TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ያላየነው ብዙ ጭካኔ ይኖር ይሁን ?

በርካቶች በጋምቤላ ተቀርፆ በተሰራጨው ጨካኔ የተሞላበት አረመኔያዊ ቪድዮ የተሰማቸውን ሀዘን በአግባቡ ሳይወጡ ዛሬ ደግሞ አንድ ቀኑ ሆነ አድራሻው የት እንደሆነ የማይታወቅ የጅምላ ርሸና ቪድዮ ተሰራጭቷል።

ለጊዜው ድርጊቱ መቼ .. ? የት ? እንዴት ? ተፈፀመ ስለሚለው ማወቅ ቢያዳግትም ከዚህ ቀደም እንዳየናቸው እጅግ በጣም ዘግናኝ እና ህጋዊ ያልሆነ የጭካኔ ተግባር ጋር ተመሳሳይ ነው።

ቀኑና ቦታው የማይታወቀው ቪድዮ በርከት ያሉ የታጠቁ ፤ የፀጥታ ኃይል ልብስም የለበሱ ፤ አንዳንዶቹ ጭንቅላታቸው ላይ ጥቁር ሻሽ ያሰሩ ሰዎች በአይሱዙ መኪና ተጭነው የነበሩ ሰዎችን እየቀጠቀጡ እያስወረዱ የጥይት እሩምታ ሲያዘንቡባቸው ይታያል።

ቪድዮውን የቀረፀው ሰው ደግሞ በጥይት ከሚደበድቡት ሰዎች አንዱ መሆኑን ንግግሩ በግልፅ ያስረዳል።

ጉዳዩ እና ሁኔታው ምንም ይሁን ምን ሰዎቹን በህግ አግባብ መጠየቅ አይቻልም ? ወደ ህግ ፊት ማቅረብ አይቻልም ነበር ? በቪድዮ እየቀረፁ የዚህን ያህል ጭካኔ ሰው ላይ መፈፀሙ ምን ይፈይዳል ?

ማነው ስለዚህ ጉዳይ ወጥቶ መቼ ፣ የት ፣ እንዴት ተፈፀመ ስለሚለው የሚያብራራው ? የትኛው አካል ነው ጉዳዩን የሚያስረዳ ? እንዲህ ያደረጉ ሰዎች ምን ተደረጉ ? በጥይት የተደበደቡትስ ፍትህ አገኙ ?

ትልቁ ጥያቄ #የፍትህ_ተቋማት መኖራቸው ፋይዳው ምንድነው ?

ባለፉት በርካታ ወራት ብዙ የጭካኔ ተግባራት አይተናል ፤ አሁንም ማየታችን ቀጥለናል፤ በቪድዮ እና በፎቶ ተቀርፀው ያልተቀመጡ እንጂ በርካታ ህጋዊ ያልሆኑ ከሰውነት ተራም የወጡ ድርጊቶች ይኖራሉ ፤ ጊዜ እየጠበቁ ይወጡ ይሆናል።

አንዳንዴ ምነው በዚህ ጊዜ ባልተፈጠርን ጭምር የሚያስብል ነው።

@tikvahethiopia