TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና‼️

በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ ካለው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እስካሁን 208 #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል።
.
.
.
በኦሮሚያና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ ላይ የህግ የበላይነትን ለማስፈን #በፀረ_ሰላም_ሀይሎች ላይ እየተወደሰ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተገለፀ።

የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የገጠር ፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ አዲሱ አረጋ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው እንዳሰፈሩት፥ በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢ ላይ የፀጥታ ችግር እንዲከሰት አድርገዋል ተብለው በቁጥጥር ስር የዋሉ ተጠርጣሪዎች ቁጥር 208 ደርሷል።

የህግ የበላይነትን ለማስፈን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ነው አቶ አዲሱ ያስታወቁት።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው ያለው ሰላም እየተሻሻለ መምጣቱንም ገልፀዋል። በቀጣይም በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም እንዲረጋገጥ በማድረግ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች እንዲመለሱ ለማድረግ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ መሆኑንም ነው አቶ አዲሱ ያስታወቁት።

ምንጭ፦ fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሙጋቤ 4 ሚሊዮን ብር ተዘረፉ‼️

ከቀድሞው የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት #ሮበርት_ሙጋቤ ላይ አራት ነጥብ ሁለት ሚሊየን ብር ሰርቀው ተሰውረዋል የተባሉ ሶስት #ተጠርጣሪዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ።

ተጠርጣሪዎቹ የሰረቁትን ገንዘብ መኪና፣ቤትና እንስሳት ለመግዛት እንዳዋሉት የተገለጸ ሲሆን የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዘመድ ደግሞ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አንዷ እንደሆነች አንድ የሃገሪቱ ጣቢያ ዘግቧል።

ዚምባ በተባለችው ገጠራማ የሃገሪቱ ክፍል የሚገኘው የቀድሞው ፕሬዝዳንት ቤት ቁልፍ በተጠርጣሪዋ እጅ በመሆኑ ዝርፊያውን ለመፈጸም ቀላል እንዳደረገላቸው ተገልጿል።

ሌሎቹ ተጠርጣሪዎች ደግሞ በቀድሞው ፕሬዝዳንት ቤት ውስጥ ከአንድ ወር በፊት በጽዳት ሰራተኝነት ተቀጥረው ይሰሩ ነበር።

ጆሃን ማፑሪሻ የተባለችው ተጠርጣሪ 20 ሺ ዶላር የሚያወጣ መኖሪያ ቤትና ተሽከርካሪ እንደገዛች የተገለፀ ሲሆን ሌላኛዋ ተጠርጣሪ ደግሞ አንድ ተሽከርካሪና ብዙ ቁጥር ያላቸው አሳማዎችና ከብቶች ገዝታለች ተብሏል።

የ94 ዓመቱ ሮበርት ሙጋቤ ባሳለፍነው ዓመት ነበር በሃገሪቱ ወታደራዊ ሃይሎች ከስልጣናች እንዲለቁ የተደረጉት። መጀመሪያ በጠቅላይ ሚኒስትርነት በመቀጠልም በፕሬዝዳንትነት ሃገሪቷን ለ37 ዓመታት መርተዋል።

ሃገሪቱ በከባድ ኢኮኖሚያዊ ችግር ውስጥ ሆና እንኳን ሮበርት ሙጋቤ እጅግ የተንደላቀቀ ህይወት ይመሩ እንደነበር ይነገራል።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት ከስልጣናቸው ከወረዱ በኋላ የመራመድ ችግር አጋጥሟቸው የነበረ ሲሆነ በሲንጋፖር የህክምና ክትትል ሲያደርጉ ነበር ተብሏል።

ሙጋቤ ስርቆቱ ሲፈጸም በቤታቸው ይኑሩ አይኑሩ የተገለጸ ነገር የለም። ተጠርጣሪዎቹ ግን በዋስ እንደተለቀቁ 'ኤኤፍፒ' ዘግቧል።

ምንጭ፦ BBC
@tsegabwoldw @tikvahethiopia
6 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ‼️

በደቡብ ጎንደር #እስቴ_ወረዳ ላይ ከሁለት መስጅዶች ቃጠሎ ጋር በተያያዘ #እጃቸው አለበት የተባሉ 6 #ተጠርጣሪዎች በአማራ ክልል ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከ250,000 ብር በላይ ድጋፍ ተደርገ🔝

በባህርዳርና በደብረ ታቦር የሚኖሩ የአስቴ ወረዳ ነዋሪዎች በቅርቡ የተቃጠሉትን ሁለት መስጅዶች ለመስራት የሚያስችል ሩብ ሚሊዮን ብርና #የሲሚንቶ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ተወላጆቹ በራሳቸው ተነሳችነት ብሩን ከመሰብሰብ ባለፈ ቦታው ደረስ በመሄድ የጎዳቱን ሁኔታ በመመልከት የአለኝታነት ድጋፋቸውን እንዳሳዩ የአማራ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ መላኩ አላምረው ለኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን
በዛሬው ዕለት ገልጸዋል፡፡

ተወላጆቹ ለመስጅዶች ግንባታ አስተባባሪ ኮሚቴ ካስረከቡት 250 ሺህ ብር በተጨማሪም ለግንባታው የሚውል 100 ኩንታል ሲሚንቶ አበርክተዋል፡፡

ተወላጆቹ ድርጊቱን አውግዘው ምንም ዓይነት እኩይ ዓላማ ያለው አካል ትንኮሳ #ቢፈፅም የሁለቱ እምነት ተከታዮች አንድነት የበለጠ ይጠናከራል እንጂ ምንም ዓይነት የሚፈጠር ነገር የለም ብለዋል፡፡

ድጋፉን ያሰባሰቡት የሁለቱም እምነት ተከታይ የወረዳዋ ተወላጆች አጥፊዎቹ ታድነው ተገቢው ቅጣት እንዲሰጣቸውም በድጋፍ ርክክቡ ወቅት ጠይቀዋል፡፡

አጥፊዎችን ለመለየት ከተያዙት 6 #ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ምርመራው #ተጠናክሮ መቀጠሉንም አቶ መላኩ ገልጸዋል፡፡ የተቃጠሉት መስጅዶች ግንባታ በፍጥነት እንደሚጀመር ተመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ መልኩ በደቡብ ጎንደር አንዳቤት ወረዳ ላይ የተቃጠለውን የጃራ ገዶ መስጅድ የአካባቢው ማህበረሰብ 27 ሺህ ብር በማዋጣት መልሶ የመስራት ሂደቱን እንደጀመረ የክልሉ መንግስት ኮሚኒኬሽን ለኢቢሲ አመልክቷል፡፡

ምንጭ፦ ebc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፌደራል ፖሊስ~ድሬዳዋ ቅርንጫፍ‼️

በሕገ-ወጥ መንገድ ከድሬዳዋ ተጭኖ ወደ ሐርጌሌ ሊጓጓዝ የነበረ ነዳጅና አምስት #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የፌዴራል ፖሊስ የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

የጽህፈት ቤቱ የወንጀል ምርመራ ባለሙያ አቶ #ሞገስ_አያሌው ለኢዜአ እንዳመለከቱት ከከተማው ሊወጣ ሲል የተያዘው 20ሺህ ሊትር ናፍጣ፣ 16 ጀሪካን የሞተር ዘይትና በድርጊቱ የተጠረጠሩት ግለሰቦች ናቸው፡፡ በተለይ ነዳጁ የተያዘው በአንድ የጭነት መኪና ከነተሳቢው በጄሪካን ተጭኖ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ነዳጁን በከተማው ከሚገኝ አንድ ነዳጅ ማደያ ገዝተው ሊያጓጓዙ የነበሩት ግለሰብና ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው የተባሉ አራት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን ገልጸዋል፡፡ ለግለሰቡ  ከፍተኛ መጠን ያለው ነዳጅ መሰጠቱ አግባብ  አለመሆኑን ያስረዱት ባለሙያው፣ በሕገ-ወጥ መንገድ ነዳጅን ጥቅም ላይ ለማዋል የሚከናወነውን እንቅስቃሴ በተቀናጀ መንገድ ለመከላከል እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ኅብረተሰቡ ማንኛውንም ሕገ-ወጥ ተግባር ለፖሊስ በማሳወቅ ትብብሩን እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡

ነዳጁ በቁጥጥር ሥር እንዲውል ጥቆማ ከሰጡት አንዱ ለኢ ዜ አ  እንዳስታወቁት በከተማዋ #የነዳጅ_እጥረት የሚከሰተው በሕገ ወጥ መንገድ በሚካሄደው ንግድ ነው፡፡ ”የቤንዚኑ ችግር ሳይፈታ ናፍጣ ቢወደድ ሌላ ችግር ስለሚፈጥር ጉዳዩን ጠርጥረን ለፖሊስ አሳውቀናል። ትብብራችንም ይቀጥላል”ብሏል፡፡

#ሐርጌሌ በሶማሌ ክልል ከድሬዳዋ በአንድ ሺህ ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ከተማ ናት። የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ከሁለት ወራት በፊት በተመሳሳይ መንገድ ሊጓዝ የነበረ ነዳጅ በቁጥጥር ሥር ማዋሉ ይታወሳል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቴፒ ግጭት ጋር በተያያዘ #ተጠርጣሪዎች እየታሰሩ ነው‼️
.
.
ማሻና አንድራቻ 12፣ ቴፒና የኪ ላይ ደግሞ 17 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰማ። እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ዋሉት በአካባቢው ለተፈጠረው አለመረጋጋት የተለያየ አስተዋፅኦ አድርገዋል በሚል መሆኑን የዞኑ የኮሙኑኬሽን ባለሙያ ለቢቢሲ አስረድተዋል።

ካለፈው ዓመት ነሐሴ 7 ጀምሮ በሸካ ዞን ውስጥ የሚገኙት ወረዳዎች ማሻ፣ አንድራቻ፣ ቴፒና የኪ ችግር ውስጥ መሆናቸውን የአካባቢው አስተዳደሮችም ሆኑ ነዋሪዎች የሚናገሩት ነው።

በዚህም የተነሳ ከፌደራልና ከክልል መንግሥት የተውጣጡ አካላት ከዞን አስተዳደር ጋር በመሆን ኮማንድ ፖስት ተቋቋሙ አካባቢውን ለማረጋጋት እየሠሩ እንደሆነ የዞኑ ኮሙኑኬሽን ባለሞያ አቶ አስማማው ኃይሉ ይናገራሉ።

በነበረው ብሔር ተኮር ግጭትና አለመረጋጋት 'ከስድስት ሺህ በላይ የተፈናቀሉ ሰዎች በቴፒ ከተማ አዳራሽ ይገኛሉ' የሚሉት ደግሞ በአካባቢው ሰላም ለማምጣት ታስቦ የተቋቋመው ኮሚቴ አባል የሆኑት አቶ መንገሻ አዲስ ናቸው።

የእነዚህን ተፈናቃዮች ጉዳይና ሌሎች የሕግ ጥሰቶችን ለከፍተኛ የመንግሥት አካላት እንዲሁም ለፌደራልና ለክልል መንግሥታት ቢሮዎች አቤት በማለታችን ማዘዣ ወጥቶብን እየታደንን ነው ይላሉ አቶ መንገሻ።

"የዞኑን ሸፍጥ የሚያጋልጡ ሰዎች ፍትኃዊ ባልሆነ መልኩ እየታሰሩ ነው" በማለትም ደረሰ ያለውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ነዋሪነታቸው አዲስ አበባ የሆነውና የአካባቢው ተወላጅ የሆኑት አቶ ስንታየሁ ወዳጆ ለስራ ጠዋት ከሚኖሩበት አካባቢ ወጥተው በሞተራቸው ሲንቀሳቀሱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሸካ ዞን ከመጡና ማዘዣ ከያዙ የፖሊስ አባላት ጋር በመሆን በቁጥጥር ስር እንዳዋሏቸውም ባለቤታቸው ከድጃ ሰይድ ነግረውናል።

ባለቤታቸው እንደሚናገሩት አቶ ስንታየሁ ኑሯቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ ስምንት ዓመት ተቆጥሯል። ነገር ግን በሸካ ዞን አንዳንድ አካባቢዎች የሚታዩትን የሕግ ጥሰቶች ለተለያዩ የፌደራል መንግሥት ቢሮዎች አቤቱታ በማስገባት የክልሉን ሰዎች ይረዱ እንደነበር አልሸሸጉም።

"ለቀይ መስቀል ስለተፈናቀሉ ሰዎች ጉዳይ መረጃ በመስጠት፣ ያለውን የሰብዓዊ መብት ጥሰት ለሚመለከታቸው አካላት በማድረስ የአካባቢውን ተወላጆች ይረዳ ነበር" ሲሉም ተናግረዋል።

አቶ ስንታየሁ የታሰሩት ወንጀሉ ተፈፀመ ከተባለበት ሥፍራ ከ90 ኪሎ ሜትር በላይ ርቆ ነው የሚሉት ወ/ሮ ከድጃ የታሰሩበት ስፍራ ከአዲስ አበባ ደግሞ 900 ኪሎ ሜትር ያህል ርቆ እንደሚገኝና ቤተሰብም ሊጠይቃቸው የሚችልበት ሁኔታ እንደሌለ ባለቤታቸው ለቢቢሲ አስረድተዋል።

አቶ መንገሻ አዲስ እንደተገሩት ከሆነ የሰላም ኮሚቴው ፀሐፊ የሆኑት አቶ ሸዋ ቱቻም ለተለያዩ የመንግሥት አካላት የቴፒን ጉዳይና ያለውን ኢፍትሀዊነት ስለሚያሰሙ በዞኑና በወረዳው የሚፈጠረውን ኢ- ፍትሃዊነት #ስለሚቃወሙ በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

የሸካ ዞን ኮሙኑኬሽን የሆኑት አቶ #አስማማው_ኃይሉ እነዚህ ግለሰቦች በዞኑ ውስጥ ችግር በመፍጠር የተያዙ መሆኑን ጠቅሰው የተያዙት መረጃ ተሰባስቦባቸው ጥፋት መሥራታቸው ተረጋግጦ ነው ይላሉ።

በዞኑ የተነሳው የመዋቅር ጥያቄ መሆኑን ያሰታወሱት አቶ አስማማው "የመዋቅር ጥያቄ የሚፈታው የመንግሥትን መዋቀር ተከትሎ ነው" በማለት፣ ንብረት እየወደመ፤ ብሔር ተኮር ጥቃት እያደረሱ፤ የሰው ሕይወት እየጠፋ የመዋቅር ጥያቄ የለም የሚለው የኮማንድ ፖስቱ ግምገማ እንደሆነ አብራርተዋል።

"እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር የዋሉት ማስረጃ ተገኝቶባቸው፤ ምስክር ተቆጥሮባቸው ነው" የሚሉት አቶ አስማማው እስካሁን ድረስ 29 ሰዎች በሕግ ጥላ ሥር ሆነው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

በቴፒ ከተማ ጥር 22/2011 ዓ.ም በተነሳ ግጭት ሰባት ሰዎች መሞታቸውን የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ የሽዋስ አለሙ ለቢቢሲ መግለፃቸው ይታወሳል።

በወቅቱ በግጭቱ 100 የሚጠጉ ቤቶች ሲቃጠሉ፤ 1500 ሰዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለው ነበር። በአጠቃላይ በዞኑ ለሚገኙ ተፈናቃዮቹ እየተደረገ ስላለው ድጋፍ BBC ለማወቅ ያደረግነው ጥረት በጉዳዮ ላይ ምላሽ የሚሰጥ አካል ባለመገኘቱ አልተሳካም።

ምንጭ፦ BBC አማርኛ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰኔ 15 ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌን አጓጉዤያችኋለሁ ያሉ ምስክር ቃላቸውን ሰጡ!

የሰኔ 15ቱን የባህር ዳር ጥቃት #ተጠርጣሪዎች ጉዳይ የሚመለከተው ፍርድ ቤት ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት ብርጋዴየር ጄነራል አሳምነው ጽጌን ወደ ጎንደር መስመር አጓጉዤያቸዋለሁ ያሉ ሹፌርን የምስክርነት ቃል አደመጠ። በጥይት ቆስለው ሆስፒታል የሚገኙት ሹፌሩ ፍርድ ቤት የቀረቡት በተሽከርካሪ ወንበር ነው።

የሹፌሩን የምክርነት ቃል ዛሬ ረፋዱን በነበረው ችሎት ያደመጠው በእነ ብርጋዴየር ጄነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተጠረጠሩ 48 ሰዎችን ቅድመ ክስ እየተመለከተ የሚገኘው የባህር ዳር እና አካባቢው ፍርድ ቤት ነው። ፍርድ ቤቱ የአማራ ክልል አቃቤ ህግ አሉኝ ያላቸውን 17 ምስክሮችን ለማድመጥ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በችሎት የቀረቡት ሁለቱ ብቻ ናቸው። 

ሁለቱም ምስክሮች የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች ባለስልጣናት በባህር ዳር በተገደሉበት ዕለት መኪና የማሽከርከር የስራ ስምሪት እንደተሰጣቸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። በሰኔ 15 ብርጋዴየር ጄነራል አሳምነውን በመኪናቸው ማጓጓዛቸውን የተናገሩት አንደኛው ሹፌር ከዚያ አስቀድሞ ወታደሮችን ከቦታ ቦታ ሲያዘዋውሩ እንደነበር ተናግረዋል።

#DW

ይህን ይጫኑና ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-27-4
የኦሮሚያ ክልል በርካታ ሰዎች መታሰራቸውን አመነ!

‹‹ፓርቲዎችን ኢላማ ያደረገ እስር የለም፣ ሁሉም እየተነሳ የፓርቲዬ አባል ታስሯል እያለ የሚያወራው ለፖለቲካ ጥቅም ነው›› አቶ ታዬ ደንደአ

አገርን ለማረጋጋት በሚደረጉ ጥረቶች #ተጠርጣሪዎች ተይዘው ለምርመራ መቅረባቸው እንደ አዲስ ነገር መታየት የለበትም ያሉት አቶ ታዬ ደንደአ፣ የክልሉ መንግሥስት ፓርቲዎቹን ለማጥቃት ያደረገው ዘመቻ ቢሆን ኖሮ የራሱን ከፍተኛ አመራሮች ባላሰረ ነበር ብለዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ

ተጨማሪ ያንብቡ
https://telegra.ph/ETH-09-18
TIKVAH-ETHIOPIA
እፀገነት አንተነህ⬆️ "የ27 አመቷ የአየር መንገድ ሒሳብ ሰራተኛ እፀገነት አንተነህ ትናንት ማክሰኞ ጠዋት ወደ ሰራ በምታመራበት ወቅት #ጭካኔ በተሞላበት ወንጀል አቃቂ መንገድ ላይ ተገድላ ተጥላ ተገኘች። ፓሊስ ምርመራ ላይ ነው። ቀብሯ ዛሬ ተፈፅሟል። ቀለበት አድርጋ ሰርግ ለመደገስ ዝግጅት ላይ ነበረች።" ጋዜጠኛ ተስፋዬ ጌትነት/#CAPITAL/ @tsegabwolde @tikvahethiopia

እፀገነትን የገደሉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የነበረችውን ወ/ሮ እፀገነት አንተነህን የገደሉ ሦስት #ተጠርጣሪዎች መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ ወ/ሮ እፀገነት አንተነህ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓ.ም በግምት ከጠዋቱ 12 ሰዓት 30 አቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ወደ ስራ ለመሄድ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ሦስቱ ተጠርጣሪዎች ወንጀል ለመፈፀም አቅደው የትራንስፖረት አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል ሟችን በባጃጅ ተሽከርካሪ ከሳፈሯት በኋላ አንቀው እንደገደሏት ተጠርጥረዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የሟችን አስክሬን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ አካባቢ መንገድ ላይ ጥለዋት እንደተሰወሩ ነው ፓሊስ የገለፀው፡፡ ወንጀሉን የፈፀሙ ግለሰቦች አለመታወቁ የፖሊስን ስራ እጅግ አስቸጋሪ ቢያደርገውም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀሉ ከተፈፀመ ጀምሮ ቀንና ሌሊት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ሦስቱን ተጠርጣሪዎች በዘጠነኛው ቀን በትናትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ በርካታ የአካባቢው ሰዎችና የሟች ቤተሰቦች በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2012 ዓ/ም ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙት መርተው አሳይተዋል፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ፒያሳ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መያዙን አስታውሷል፡፡ ህብረተሰቡም ወንጀለኞችን አጋልጦ በመስጠት እና ምስክር በመሆን እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አድንቆ ይህንኑን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዲስ አበባ ፖሊስ እነዚህን #ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ለማዋል ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከፍተኛ ክትትል እንዳደረገና፤ ሦስቱን ወንጀል ፈፃሚዎች ወንጀሉን በፈፀሙ በዘጠነኛው ቀን መስከረም 15 ቀን 2012 ዓ/ም በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia