TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update 2 ጉዳዮች ከጋምቤላ፦ ዛሬ የጋምቤላ ክልል ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አጉቱ አዲንያግ በወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር። በዚህም ክልሉ ንፁሃን ላይ የሚደርስን ጉዳት ለመቆጣጠር ከፀጥታ ኃይሎች በቅንጅት እየሰራ ነው ብለዋል። ኃላፊው በከተማይቱ ብሄርን መሰረት አድርጎ ጥቃት አልተፈፀመም ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የሚነገረው ወሬ ሁሉ ከእውነት የራቀ ነው ብለዋል። ነገር ግን…
ጋምቤላ ክልል ፡ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ከሕግ አግባብ ውጭ የተፈጸሙ የኃይል እርምጃዎች

ሰኔ 7 ቀን 2014 ዓ.ም. በጋምቤላ ከተማ፣ ጋምቤላ ክልል ከጠዋት እስከ ምሽት የቀጠለ ግጭት እና የፀጥታ እና የደኅንነት ችግርን ተከትሎ ለአንድ ቀን የከተማዋ የመንግሥት አገልግሎቶች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና ሌሎችም አገልግሎቶች ተቋርጠው መዋላቸው ይታወሳል።

ጥቃቱ በኦሮሞ ነጻነት ግንባር (በተለምዶ ኦነግ ሸኔ) እና በጋምቤላ ነጻነት ግንባር ታጣቂዎች የተከፈተ እንደነበር እና ክስተቱ በቁጥጥር ሥር እንደዋለ የክልሉ መንግሥት አሳውቋል።

በዕለቱ የመንግሥት የፀጥታ አካላት በወሰዱት እርምጃ የከተማዋ ፀጥታ የተረጋጋ እና በአሁኑ ወቅት የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት በከተማው የሚገኝ ቢሆንም እስከ አሁንም ድረስ የተሟላ መረጋጋት አለመስፈኑን፣ የነዋሪዎች የእለት ተዕለት እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ አለመጀመሩን እና በተለይም የንግድ አካባቢዎችን ጨምሮ በአንዳንድ ስፍራዎች ዘረፋ እንደተፈጸመ ነዋሪዎች ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስረድተዋል። 

በተጨማሪም ከሰኔ 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ በመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች (በክልሉ ልዩ ኃይል እና መደበኛ ፖሊስ) በተወሰዱ የኃይል እርምጃዎች ምክንያት ነዋሪዎች ለተለያዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች እየተጋለጡ መሆናቸውን እና ከሕግ ውጭ ግድያ ስለመፈጸሙ ለኢሰመኮ መረጃዎች እየደረሱት ይገኛል።

በተለይም በጥቃቱ ተሳትፈዋል ወይም ተባብረዋል ተብለው በተጠረጠሩ ግለሰቦች ላይ #ቤት_ለቤት በመሄድ ጭምር ግድያዎች እንደተፈጸሙ ኢሰመኮ ከምስክሮችና የተንቀሳቃሽ ምስል ማስረጃዎች ጭምር ካሰባሰባቸው መረጃዎች ለመረዳት ችሏል። 

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የሰዎችን ደኅንነትና የከተማዋን ሰላም ማረጋገጥ ቀዳሚው ተግባር መሆኑን አስታውሰው፣ ይህንን ተግባራዊ ለማድረግ የሚወሰዱ እርምጃዎች በሙሉ የሰብአዊ መብቶችን መርሆች ሊከተሉ እንደሚገባ አሳስበዋል።

በተለይ የፀጥታ ኃይሎች ሕይወት ሊያጠፋ ከሚችል ተመጣጣኝ ያልሆነ የኃይል እርምጃ እንዲቆጠቡና በፀጥታ ኃይሎች የተወሰዱ ሕገ ወጥ ተግባራት ላይ በአስቸኳይ ማጣራት ተደርጎ ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን
ሰኔ 10 ቀን 2014 ዓ/ም

@tikvahethiopia
ያላየነው ብዙ ጭካኔ ይኖር ይሁን ?

በርካቶች በጋምቤላ ተቀርፆ በተሰራጨው ጨካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ቪድዮ የተሰማቸውን ሀዘን በአግባቡ ሳይወጡ ዛሬ ደግሞ አንድ ቀኑ ሆነ አድራሻው የት እንደሆነ የማይታወቅ የጅምላ ርሸና ቪድዮ ተሰራጭቷል።

ለጊዜው ድርጊቱ መቼ .. ? የት ? እንዴት ? ተፈፀመ ስለሚለው ማወቅ ቢያዳግትም ከዚህ ቀደም እንዳየናቸው እጅግ በጣም ዘግናኝ እና ህጋዊ ያልሆነ የጭካኔ ተግባር ጋር ተመሳሳይ ነው።

ቀኑና ቦታው የማይታወቀው ቪድዮ በርከት ያሉ የታጠቁ ፤ የፀጥታ ኃይል ልብስም የለበሱ ፤ አንዳንዶቹ ጭንቅላታቸው ላይ ጥቁር ሻሽ ያሰሩ ሰዎች በአይሱዙ መኪና ተጭነው የነበሩ ሰዎችን እየቀጠቀጡ እያስወረዱ የጥይት እሩምታ ሲያዘንቡባቸው ይታያል።

ቪድዮውን የቀረፀው ሰው ደግሞ በጥይት ከሚደበድቡት ሰዎች አንዱ መሆኑን ንግግሩ በግልፅ ያስረዳል።

ጉዳዩ እና ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሰዎቹን በህግ አግባብ መጠየቅ አይቻልም ? ወደ ህግ ፊት ማቅረብ አይቻልም ነበር ? በቪድዮ እየቀረፁ የዚህን ያህል ጭካኔ ሰው ላይ መፈፀሙ ምን ይፈይዳል ?

ማነው ስለዚህ ጉዳይ ወጥቶ መቼ ፣ የት ፣ እንዴት ተፈፀመ ስለሚለው የሚያብራራው ? የትኛው አካል ነው ጉዳዩን የሚያስረዳ ? እንዲህ ያደረጉ ሰዎች ምን ተደረጉ ? በጥይት የተደበደቡትስ ፍትህ አገኙ ?

ትልቁ ጥያቄ #የፍትህ_ተቋማት መኖራቸው ፋይዳው ምንድነው ?

ባለፉት በርካታ ወራት ብዙ የጭካኔ ተግባራት አይተናል ፤ አሁንም ማየታችን ቀጥለናል፤ በቪድዮ እና በፎቶ ተቀርፀው ያልተቀመጡ እንጂ በርካታ ህጋዊ ያልሆኑ ከሰውነት ተራም የወጡ ድርጊቶች ይኖራሉ ፤ ጊዜ እየጠበቁ ይወጡ ይሆናል።

አንዳንዴ ምነው በዚህ ጊዜ ባልተፈጠርን ጭምር የሚያስብል ነው።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA

ሮይተርስ ባወጣው የምርመራ ሪፖርት " በሺሕዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች፣ ያለፍርድ በጊዜያዊ እስር ቤቶች ተይዘው ይገኛሉ " ብሏል።

እንደ ምርመራ ሪፖርቱ በአሁኑ ወቅት ላይ 9‚000 የሚኾኑ ተወላጆች በእስር ቤቶቹ ሲገኙ፣ ቢያንስ 17 እስረኞች ለኅልፈት ተዳርገዋል፡፡

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በህወሓት መካከል የሚካሔደው ጦርነት 19 ወራትን በአስቆጠረበት ኹኔታ፣ 3‚000 የሚሆኑ እስረኞች፣ በሚዛን ተፈሪ ከተማ በሚገኙና በእጅጉ በቆሸሹ 18 የእስር ቤት ክፍሎች ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ ብሏል ሪፖርቱ።

በተመድ (UN) እንደተገመተው መንግሥት ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ተከትሎ ከኅዳር እስከ የካቲት ባሉት ወራት 15,000 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች ተይዘዋል።

ሮይተርስ ምርመራ ሪፖርት በበኩሉ ከ17 የቀድሞ እስረኞች እና በሳተላይት ፎቶ ተደግፎ ባደረገው ማጣራት፣ ያለፍርድ ተይዘዋል ያላቸው እስረኞች ብዛት ተመድ ከሚገምተው ቢያንስ በ3‚000 እንደሚበልጥ ተመልክቷል።

ሪፖርቱ ፤ መንግሥት አብዛኞቹ እስረኞች ተለቀዋል ቢልም 9,000 የሚሆኑ የትግራይ ተወላጆች አሁንም ታስረው ይገኛሉ።

አብዛኞቹ የእስር ቦታዎች ለሌላ ተግባር የተሠሩ፣ ጠባብና የቆሸሹ ናቸው ይላል የምርመራው ሪፖርት ። ሪፖርቱ በመቀጠል የእስረኞቹ አያያዝም ዓለም አቀፍ ሥርዓትን ያልተከተለ ነው ብሏል።

ያንብቡ

#አማርኛhttps://telegra.ph/Reuters-Amh-06-18

#እንግሊዘኛhttps://www.reuters.com/investigates/special-report/ethiopia-conflict-prisoners/

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AmharaBank የአማራ ባንክ ነገ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ሥራውን በይፋ ይጀምራል። ባንኩ ነገ በይፋ ስራ የሚጀምርበትን የምረቃት ስነስርአት ከጥዋት 3:00 ጀምሮ ለገሃር በሚገኘው ዋናው መስሪያ ቤት ያካሂዳል። ነገ ቅዳሜ ሰኔ 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሚያካሂደውን የምርቃ ስነስርዓት በማስመልከት በልዩ ሁኔታ ለአዲስ አበባ እና ዙሪያው #አንበሳ አውቶቡስ ተጠቃሚዎች በሙሉ የሙሉ ቀን (ከጠዋቱ…
ፎቶ ፦ አማራ ባንክ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ሥራውን በይፋ ጀምሯል።

የባንኩ የምረቃ እና ስራ ማስጀመሪያ ሰነ ስርዓት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ነው የተካሄደው።

በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፦
- የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ፣
- የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣
- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ባንኩ ከ70 በላይ የሚሆኑ ቅርንጫፎቹ በይፋ ስራ መጀመራቸው ተነግሯል።

አማራ ባንክ ዘመኑ የደረሰበትን የኮር ባንኪንግ ሲስተም በመጠቀም ከ165,000 በላይ ባለአክሲዮኖችን በመያዝ የተመሰረተ ባንክ ነው።

አማራ ባንክ ከቀደሙት ባንኮች ብዙ በመማር በተለይም ዝቅተኛውን የህብረተሰብ ክፍል ለማቀፍ ተደራጅቶ " ከባንክ ባሻገር " በሚል መሪ ቃል የተመሰረተ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የቀጠለው ግድያ በአሜሪካ ! ትላንት አንድ የ23 ዓመት ወጣት በምዕራብ ሜሪላንድ ስሚዝበርግ ገጠራማ አካባቢ በሚገኝ የማምረቻ ድርጅት (Columbia Machine) ተኩስ ከፍቶ 3 ሰራተኞችን ገድሏል። ግለሰቡ በድርጅቱ ውስጥ ሰራተኛ ሲሆን ተኩስ ከፍቶ 3 ሰራተኞችን ለመግደል ያነሳሳው ጉዳይ ምን እንደሆነ አልታወቀም። ተኩስ ከፍቶ ከገደላቸው 3 ሰዎች በተጨማሪ ከአንድ ሜሪላንድ ግዛት ፖሊስ ጋር ተኩስ…
በአሜሪካ የቀጠለው ግድያ !

ደቡባዊ አሜሪካ በምትገኘው በአላባማ ክፍለ ሀገር ጥቂት ሰዎች በተሰባሰቡበት ቤተ ክርስቲያን ታጣቂ ተኩስ ከፍቶ 3 ሰዎች ገድሏል።

ባለሥልጣናት በርሚንግሃም ከተማ አቅራቢያ በሚገኝ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ጥቃቱን በማድረስ የተጠረጠረው ማንነቱ ያልታወቀ ሰው ተይዟል ብለዋል።

አሜሪካ ውስጥ ሰሞኑን የመሳሪያ ጥቃት በተከታታይ መድረሱ የመሳሪያ ቁጥጥር ለውጥ እርምጃን አስፈላጊነት የሚመለከተውን ክርክር መቀስቀሱን ቪኦኤ ዘግቧል።

ባለፈው ወር ኒው ዮርክ ባፈሎ ከተማ ውስጥ በሚገኝ የምግብ እና ሸቀጣ ሸቀጥ መደብር በዘረኛ ጥቃት አስር ጥቁር አሜሪካውያን ተገድለዋል።

ከዚያም ወዲህ ቴክሳስ ዩቫልዴ ከተማ ትምህርት ቤት ውስጥ ተኩስ የከፈተ አጥቂ አስራ ዘጠኝ ተማሪዎች ጨመሮ ሃያ አንድ ሰዎች ገድሏል።

በተጨማሪ ከሳምንታት በፊት በተለያዩ ከተሞች በተከፈቱ ተኩሶች እና ጥቃቶች 9 ሰዎች ሲገደሉ በርካቶች መቁሰላቸው እንዲሁም በምዕራብ ሜሪላንድ ገጠራማ አካባቢ በሚገኝ የማምረቻ ድርጅት ተኩስ ተከፍቶ 3 ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
#ማሳሰቢያ📣

" ከሚመለከታቸው የጸጥታ አካላት ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ ነው " - የደብረ ማርቆስ ፖሊስ መምሪያ

በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ማንኛውም ግለሠብ ከፀጥታ ሀይሎች ውጭ ያሉ ግለሠቦች ያለበቂ ምክንያት በከተማ ውስጥ መሣሪያ ይዞ መንቀሳቀስ የተከለከለ መሆኑን የከተማው ፖሊስ አሳስቧል።

መሣሪያን በመዝናኛ ቦታዎች ጨምሮ በሌሎች አካባቢዎች ያለበቂ ምክንያት ይዞ መንቀሳቀስ የፀጥታ ሀይሉን የሚያዘናጋ እና እኩይ ተግባር ያላቸውን ግለሰቦች ለይቶ ለመቆጣጠር የማያስችል ነው ተብሏል።

ከዚህ ባለፈ የጸጥታ ሀይሉ የህግ ማስከበር ስራውን ለመስራት እንቅፋት እንደሆነበትና የተዝረከረከ የጦር መሣሪያ አያያዝ ለከተማው ህዝብ ደህንነት ስጋት እየሆነ በመምጣቱ በህግ ማስከበር ስራ ላይ ከተሠማራ የጸጥታ ሀይል ውጪ ከሚመለከተው አካል ፈቃድ ሳያገኝ በየትኛውም በከተማው ክልል ውስጥ በማንኛውም ሰአት መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እና ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይ ፦
- በአልጋ ድርጅቶች እና ሆቴሎች ፣
- በወለል ቤቶች ፣
- በዶርም ፣
- በመኖሪያ ቤት በእንግድነት የሚመጡ ግለሠቦች መሣሪያ ይዘው የመጡበትን ጉዳይ ቅድሚያ ለፖሊስ እውቅና ሳይፈጥሩ እና ፈቃድ ሳያገኙ አገልግሎት ማግኘት የለባቸውም ተብሏል።

የአልጋ ድርጅቶች ፣ ወለል አከራዮች እና የዶርም አከራዮች የተከራዮችን ማንነት እስከ ታጠቁት መሣሪያ ሙሉ አድራሻውን በመመዝገብ በየጊዜው ለፖሊስ ማሳወቅ ይገባቸዋል ተብሏል።

ማህበረሰቡ ከፀጥታ ኃይል ውጭ የጦር መሣሪያ ይዞ የሚንቀሳቀስ አካላትን በሚመለከትበት ግዜ ፦
0587711232 (3ኛ ፖሊስ ጣቢያ)
0587711669 (1ኛ ፖሊስ ጣቢያ)
0581785658 (2ኛ ፖሊስ ጣቢያ) በመደወል ጥቆማ እንዲሰጥ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba ነገ የሚዘጉ መንገዶች !

( ከንጋቱ 11:30 ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:00 ድረስ)

የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በ #መሰቀል_አደባባይ ባዘጋጀው ስፖርታዊ ዝግጅት እና መነሻና መድረሻውን መስቀል አደባባይ በሚያደርገው የ5 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር ምክንያት ነገ እሁድ ሰኔ 12 ቀን 2014 ዓ.ም ከንጋቱ 11 ከ30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወሰዱ መንገዶች ዝግ እንደሚደረጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የሚዘጉት መንገዶች ፦

🛣 ከወሎ ሰፈር መገንጠያ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ደንበል ሲቲ ሴንተር ኦሎምፒያ አደባባይ አካባቢ

🛣 ከመገናኛ ፣ በሃያ ሁለት ወደ መስቀል አደባባይ እንዲሁም ከቦሌ መድሃኒያለም፣ በአትላስ ሆቴል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ኡራኤል ቤተ-ክርስቲያን በሰዓት 50 እና 80 ኪ.ሜ በተፈቀደባቸው በሁለቱም አቅጣጫ

🛣 ከጌጃ ሰፈር ፣ ጤና ጥበቃ፣ ብሄራዊ ቲያአትር የሚወስደው የቀድሞ ደሳለኝ ሆቴል

🛣 ከንግድ ማተሚያ ቤት በኦርማ ጋራዥ በፍል ውሃ ወደ መስቀል አደባባይ ኦርማ ጋራዥ መስቀለኛው ላይ
ከ4 ኪሎ ወደ መስቀል አደባባይ ኮንሰን ወይም ወደ ሸራተን ሆቴል የሚወስደው መንገድ ላይ፡፡

🛣 ከሳር ቤት አካባቢ ለሚመጡ አሸከርካሪዎች አፍሪካ ህብረት ትራፊክ መብራት

🛣 ከፒያሳ አካባቢ በቸርቸር ጎዳና ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ፖስታ ቤት ትራፊክ መብራት ላይ

🛣 ከካዛንቺስ በፍል ውሃ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ እና በተመሳሳይ ካዛንቺስ የትራፊክ መብራት በባምቢስ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ የትራፊክ መብራት ላይ

🛣 ከጎፋ በቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ ወደ ለገሐር አዲሱ መንገድ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ቂርቆስ ቤ/ክ መስቀለኛው ላይ

🛣 ከቄራ ወደ ሜክሲኮ ለሚመጡ አሽከርካሪዎች ጠማማ ፎቅ አካባቢ

🛣 ከጦር ኃይሎች ፣ በልደታ ፣ ፖሊስ ሆስፒታል ወደ መስቀል አደባባይ የሚወሰደው መንገድ ባልቻ ሆስፒታል መስቀለኛ

🛣 ከመርካቶ በበርበሬ በረንዳ ወደ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው አረቄ ፋብሪካ አካባቢ

🛣 ከሳሪስ በጎተራ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ አሸከርካሪዎች አጎና ሲኒማ አካባቢ

🛣 ከጎተራ በመሿለኪያ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚሄዱ አሽከርካሪዎች የቀድሞ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ መንገዱ ይዘጋል።

ህብረተሰቡ የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚጠቁሙት አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀም እና ለትራፊክ ፖሊስ አባላት ትዕዛዝ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል።

ውድ ቤተሰቦቻችን ነገ እሁድ የሚያንቀሳቅሳችሁ ጉዳይ ካለ ከላይ በተገለፀው መረጃ መሰረት እንዳትጉላሉ አማራጭ መንገዶችን ተጠቀሙ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ አማራ ባንክ በዛሬው ዕለት ተመርቆ ሥራውን በይፋ ጀምሯል። የባንኩ የምረቃ እና ስራ ማስጀመሪያ ሰነ ስርዓት ለገሃር በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ነው የተካሄደው። በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ ፦ - የብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ፣ - የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አገኘሁ ተሻገር ፣ - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ የተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት…
#AmharaBank

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ዶ/ር ይናገር ደሴ ዛሬ በዛሬው የአማራ ባንክ ይፋዊ ምረቃና ስራ ማስጀመሪያ ስነስርዓት ላይ የተናገሩት ፦

" አማራ ባንክ ወደ ገጠሩ ማህበረሰብ በመድረስና ከፍተኛ የአክስዮን ድርሻን በመሸጥ እንዲሁም ከፍተኛ የተከፈለ ካፒታል ይዞ የባንክ ኢንዱስትሪውን በመቀላቀል ቀዳሚው ነው።

በቴክኖሎጂ እና በአገልግሎት አሰጣጥም ተወዳዳሪ በመሆን ቀዳሚ መሆን እንዲችል ራሱን ሊያዘጋጅ ይገባል።

ይህ ከሃገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ከሚታሰቡ የውጭ ባንኮች ጋር ጭምር ለመወዳደር ያስችላል።

ወደ ሀገር እንደሚገቡ ከሚጠበቁት የውጭ ባንኮች ጋር ለመወዳደር ትልቅ ዝግጅት ይጠብቀናል። ለዚህም አማራ ባንክን ጨምሮ ሌሎች የኢትዮጵያ ባንኮች ራሳቸውን ሊያዘጋጁ ይገባል።

አማራ ባንክ ይህን የሚያደርግና የቁጠባ ገንዘብ አቅሙን ለማሳደግ የሚችል ከሆነ በአጭር አመታት ውስጥ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል።

... 60 ሚሊዮን ገደማ ኢትዮጵያውያን የተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) ተጠቃሚ ናቸው ፤ አማራ ባንክ የተፋጠነ የሞባይል አገልግሎትን በየደረጃው ለመስጠት መስራት አለበት።

የሞባይል አገልግሎት የሚሰጡ የውጭ ተቋማት በቅርብ ጊዜ የአገልግሎት ፈቃድ ሊያገኙ ይችላሉ፤ በአሁኑ ወቅት ቴሌ ብር ብቻ ነው አገልግሎቱን እየሰጠ የሚገኘው በመሆኑም አማራ ባንክ ቅርንጫፎችን ከመክፈት በዘለለ በቴክኖሎጂ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ወደ ከፍታ ሊወስደው እንደሚችል አስባለሁ "

#ALAIN

@tikvahethiopia