TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት መቼ ይገለጻል?

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ የትምህርት ሚኒስቴርን ጠይቀናል።

ሚኒስቴሩ በተለያዩ ምክንያቶች ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመስጠት ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ሰምተናል።

አጠቃላይ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ውጤት ከሁለተኛ ዙር ፈተና በኋላ የሚገለጽ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

More : @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
ፎቶ፦ በአፍሪካ ህብረት/AU መሪነት የተካሄደውን የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ስምምነትን የመሩት ፤ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንትና በአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን አባሳንጆ የተመራ ልዑክ ዛሬ መቐለ ገብቷል።

Photo Credit : ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት አድርጉ " - የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ

በተለያየ ምክንያት የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን በታህሳስ ወር መጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርይ መምሪያ አሳውቋል።

ትምህርት መምሪያው ፦

- በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በመሸጋገሪያ ድልድይ ተሰብሮ በደረሰው አደጋ ምክንያት የመጀመሪያውን ቀን ፈተና ያልተፈተኑ፤

- በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ፤

- የተለያየ ማህበራዊ ችግር አጋጥሟቸው ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል አሳውቀው ለፈተና ያልተቀመመጡ ፤

- በሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ፤ " ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች በታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም በመጀሪያ ሳምንት አከባቢ ፈተናው ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው " ያለ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አውቀው ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

" ሀይድሮሴፋለስ እና ስፓይና ቢፊዳ / የነርቭ ዘንግ " ክፍተት በጽንስ ላይ በቅድመ ወሊድ ወቅት ሊከሰቱ የሚችሉ ለህይወት አስጊ የጤና እክሎች ናቸው፡፡

የነርቭ ዘንግ ክፍተት ተጠቂ በሆኑ ላይ የመንቀሳቀስ ዕክል፣ የስሜት ማጣት፣ ሽንትና ሰገራ የመቆጣጠር ችግሮች እና ትምህርት/ነገሮችን የመረዳት ዕክልን ያስከትላል፡፡

በዚህም መሰረት ለነረቭ ዘንግ ክፍተት ተጠቂዎች የሚያስፈልገውን ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ ለማድረግ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል፡፡

ትላንት የጤና ሚኒስቴር ከሆፕ ኤስ. ቢ. ኤች. ጋር በመተባበር በአለም አቀፍ ፌዴሬሽን በተወሰነው መሰረት “ድምፃችንን ከፍ እናድርግ” በሚል መሪ ቃል የስፓይና ቢፊዳ እና ሃይድሮሴፋለስ ቀን በሃገር አቀፍ ደረጃ አክብሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ፦ በአፍሪካ ህብረት/AU መሪነት የተካሄደውን የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የሰላም ስምምነትን የመሩት ፤ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንትና በአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን አባሳንጆ የተመራ ልዑክ ዛሬ መቐለ ገብቷል። Photo Credit : ትግራይ ቴሌቪዥን @tikvahethiopia
#Update

" በሁለት ሶስት ቀን ውስጥ ሽረ ላይ ስብሰባ ይደረጋል ፤ በአንዳንድ ቴክኒካል ጉዳዮች ዘሪያ የሁለቱም ጦር ተወካዮች ተገናኝተው ይወያያሉ "

ትላንት በኢትዮጵያ መንግስት እና በህወሓት መካከል የተካሄደውን የሰላም ድርድር / ስምምነቱን የመሩት የቀድሞው የናይጄሪያው ፕሬዜዳንት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ የትግራይ መዲና ፤ #መቐለ መግባታቸው ይታወሳል።

ኦባሳንጆ ወደ መቐለ ያመሩት የቀድሞ የደቡብ አፍሪካ ምክትል ፕሬዜዳንት ፑምዝሎ ማላምቦ፣ የአፍሪካ ህብረት የፖለቲካ ጉዳዮች የፀጥታ እና የሰላም ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሊ አዱዬ ከያዘ ልዑክ ጋር ነበር።

በመቐለ ከሃይማኖት አባቶች ጋር እንዲሁም ክልሉን እያስተዳደሩ ካሉት አካላት ጋር ምክክር አድርገውም ነበር።

በምክክሩን ምን ተነሳ ? ምን ተባለ ?

(ከሃይማኖት አባቶች ጋር በነበረ ውይይት/ የሃይማኖት አባቶች የተናገሩት)

- የትግራይ ህዝብ የሰብዓዊ እርዳታ / መድሃኒት በፍጥነት ማግኘት ባለመቻሉ ለከፍተኛ አደጋ መጋለጡን ገልፀዋል።

- የኤርትራ ኃይሎች በያዟቸው ቦታዎች ከፍተኛ ግፍ እየተፈፀመ መሆኑን አስረድተዋል።

(ልዑካን ቡድኑ)

- አፋጣኝ ሰብዓዊ እርዳታ እንዲገባ የውጭ ኃይሎችም እንዲወጡ ከመንግስት ጋር መነጋገራቸውን ገልፀዋል።

ክልሉን እያስተዳደሩት ካሉት ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮች ጋር በተደረገው ውይይት ወቅት ስለተነሱት ሃሳቦች አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው የተናገሩት ፦

- የልዑካን ቡድኑ የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ አፈፃፀሙ ምን እንደሚመስል ለመመልከት ፤ ለስምምነቱ ተግባራዊነት መስጠት የሚችሉት ድጋፍ  ይኖር እንደሆነና ድጋፍ ለመስጠት ነው መቐለ የገቡት።

- ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካሄል እስካሁን ስምምነቱን ለማስፈፀም እየተሰሩ ስላሉት ስራዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

- ስምምነቱ ትልቅ ስምምነት መሆኑንና በሁሉም ትብብር ሊፈፀም የሚገባው በመሆኑ ባለፉት ሁለት ሳምንታት አጠቃላይ ህዝቡ የመንግስት ፣ የድርጅት አመራሮች፣ ሰራተኞች፣ ከላይ እስከታች ያሉ ወታደራዊ አካላት እንዲወያዩበትና መግባባት ላይ እንዲደረስ የተሰራ ሲሆን አጠቃላይ ህዝቡ ስምምነቱን መቀበሉን ዶ/ር ደብረፅዮን ተናግረዋል።

- ዶ/ር ደብረፅዮን  ፤ ለልዑካን ቡድኑ ህዝቡ በሰላም ስምምነቱ ላይ መስማማቱን አስረድተዋል።

- ስምምነቱ ጥሩ ነው ግን እርዳታ በብዛት ከማስጋባት እና ከአገልግሎት መጀመር ጋር በተያያዘ ከሚፈለገው ፍጥነት አንፃር እየሄደ አይደለም ፤ አገልግሎት ለማስጀመር እየታዩ ያሉት ምልክቶች ጥሩ ናቸው ግን ካለው ችግር አንፃር ፍጥነት ያንሰዋል የሚል ነገር ተነስቷል።

- ስምምነቱ ሰፊ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ስምምነቱን የማስፈፀሚያ ፕላን መሰራቱ ተብራርቷል።

- " በተደረገው የሰላም ስምምነት የስምምነቱ ፈራሚ ያልሆኑ አካላት አሉ ፤ ፈራሚ አለመሆን ብቻ ሳይሆን ስምምነቱ እንዲደናቀፍ የሚፈልጉ ኃይሎች አሉ ዋናው የኤርትራ መንግስት ነው ፤ የኤርትራ መንግስት እኛ ኢትዮጵያውያን የቤታችንን ጉዳይ ለማስተካከል የተስማማነውን ስምምነት ለማፍረስ እየናካካን ነው ፤ ጦርነቱ ድጋሚ እንዲጫር ለማድረግ ወንጀል እየሰራ ነው ፤ በሺዎች እያለቁ ስለመሆኑ ብዙ ማስረጃ አለን እሱን ማስረጃ ለልዑካኑ ተናግረናል " ሲሉ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ተናግረዋል።

- "አሁን ላይ ሰራዊቱ መካከል በጣም ተስፋ የሚሰጥ ግኝኑነት ነው እየተፈጠረ ያለው ፤ ይሄ ቀረ ሊባልበት በማይችል ሁኔታ ሰራዊቱ ተግባብቶ እየሰራ ነው። በሁለት ሶስት ቀን ውስጥ ሽሬ ላይ ስብሰባ ይደረጋል በአንዳንድ ቴክኒካል ጉዳዮች ዘሪያ የሁለቱም ጦር ተወካዮች ተገናኝተው ይወያያሉ። " ሲሉ አምባሳደር ወንድሙ ተናግረዋል።

- " አሁን ላይ ችግር እየሆነ ያለው የኤርትራ ሰራዊት ነው ፤ የሰላም አጋጣሚውን ለማፍረስ ፤ እኛም ደግሞ በቁጣ ተነሳስተን ጦርነት እንድንገባ ህዝቡን እየፈጀ ነው ፤ ስለዚህ አንደኛ የኢትዮጵያ መንግስት ኃላፊነት አለበት ፤ ሁለተኛ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ኃላፊነት አለበት እየተፈፀመ ያለው ወንጀል ዓለም አቀፍ ነው ፤ ስምምነቱ የተፈረመው በዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምስክርነት ነው ኃላፊነት አለባችሁና አስቁሙልን ብለናቸዋል። ጦርነቱን እዚህ ያደረሰው ይኸው ኃይል ነው፤ እንዳይቆምም እየሰራ ነው ስለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት እኛ ሁላችንም ኢትዮጵያውያን እና የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይሄን ወንጀል ለማስቆም ጥረት ማድረግ አለብን ብለን ገልፀንላቸዋል " ሲሉ አምባሳደር ወንድሙ አሳምነው ለክልሉ የመገናኛ ብዙሃን ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
#UN

እ.ኤ.አ. ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሰብአዊ ድጋፍ አጋሮች አማካኝነት ከ17,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የእርዳታ እህል ትግራይ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዛሬ አሳውቋል።

ድርጅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ተጨማሪ በግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለመድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UN እ.ኤ.አ. ከህዳር አጋማሽ ጀምሮ በኢትዮጵያ መንግስት እና በሰብአዊ ድጋፍ አጋሮች አማካኝነት ከ17,000 ሜትሪክ ቶን በላይ የእርዳታ እህል ትግራይ መድረሱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ዛሬ አሳውቋል። ድርጅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል ተጨማሪ በግጭት የተጎዱ ወገኖችን ለመድረስ ጥረት እየተደረገ መሆኑን አሳውቋል። @tikvahethiopia
#WFP

ከሰላም ስምምነቱ በኃላ...

(የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) የዛሬ ሪፖርት)

- የዓለም ምግብ ፕሮግራም #አራቱም የተከፈቱትን የመንገድ ኮሪደሮች በመጠቀም ስራ ከጀመረበት እኤአ ከህዳር 15 ጀምሮ በ96 የጭነት መኪናዎች 170 ሺህ ሰዎችን ሊመግብ የሚችል ከ2,400 ሜትሪክ ቶን በላይ ምግብ እንዲሁም 100,000 ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ አጓጉዟል።

- በWFP የሚመራው የሎጂስቲክስ ክላስተር 250 ሜትሪክ ቶን የሰብአዊ ድጋፍ ካርጎ ከጎንደር፣ ኮምቦልቻ እና ሰመራ ለስምንት ተባባሪ አጋሮች የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ በአየር እንዲጓጓዝ አመቻችቷል።

- ካለፈው እኤአ ነሃሴ ወር መጫረሻ በኃላ የWFP የUNHAS የመንገደኞች በረራ ዛሬ ወደ #መቐለ አድርጓል። በረራውን ደረገው ከፌዴራል ፍቃድ ካገኘ በኃላ ሲሆን ወደ መቐለ መደበኛ የUNHAS በረራ መቀጠል አለበት ብሏል።

- WFP ፤ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ እና ደቡብ ዞኖች ለሚገኙ ወረዳዎች በአማራ በኩል አዲስ የሰብአዊ ድጋፍ አገልግሎት ቢያገኙም ወደ አንዳንድ የትግራይ #ምስራቃዊ እና #ማዕከላዊ ዞኖች አሁንም መግባት ውስን መሆኑንና እስከ 170 ሺህ የሚደርሱ እናቶችና ህፃናት የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው WFP አሳውቋል።

- ወደ ትግራይ የሚያስገቡ መንገዶች ከተከፈቱ ወዲህ WFP በሰሜን ምእራብ ዞን ማይ ፀብሪ እና በደቡብ ዞን አላማጣ ላሉ ከ100,000 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች እህል ማቅረቡን ገልጿል። በህዳር ወር መጀመሪያ ላይም በመቐለ 540,000 ሰዎችን ደርሷል። ከህዳር ወር መጀመሪያ ጀምሮ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ፤ በትግራይ ክልል የምግብ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው 2.1 ሚሊዮን ሰዎች ውስጥ መድረስ የቻለው 29 በመቶውን መሆኑን ገልጿል።

ተጨማሪ ያንብቡ : https://telegra.ph/WFP-11-25

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በከፊል ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆን መንገድ !

ከዛሬ ቅዳሜ ጀምሮ ከ10 እስከ 15 ለሚሆኑ ቀናቶች ከሱሉልታ ኬላ ጀምሮ እስከ ድልበር የመንገድ ማሻሻያ ስራ ስለሚከናወን ከኬላ ወደ ድልበር የሚወስደዉ መንገድ ብቻ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆን የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ኤጀንሲ አሳውቋል።

ኤጀንሲው ፤ አሽከርካሪዎች ከሱልልታ ወደ አዲስ አበባ ሲመጡ በአማራጭ መንገድ ከኬላ ወደ ግራ በመታጠፍ ወደ እንጦጦ ፓርክ በሚያስኬደዉ መንገድ በመጠቀም በእንጦጦ ኪዳነ ምህረት በማድረግ ሽሮ ሜዳ መግባት የሚችሉ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
ሀሰተኛው ዶክተር ?

ዛሬ ከአዊ ብሔረሰብ ዞን ፍትሕ መምሪያ በወጣ መረጃ ፤ አንድ በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ዶክተር ነኝ ብሎ ሲሰራ የነበረ ግለሠብ በፅኑ እስራት እና በገንዘብ እንዲቀጣ መደረጉን ይገልፃል።

እንደ መምሪያው መረጃ፤ የጃዊ ሆስፒታል ቅጥር ሰራተኛ ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ጌትነት ወንድአወቅ የተባለ ተከሳሽ በድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ሳይማር #በሜዲስን የዶክትሬት ዲግሪ እንደተማረ በማስመሰል በሀሰት በተዘጋጀ የዶክትሬት ሰርቲፊኬት የትምህርት ማስረጃ ያቀርባል።

ግለሰቡ በአብክመ ጤና ቢሮ ከ4/2/2014 - 4/2/2019 የሚያገለግል የሚል የሀሰት የሙያ ፈቃድ በመያዝ በአብክመ ጤና ቢሮ ሥር ባሉት ሆስፒታሎች በማችንግ ፈንድ ኘሮግራም የቋሚ ቅጥር ማስታወቂያ ተወዳድሮ 50% በማምጣት በደረጃ 14 ብር 9056 እየተከፈለው ሲሰራ እንደነበር ይገልፃል።

እዚህ ጋር በሀሰተኛ የትምህርት ማስረጃ ዶክተር ነኝ ያለው ግለሰብ እንዴት የተሰጠውን ፈተና 50% ሊያልፍ እንደቻለ የተባለ ነገር የለም።

ግለሰቡ፤ በህክምና የእውቀት ችግር ምክንያት በተፈጠረ ስህተት አንዲት የ7 ወር ህፃን እና አንዲት የ25 ዓመት ወጣት ለሞት መዳረጉ ተመላክቷል።

በፈፀመው የሙስና ወንጀል መንግሥታዊ ወይም ህዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሀሰት መለወጥ / በሀሰተኛ ሰነድ መገልገል ሙስና ወንጀል በዐ/ህግ ክስ ቀርቦበት በ11 ዓመት ጽኑ እስራትና በብር 5 ሺህ መቀጣቱ ተገልጿል።

ከላይ አንድ ደብዳቤ የተያያዘ ሲሆን ደብዳቤው ግለሰቡ እድሜው 35 መሆኑና የትምህርት ደረጃውም 12+4 መሆኑን ይገልፃል ፤ እንዴት ከሳች ግለሰቡን " ዶክተር " ብሎ ይጠራዋል ? እንዴት ፈተናውን ሊያልፍ ቻለ ? ግለሰቡ ይሄን ያህል ርቀት ሲጓዝ ከጀርባው ማን ነበር ? የሚሉ ጥያቄዎችን ያስነሳል።

@tikvahethiopia
#Passport

ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ አስቸኳይ ፓስፖርት እንዲያገኙ ሊደረግ ነው።

የኢሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን በማንሳት፣ ክፍያ የፈጸሙ ተገልጋዮች ሁሉ በአስቸኳይ እንዲያገኙ ለማድረግ በዝግጅት ላይ መሆኑን ማስታወቁን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል።

ቅድመ ሁኔታዎች ሲነሱ አሁኑ ላይ አስቸኳይ ፓስፖርት ለማግኘት ተገልጋዮች ማቅረብ ሚጠበቅባቸውን የሕክምና ደብዳቤ ፣ ነፃ የትምህርት ዕድል ማስረጃ... የመሳሰሉትን ማቅረብ አይጠበቅባቸውም፡፡

በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት በፀደቀው የአገልግሎት ክፍያ ተመን ላይ ፓስፖርት በአንድና በአምስት ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት የተቀመጠውን ክፍያ " መክፈል የቻለ ሁሉ " ፣ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንደሚሆን የኢሚግሬሽን ዜግነት አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምሩ ግንበቶ መናገራቸውን ሪፖርተር ገልጿል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

- #በአስቸኳይ_ፓስፖርት ለማግኘት የተቀመጡትን ቅድመ ሁኔታዎችን ለማንሳት ዝግጅት እየተደረገ ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጡ ከሙስናና ከብልሹ አሠራር ጋር የተያያዘ በመሆኑ ነው፡፡

- " አስቸኳይ ፓስፖርት ከውስጥ ሠራተኞች ተነጋግረን እናስጨርሳለን " የሚሉ ደላሎች አሉ ከብልሹ አሠራሮች ጋር በተያያዘ ፣ በዓመት ግፋ ቢል ከ50 ሰዎች በላይ እያባረርን ነው። ከአስቸኳይ ፓስፖርት አሰጣጥ ጋር የተያያዙ ችግሮችን ሥር ነቀል በሆነ መንገድ ለመፍታት ያስችላል ተብሎ የታሰበው መፍትሔ አገልግሎቱን ለማግኘት የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን ማንሳት ነው።

- አሁን ባለው አሠራር ፓስፖርት በአስቸኳይ ለማግኘት ከሚያስችሉ ማስረጃዎች መካከል ፦

• ወደ ውጭ ሄደው መታከም እንዳለባቸው የሚገልጽ የሕክምና ደብዳቤ ፣
• ለሁለተኛ ዲግሪና ከዚያ በላይ የሆነ የትምህርት ዕድል ማግኘትን የሚገልጽ ደብዳቤ
• የዲቪ ሎተሪ ዕድል ማግኘትን የሚያሳይ ማስረጃ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች ተነስተው ሥራ ሲያስጀምር ደንበኞች የሚስተናገዱት በአዲሱ የክፍያ ተመን ይሆናል።

- ቅድመ ሁኔታዎችን አንስቶ አገልግሎቱን ለመጀመር ጥናት ተጠንቷል፤ ይህንን አገልግሎት ለማስጀመር የፓስፖርት ወረቀት ፣ ላምኔት ፣ የማተሚያ ቀለም እና የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ መለዋወጫዎችን ... የመሳሰሉ ግብዓቶች መሟላት እንዳለባቸው በጥናቱ ታይቷል።

የሚግሬሸንና ዜግነት አገልግሎት የኦንላይን ፓስፖርት ቡድን መሪ አቶ ዳንኤል የሻነው ለሪፖርተር የሰጡት ቃል ፦

• በአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ የአስቸኳይ ፓስፖርት የሚሰጥባቸው መስኮቶች ሁለት ናቸው የአስቸኳይ ፓስፖርት አገልግሎትን ያለገደብ ለማስጀመር እንዲቻል ቢያንስ ስድስት መስኮቶች መኖር አለባቸው።

• አገልገሎቱን ለማስጀመር ሚያስፈልጉ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተጀምሯል ፤ ምን ያህል ብር እንደሚጠይቅም አዘጋጅተን ለሚመለከተው ክፍል አቅርበናል።

• አገልግሎቱ እንዲጀመር ተጨማሪ በጀት ይጠይቃል ፤ በጀቱ የሚፈቀድልን ከሆነ #በቅርብ_ወራት ውስጥ ይኼንን አስጀምረን አገልግሎት አሰጣጡን እናሻሽላለን።

አሁን ያለው የአስቸኳይ ፓስፖርት ክፍያና የሚሻሻለው ክፍያ ምን ይመስላል ?

አሁን በሥራ ላይ ባለው አሠራር መሠረት ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ በአስቸኳይ ለማግኘት 2,186 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ ይኼንኑ ፓስፖርት በሁለት ቀናት ውስጥ ለማግኘት 3,279 ብር ክፍያ ይፈጸማል፡፡

በቅርቡ በሥራ ላይ መዋል ይጀምራል የተባለው አዲስ የአገልግሎት ክፍያ ተመን በ5 ቀናት ውስጥ ባለ 32 ገጽ ፓስፖርት ለማግኘት የሚጠየቀውን ገንዘብ ወደ 5,000 ብር አሳድጎታል፡፡

ፓስፖርቱን በአንድ ቀን ለማግኘት ደግሞ 6,500 ብር ክፍያ መፈጸም እንዳለበት ደንቡ ያስረዳል፡፡

የባለ 64 ገጽ ፓስፖርት በ5 ቀናት ውስጥ ለማግኘት 6,500 ብር የሚከፈል ሲሆን፣ በአንድ ቀን ለማግኘት የሚከለፈለው ክፍያ 8,000 ብር ይደርሳል።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ (ethiopianreportr.com)

@tikvahethiopia
ከ 3 ሚሊዮን 5 መቶ ሺህ ብር በላይ የዋጋ ግምት ያለው ተሽከርካሪ በጨረታ አሸንፎ የወሰደው ግለሰብ ያቀረበው ሰነድ ሲረጋገጥ ሃሰተኛ ሆኖ በመገኘቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

ተጠርጣሪው ግለሰብ ወንጀሉን የፈፀመው የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ለጨረታ ባቀረባቸው ተሽከርካሪዎች ላይ ተጫራች ሆኖ በመሳተፍ ነው፡፡

ጥቅምት 15 ቀን 2015 ዓ/ም በተካሄደው በዚሁ ጨረታ ላይ የተሳተፈው ተጠርጣሪው፤ ለማስያዥያነት በዳሽን ባንክ ስም የተዘጋጀ ሀሰተኛ ሲፒዮ እንዲሁም ጨረታውን ካሸነፈ በኋላ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መስቀል ፍላወር ቅርንጫፍ 3 ሚሊዮን 565 ሺህ ብር  ገቢ ተደርጓል የሚል ሃሰተኛ ደረሰኝ ለድርጅቱ በማቅረብ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2-B87869 አ/አ የሆነ ተሽከርካሪ ወስዶ ከአካባቢው መሰወሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት ሰነድ የማረጋገጥ ስራ በሚሰራበት ወቅት ጨረታውን አሸንፎ ተሽከርካሪውን የወሰደው ግለሰብ ያቀረበውን ሰነድ ትክክለኛነት ተጠራጥሮ ለፖሊስ ካመለከተ በኋላ ፖሊስ ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ግለሰቡን ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር  በማዋል እና የሰነዱን ሃሰተኛነት በማረጋገጥ በህግ አግባብ ተጠያቂ እንዲሆን እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ።

ተቋማት በተለያዩ ምክንያቶች የሚቀርቡላቸውን ገንዘብን ተክተው የሚሰሩ እና ከገንዘብ ጋር ግንኙነት ያላቸውን ሌሎች ሰነዶች አስቀድመው በማረጋገጥ ሊፈፀምባቸው ከሚችል ወንጀል ራሳቸውን ሊከላከሉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ  መልዕክቱን አስተላልፏል።

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia