TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ " 10 ሰዓት ተኩል ላይ ነዳጁን ማራገፋቸውን ሪፖርት ካላደረጉ ርምጃ ይወሰዳል " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ከጂቡቲ ተነስተው አዲስ አበባ እና የተለያዩ ዋና ከተሞች መድረስ የነበረባቸው 200 ነዳጅ ጫኝ ቦቴዎች ከአዲስ አበባ ውጪ በየሠፈሩ ተደብቀው መገኘታቸውን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታወቀ። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሰዓረላ አብዱላሂ በሰጡት መግለጫ " በተለይ…
#Update

ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ትናንት እስከ ቀኑ 10፡30 ድረስ ወደየመዳረሻ ከተሞች ገብተው የጫኑትን ነዳጅ እንዲያራግፉ ያንን ካላደረጉ ግን እንዲወረሱ ውሳኔ መተላለፉ ይታወሳል።

ትላንት ነዳጁን እንዲያራግፉ ማሳሰቢያ ከተሰጣቸው 200 ቦቴዎች መካከል እስካሁን ትዕዛዙን የፈፀሙት 22 ብቻ ናቸው ተብሏል።

ከመካከላቸው 18ቱ አዲስ አበባ የገቡ ሲሆን 3ቱ ዱከም፣ 1ዱ ሞጆ፣ 1ዱ አዳማና ሌላ 1 ቦቴ ቢሾፍቱ ከተማ ገብተው ማራገፋቸው ተነግሯል፡፡

ምናልባት ቦቴዎች ደርሰው ግን ሪፖርት ያላደረጉ የክልል ከተሞች ካልተገኙ በቀር ቀሪዎቹ 180 የሚጠጉት ቦቴዎች የጫኑን ነዳጅ መንግስት በውሳኔው መሰረት #ይወርሳል ተብሏል፡፡

ከጅቡቲ የተነሱና ነዳጅ የጫኑ ቦቴዎች ወደ አዲስ አበባና ወደ ተለያዩ መዳረሻ ቦታዎቻቸው ገሚሱ ከቀናት በፊት፤ ገሚሱ ከሳምንት በፊት መድረስ የነበረባቸው ቢሆንም 200 ያህሉ በየጥጋጥጉ ተደብቀው ተገኝተዋል።

የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ዳሬክተር ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ፥ እስከ ትናንት ቀኑ 10፡30 ድረስ ወደየመዳረሻቸው ደርሰው ነዳጁን አራግፈው ሪፖርት ካላደረጉ እንደሚወረሱ ለባለቤቶቹ መነገሩን ያስታወሱት ዳይሬክተሯ ዛሬ ሪፖርቱ ተጣርቶው ውሳኔው ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል።

እንዲህ ባለ አሻጥር ምክንያት ለአዲስ አበባ ከተመደወበው ኮታ 1/3ኛ ያህሉ ብቻ ናፍጣ እየገባ ስነበር ከሰሞኑ በከተማዋ የተከሰተውን እጥረትም አንስተዋል፡፡

ችግሩ እንዲፈጠር ምክንያት የሆኑትን መረጃቸውን ለፍትህ ሚኒስቴር ልከን #ክስ እንዲመሰረትም እናደረጋለን ብለዋል።

(ሸገር ኤፍ ኤም 102.1)

@tikvahethiopia