TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተርኪዬ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) ከአንካራ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት በድርጅቱ የቱርክ ሪፐብሊክ የሀገሪቱን ስም ከ "ቱርክ" ወደ "ተርኪዬ" መቀየሩን ዛሬ አሳውቋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቃል አቀባይ ስቴፋን ዱጃሪች ፤ ከቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ለዋና ፀሃፊው አንቶኒዮ ጉተሬዝ የተላከው ደብዳቤ ለሁሉም ጉዳዮች የሀገሪቱ ስም ከ "ቱርክ" ይልቅ "ተርኪዬ" የሚለው…
ቱርክ (ተርኪ) ስሟን ወደ ተርኪዬ መቀየር ለም አስፈለጋት ?

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (UN) በድርጅቱ የቱርክ /ተርኪ ስያሜ ወደ ተርኪዬ መቀየሩን ዛሬ በይፋ አሳውቋል።

ይህ ተርኪዬ የሚለው ስያሜ የቱርክን ሕዝብ ባህል፣ ሥልጣኔ እና ዕሴቶችን በበለጠ የሚወክል አገላለጽ ነው " በማለት ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ባለፈው ወር ተናግረው ነበር።

ለውጡን ተከትሎ TRT የተሰኘው የሀገሪቱ የመንግስት ወዲያው ተግባራዊ አድርጓል።

ሚዲያው ለሀገሪቱ ስያሜ ለውጥ ምክንያት ብሎ ካስቀመጣቸው ነገሮች መካከል " ቱርኪ " የሚለው ስያሜ ምዕራባውያን በዓል ወቅት ለምግብ ከምትቀርበው የዶሮ ዝርያ ጋር መያያዙ እንደሆነ ገልጿል።

በተጨማሪ በኬምብሪጅ የእንግሊዝኛ መዝገበ ቃላት ላይ ለቃሉ ተሰጠው ትርጉም እንደሆነ ተመላክቷል። በመዝገበ ቃላቱ 'ተርኪ' የሚለው ቃል፤ 'ሙሉ በሙሉ ያልተሳካ' ወይም 'ውድቀት የሆነ ነገር' የሚል ትርጓሜን ይሰጣል።

የቱርክ /ተርኪ መንግስት ሀገሪቱን በአዲስ ስያሜ ተርኪዬ ለማስተዋወቅ ዘመቻ ማድረግ የሰነባበተ ሲሆን በአገሪቱ ተመርተው ወደ ውጪ የሚላኩ ሁሉም ምርቶች ላይ አዲሱ ስያሜ እንዲሰፍር ተደርጓል።

ካለፈው ጥር ወር ጀምሮም  "ሄሎ ተርኪዬ" የሚል የቱሪዝም ዘመቻ እየተካሄደ ነው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#Hulugram

አንድ አፕ፣ ብዙ አማራጭ ! በሁሉግራም ይሸምቱ፣ ፎቶዎን ያጋሩ፣ አዲስ ስው ይተዋወቁ!

ሁሉም በሁሉግራም ይቻላል!
Download Hulugram SuperApp 👇

https://play.google.com/store/apps/details?id=plus.ride.huluchat
#ችሎት

6 ሺህ 1 መቶ ብር የወራዊ ደሞዝ ተከፋይ ለነበረ የመንግስት ሠራተኛ በተጭበረበረ መንገድ 69 ሺህ 1መቶ ብር እንዲከፈለው ያደረጉ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ።

የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአቃቤ ህግ ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም የቀረበለት ክስ መርምሮ ውሳኔ መስጠቱን አስታውቋል።

የቅጣት ውሳኔ ያሳለፈው በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ የሙስና ወንጀል ህጎች አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀጽ 13 አንድ ሐ ላይ የተመለከተውን ተላልፈው በተገኙ 3 ግለሰቦች ላይ ነው።

• 1ኛ ተከሳሽ ጌታቸው ሻሜቦ በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የሂሳብ ባለሙያ ፤

• 2ኛ ማርቆስ ሄራሞ ተከሳሽ በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የክፍያ ክፍልና የጥሬ ገንዘብ አስተዳደር ቡድን መሪ፤

• 3ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ታዬ አለሙ በምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት መምህር፤

ለ3ኛ ተከሳሽ ተስፋዬ ታዬ ሊከፈል የሚገባው እና ያልተጣራ ወራዊ ደምወዝ ጣሪያ 6 ሺህ 1መቶ 46 ብር ሆኖ በዚህ ደምወዝ የተጣራ በእጁ ላይ መድረስ የነበረበት 4 ሺህ 7መቶ 12 ብር ከ32 ሳንቲም መሆን ነበረበት።

1ኛ ተከሳሽ ለወረዳው ፋይናንስ ከተሰጠው የክፍያ ትዕዛዝ ውጭ ያለ አግባብ ያልተጣራ የወር ደምወዝ ጣሪያ 69 ሺህ 1መቶ 46 ብር በእጁ የሚደርስ የተጣራ ገንዘብ ደምወዝ መጠን 41ሺህ 6መቶ አራት ብር ከ68 ሳንቲም የሚያገኝ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ የደምወዝ ፔሮል አዘጋጅቷል።

2ኛ ተከሳሽ በበኩሉ የተዘጋጀውን የደምወዝ ፔሮል አጽድቆ ወጪ እንዲሆን አዟል።

3ኛ ተከሳሽ ሊከፈለው የማይገባውን ገንዘብ በልዩነት 36 ሺህ 8 መቶ 92 ብር ከ36 ሳንቲ ለ1 ወር ከምዕራብ ባደዋቾ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሂሳብ ቁጥር ተቀናሽ ተደርጎ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በግለሰቡ የሂሳብ ቁጥር ገቢ ተደርጓል።

ተከሳሾቹ በዋና ወንጀል አድራጊነትና በልዩ ወንጀል ተካፋይነት በመንግሥት ሀብት ላይ ጉዳት በማድረስ ለራሳቸው ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በፈጸሙት የመንግሥት ስራን በማያመች አኳኋን በመምራት የሙስና ወንጀል አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል።

የክሱን ሂደት ሲመረምር የቆየው የሀዲያ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 12/2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾች በምክንያትነት ያቀረቡትን የቅጣት ማቅለያ እና ገንዘቡ ለመንግሥት ተመላሽ መሆኑን ከግንዛቤ በማስገባት ውሳኔ ሰጥቷል።

በዚህ መሠረት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 2 ዓመት እና የ3 ሺህ ብር መቀጮ እንዲሁም 3ኛው ተከሳሽ 1 ዓመት ከ8 ወር ጽኑ እራት እንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል።

ምንጭ፦ የሃዲያ ዞን ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።

እየተቆራረጠም ቢሆን የነበረው የኤሌክትሪክ ኃይል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ተቋርጧል።

በዚህ የኃይል እጦት ደግሞ የትግራይ ትልቁ የህክምና ተቋም አይደር ሪፈራል ሆስፒታል ስራዎቹን ሊቋርጥ ተገዷል።

ሆስፒታሉ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ በነበረው የኤሌክትሪክ አገልግሎት እና በሚያገኘው የነዳጅ አቅርቦት ኃይል እያገኘ መቆየቱን የገለፀ ሲሆን አሁን ላይ ኤሌክትሪክ በመቋረጡ በቂ ነዳጅም ማግኘት ባለመቻሉ አገልግሎት ለማቋረጥ ተገጿል።

የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ክብሮም ገ/ስላሴ ለዶቼ ቨለ ሬድዮ በሰጡት ቃል "በኤሌክትሪክ በሚሰራ ቬንቲሌተር ለሚተነፍሱ የነበሩ ታካሚዎች ይሰጥ የነበረው ህክምና ተቋርጧል። ከቀናቸው በፊት ለተወለዱ ህፃናት ይሰጥ የነበረ ሜካኒካል የትንፋሽ እና ሙቀት የመስጠት አገልግሎት ተቋርጧል። ያለ ኤሌክትሪክ ኦፕሬሽን መስራት አንችልም። ስለዚህ ሆስፒታሉ እንደ ሪፈራል ሆስፒታል ይሰጠው የነበረው አገልግሎት ሁሉ አቋርጧል። ማድረግ የምንችለው ለድንገተኛ አደጋ የመጀመሪያ ደረጃ ድጋፍ መስጠት ወይም መድሃኒት እንዲገዙ ወረቀት ፅፎ መስጠት እንጂ ምርመራ እና ክትትል ማድረግ የለም " ብለዋል።

አክለውም " ይህን ችግር እንዲፈቱልን የሚገባቸው መንግስታዊ ያልሆኑ አለም አቀፍ ድርጅቶች አሉ ለእነሱ አንድ በአንድ እየሄድን ያለውን ችግር ገልፀናል ኤሌክትሪክ ማግኘት የሚያስችለን ነዳጅ ማስገባት የሚችሉ እንደ OCHAና WFP ያሉ ድርጅቶችን አሳውቀናቸው ነበር ይሁንና ያደረጉልን ምንም አይነት ድጋፍ የለም ። ይሄ ትልቅ ሆስፒታል እንዳይዘጋ ለማድረግ ምንም አይነት ምላሽ አለመስጠታቸው ያሳዝናል" ሲሉ አስረድተዋል።

ያንብቡ : telegra.ph/Tig-06-03

@tikvahethiopia
የ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት ፦

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባ በ2015 የፌዴራል መንግስት በጀት ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡

በዚህም መሰረት ለ2015 በጀት ዓመት ለመደበኛ ወጪ ብር 347.12 ቢሊዮን፣ ለካፒታል ወጪ ብር 218.11 ቢሊዮን እንዲሁም ለክልል መንግሥታት ድጋፍ ብር 209.38 ቢሊዮን እና ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ብር 12.0 ቢሊዮን የተያዘ ሲሆን አጠቃላይ የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ብር 786.61 ቢሊዮን ሆኖ ቀርቧል፡፡

ከ2014 በጀት ዓመት በጀት ጋር ሲነጻጸር የብር 111.94 ቢሊዮን ወይም የ16.59 በመቶ እድገት አሳይቷል፡፡

ም/ ቤቱ በቀረበለት የፌዴራል መንግሥት የ2015 በጀት ላይ ከተወያየ በኋላ ግብዓቶችን በማከል ይጸድቅ ዘንድ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የጠ/ሚ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በአዲስ አበባ በመንገድ ግንባታ ምክንያት ዝግ የሚሆን መንገድ !

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከወሎ ሰፈር ወደ ኡራኤል አደባባይ መታጠፍ የሚያስችል የትራፊክ መብራት ኡራኤል ቤተክርስቲያን መዳረሻ አካባቢ ሊተከል እንደሆነ አሳውቋል።

በዚህም ከቅዳሜ ግንቦት 27 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ሰኞ ጠዋት ግንቦት 29 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ከወሎ ሰፈር ወደ ኡራኤል እና ከኡራኤል ወደ አትላስ እና ወደ ወሎ ሰፈር ሚወስዱት መንገዶች ለትራፊክ ዝግ ሆነው ይቆያሉ ብሏል።

አሽከርካሪዎች በተጠቀሱት ቀናት ከወሎ ሰፈር አደባባይ በቦሌ ሩዋንዳ ወደ አትላስ እና ኡራኤል፤ እንዲሁም ከመገናኛ በ22 ወደ ኡራኤልና አትላስ ለሚሄዱ ደግሞ ከጎላጎል ህንፃ በኤድናሞል በኩል ወደ አትላስ የሚወስደውን እና ሌሎች አማራጭ መንገዶችን እንዲጠቀሙ ባለስልጣኑ መልዕክት አስተላልፏል።

@tikvahethiopia
#WFP #ETHIOPIA

የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ወደ ትግራይ እና በግጭት ወደ ተጎዱ አካባቢዎች ኮንቮይዎችን መላክ መቀጠሉን እንደገፋበት አመልክቷል።

በሚያዝያ/ግንቦት በ1,045 የጭነት ተሽከርካሪዎች አማካኝነት 50,000 (ሃምሳ ሺህ) ቶን ምግብ ማቅረብ መቻሉንና 350 ሺህ ሰዎችን በህይወት አድን ምግብ መድረስ መቻሉን ድርጅቱ አሳውቋል።

ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው የማህበረሰብ ክፍሎች ቀጣይነት ያለው የአቅርቦት ፍሰት እንዲኖር እና ድጋፍ እንዲደርሳቸው ለማድረግ ከባለሥልጣናት ጋር እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" እርምጃ ተወስዶባቸዋል " በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የመተማ ወረዳ ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት አስታወቀ። የወረዳው ሰላምና ደህንነት ፅ/ቤት ፥ " የማህበረሰብ እንቅስቃሴ ሲያውኩ የነበሩ ሶስት ጸረ-ሰላም ኃይሎች በጥምር የጸጥታ ኃይል (ልዩ ኃይል ፣ ፀረሽምቅ እና ፖሊስ) ርምጃ ተወስዶባቸዋል " ብሏል። በጣምራ…
#Metema

የመተማ ወረዳ ፖሊስ #ሰው_በማገት_ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ ግለሠቦች በተካሄደ ኦፕሬሽን መመታታቸውን እንዲሁም ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አሳወቀ።

ትላንት በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ መቃ ቀበሌ ልዩ ስሙ " ጎርድም " በተባለው ተራራ በተደረገ ኦፕሬሽን ሰው በማገት ወንጀል ሲፈለጉ የነበሩ 4 ግለሰቦች መመታታቸው እና ቆስለው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።

ፖሊስ ይፋ ባደረገው መረጃ ባዜ ብርሀኑ እና ላቀው የኔሁን የተባሉ ግለሰቦች የተመቱ ሲሆን አያናው አማረ እና ወርቁ ድረስ የተባሉ ግለሰቦች ደግሞ ቆስለው በህግ ጥላ ስር መሆናቸው ተገልጿል።

ከቀናት በፊት በዚሁ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ሰው በማገት ፣ ሰው በመግደል ሲፈለጉ የነበሩ 3 ግለሰቦች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ማስታወቁ ይታወሳል።

በሌላ በኩል ፤ በወረዳው አኩርፈው ሆነ ሸፍተው የሚንቀሳቀሱ ኃይሎች በተደረገው የምህረት አዋጅ እድል ተጠቅመው በሰላም ገብተው ከህብረተሰቡ ጋር በሰላም እንዲኖሩ ፖሊስ ጥሪ ቀርቧል።

@tikvahethiopia
መንገድ ስቶ የወጣ መኪና የ2 ህፃናትን ህይወት ቀጠፈ።

በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ አዶሼና አቱርቸ ቀበሌ ልዩ ስሙ " አሞራ ሜዳ " በሚባል ቦታ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ2 ህፃናት ህይወት ማለፉን የቸሃ ወረዳ ፖሊስ አሳውቋል።

አደጋው የደረሰው በቀን 25/09/2014 ዓ.ም ከምሽቱ 3 ሰዓት ከሆሳዕና ወደ ወልቂጤ በሚወስደው መስመር አረቅጥ ከተማ ገረጋንቲ አራግፎ ሲመለስ የነበረ UD ገልባጭ መኪና የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3 ኢት 33832 መንገድ ስቶ በመውጣቱ ነው።

መንገድ ስቶ የወጣው ተሽከርካሪ አቶ ሀሰን ዱላ የተባሉ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ በመግባት በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

በዚህም ቤት ውስጥ የነበሩ ሶስት ህፃናት ላይ መኪናው በመውጣቱ ምክንያት የ8 አመት ሴት ልጅና የ4 አመት ወንድ ልጅ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል እንደደረሱ ህይወታቸው አልፏል።

አንዱ ህፃን በወልቂጤ ሪፈራል ሆስፒታል ህክምና ላይ ይገኛል።

አሽከርካሪውም ጉዳት ደርሶበት በህክምና ላይ ይገኛል።

መረጃው የቸሀ ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#NewsAlert

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት የተለያዩ ሹመቶች ሰጥተዋል።

በዚሁ መሰረት፥

1. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን - የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር

2. አቶ ካሊድ አብዱራህማን - በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የፕሮጀክቶች ክትትል

3. አቶ ወንድሙ ሴታ - የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

4. አቶ ሄኖስ ወርቁ - የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚከተሉትን ሸመቶች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲያጸድቅላቸው ጠይቀዋል፦

1. ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ዋና ኦዲተር

2. አቶ አበራ ታደሰ - የፌደራል ዋና ኦዲተር መሥሪያ ቤት ምክትል ዋና ኦዲተር

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" የግራ ዓይኑ ስር አብጦ የለበሰው ቲ-ሸርት ተቀዶ አግኝተነዋል " - ታሪኩ ደሳለኝ (የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም) በእስር ላይ የሚገነው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለለኝ ደብደባ እንደተፈፀመበት ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገልጿል። የጋዜጠኛ ተመስገን ወንድም የሆነው ታሪኩ ደሳለኝ ፤ ዛሬ ግንቦት 25/2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ፖሊስ በተለምዶ 3ተኛ ወንድሙን ጋዜጠኛ ተመስገንን ለመጠየቅ ፖሊስ ጣቢያ ተገኝቶ…
#Update

ድብደባ የተፈፀመበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ህክምና መከልከሉን ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ አሳወቁ።

ዛሬ ግንቦት 26/2014 ዓ.ም የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ጠበቃ ሄኖክ አክሊሉ ደንበኛቸውን እንዳነጋገሩት ትላንት ማታ የ3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሀኪም እንዳዩት የአይኑ ስር እብጠት መሻሻል እንዳሰየ ነገርግን በትላንትናው ድብደባ ጎኑ (ribs) እንደተጎዳ ተናግረው ለዚህም " ወጥቶ ህክምና ማግኘት አለበት" በማለት እንዲታከም ለራስ ደስታ ሆስፒታል ሪፈር ፅፋውለት ነበር ብለዋል።

ዛሬ ግንቦት 26 ቀን 2014 ዓ.ም ከቀኑ 5:40 ላይ ወደ ራስ ደስታ ሆስፒታል በአጃቢና በመኪና መሄድ ከጀመረ በኃላ ግን በሬዲዮ መገናኛ በተሰጠ ትዕዛዝ ሆስፒታል ሳይደርስ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንዲመለስ ተደርጓል ሲሉ ጠበቃ ሄኖክ አስረድተዋል።

ጠበቃ ሄኖክ አክለውም ፤ በአሁኑ ሰዓት ጋዜጠኛ ተመስገን በፖሊሶቹ የተመታው ጎኑን (ribs) የህመም ስሜቱ እንዳልታገሰለት ተናግረው ጋዜጠኛ ተመስገን በዚህ የህመም ሁኔታ ውስጥ እያለ ህክምና መከልከሉን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia