TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#QatarWorldCup 🇶🇦

የኳታሩ የ22ኛው የዓለም ዋንጫ ጀመረ።

ይኸው እጅግ ተጠባቂ ውድድር አስተናጋጇ ኳታር እና ኢኳዶር በሚያደርጉት ፍልሚያ አንድ ተብሎ ተጀምሯል።

አስተናጋጇ ሀገር ውድድሩ #የህዝቧን እና #ሀገሯን ክብር በጠበቀ ሁኔታ እንዲካሄድ ለማድረግ ጠበቅ ያሉ ህጎችን እያተገበረች ነው የሚገኘው።

ስለኳታር ዓለም ዋንጫ ፦

- " ኳታር " እስከዛሬ የዓለም ዋንጫውን ካዘጋጁ ሀገራት በጣም ትንሿ ሀገር ስትሆን ፤ #በአረብ ሃገር የተዘጋጀ የመጀመሪያው የዓለም ዋንጫ ነው።
- ለዓለም ዋንጫው በአጠቃላይ 220 ቢሊዮን ዩሮ አውጥታለች።
- ለዓለም ዋንጫው 3.2 ሚሊዮን ትኬቶች ተዘጋጅተዋል።
- የመጀመሪያው በበጋ የሚከናወን የዓለም ዋንጫ ነው።
- ኳታር በእግር ኳስ ታሪክ የመጀመሪያ የሆኑ የአየር ሁኔታ ማስተካከያ የተገጠመላቸው ስቴድየሞች (air-conditioned stadiums) አዘጋጅታለች።
- በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ዳኞች ዋና ዳኛ ሆነው የሚሳተፉበት ነው።

በተጨማሪ ፦

• በስቴዲየሞች ቢራም ሆነ ሌላ አልኮል መጠጥ ይዞ መገኘት በፍፁም አይፈቀድም።
• ከስቴዲየሞች ውጭ በፊፋ ፈን ዞኖች ፣ በተፈቀደላቸው የመዝናኛ ቦታዎች አልኮል ማግኘት ይቻላል።

Credit : ቲክቫህ ስፖርት ፣ ፍራንስ 24 ፣ ኢብኮ

ቲክቫህ ስፖርት
https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x

ቲክቫህ ጎል
https://publielectoral.lat/+rbdEU4UaEdQxYWFk
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ኦሮሚያ #ትኩረት

በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ የወለጋ አካባቢዎች አሁንም በቀጠለው የፀጥታ ችግር በርካቶች ህይወታቸው እያለፈ ፣ አካላቸው እየጎደለ፣ ንብረታቸው እየወደመ እንደሚገኝ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

ባለፉት ዓመት ህዝቡ በሰላም እጦት ብዙ ቢሰቃይም መፍትሄ ሳይገኝ አሁንም እየተባባሰ በመቀጠሉ ንፁሃን ክፉኛ እየተጎዱ እና ስቃያቸውም እየተባባሰ እንደሚገኝ ነው ቤተሰቦቻችን የገለፁት።

ከጥቂት ቀን በፊት የፀጥታ ችግር ባለባቸው በወለጋ የተለያዩ አካባቢች ላይ #ንፁሃን እንዲጠበቁ ፣ የህዝቡ ስቃይ ትኩረት ባለማግኘቱ የሰሜን ክፍሉን ያህል ትንሽ እንኳን ትኩረት እንዲሰጠው እና ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈለግ ቤተሰቦቻችን ተማፅኖ ማሰማታቸው አይዘነጋም።

ከሰሞኑን በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ በሚገኙት ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ጃርዳጋ ጃርተ ወረዳ እና በምስራቅ ወለጋ ኪረሙ ወረዳ ውስጥ በርካቶች ህይወታቸው አልፏል፣ ንብረታቸው ወድሟል ፣ #ሰላምን_ፍለጋ ሸሽተው ወደ ሌሎች አካባቢዎችም መግባታቸውን ለመስማት ችለናል።

አንድ የቤተሰባንች አባል ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ፤ " ለንፁሃን ጭፍጨፋ ፣ ለንብረት ውድመት ለዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ተጠናቂነት መኖር አለበት " ብሏል።

" እውነት መንግስት / አስተዳዳሪ ነኝ ፤ የህዝብንም ደህንነት አስጠብቃለሁ የሚል ካለ የትኛው አካል ለሚፈጠሩት ችግሮች ምክንያትና መንገድ እየሆነ እንዳለ ፣ ማን ግፍ እየፈፀመ እንዳለና ለዚህም ድርጊት ተባባሪ እየሆነ እንዳለ ምርመራ በማድረግ ማሳወቅ አለበት ፤ በየዕለቱ ሰዎች እየረገፉ ፣ እየተፈናቀሉ ፣ እየተራቡ እያዩ ዝም ያሉት ዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ከእንቅልፋቸው ነቅተው መፍትሄ እንዲመጣ ንፁሃንን ከሞት እንዲድኑ ድምፃቸውን ማሰማት መቻል አለባቸው ። " ብሏል።

የመንግስት ዋናው ስራ የዜጎችን ደህንነት ማስጠበቅ ፤ ከየትኛውም የታጠቁ አካላት የሚደርስን ጥቃት መከላከል ፣ አጥፊዎችን መቅጣት ነው ይህን ማድረግ ባይቻል እና ንፁሃን ቢጎዱ ተጠያቂነት መኖር አለበት ሲል አክሏል።

በኦሮሚያ ክልል ባለው ፀጥታ ጉዳይ ፤ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚታዩ ችግሮች መኖራቸውን ይህም በተደጋጋሚ መገለፁን ነገር ግን እስካሁን መፍትሄ እንዳልተገኘለት ገልጿል።

" ህዝብ መንግስት አለኝ ሚለው ደህንነቱ እንዲጠበቅ እንጂ በየዕለቱ ያለበት ችግር እየተባባሰ ህይወቱን እያጣ፣ እጅግ ደክሞ ያፈራው ንብረቱ እየወደመበት እንዲቀጥል አይደለም " ያለው ይኸው የቤተሰባችን አባል ባለፉት ጊዜያት እሱን ጨምሮ ቤተሰቦቻቸው በግጭት ቀጠና ውስጥ ያሉ ወገኖች ያሳለፉት ስቃይ በቃላት የሚገለፅ እንዳልሆነ አስረድቷል።

በኦሮሚያ ውስጥ የፀጥታ ችግሮች ባለባቸው ቦታዎች ስለሚደርሰው ስቃይ ብዙ ቢነገርም መፍትሄ ሳያገኝ ዛሬም የሰዎች ህይወት እየተቀጠፈ እንደቅጠል እየረገፈ ይገኛል።

የአንድ ሀገር ዜጎች ህይወታቸው በግፍ እየረገፈ እየታየ ለችግሩ መፈጠር በተለያዩ አቅጣጫዎች የተለያዩ ምክንያቶች እየተደረደሩ ፣ ጥላቻዎችም እየተሰበኩ፣ ሁኔታዎችም #ከመሻሻል ይልቅ ክፉኛ እየተባባሱ ቀጥለዋል።

ህዝቡ ሰላም ርቆት፣ ኢኮኖሚው ደቆ፣ አርሶ እንዳይበላ ሆኖ፣ እየታፈነ ሚሊዮኖች እየተጠየቀበት ፣ መውጫ እና መግቢያ አጥቶ ፣ የሚወዳቸውን እየተነጠቀ፣ ዓመታትን በገፋበት የግጭት ቀጠናዎች መፍትሄ እንዲያገኝ ግፊት ማድረግ እንደሚገባ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የUNHCR ኮንቮይ መቐለ ገብቷል።

የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ኮንቮይ መቐለ መግባቱን አሳውቋል። ይህ ካለፈው ዓመት ነሀሴ ወር በኃላ መቐለ የገባ የመጀመሪያው የUNHCR ኮንቮይ መሆኑ ተገልጿል።

መቐለ የገባው ኮንቮይ ህይወት አድን ሰብአዊ እርዳታን ጨምሮ የታሙሙትን ለማከም መድሀኒት እና የወደሙ ቤቶችን ለመጠገን የሚውሉ የመጠለያ ቁሳቁሶችን የያዘ ነው።

ተጨማሪ ድጋፎችም በመንገድ ላይ መሆናቸው ተጠቁሟል።

እስካሁን የሰላም ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ ፦

- የዓለም ምግብ ፕሮግራም ሰብአዊ ድጋፎችን ወደ ትግራይ ማስገባት ጀምሯል፤ ድጋፍ ማስገባት የጀመረው በምድር እና በአየር ነው።

- የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ አስፈላጊ ድግፎችን ወደ ትግራይ ክልል ማስገባት ጀምሯል ፤ ድጋፉን እያስገባ ያለው በምድር እና በአየር ነው።

- ዛሬ ደግሞ UNHCR ድጋፍ የጫነ ኮንቮይ መቐለ መድረሱን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የሰላም ስምምነቱን መደገፋችንን እንቀጥላለን " - አውሮፓ ህብረት የአውሮፓ ህብረት የሰላም ስምምነቱን መደገፉን እንደሚቀጥል ዛሬ ባሰራጨው ፅሁፍ አረጋግጧል። " ከሰላም ውጭ አማራጭ የለም " ያለው ህብረቱ አጋሮቹ UNICEF እና PLAN የህብረቱን የገንዘብ ድጋፍ በተግባር ላይ ማዋል ይጀምራሉ ሲል አመላክቷል። የአውሮፓ ህብረት ፤ ለሕዝብ አፋጣኝ ቀጥተኛ ድጋፍ ለማረጋገጥ ሥራችንን እንቀጥላለን ብሏል።…
" 2 ሚሊየን የሚደርሱ ህፃናት  ከትምህርት ገበታቸው ውጭ ሆነዋል " - ሮላንድ ኮቢያ

የአውሮፓ ህብረት በጦርነት ምክንያት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል እና ለተማሪዎች ምገባ የሚውል የ33 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ ማድረጉን ኤፍ ቢሲ ዘግቧል።

ጦርነቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች 8 ሺህ 500 ትምህርት ቤቶች መውደማቸውና 1 ሺህ 500 ትምህርት ቤቶች ከአገልግሎት ውጭ መሆናቸው ተገልጿል።

በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ 2 ሚሊየን የሚደርሱ ህፃናት  ከትምህርት ገበታቸው ውጭ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡

ለሰላም ስምምነቱ በሚደረገው ጉዞ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል ብለዋል።

ድጋፉ ፦
- የትምህርት ቤቶች ግንባታ፣
- የምገባ ፕሮግራም፣
- የንፅህና መጠበቂያ፣
- የጤና እና መሰል አገልግሎት ለተማሪዎች ተደራሽ በማድረግ ጥራት ያለው ትምህርትን ለመተግበር የሚደረገውን ጉዞ ያግዛል ብለዋል።

ዓለም አቀፉ የህጻናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) እና የዓለም ምግብ ፕሮግራም ከህብረቱ ጋር በጋራ እንደሚያስፈፅሙት ተጠቁሟል።

በድጋፉ 80 ሺህ የሚደርሱ ተማሪዎች ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚቻል የተገለጸ ሲሆን 60 ትምህርት ቤቶች እንደሚገነቡ መጠቆሙን የኤፍ ቢ ሲ ዘገባ ያስረዳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የUNHCR ኮንቮይ መቐለ ገብቷል። የተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ኮንቮይ መቐለ መግባቱን አሳውቋል። ይህ ካለፈው ዓመት ነሀሴ ወር በኃላ መቐለ የገባ የመጀመሪያው የUNHCR ኮንቮይ መሆኑ ተገልጿል። መቐለ የገባው ኮንቮይ ህይወት አድን ሰብአዊ እርዳታን ጨምሮ የታሙሙትን ለማከም መድሀኒት እና የወደሙ ቤቶችን ለመጠገን የሚውሉ የመጠለያ ቁሳቁሶችን የያዘ ነው። ተጨማሪ ድጋፎችም በመንገድ…
#Tigray

6 የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የጭነት ተሽከርካሪዎች ምግብና ተጨማሪ የህክምና ቁሳቁሶችን ይዘው ትላንትና ለሊት መቐለ ገብተዋል።

ባለፈው ሳምንት በትግራይ ያሉ የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ እና የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ቡድኖች በከተማ እና በከተማ ዙሪያ ላሉ ለ9 የጤና ተቋማት አስቸኳይ የህክምና ቁሳቁስ ማከፋፈላቸው ተገልጿል።

በሌላ በኩል ፤ ከሰላም ስምምነቱ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተመድ የህፃናት መርጃ ድርጅት (UNICEF) ሰብአዊ እርዳታ ዛሬ ትግራይ ገብቷል።

ይህ የነፍስ አድን ድጋፍ ለሴቶች እና ልጆች ወሳኝ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በአፋር እና አማራ ክልል ጨምሮ በግጭት ለተጎዱ አካባቢዎች ሁሉ ተጨማሪ የሰብዓዊ ድጋፍ ይደርሳል ተብሏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ችሎት #ክርስቲና_መላኩ #ጊዮናዊት_መላኩ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ፤ የህጻን ግዮናዊት መላኩ እና ህጻን ክርስቲና መላኩን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች የተባለችው ተጠርጣሪ ላይ ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራ እንዲያደርግ የ14 ቀን ጊዜ ሰጠ። ተጠርጣሪ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠኋቱ 3:30 ላይ በለሚ ኩራ…
#Update

2 ህጻናትን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች ተብላ የተከሰሰችው የቤት ሰራተኛ የጥፋተኝነት ፍርድ ተላለፈባት።

የጥፋተኝነት ፍርዱ ተከሳሿ የመከላከያ ማስረጃ የለኝም ማለቷን ተከትሎ ነው የተሰጠባት።

የጥፋተኝነት ፍርዱን የሰጠው የፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የከባድ ግድያና የውንብድና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሿ ወንጀሉን አልፈጸምኩም ማለቷን ተከትሎ በጥቅምት 30 ቀን በነበረ ቀጠሮ ዓቃቢህግ  የሟች ግዮናዊት እና ክርስቲና  መላኩ ወላጆችን ጨምሮ ስድስት ምስክሮችን አቅርቦ የምስክርነት ቃላቸውን አሰምቶ ነበር።

ፍ/ቤቱም የምስክር ቃል መርምሮ ተከሳሿ በተሰሰችበት ወንጀል እንድትከላከል በዛሬው ቀጠሮ ብይን ሰየሰጠ ቢሆንም ተከሳሿ የመከላከያ ማስረጃ እንደሌላት ገልጻለች።

ፍ/ቤቱም የተከሳሽን በፖሊስ ጣቢያ ቃል በመያዝና የዓቃቢህግ የሰው ምስክሮችን ቃል መርምሮ በተከሰሰችበት ተደራራቢ ወንጀል ጥፋተኛ ብሏታል።

ከቀጠሮ በፊት የዓቃቢህግ  የቅጣት ማክበጃ አስተያየት እና የተከሳሽ የቅጣት ማቅለያ አስተያየት ካላት በጽ/ቤት እንዲቀርቡ ያዘዘ ሲሆን የቅጣት አስተያየትን ተመልክቶ የቅጣት ውሳኔ ለመስጠት ለህዳር 26/2015 ዓ/ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ተከሳሽ ህይወት መኮንን ሀይሉ በነሃሴ 26 ቀን 2014 ዓ/ም ከጥዋቱ 3:30 ላይ አራብሳ ኮንዶሚኒዬም በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ በምትሰራበት መኖሪያ ቤት ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ህጻን ግዮናዊት መላኩ እና ህጻን ክርስቲና መላኩን በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርጋለች በዚህም በግድያ ወንጀልና በወቅቱ የሟች ቤተሰቦችን የሰነድ ማስረጃዎች ቀዳዳ በመጣል በአጠቃላይ በተደራራቢ ክስ  ዓቃቤ ህግ ጥቅምት 15 ቀን ክስ መመስረቱ ይታወሳል።

Credit : ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ

@tikvahethiopia
" ከተወሰኑ ሳምንታት በኃላ የማህበራት የቤት ዕጣ ይወጣል " - አቶ ሽመልስ ታምራት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከሚገነባቸው ቤቶች ውስጥ ሃያ በመቶው በነባሩ የመንግስት አስተባባሪነት የሚገነቡ ሆነው እንደሚቀጥሉ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ገልጿል።

የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር አቶ ሽመልስ ታምራት ለብሄራዊ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ " ያሉ ያልተጠናቀቁ ቤቶችን የማጠናቀቅ፣ የማስረከብ ስራ ይሰራል " ያሉ ሲሆን ቆጣቢው በሌሎችም መንገዶች ቢሆን ቅድሚያ የሚያገኝበት ዕድል እየተመቻቸ ነው " ብለዋል።

አቶ ሽመልስ ከተወሰኑ ሳምንታት በኃላ የማህበራት ቤት ዕጣ የሚወጣበት ሁኔታ ይፈጠራል ሲሉ ተግረዋል።

" ከቆጣቢዎቹ ነው ምዝገባ እንዲደረግ የተደረገው ፤ ቆጣቢ ሆነው በማህበር ተደራጅቼ ቤት መስራት ፈልጋለሁ የሚለው አካል በፍቃደኝነት መጥቶ እንዲመዘገብ ተደርጓል ፤ በዛ መሰረት የተለዩ የተደራጁ ማህበራት አሉ እነሱን አሁን ወደ ስርዓት እናስገባለን " ሲሉ አስረድተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውና መቆጠብ የማይችሉ ነዋሪዎችን በኪራይ ቤቶች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #USA

ትላንት አንቶኒ ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በስልክ መነጋገራቸውን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አሳውቋል።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት የሰላም ስምምነቱ አተገባበር ላይ እና በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም ለመፍጠር እየተደረገ ስላለው ጥረት መምከራቸውን ተገልጿል።

ብሊንከን ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ክልል እንዲሁም በአጎራባች አፋር እና አማራ ክልሎች ያልተገደበ ሰብአዊ ርዳታ እና መሰረታዊ አገልግሎቶችን ወደ ነበረበት ለመመለስ እያደረገ ያለውን ጥረት እውቅና ሰጥተዋል።

ሁሉም የውጭ ሃይሎች ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ እና የትግራይ ሃይሎችን ትጥቅ ማስፈታትን ጨምሮ የግጭት ማቆም ስምምነቱን በአስቸኳይ ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስምረውበታል።

ብሊንከን ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ጋር በነበራቸው ውይይት ሀገራቸው አሜሪካ በአፍሪካ ህብረት የሚመራውን የሰላም ሂደት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኗን እንዳረጋገጡ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
#Tigray

በናይሮቢው የሰላም ስምምነት ሰነድ ላይ ፊርማቸውን ያኖሩት የትግራይ ኃይሎች አዛዥ ጄነራል ታደሰ ወረደ በናይሮቢው ስምምነት የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ባለፉት ቀናት ለኃይሎቻቸው ኦረንቴሽን ሲሰጥ እንደነበር እና ይኸው ኦረንቴሽን በቀጣይ ሁለት ቀን እንቀሚያልቅ ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት በክልሉ ለሚገኙት የመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ነው።

ጄኔራል ታደሰ ወረደ ምን አሉ ?

" በናይሮቢው ሰላም ስምምነት ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የመጀመሪያው ከሰራዊቱ ጋር መግባባት ነው ስለ ሰላሙ ጉዳይ አጠቃላይ መግባባት መፍጠር ነው (orientation phase) ። ህዝቡ ጋርም ማለት ነው ፤ ምክንያቱም ህዝቡም ማወቅ አለበት ፤ ሰራዊቱም ማወቅ አለበት።

ቀጥታ ከእኛ ከስራችን ጋር በተያያዘ ፤ ከሰራዊቱ ጋር እየጨረስን ነው ፤ ከሰራዊት አዛዦች እስከታች ድረስ ስለሰላሙ የመግባባት ሁኔታ (ኦረንቴሽን) እየጨረስን ነው ያለነው ፤ ምነልባትም በዚህ ሁለት (2) ቀን ሙሉ በሙሉ እንጨርሳለን እስከታች ድረስ።

ከዛም ቀጥሎ ወደ ሰራዊቱ Disengage አድርጎ / ተላቆ ካለበት ቦታ የውጊያ ግንባሮች የማፍረስ ሰራዊቱ ወደ ተቀመጠለት ቦታ አለ እሱን ጨርሰናል ማን የት ይንቀሳቀሳል የሚለው  ወደዛ የማጓጓዝ ጉዳይ ነው ይሄ ደግሞ ተከታትሎ የሚጀምር ነው የሚሆነው ፤ የሎጅስቲክስ አቅማችን ወይም የማጓጓዝ አቅማችን እስከፈቀደ ድረስ በአንድ ጊዜም ልናነሳው እንችላለን ምናልባት የተወሰኑ ቀናት ሊወስድ ይችላል ማጓጓዝ፤ ይሄ ይጀመራል፤ Already #ጀምረነዋል

የመጀመሪያው ስራ የመግባባት ( #orientation ) ፣ የማሳመን ፣ የመተማመን ሁኔታውን ከጀመርን ጀምረናል ማለት ነው፤ በዛ ነው የጀመርነው፤ ይሄ በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በኩልም እንደተጀመረ እየሰማሁ ነው።

ከእኛ በኩል እየጨረስን ነው ያለነው፤ አንድ ከፍተኛ ስራ ይሄ ነው፤ ስምምነቱን ከማድረግ አንፃር፤ why የሚሉ ነገሮችን መመለስ ነው ፤ ሰራዊቱን አንድ አስተሳሰብ አንድ ዕዝ ሆኖ እንዲንቀሳቀስ ማድረግ በቆየበት ማድረግ ነው ስለዚህ አንዱ ትልቅ ስራ ይሄ ይመስለኛል፤ ጀምረናል ብቻ ሳይሆን እየጨረስን ነው ያለነው። ከዚህ በኃላ የሚቀጥሉት ስራዎች ቀላል ናቸው።

ከእኛ በኩል ፤ #ማንኛውም በትግራይ ውስጥ ያለው የትግራይ ኃይል ከአንድ የኮማንድ ስርዓት ውስጥ ሆኖ የሚንቀሳቀስ ፣ ግዳጅ የሚፈፅም ነው ከዚህ ውጭ የሆነ ኃይል #የለንም ፤ ከዚህ ውጭ የሆነ የታጠቀ የሚባልም ኃይል የለም ፤ ትግራይ ውስጥ ያለው የኢትዮጵያ ኃይል ተመሳሳይ ነገር ነው ያለው ስለዚህ ከቁጥጥር ውጭ የሚሆን ነገር የሚኖር አይመስለኝም።

የስነምግባር ደንብ ሊሆን ሚችል ሰላሙን ለማስከበር ስምምነቱንም ተግባራዊ ለማድረግ (code of conduct) አውጥተናል እያንዳንዱ ይሄኛውን code of conduct እንዲያውቀው አድርገናል አመራሩም አባሉም ሁለተኛው ስራ ይሄ ነው ከኦረንቴሽን ጋር የተያያዘ ነው።

ኃይል ማንቀሳቀሱ ቀላል ነው የሚሆነው ፤ አቅም ነው የሚወስነው ይሄ የሎጅስቲክስ ጉዳይ ነው ፤ ስለዚህ ትግበራው ተጀምሯል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንዶቹ በሁለቱም ዶክመንቶች ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች አሉ more የፖለቲካው ስራ ፈጥኖ ተጀምሮ መፍታት ያለበት/ ሊፈታቸው የሚገባ። በስምምነቱ መሰረት  በክልሉ ውስጥ ያለ መስተዳደር አለ ስለዛ ትንሽ የተባለ አለ local መስተዳዳሮች በየዞኑ በየወረዳው በየቀበሌው ያሉ መስተዳደሮች አሉ ስርዓት ያለው ህዝብ የራሱ የአስተዳደር ማዋቅር ያለው ህዝብ ነው ከምስራቅ ይሁን ከደቡብ ከየትኛውም እነዚህ እንደሚቀጥሉ ነው ተስፋ የማደረገው እንጂ እኚህ እንዲፈርሱ አይደለም።

ሰራዊቱ ነው እንጂ disengage የሚያደርገው እንጂ ሲቪል መስተዳደሩን disengage የሚያደርገው የለም ይቀጥላል። የእነዚህን ደህንነት በሚመለከት መሰራት ያለበት ነገር አለ ፤ የቆየ ፖሊስ አለ እንደ አደረጃጀት ፖሊስ አለ እሱ በቀጣይ የpolitical dialogue መፍታት ያለበት ነገር አለ።

አሁን ላይ disengage ከምናደርግባቸው ግንባሮች ዓዲግራት ፣ ማይጨው ... ወዘተ የመሳሰሉ ትላልቅ ከተሞች ፤ የዞን የመስተዳደር ማዕከሎች ይቅርና እነሱ ጋርም ያሉት አክሱም ፣ ሽረ አይነትም አዲስ መስተዳደር ይቆማል ይፈርሳል ምናም የሚባል ነገር አይደለም ፤ እነዛም reset መደረግ አለበት የሲቪል መስተዳደሩ ፤ የ Poltical Dialogue ይሄን መፍታት አለበት መፍጠን ያለበት ይሆናል ፤ ይሄ በዘገየ ቁጥር ለ Conflict መነሻ ሊሆን ይችላል፤ እነዚህ ዝርዝር ነገሮች አሉ ንፁሁ የ Security Agreement መተግበር ግን ጀምረናል በጣም ጥሩ ሆኖ እንዲተገበር የ Political Dialogue ፈጥኖ መጀመር ያለበት ይሆናል። "

@tikvahethiopia