TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ፦ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በላከልን መልዕክት በዛሬው ዕለት የመሰረተ ልማት መጋራት እና #በደንበኞች_መካከል_የግንኙነት_ልውውጥ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙርያ ከበርካታ ዙር ውይይቶች በኋላ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር ስምምነት ላይ መድረሱን ገልጾልናል። ውይይቶቹ በኢትዮጵያ ኮሚዩኒኬሽን ባለሥልጣን የተመሩ መሆኑን የገለፀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለሥልጣኑ ላሳየው ብቁ የአመራር ጥበብ ምስጋና…
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከምን ደረሰ ?

ሳፋሪኮ ኢትዮጵያ የቴሌኮም አገልግሎት ለመጀመር እያደረገ ስላለው እንቅስቃሴ እንዲሁም አሁናዊ የተቋሙን እንቅስቃሴ በተመለከተ በቀጣይ ሳምንት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ አሳውቋል።

ተቋሙ ዛሬ ባሰራጨው መልዕክት ፤ " ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አገልግሎት ሊጀምር ነው " የሚሉ፣ ቀኖች እና ሌሎች ተቋማዊ መረጃዎችን ያካተቱ ዜናዎችና መረጃዎች በማሕበራዊ ድረገጾች መውጣታቸውን እንዳስተዋለ ገልጿል።

#በያዝነው_የፈረንጆች_ዓመት ውስጥ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀና #በሁሉም_የኢትዮጵያ_ክፍሎች ምርጥ የደንበኞች አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችሉትን ዝግጅቶች እያደረግ መሆኑን የገለፀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለዚህም፦

- የኔትወርክ ግንባታ፣

- የሰው ኃብትን #በኢትዮጵያዊያን_ሠራተኞች ማደራጀት

- የጥራት ፍተሻዎችን እያደረገ እንደሚገኝ አሳውቋል።

በቀጣይ ሳምንት ስለተቋሙ እንቅስቃሴ ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ እንደሚሰጥ የገለፀ ሲሆን የአገልግሎቱን መጀመረ የሚጠባበቁ ሁሉ ትክክለኛ መረጃዎችን ከተቋሙ ትክክለኛ አድራሻ ብቻ እንዲካታተሉ መልዕክቱን አስተላልፏል።

ፎቶ ፦ ፋይል

@tikvahethiopia
#BahirDar

በባሕር ዳር የባጃጆች ሰዓት ገደብ ተጣለ።

በባሕር ዳር ከተማ የባጃጅ ወይም የባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ እንዲሆን ገደብ ተጣለ።

የባሕር ዳር ከተማ ፀጥታ ም/ቤት ባወጣው መግለጫ ፤ ምክር ቤቱ በአደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የሕዝብን ሰላምና ደኅንነት የሚያስጠብቁ ያላቸውን ውሳኔዎችን ማሳለፉን አስታውቋል።

በዚህም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን እስከ ምሽት 2 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ትዕዛዝ ተላልፏል።

ምክር ቤቱ አሁን ካለው ሀገራዊ እና ክልላዊ ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ለከተማው ሰላምና ደኅንነት ሲባል ውሳኔው መተላለፉን አሳውቋል።

ከዛሬ ምሽት ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ ማንኛውም የባጃጅ ወይም የባለሦስት እግር ተሽከርካሪ እስከ ምሽቱ 2:00 ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ የተባለ ሲሆን ከምሽቱ 2 ሰዓት በኋላ ሲንቀሳቀስ የተገኘ ማንኛውም የባጃጅ ተሽከርካሪ ላይ ለሚወሰድበት ማንኛውም ቅጣትና እርምጃ ኀላፊነቱን ባለቤቱ ወይም አሽከርካሪው ይወስዳል ሲል ምክር ቤቱ አሳስቧል።

#AMC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሱዳን ኢንተርኔት ዘጋች። ሱዳን ዛሬ ሀሙስ ከሚካሄደው ታላቁ የ #June30 የተቃውሞ ሰለፍ ጋር በተያያዘ ከጥዋት ጀምሮ የኢንተርኔት አገልግሎት አቋርጣለች። የኢንተርኔት ጉዳይን የሚከታተለው ኔት ብሎክስ ፤ ዛሬ #June30 ሊካሄድ ከታሰበው የሱዳን ፀረ ጁንታ (ወታደራዊ አገዛዝ) ተቃውሞ እና የሲቪል አስተዳደር እንዲመሰረት ከሚጠይቀው ሰልፍ ጋር በተገናኘ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ገልጿል። @tikvahethiopia
" የቡርሃን አገዛዝ ይውደቅ ፤ ብንሞትም እንኳን ወታደሩ አይገዛንም " - የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝን ሊያወግዙ አደባባይ የወጡ ዜጎች

ዛሬ ሱዳን በተቃውሞ ስትናጥ ዋለች።

ዛሬ ሀሙስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ጎዳናዎች ላይ ወታደራዊ አገዛዙን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

የተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኙት ሱዳናውያን ባለፈው አመት በመፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን ስልጣን የተቆጣጠሩት የጦር ሰራዊት አዛዥ ሌ/ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃንን በመጥቀስ " የቡርሃን አገዛዝ ይውደቅ ፤ ብንሞትም እንኳን ወታደሩ አይገዛንም " ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ከካርቱም በተጨማሪ በሌሎችም የሀገሪቱ ክፍሎች የተቃውሞ ሰልፍ ስለመካሄዱ ለማወቅ ተችሏል።

ከሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ በተገኘው መረጃ በዛሬው ሰልፍ ላይ 5 ሰዎች ተገድለዋል (አንድ ከካርቱም ፤ 4 ከኦምዱርማን)። ከጥቅምት 25/2021 አንስቶ እስከዛሬ የሞቱ ሰዎች 108 ደርሰዋል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንደዘገበው ከጥዋት ጀምሮ የኢንተርኔት እና የስልክ መስመሮች ተቋርጠዋል።

መረጃው ፦ ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እና ከሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰባሰበ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፋቱዋ ቤንሱዳ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ። የተመድ የሰብዓዊ መብቶች ም/ቤት፤ በኢትዮጵያ ተፈጽመዋል የሚባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምር ያቋቋመውን ዓለም አቀፍ የባለሙያዎች ኮሚሽን በሊቀመንበር ሲመሩ የነበሩት ፋቱዋ ቤንሱዳ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ። በምትካቸው ኬንያዊቷ የህግ ባለሙያ ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ ተሹመዋል። ጋምቢያዊቷ ፋቱዋ ቤንሱዳ ለምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት በፃፉት ደብዳቤ ከሊቀ መንበርነታቸው…
#UN #NewsAlert

የተመድ መርማሪዎቹ አዲስ አበባ እንዲገቡ ፍቃድ ማግኘታቸውን አስታወቁ።

በሰሜን ኢትጵያ በተካሄደ ጦርነት ተፈፀሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲያጣሩ የተሰየሙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች አዲስ አበባ እንዲገቡ ፈቃድ ማግኘታቸውን ዛሬ ሀሙስ አስታወቁ። ሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች መግባት እንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል።

የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጦርነቱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ ጀምሮ ተፈፅመዋል የተባሉ ጥሰቶችን የሚመረምር በየዓመቱ የሚታደስ ሥልጣን የተሰጠውና ሦስት የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሙያዎች ያሉበትን አጣሪ ኮሚሽን ባለፈው ታኅሳስ መሰየሙ ይታወሳል።

የኮሚሽኑ ምርመራው ዋና ትኩረት የሆኑት የሰብዓዊ መብቶች፣ የሰብዓዊነትና የስደተኛ ህግጋት ጥሰቶች እና በደሎች አሁንም በግጭቱ ውስጥ እየተሳተፉ ባሉ የተለያዩ ወገኖች ያለምንም ተጠያቂነት መቀጠላቸው እንደሚያሳስባቸው የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ካሪ ቤቲ ሙሩንጊ ለምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር አመልክተዋል።

አክለውም የኢትዮጵያ መንግሥት በግዛቱ ውስጥ የሚፈፀሙ ጥሰቶችን የማስቆምና ተጠያቂዎችን ለፍርድ የማቅረብ ኃላፊነት እንዳለበት ኮሚሽኑ አበርትቶ እንደሚያሳስብ መግለፃቸውን አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።

“ ኦሮምያ ክልል ውስጥ የተፈፀሙትን ጨምሮ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ የጭካኔ አድራጎቶች በጥልቅ አሳስበውናል” ሲሉ ሊቀመንበሯ አክለው ተናግረዋል።

“ሲቪሎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን የሚያቀጣጥል የጥላቻ ንግግርና በጎሣ ማንነትና በፆታ ላይ የተመሠረቱ ጥቃቶች እንዲፈፀሙ ቅስቅሳ ማካሄድ የጭካኔ ወንጀል አድራጎቶችን እንደሚያስከትሉ እንደቅድመ ማስጠንቀቂያ የሚወሰድ ነው” ብለዋል

በመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት የተቋቋመው መርማሪ ኮሚሽን በግጭቱ ውስጥ በሚሣተፉት በሁሉም ወገኖች ተፈፅመዋል የተባሉትን ጥሰቶች የሚመረምር ሲሆን የሽግግር ፍትኅና የብሄራዊ ዕርቅ መመሪያም በማዘጋጀት ላይ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ አመልክቷል።

ከኢትዮጵያ የፍትህ ሚኒስትር ጋር ባለፈው ግንቦት ወር ላይ የተገናኙት የተመድ መርማሪዎች ግጭት በተካሄደባቸው የሀገሪቱ አካባቢዎች የመብቶች ጥሰቶች ሰለባዎች ናቸው የተባሉ ሰዎችን ለማነጋገር ፈቃድ የጠየቁ ሲሆን አዲስ አበባን ለመጎብኘት ከኢትዮጵያ መንግሥት አዎንታዊ ምላሽ ማግኘታቸውን የኮምሽኑ ሊቀ መንበር አስታውቀዋል።

ሊቀመንበሯ በማከል “አዲስ አበባ ላይ በምናደርገው ውይይት መርማሪዎቻችን ጥሰቶች ወደተፈፀሙባቸው አካባቢዎች መግባትና ከተጎጂዎችና ከዕማኞች ጋር ለመነጋገር እንዲችሉ ፈቃድ ያገኛሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ብለዋል።

መረጀውን አጃንስ ፍረንስ ፕሬስን ዋቢ አድርጎ ያጋራው ቪኦኤ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የቡርሃን አገዛዝ ይውደቅ ፤ ብንሞትም እንኳን ወታደሩ አይገዛንም " - የሱዳን ወታደራዊ አገዛዝን ሊያወግዙ አደባባይ የወጡ ዜጎች ዛሬ ሱዳን በተቃውሞ ስትናጥ ዋለች። ዛሬ ሀሙስ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ጎዳናዎች ላይ ወታደራዊ አገዛዙን በመቃወም ሰልፍ መውጣታቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል። የተቃውሞ ሰልፉ ላይ የተገኙት ሱዳናውያን ባለፈው አመት በመፈንቅለ መንግስት…
#Update

በሱዳን ወታደራዊውን መንግስት ለመቃወም በወጡ ሰልፈኞች ላይ ጦሩ በወሰደው እርምጃ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ስድስት (6) መድረሱን የሱዳን ዶክተሮች ማዕከላዊ ኮሚቴ አስታወቀ።

ዛሬ በነበረው ሰልፍ የተገደለው 6ኛ ሰው በባህሪ ከተማ ሲሆን ህፃን ልጅ እንደሆነና ከጀርባው በጥይት ተመቶ እንደተገደለ ኮሚቴው ገልጿል።

እስካሁን ድረስ የሱዳንን ወታደራዊ መንግስት መቃወም ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ (ጥቅምት 25/2021) የተገደሉ ህፃናት 18 ደርሰዋል ፤ አጠቃላይ ሟቾች 109 ደርሰዋል።

ዛሬ ሱዳናውያን በመፈንቅለ መንግስት የሀገሪቱን ስልጣን የተቆጣጠሩት የጦር ሰራዊት አዛዥ ሌ/ጄኔራል አብደል ፈታህ አል-ቡርሃንን በመጥቀስ " የቡርሃን አገዛዝ ይውደቅ ፤ ብንሞትም እንኳን ወታደሩ አይገዛንም " ሲሉ ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ ነው የዋሉት።

@tikvahethiopia
#ቹ_የቋንቋ_ትምህርት_ቤት

በዓለም በስፋት (በተናጋሪ ብዛት) ከሚነገሩ ቋንቋዎች በአንደኝነት የሚቀመጠውን፣ የተባበሩት መንግስታት የስራ ቋንቋ የሆነውን፣ ቻይንኛ ቋንቋን ይማሩ!!

ቹ * ቻይንኛ እና ቻይንኛ ብቻ የሚማሩበት የከተማችን የቋንቋ ት/ቤት ነው፡፡
*ለተማሪዎች በክረምት ወቅት የሚሰጥ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

አድራሻ፡
*ቦሌ፡ ፋንቱ ሱፐር ማርኬት አካባቢ፣ ሳይ ኬክ ቤት ያለበት ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
*ስታድየም፡ ትንሸዋ ስታድየም ጀርባ፣ ናሽናል ታወር ፣ 3ኛ ፎቅ
*አያት 49 የአየር መንገድ ቤቶች ፊት ለፊት ማይ ፕላዛ ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ በ 0947202020 ይደውሉ፡፡
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ " 10 ሰዓት ተኩል ላይ ነዳጁን ማራገፋቸውን ሪፖርት ካላደረጉ ርምጃ ይወሰዳል " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ከጂቡቲ ተነስተው አዲስ አበባ እና የተለያዩ ዋና ከተሞች መድረስ የነበረባቸው 200 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በየሠፈሩ ተደብቀው መገኘታቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰዓረላ አብዱላሂ በሰጡት መግለጫ " በተለይ…
#Update

ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ትናንት እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ ወደየመዳረሻ ከተሞች ገብተው የጫኑትን ነዳጅ እንዲያራግፉ ያንን ካላደረጉ ግን እንዲወረሱ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።

ትላንት ነዳጁን እንዲያራግፉ ማሳሰቢያ ከተሰጣቸው 200 ቦቴዎች መካከል እስካሁን ትዕዛዙን የፈፀሙት 22 ብቻ ናቸው ተብሏል።

ከመካከላቸው 18ቱ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን 3ቱ ዱከም፣ 1ዱ ሞጆ፣ 1ዱ አዳማና ሌላ 1 ቦቴ ቢሾፍቱ ከተማ ገብተው ማራገፋቸው ተነግሯል፡፡

ምናልባት ቦቴዎች ደርሰው ግን ሪፖርት ያላደረጉ የክልል ከተሞች ካልተገኙ በቀር ቀሪዎቹ 180 የሚጠጉት ቦቴዎች የጫኑን ነዳጅ መንግስት በውሳኔው መሰረት #ይወርሳል ተብሏል፡፡

ከጅቡቲ የተነሱና ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ አዲስ አበባና ወደ ተለያዩ መዳረሻ ቦታዎቻቸው ገሚሱ ከቀናት በፊት፤ ገሚሱ ከሳምንት በፊት መድረስ የነበረባቸው ቢሆንም 200 ያህሉ በየጥጋጥጉ ተደብቀው ተገኝተዋል።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዳሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ፥ እስከ ትናንት ቀኑ 10፡30 ድረስ ወደየመዳረሻቸው ደርሰው ነዳጁን አራግፈው ሪፖርት ካላደረጉ እንደሚወረሱ ለባለቤቶቹ መነገሩን ያስታወሱት ዳይሬክተሯ ዛሬ ሪፖርቱ ተጣርቶው ውሳኔው ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

እንዲህ ባለ አሻጥር ምክንያት ለአዲስ አበባ ከተመደወበው ኮታ 1/3ኛ ያህሉ ብቻ ናፍጣ እየገባ ስነበር ከሰሞኑ በከተማዋ የተከሰተውን እጥረትም አንስተዋል፡፡

ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑትን መረጃቸውን ለፍትህ ሚኒስቴር ልከን #ክስ እንዲመሰረትም እናደረጋለን ብለዋል።

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ /ቪድዮ ፦ በአዲስ አበባ ከተማ ረጃጅም የታክሲ ሰልፎች እየተስተዋሉ ነው። ነዋሪዎች ታክሲ አግኝተው ወደሚፈልጉት ጉዳይ ለመሄድ ረጅም ሰዓት ሰልፍ ለመጠበቅ ሲገደዱ ተስተውሏል። ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በከተማይቱ እየጣለ ያለው ከባድ ዝናብ በመሆኑ ሁኔታውን አስቸጋሪ አድርጎታል። በተመሳሳይ በማደያዎች ላይ ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች ታይተዋል ፤ መልዕክታቸውን የላኩ የታክሲ አገልግሎት…
#AddisAbaba

የኢትዮጲያ ነዳጅ ማደያዎች ማህበር ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሰጠው ቃል ፤ የሚታየውን የነዳጅ ሰልፍ ለመቅረፍ እንዲሁም የነዋሪዎችን እንግልት ለማስቀረት የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች ( ታክሲዎችና ሃይገሮች) ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ነዳጅ እንዲያገኙ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል።

" እየተስተዋለ ያለው የህዝቡ መጉላላት አሳስቦኛል " ያለ ሲሆን ያለውን ረጃጅም የትራንስፖርት ሰልፎች ፋታ ለመስጠት እና የህዝብ ትራንስፖርት ችግሩን ለማቃለል የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎች ቅድሚያ እንዲሰጣቸው ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

የማህበሩ ቦርድ አባል አቶ ደሳለኝ አበባየሁ፣ በየማደያዎቻችን አሁንም የተሸከርካሪ ሰልፎች እንደቀጠሉ ናቸው ያሉ ሲሆን የህዝብን እንግልት ለመቀነስ በማሰብ ማህበሩ ይህንን ለመተግበር መወሰኑን ገልጸዋል።

ይህ እቅድ የህዝቡን ችግር የሚፈታ በመሆኑም የመንግስትን እና የፖሊስን ድጋፍ ካገኘን በየማደያዎቹ አሰራሩ ይተገበራል ሲሉ ተናግረዋል።

ማህበሩ አሁን ካለው የነዳጅ ችግር ጋር በተያያዘ ከሌሎች ዘርፎች በበለጠ ለህብረተሰቡ ትኩረት መሰጠት እንደሚገባው በማመን ያቀረበዉ ምክረሃሳብ መሆኑን ገልጿል፡፡

አሽከርካሪዎች እና የመንግስት አካላት ይህንኑ እንዲረዱም መጠየቁን ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወንጀል ላይ ተሳትፎ ያላቸውን አካላት በመለየት ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለማድረግ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየሰራን ነው " - FIS የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ አካላት በአጭር ጊዜ ውስጥ ‘ትርፋማ እናደርጋለን‘ በሚል በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች በሚያደርጉት የቅስቀሳ ተግባር ከህብረተሰቡ በርካታ ገንዘቦችን በተለያዩ የክፍያ አማራጮች እየሰበሰቡ እንደሆነ ገልጿል።…
" ለህግ አካላት ጠቁሙ "

በ " FIAS " ገንዘባቸውን ያጡ ለህግ አስከባሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጡ ጥሪ ቀርቧል።

የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ለኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሰጠው ቃል ፤ FIAS በተባለው የኦንላይን ማጭበርበሪያ ድርጊት ገንዘባቸውን ያጡ ለህግ አካላት ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበሩ ጠይቋል።

በኦንላይን የማጭበርበር ድርጊቶች የሚፈፅሙ አካላት ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ከብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ተቋም ጋር በጋራ እየሰራው ነው ብሏል።

ገንዘብ ሰብሰበው በተሰወሩት ላይ ከህግ አስከባሪ አካላት ጋር የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ያለው ተቋሙ በተለያዩ መንገዶችን ገንዘብ የሰበሰቡትን አካላት ሁኔታው እስኪጣራ የባንክ ሂሳባቸው እንዳይንቀሳቀስ የሚደረግበት አግባብ መኖሩን አመልክቷል።

አሁን ላይ አጠቃላይ የወንጀል ምርመራ ሂደቱ በጅምር ላይ ያለ በመሆኑ ጉዳዩ ተጣርቶ እስኪያበቃ በዝርዝር መረጃ ለማቅረብ እንደሚያስቸግር አገልግሎቱ አስረድቷል።

ህብረተሰቡ የማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም የሚሰሩ ስራዎች ላይ ሲሳተፍ በቅድሚያ የብረውት የሚሰሩት አካላት በኢትዮጵያ ህጋዊ እውቅና ያላቸው መሆኑን ትክክለኛ ማንነታቸውን እና አድራሻቸውን ማረጋገጥ እንደሚገባ አስገንዝቧል።

ያለምንም ስራ እንደቀልድ የሚሰበሰብ ሃብት ሊኖር እንደማይችል በመገንዘብም መሰል ስራዎች ላይ በጥንቃቄ መንቀሳቀስ ይገባል ሲል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ለቴሌቪዥን ጣቢያው በሰጠው ቃል አሳስቧል።

@tikvahethiopia
ቅዱስ ጊዮርጊስ🏆

ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሆነ።

አንጋፋው የስፖርት ክለብ ቅዱስ ጊዮርጊስ የዘንድሮው የውድድር ዘመን የኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ አሸናፊ ሆኗል።

ተጨማሪ መረጃዎችን እና ፎቶዎችን በቲክቫህ ስፖርት https://publielectoral.lat/+VvwzStMNcNHmhK0x ይከታተሉ።

@tikvahethsport
#Asossa | የተባበሩት ማደያ ንግድ ፈቃድ ተሰረዘ።

በህገ ወጥ መንገድ ነዳጅና ቤኒዚን ሲያሰራጭ በተገኘው የተባበሩት ማደያ ላይ እርምጃ መወሰዱን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አስታወቀ።

የማደያው ንግድ ፍቃድ ሙሉ በሙሉ የተሰረዘ መሆኑንም ቢሮው ገልጿል፡፡

ላለፉት ጊዜያት ከህጋዊ አሰራር ባፈነገጠ መልኩ ሲሰራ የነበረው የተባበሩት ማደያ ወደ ህጋዊ መስመር ገብቶ ህብረተሰቡን እንዲያገልገል በቃልና በጹሁፍ ማስጠንቀቂ ቢሰጠውም ማስጠንቀቂያውን ወደ ጎን በመተው በህገ-ወጥነት በመቀጠሉ የተነሳ የንግድ ፍቃዱ ሙሉ በሙሉ መሰረዙን ቢሮው አሳውቋል።

ከዚህ በፊት ለታፍ ማደያም ማስጠንቀቂያ መስጠቱ የተገለፀ ሲሆን ቢሮው በተሰጠው ስልጣን መሰረት በህገ-ወጦች ላይ የሚወስደውን ዕርምጃ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል።

አሶሳ ውስጥ 7 ማዳያዎች ያሉ ሲሆን በአገልግሎታቸው ህብረተሰቡን ማርካት አልቻሉም ተብሏል።

#BGMMA

@tikvahethiopia
#Sudan

ሱዳን በጋረጠችው የፀጥታ ችግር ሳቢያ በምዕራብ አርማጭሆ አንድ ጋሻ የሚጠጋ የእርሻ መሬት ለ1 ዓመት ያህል ሳይታረስ መቆየቱ ተገልጿል።

የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ተሻግረው መግባት ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ነው መሬቱ ያልታረሰው።

የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ም/ል ኃላፊ ደሴ ዘውዓለ ለአሐዱ በሰጡት ቃል፤ በምዕራብ አርማጭሆ ኢንቨስትመንት ቀጠና በስፋት ጥጥ፣ አኩሪ አተር፣ ማሽላና ሰሊጥ ይመረታል ብለዋን።

በ2013/14 የምርት ዘመን በአካባቢው የእርሻ ስራ ማከናወን ባለመቻሉ በርካታ ገንዘብ ስለመታጣቱን አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይ በዞኑ መተማ ወረዳ በሱዳን ኃይሎች ሳቢያ በ2013 ዓ.ም ከእርሻ ስራ የወጡ 76 ባለሃብቶች መኖራቸውን የወረዳው ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ ምህረቱፍቃድ ገላው ተናግረዋል፡፡

የሰሞኑን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ ግን ከእርሻ ስራቸው የተፈናቀሉ ባለሃብቶች አለመኖራቸውን አስረድተዋል፡፡

በወረዳው ደለሎ በሚባለው የኢንቨስትመንት ቦታ ከሱዳን የሚተኮሰው መሳሪያ በእርሻ ስራ ላይ #ከስጋት ባለፈ ያስከተለው ጉዳት እንደሌለ ገልፀዋል።

የሚተኮሰው መሳሪያ የሚያርፈው ከኢንቨስትመንት ስፍረው በ500 ሜትር ርቀት ላይ መሆኑን ነው የጠቀሱት፡፡

በመተማ ወረዳ በ3 የኢንቨስትመንት ቀጣና 256 ባለሃበቶች ተሰማርተው የቆዩ ቢሆንም ሱዳን ገፍታ በመምጣቷ ሳቢያ በአሁኑ ወቅት 76ቱ ከስራ ውጭ ናቸው፡፡

የሱዳን ኃይሎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ከገቡበት ዕለት አንስቶ እስካሁን በምዕራብ ጎንደር ዞን 276 የሚደርሱ ባለሃብቶች ከስራቸው ተፈናቅለዋል።

መንግስት የጉዳዩን አሳሳቢነት በመመልከት የተለያዩ ዲፕሎማሲያዊ ስራዎችን በመስራት የተስተጓጎሉ የእርሻ ስራዎች እንዲቀጥሉ ማድረግ እንደሚገባው የወረዳው ባለስልጣናት ጥሪ ማቀረባቸውን አሐዱ ቲቪ ዘግቧል።

@tikvahethiopia