TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Mekelle

ላለፉት ዓመታት በጦርነት ውስጥ ያሳለፈችው ትግራይ ከተደረገው የሰላም ስምምነት በኃላ አሁን ላይ በመጠኑም ቢሆን ፊቷን ወደ #ልማት ስራዎች እያዞረች ትገኛለች።

በክልሉ መዲና መቐለ በጦርነቱ ምክንያት ተስተጓግሎ የነበሩ የመቐለ የመንገድ ፕሮጆክቶች ለማስጀመር ጥረት እየተደረገ ነው ተብሏል።

ትላንት መቐለ ከተማ እና ሱር ኮንስትራክሽን አንድ ውል ተፈራርመዋል። የመቐለ ከተማ እና ሱር ኮንስትራክሽን የተፈራረሙት 62 ኪ.ሜ ርዝመት ያለው የአስፓልት እና ጠጠር መንገድ ለመገንባት ነው።

ለዚሁ ፕሮጀክት የስድስት ነጥብ አንድ ቢልዮን ብር በጀት እንደተያዘለት ነው የተነገረው።

ይህ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተስፋ የሚሰጥ እንዲሁም ትግራይን ደግም ለመገንባት በሚደረገው ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ተስፋ ሰጪ ነው ተብሎለታል።

ፕሮጀክቱ ከሁለት እስከ ሶስት አመት ባለው ግዜ ውስጥ ገንብቶ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ በውል ስነስርዓቱ ላይ ስለመገለፁ ድምፂ ወያነ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba 🛫 #Mekelle

ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ትግራይ መቐለ አቅንተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ዛሬ ወደ መቐለ አቅንተዋል።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው ነው ወደ መቐለ የተጓዙት።

ቅዱስነታቸው ወደ ትግራይ፣ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ቦሌ ኤርፖርት ተገኝተው  ከቅዱስነታቸው ቡራኬ መቀበላቸውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልጹ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ምንጭ፦ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልጹ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
#Mekelle

የኢፌዴሪ የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን የባለድርሻ እና አጋር አካላት የውይይት መድረክ #በመቐለ ለመጀመርያ ጊዜ ይካሄዳል።

ኮሚሽኑ ባወጣው መግለጫ የባለድርሻ እና አጋር አካላት መድረክ ለመጀመርያ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በመቐለ እንዲደረግ የተወሰነበት ምክንያት ከሰላም ስምምነቱ ብኋላ ክልሉ ላይ አንፃራዊ  መረጋጋት መፈጠሩ እና በሁለቱም ተስማሚ ወገኖች የመተማመን ጉዳዩ መጎልበቱን ማሰያ ነው ብሏል።

በመድረኩ ለመሳተፍ የተለያዮ ባለድርሻ እና አጋር  አካላት ከፌዴራል መንግስት የተላከ የልኡኳን ቡድን  በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ መሪነት ዛሬ መቐለ ገብቷል።

የፌደራል መንግስቱ ልኡኳን ብድኑ ከጠቅላይ ሚኒስተር ፅህፈት ቤት፣ የሰላም ሚኒስቴር ፣ የመከላከያ ሰራዊት፣ የሰቪክ ማህበራት፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  እንዲሁም ከንግድ ሚኒስቴር እና የተለያዮ ክልሎች ተወካዮች ያካተተ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

#ድምፂወያነ

@tikvahethiopia
#Mekelle

በዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራ ልዑክ መቐለ ገባ።

በጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ የተመራው የጤና ሚኒስቴር ልዑካን ቡድን ዛሬ መቐለ ገብቷል።

ልዑኩ ከክልሉ አስተዳደር ጋር በተለያዩ የጤና ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚነጋገር ይጠበቃል።

ፎቶ ፦ ድምፂ ወያነ

@tikvahethiopia
#Mekelle

የመቐለ ወደብና ተርሚናል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አስታውቋል።

በጦርነት ተቋርጦ የቆየው የመቐለ ወደብና ተርሚናል ወደ መደበኛ አገልግሎት መመለሱ ተገልጿል።

በዚህም መዳረሻቸው መቐለ ወደብና ተርሚናል ለሆኑ ገቢ ጭነቶችን  ከዛሬ ሚያዝያ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ ከመነሻ የባሕር ወደብ ለመቐለ ኦፕሬሽን መክፈት የሚቻል መሆኑ ተነግሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሰላም ልኡካኑ መቐለ ትግራይ ሲደርሱ በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ካብኔ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ አማኑኤል አሰፋ እና ሌሎች የክልሉ አመራሮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ልዑኩ በመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ…
#Mekelle

በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የተመራው የሰላም ልኡክ ዛሬ ከሰአት በተለምዶ " መቐለ 70 ካሬ " ተብሎ በሚጠራው የተፈናቃዮች መጠለያ ጉብኝት አድርጓል።

በጉብኝቱ ተፈናቃዮች " ቅዱስ ሲኖዶሱ ለበዳዮች ወግንዋል " በማለት በድምፅና በፅሁፍ ተቋውሞ ማሰማታቸውን በስፍራው የነበሩ የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ገልጸዋል።

ቅዱስ ፓትሪያርኩ ፤ " በውስጣችሁ የሚሰማችሁን እንኳን ተናገራችሁ " ካሉ በኋላ ፤ " ሰሚ ከተገኘ ወደ ቀያችሁ እንድትመለሱ ለሚመለከተው እንናገራለን " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#Mekelle

" በመቐለ ከተማ ከ184 ሄክታር በላይ የመንግስትና የህዝብ መሬት መጭበርበሩ በጥናት ተረጋግጧል " - የከተማዋ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ

በትግራይ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ከተሞች ህገ ወጥነት ተንሰራፍቶ በርካታ ወንጀሎች መፈፀማቸው የመቐለ ከንቲባ ይትባረክ ኣማሃ ገለፁ።

ከንቲባው ፤ የመንግስትና የህዝብ መሬት ዘረፋና የፀጥታ መደፍረስ ዋነኛ ተጠቃሽ ችግሮች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

የመሬት ወረራው የተካሄደው ለምቶ ወደ ተጠቃሚዎች ለመተላለፈ በተዘጋጀ ፤ በእርሻና በመንግስት ክፍት ቦታ ፤ ከገጠር ወደ ከተማ በተካለለና በተቀሙ የኢንቨስትመንት መሬቶች መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ ፤ " በህገወጥ ተግባሩ 3337 ሰዎች ተሳትፈዋል " ብለዋል።

" በመሬት ወረራው የተሳተፉ ህገወጦች በህግ እንዲጠየቁ የህዝቡ ጥያቄ ጭምር ነው " ያሉት ከንቲባ ይትባረክ " ከእርምጃው በፊት የተወረረው መሬት ማጥናት ፣ ቦታዎቹ የሰነዱ ፋይሎች ድህንነት ማረጋገጥ ተጠናቅቆ ወደ ተግባር ተገብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሳሳቢ የሆነውን የከተማዋ የፀጥታ ጉዳይ ለመፍታት እየተሰራ  መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ በተካሄደው ጥናትና ክትትል በቡድን የሚዘርፉ ፣ ህገ-ወጥ ሕትመት የሚያካሂዱ ፣ የመሬት ፕላን ሰርተው የሚሸጡ ፣ አደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ የፎርጅድ ገንዘብ ማተምያ ማሽንና የተለያዩ ህገ ወጥ ገንዘቦች እጅ በፈንጅ ተይዘዋል ብለዋል።

የመሬት ወረራ ሆነ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራት ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑ ያብራሩት ከንቲባው ህዝቡ መረጃና ሰነዶች ከመስጠት እስከ መመስከር ንቁና ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃውን የመቐለ ቲክቫህ አባል የተላከ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በመቐለ ከተማ በተወረወረ የእጅ ቦምብ የ5 ሰዎች ህይወት አለፈ። ቦምብ ተወርውሮ የሞት አደጋው ያጋጠመው ነሃሴ 18 /2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 8:00 ሰአት ነው። የአይን እማኞች ለቲክቫህ የመቐለ ቤተሰብ እንደገለፁት ፤ የቦምብ አደጋው ያጋጠመው በከተማው ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራው መጠጥ ቤት ነው።  የአይን እማኞቹ አክለው እንደገለፁት ፤ በመጠጥ ቤቱ ሰዎች በብዛት…
#Mekelle

የመቐለ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ትላንት ለሊት 8 ሰዓት ላይ ቀበሌ 15 " ዳዕሮ " በሚባለው መጥጥ ቤት ቦንብ የተወረወረው " በቀድሞ ተሰናባች ታጋይ " በነበረ ግለሰብ መሆኑን ታውቋል።

እንደ ፖሊስ መረጃ ተጠርጣሪው እስካሁን አልተያዘም።

የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊው ኮማንደር ወልዳይ ማውጫ ፤ " ከአሸንዳ በዓል ጋር በተያያዘ በከተማዋ ከፍተኛ የፀጥታ ቁጥጥር ሲደረግ ቆይቷል " ብለዋል።

" በበዓሉ መዝጊያ ቀን ትናንት ግን በከተማዋ ቀዳማይ ወያነ ክፍለከተማ አሳዛኙ የቦንብ ጥቃት ተፈፅሞ ለበርካቶች ሞት እና ጉዳት ምክንያት ሆኗል " ሲሉ ገልጸዋል።

" ጥቃቱን የፈፀመው ግለሰብ ማንነቱ ተለይቷል " ያሉት ኮማንደር ወልዳይ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና በቁጥጥር ስር ለማዋል ክትትል እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

የተወረወረው ኤፍዋን የተባለ የእጅ ቦንብ መሆኑን ፖሊስ አረግጧል። የጥቃቱ አላማም " የግለሰቦች ጠብ " መሆኑን አስረድቷል።

ዓይደር ሪፈራል ሆስፒታል በበኩሉ 20 በቦንብ ጥቃት የቆሰሉ ሰዎች ከሌሊቱ 8 ሰዓት ጀምሮ መቀበሉን ለዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በሰጠው ቃል ገልጿል።

ትላንት ለሊት በተወረወረው ቦንብ 5 ሰዎች መሞታቸውንና በርካቶችም መቁሰላቸውን የመቐለ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል የሆስፒታል ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Mekelle

በመቐለ ቀዳማይ ወያነ ክፍለ ከተማ ቀበሌ 15 " ትላንት ለሊት " ዳዕሮ " ተብሎ በሚጠራ መጠጥ ቤት ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት የቀጠፈውና ለጉዳት የዳረገው ተጠርጣሪ ግለሰብ ስሙ ሙሉጌታ እንደሚባል ታውቋል።

ፖሊስ ግለሰቡ የተሰናበተ የቀድሞ ታጋይ መሆኑንና " በቁጥጥር ስር ለማዋል " ክትትል እየተደረገ መሆኑን ገልጾ ህዝቡ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

ተጠርጣሪው በመቐለ ከተማ በተለይ ቀበሌ 14 ፣ 15 ፣ 16፣ 17 በደንብ ይታወቃል ያሉን የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ፤  የቀድሞ ታጋይና የኮሌኔልነት መአርግ ያለው ጭምር ነው በማህበረ ረድኤት ትግራይ /ማረት/  ሹፌር ሆኖም ሲሰራ ነበር ብለዋል።

ተጠርጣሪው በ2013 ዓ.ም መልሶ ወደ ትጥቅ ትግል መግባቱን በኃላም ከትግል መሰናበቱን የመቐለ ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አመልክተዋል።

ፖሊስ ተሰናባቹን የቀድሞ ታጋይና ቦንብ ወርውሮ የሰዎችን ህይወት ያጠፋውን እንዲሁም መከፍተኛ የአካል ጉዳት የዳረገውም " ሙልጌታ "ን በቁጥጥር ስር ለማዋል ሁሉም እንዲተባበር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia