትግራይ ኢትዮጵያ የሚደረገው ህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር አልተቋረጠም ያሉ ሲሆን " ስደተኞቹ ተይዘው ህጋዊ ፎርማሊቲ ካሟሉ በኋላ ወደ ሚመለከተው አካል ተላልፈው ይሰጣሉ " ብለዋል።

አከባቢው ከባድ ጦርነት ያሰተናገደ ሰለሆነ ከተቀበሩና ከተጣሉ ፈንጅ ፣ የእጅ ቦምብ የመሳሰሉ የጦር መሳሪዎች ሙሉ በሙሉ የፀዳ አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

የወዳደቁ ብረቶች ሰብስቦ ለመሸጥ ከመከፈለግ የተነሳ አንዳንድ ግለሰቦች ያልተተኮሱ የጦር መሳሪዎች ጭምር ሰብስበው ተሽከመው ሲንቀሳቀሱ በፀጥታ መዋቅሩ ተይዘው ከጉዳት የዳኑ እንዳሉ ጠቁመዋል።

" ህገወጥ ኮንትሮባንዲስቶች እና ህዝቡ ለአደጋ እንዳይጋለጡ አስፈላጊውን ትምህርት ይሰጣል " ያሉት አቶ ሃፍቶም " ከዚሁ ጎን ለጎን በፕሪቶሪያ የተደረሰው የሰላም ስምምነት ተጠናክሮ እንዲዘልቅ የሚያግዙ የተቀናጁ ስራዎች ይሰራሉ ብለዋል።

ህዝቡ ሰላሙ እየጠበቀ ከአከባቢው በህገ ወጥ መልክ ወደ ኤርትራ የሚተላለፉት መሰረታዊ ሸቀጦችና የኢንዳስትሪ መሳሪዎች በመከላከል ረገድ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።

#ቲክቫህኢትዮጵያ #ፋፂ #ትግራይ

@tikvahethiopia