TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#AddisAbaba 🛫 #Mekelle

ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ ትግራይ መቐለ አቅንተዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በብፁዕ አቡነ ዮሐንስ የሽኝት ሥነ ሥርዓት ላይ ለመገኘት ዛሬ ወደ መቐለ አቅንተዋል።

ቅዱስነታቸው ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትንና ሊቃውንትን አስከትለው ነው ወደ መቐለ የተጓዙት።

ቅዱስነታቸው ወደ ትግራይ፣ መቐለ ሲጓዙ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ፣ የኒውዮርክ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ቦሌ ኤርፖርት ተገኝተው  ከቅዱስነታቸው ቡራኬ መቀበላቸውን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልጹ ፅ/ቤት አሳውቋል።

ምንጭ፦ የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልጹ ፅ/ቤት

@tikvahethiopia