#Mekelle

" በመቐለ ከተማ ከ184 ሄክታር በላይ የመንግስትና የህዝብ መሬት መጭበርበሩ በጥናት ተረጋግጧል " - የከተማዋ ከንቲባ ይትባረክ ኣምሃ

በትግራይ የነበረውን ጦርነት ተከትሎ በክልሉ ከተሞች ህገ ወጥነት ተንሰራፍቶ በርካታ ወንጀሎች መፈፀማቸው የመቐለ ከንቲባ ይትባረክ ኣማሃ ገለፁ።

ከንቲባው ፤ የመንግስትና የህዝብ መሬት ዘረፋና የፀጥታ መደፍረስ ዋነኛ ተጠቃሽ ችግሮች እንደሆኑ ጠቁመዋል።

የመሬት ወረራው የተካሄደው ለምቶ ወደ ተጠቃሚዎች ለመተላለፈ በተዘጋጀ ፤ በእርሻና በመንግስት ክፍት ቦታ ፤ ከገጠር ወደ ከተማ በተካለለና በተቀሙ የኢንቨስትመንት መሬቶች መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ ፤ " በህገወጥ ተግባሩ 3337 ሰዎች ተሳትፈዋል " ብለዋል።

" በመሬት ወረራው የተሳተፉ ህገወጦች በህግ እንዲጠየቁ የህዝቡ ጥያቄ ጭምር ነው " ያሉት ከንቲባ ይትባረክ " ከእርምጃው በፊት የተወረረው መሬት ማጥናት ፣ ቦታዎቹ የሰነዱ ፋይሎች ድህንነት ማረጋገጥ ተጠናቅቆ ወደ ተግባር ተገብቷል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሳሳቢ የሆነውን የከተማዋ የፀጥታ ጉዳይ ለመፍታት እየተሰራ  መሆኑ የገለፁት አቶ ይትባረክ በተካሄደው ጥናትና ክትትል በቡድን የሚዘርፉ ፣ ህገ-ወጥ ሕትመት የሚያካሂዱ ፣ የመሬት ፕላን ሰርተው የሚሸጡ ፣ አደንዛዥ ዕፅ የሚያዘዋውሩ የፎርጅድ ገንዘብ ማተምያ ማሽንና የተለያዩ ህገ ወጥ ገንዘቦች እጅ በፈንጅ ተይዘዋል ብለዋል።

የመሬት ወረራ ሆነ የሚፈፀሙ ህገወጥ ተግባራት ለመቆጣጠር እየተሰራ መሆኑ ያብራሩት ከንቲባው ህዝቡ መረጃና ሰነዶች ከመስጠት እስከ መመስከር ንቁና ተባባሪ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃውን የመቐለ ቲክቫህ አባል የተላከ ነው።

@tikvahethiopia