ሰኔ 15 ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌን አጓጉዤያችኋለሁ ያሉ ምስክር ቃላቸውን ሰጡ!

የሰኔ 15ቱን የባህር ዳር ጥቃት #ተጠርጣሪዎች ጉዳይ የሚመለከተው ፍርድ ቤት ጥቃቱ በተፈጸመበት ዕለት ብርጋዴየር ጄነራል አሳምነው ጽጌን ወደ ጎንደር መስመር አጓጉዤያቸዋለሁ ያሉ ሹፌርን የምስክርነት ቃል አደመጠ። በጥይት ቆስለው ሆስፒታል የሚገኙት ሹፌሩ ፍርድ ቤት የቀረቡት በተሽከርካሪ ወንበር ነው።

የሹፌሩን የምክርነት ቃል ዛሬ ረፋዱን በነበረው ችሎት ያደመጠው በእነ ብርጋዴየር ጄነራል ተፈራ ማሞ መዝገብ የተጠረጠሩ 48 ሰዎችን ቅድመ ክስ እየተመለከተ የሚገኘው የባህር ዳር እና አካባቢው ፍርድ ቤት ነው። ፍርድ ቤቱ የአማራ ክልል አቃቤ ህግ አሉኝ ያላቸውን 17 ምስክሮችን ለማድመጥ ቀጠሮ ይዞ የነበረ ቢሆንም ዛሬ በችሎት የቀረቡት ሁለቱ ብቻ ናቸው። 

ሁለቱም ምስክሮች የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና ሌሎች ባለስልጣናት በባህር ዳር በተገደሉበት ዕለት መኪና የማሽከርከር የስራ ስምሪት እንደተሰጣቸው ለፍርድ ቤቱ ገልጸዋል። በሰኔ 15 ብርጋዴየር ጄነራል አሳምነውን በመኪናቸው ማጓጓዛቸውን የተናገሩት አንደኛው ሹፌር ከዚያ አስቀድሞ ወታደሮችን ከቦታ ቦታ ሲያዘዋውሩ እንደነበር ተናግረዋል።

#DW

ይህን ይጫኑና ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-27-4