TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ተማሪዎች ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት አድርጉ " - የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ

በተለያየ ምክንያት የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ሙሉ በሙሉ ወይንም በከፊል ላልተፈተኑ ተማሪዎች ፈተናውን በታህሳስ ወር መጀመሪያ ሳምንት ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርይ መምሪያ አሳውቋል።

ትምህርት መምሪያው ፦

- በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በመሸጋገሪያ ድልድይ ተሰብሮ በደረሰው አደጋ ምክንያት የመጀመሪያውን ቀን ፈተና ያልተፈተኑ፤

- በወሊድ ምክንያት ፈተናውን ያልወሰዱ፤

- የተለያየ ማህበራዊ ችግር አጋጥሟቸው ጉዳዩ ለሚመለከተው አካል አሳውቀው ለፈተና ያልተቀመመጡ ፤

- በሀዋሳ ከተማ ማዕከላዊ ማረሚያ ትምህርት ቤት የሚገኙ ተማሪዎች ፈተናውን ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ነው ብሏል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ፤ " ትምህርት ሚኒስቴር ፈተናውን ላልወሰዱ ተማሪዎች በታህሳስ ወር 2015 ዓ.ም በመጀሪያ ሳምንት አከባቢ ፈተናው ለመስጠት ቅድመ ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው " ያለ ሲሆን ተማሪዎች ይህንን አውቀው ፈተናውን ለመፈተን ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል።

ምንጭ፦ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ

@tikvahethiopia