TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update የጉጂ ኦሮሞ አባገዳዎች አለመግባባቶች #በድርድር እንዲፈቱ ፣ የህግ የበላይነት እንዲከበርና ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ጥሪ አቀረቡ፡፡ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ ጥር 2 ቀን 2011 ዓ.ም. በነገሌ ከተማ በባህላዊ የገዳ ስርዓት የሰላም ሳምንት እንደሚታወጅ አባ ገዳ ጂሎ ማኖ አስታውቀዋል። የሰላም ሳምንትን አስመልክቶ ከአዶላና ሻኪሶ ወረዳዎች የሀገር ሽማግሌዎችና ከኃይማኖት አባቶች እንዲሁም ከሌሎች ነዋሪዎች ጋር የሰላም ውይይት መደረጉን ገልጸዋል፡፡ አባ ገዳ ጂሎ ማኖ የሰላም እጦት ጎልቶ በሚታይበት በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን ካለፈው ሰኞ ጀምሮ የሰላም ሳምንት መታወጁን አስታውሰዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ድርድርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ ? ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦ " እስካሁን የተደረገ ድርድር የለም፤ እስከዚህ ደቂቃ ድረስ ፤ ስለድርድር ብዙ ሲወራ ሰማለሁ ግን እስካሁን ድርድር አላደረግንም፤ አላደረግንም ማለት እስከነአካቴው ድርድር የሚባል ነገር አይኖርም ማለት አይደለም። ድርድር ፣ ውይይት ማለት ችግር ተወግዷል ማለት ሳይሆን ችግር ለማስወገድ አማራጭ Alternative መንገድ አለው…
#ተጨማሪ

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ስለ ድርድር የተናገሩት ፦

" ... አንድ የእስራኤል ፕሬዜዳንት በአንድ ወቅት ያሉትን ማስታወስ ፈልጋለሁ፤ እኚህ ፕሬዜዳንይ እስራኤል እየተዋጉ ከሀማሶች ጋር ከሂዝቦላህ ጋር ይደራደራሉ።

በነገራችን ላይ TPLF ከኦነግ ጋር ይደራደር ነበር፣ ደርግ ከሻዕቢያ እና TPLF ጋር ይደራደር ነበር ድርድር ማለት እርቅ ማለት አይደለም። ድርድር ውስጥ ብዙ የሚገኙ ነገሮች አሉ። ከምሳሌ ... ምሳሌው ይቅርብኝ ግን አሉ ጥቅሞች።

እናም እኚህ የእስራኤል ፕሬዜዳንት በጦርነት ጊዜ ምንም የሰላም ጫላንጭል እንደሌለ ሰላም ተስፋ እንደሌለው አስበን ጨክነን እንዋጋለን ፤ በድርድር ጊዜ ተጋጭተን እንደማናውቅ ጦርነት የሚባል እንዳልነበር በሰከነ መንፈስ እንደራደራለን ሁለቱንም የምናደርገው ለእስራኤል ጥቅም ነው ብለዋል።

እኛ በውጊያው ጊዜ የነበረን አቋም እና ሂደት ለምክር ቤት መግለፅ አይጠበቅብኝም አቋማችን ግልፅ ነው። በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ምንም የማንደራደር መሆኑ ግልፅ ነው።

አሁንም የምናደርገው የዛ ተገላቢጦሽ ሆኖ መታየት አለበት። ታስታውሳላችሁ በዝግ ስንወያይ ኢትዮጵያን አፍርሰው እነዚህ ሰዎች አዲስ አበባ አይገቡም ብያቹ ነበር በቲቪ አልተላለፈም ያ ውይይት ነበራችሁ ብዙዎቻችሁ ያኔ የተወያየነው ነገር ነው ተፈፅሞ ያየነው።

አሁንም #በድርድር የሚባል ነገር ካለ በዛው sprint ማየት ጥሩ ነው። የሰላም አማራጭ ካለ ፤ TPLF ቀልብ ከገዛ በጦርነት እንደማያዋጣው እንደማያሸንፍ ከተገነዘበ እኛ በደስታ ነው የምናየው። "

@tikvahethiopia
" አሁንም ያለው ችግር በውይይት እና በድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች ይደረጋሉ " - የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት

የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት አገልግሎት ዛሬ ምሽት መግለጫ አውጥቶ ነበር።

በዚሁ መግለጫው በአማራ ክልል ያለው ችግር አሁንም በ #ውይይት እና በ #ድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ እንዳልሆነ ጠቁሟል።

መ/ቤቱ በመግለጫው ፤ " ከድርድር እና ውይይት ይልቅ መንግሥታዊ ሥልጣንን በኃይል ለመያዝ የሚጥሩ እንዲሁም አጋጣሚዎችን በማቀነባበር ዝርፊያ ለመፈጸም የሚፈልጉ የታጠቁ ቡድኖች፣ ፅንፈኛና አክራሪ ኃይሎች ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ጋር በመቀናጀት ሀገራዊ የጸጥታ ሥጋት ለመደቀን ሙከራ እያደረጉ ነው " ብሏል።

በአማራ ክልልም እየታየ ያለው ሁኔታ ይኸው ነው ሲል ገልጿል።

" ከኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ጋር በተያያዘ የተከሰቱ ችግሮች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ ጥረቶች ቢደረጉም ችግሩ በሚፈለገው ልክ አልተፈታም " ያለ ሲሆን ፤ " ለዘረፋ የተደራጁ ጥቂት ኃይሎች አሁን ላይ መንግሥታዊ መዋቅሮች እንዲፈርሱ፤ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት እንዲቋርጡ፤ አንዳንድ ከፌዴራል መንግሥት ጋር የሚያገናኙ የመንገድ መሠረት ልማቶች እንዲዘጉ በማድረግ፤ ሕዝቡ ላይ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጫና ለመፍጠር ሙከራ እያደረጉ ይገኛሉ " ብሏል።

ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሚያስፈፅመው የጠቅላይ መምሪያ ዕዝን በማስተባበር የክልሉን ሰላምና ደኅንነትን በአጭር ጊዜ ለማረጋገጥ የሚያግዝ ስምሪት ወስዶ እየሠራ መሆኑን ገልጾ " በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ከድርጊታቸው ይቆጠቡ " ሲል አሳስቧል።

አሁንም በአማራ ክልል ያለው ችግር #በውይይትና #በድርድር የሚፈታበት መንገድ ዝግ ባለመሆኑ ተከታታይ ጥረቶች ይደረጋሉ ሲል አሳውቋል።

" ለዝርፊያ ከተደራጁ ቡድኖች ጋር የሚንቀሳቀሱ አካላት ካሉ ግን አስፈላጊው እርምጃ እንደሚወሰድ እና ሕግ የማስከበር ሂደቱ ተጠናክሮ ይቀጣላል " ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አንድ ዓመት ስለደፈነው የፕሪቶሪያው ሰላም ስምምነት የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፣ ህወሓት እና ሀገራት ምን አሉ ? የኢትዮጵያ መንግሥት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ የፕሪቶሪያው ግጭት የማስቆም ስምምነት ዋና ዉጤት " የጦር መሣሪያ ላንቃ መዘጋቱ " እንደሆነ አሳውቋል። ሚኒስቴር ከግጭት ማቆሙ ስምምነት በኋላ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች የምትጠቀስበት…
" ዳግም ወደ ግጭት ሊወስዱ የሚችሉ አከራካሪ እና አሻሚ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት መፍጠር ይገባል " - ነእፓ

የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች ጉዳይ ህጋዊ እና ፍትሀዊ መልስ ያገኝ ዘንድ የትግራይ፣ የአማራ እና የፌዴራል መንግስት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን ጥረት እንዲያደርጉ ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ / ነእፓ ጥሪ አቀረበ።

ነእፓ የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት አንደኛ ዓመትን አስመልክቶ በላከል መግለጫ ነው ይህን ጥሪ ያቀረበው።

ፓርቲው በላከልን መግለጫ ፤ በሰላም ስምምነቱ ያልተፈጸሙ ጉዳዮች በአፋጣኝ እንዲፈጸሙ ፤ ዳግም ወደ ግጭት ሊወስዱ የሚችሉ አከራካሪ እና አሻሚ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባት ለመፍጠር በተለይም የፌደራል መንግስት እና የትግራይ ከልል ጊዜያዊ አስተዳደር በከፍተኛ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪውን አቅርቧል።

በጦርነቱ ምክንያት ከፉኛ የወደሙ የትግራይ፣ የአማራ እና የአፋር ክልል መሰረተ ልማቶች በተቻለ አቅም ባጠረ ጊዜ እንዲገነቡ ማእከላዊው መንግስት ድጋፍ እንዲያደርግ ብሏል።

የወልቃይት እና የራያ አካባቢዎች ጉዳይ ህጋዊ እና ፍትሀዊ መልስ ያገኝ ዘንድ የትግራይ፣ የአማራ እና የፌዴራል መንግስት እንዲሁም ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ጥሪውን አቅርቧል።

የትግራዩን የሰላም ስምምነት እንደ ጥሩ ተሞከሮ በመውሰድ በሌሎች የሀገራችን አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች እና ግጭት ቀስቃሽ የፖለቲካ ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ የሚፈቱበትን መንገድ ለመጠቀም መንግስትም ሆነ ነፍጥ አንግበው የሚታገሉ አካላት ልዩነቶቻቸውን #በድርድር ለመፍታት የበኩላቸውን እንዲያደርጉ ነእፓ በላከልን መግለጫው ይፋዊ ጥሪውን አቅርቧል።

ነፃነት እና እኩልነት ፓርቲ ፤ የፖለቲካ ልዩነቶችን በአፈሙዝ መፍታት እንደማይቻል የሀገራችንም ሆነ የዓለም ተሞከሮ ያሳያል ያለ ሲሆን ከአንድ አመት በፊት ልክ በዛሬዋ ቀን በድርድር የተቋጨው የትግራይ ጦርነት ለዚህ ህያው ምስክር ነው ሲል ገልጿል።

ከዚህ ቀደም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሲካሄዱ የነበሩ ግጭቶች በድርድር ይፈቱ ዘንድ ጥሪ ሲያደርግ እንደቆየ ያስታወሰው ፓርቲው ዛሬም በሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በአፋጣኝ ቆመው የፖለቲካ ልዩነቶች በሰላማዊ መንገድ እና " በአብሮ በማሸነፍ " መርህ አንዲፈቱ የሰላም ጥሪውን አቅርቧል።

(ፓርቲው የላከው መግለጫ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia