TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#TechZone

ውፍረትን እና ቦርጭን መቀነስ ይፈልጋሉ? 0929088890
ያሉበት ድረስ ከነፃ ማድረሻ ጋር!              
ሙሉ ከወገብ በላይ(ቦዲ) - 899ብር
የቦርጭ ብቻ -599  ብር
ሙሉ በሙሉ ቦርጭን በአጭር ጊዜ የሚያጠፋ እና
ማራኪ-ቁመና የሚያላብስ ።
ተጨማሪ : የቴሌግራም አድራሻችን ይጎብኙ
( ክልል ከተሞች እንገኛለን ) @አ.አ = ቦሌ መዳሃንያለም
#DStv

አስኳላ-ምዕራፍ 2

በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ሲትኮም

ረቡዕ ማታ 01፡30 በድጋሚ 03:30 እንዲሁም ቅዳሜ ማታ 01:30 እና እሁድ ከሰዓት 10:00 ሰዓት ላይ ይቀርባል፡፡

በአቦል ቲቪ ቻናል ቁጥር (146) ላይ ብቻ ያገኙታል!

https://publielectoral.lat/DStvEthiopiaOfficial
#እንድታውቁት

አትላስ አካባቢ የሚገኘው ነባር ድልድይ በጥገና ስራ ላይ ይገኛል።

የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከአትላስ ወደ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘውን እና 35 ሜትር ርዝመትና 10 ሜትር ከፍታ ያለውን ነባር ድልድይ የድጋፍ ግንብ እየጠገነ ይገኛል፡፡

ይህ ድልድይ ተገንብቶ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ በርካታ ዓመታትን አስቆጥሯል።

አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ወደ ወንዙ በሚለቁት ከፍተኛ መጠን ያለው ደረቅ ቆሻሻ ሳቢያ የወንዙ ተፈጥሯዊ የውሃ ፍሰት እየተስተጓጎለ በመምጣቱ በክረምት ወራት የወንዙ ውሃ ሲጨምር የድልድዩን ተሸካሚ ምሰሶ የሚያቅፈው የድጋፍ ግንብ እንዲቦረቦር ምክንያት እንደሆነ ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

አሁን ላይ ባለስልጣን መ/ቤቱ የድጋፍ ግንብ ጥገና ሥራውን ለማከናወን ያስችለው ዘንድ ከድልድዩ ስር የተከማቸውን ከፍተኛ መጠን ያለውን ደረቅ ቆሻሻ የማንሳት ስራ እያከናወነ መሆኑን አመልክቷል።

መንገዱ ከሚያስተናግደው ከፍተኛ የትራፊክ ፍሰት አንፃር አጭር ጊዜ ውስጥ የጥገና ስራውን ሙሉ ለሙሉ የሚያጠናቀቅ ይሆናል ብሏል።

የጥገና ስራው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ከአትላስ ወደ ኡራኤል የሚጓዙ አሽከርካሪዎች በስፍራው የተቀመጡ ምልክቶችን በማስተዋል ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ እንዲያሽከረክሩ ማሳስቢያ ተላልፏል።

የአካባቢው ማህበረሰብ የጥገና ስራው ከተጠናቀቀ በኋላ ድልድዩ ስር ቆሻሻ ባለመድፋት የጋራ የሆነውን የመንገድ ሀብት በጋራ እንዲጠብቅ መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopia
#Update

በሀርቡ ከተማ ተቋርጦ የነበረውን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመልሶ ተገናኝቷል።

በሀርቡ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተመለሰው ዛሬ ታህሳስ 4 ቀን 2014 ዓ.ም ነው።

የጃማ እና ወረኢሉ ከተሞችን ኃይል ለመስጠት በሚያስችል ደረጃ የጥገና ስራ የተጠናቀቀ መሆኑን ተነግሯል።

#EEU

@tikvahethiopia
#Hayke

ከደሴ 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው ሀይቅ ከተማ ከፍተኛ ጉዳት ካስተናገዱ ከተሞች አንዷን መሆኗን ከአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ያገኘነው መረጃ ያሳል።

በጦርነት ምክንያት በከተማው ላይ የሰዎች ህይወት ጠፍቷል፤ የግልና የመንግስት ንብረቶችን እንዳልነበሩ ሆነዋል፤ በከባድ መሳሪያ የተደበደቡ የሲቪል ሰዎች ቤቶችም ስለመኖራቸውም ተገልጿል።

በከተማይቱ ጨረቃው መንደር (ቀበሌ 02 እና 04) በአንድ ቤት ውስጥ ብቻ 3 ሰዎች ሞተው እዛው ግቢ ውስጥ መቀበራቸውን ነዋሪዎች አሳውቀዋል።

የሀይቅ ከተማ ከህወሓት ወረራ ከተለቀቀች አንድ ሳምንት እየተቃረባት ሲሆን እስካሁን ድረስ በተጣራ መረጃ 48 ንፁሃን ሰዎች መሞታቸውን የከተማይቱ ባለስልጣናት ለሬድዮ ጣቢያው ሪፖርት አድርገዋል።

በተጨማሪ ሆስፒታሎች፣ ት/ቤቶች ሌሎች ህብረተሰቡ የሚጠቀምባቸው አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በውስጣቸው የነበሩ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል።

በሀይቅ ከተማ ብዙዎቹ የመንግስት ተቋማት መረጃ የሚባል ነገር እንዳይኖራቸው ኮምፒውተሮች በጠቅላላ ወድመዋል፤ የተረፉት መዘረፋቸውን የአካባቢው ባለስልጣናት አመልክተዋል።

የተዘረፈው በአብዛኛው በህወሓት ኃይሎች ሲሆን የአካባቢው ህብረተሰብ ንብረቶችን ለማትረፍ ሲል ወደ ቤቱ ይዟቸው የሄዱ አሉ፤ በአንዳንድ የህበረተሰቡ አባላት የተዘረፉም አሉ።

የሀይቅ ከተማ ባለልስጣናት የተዘረፉትን የማስመለስ ስራ እንዲሁም የህወሓት ኃይሎች እንዳይዘርፏቸው በማለት ወደቤት የተወሰዱትን ንብረቶች ለማስመለስ እየተሰራ መሆኑን ለሬድዮ ጣቢያ አሳውቀዋል።

በሌላ በኩል በደሴ እና ኮምቦልቻ እንዲሁም በሰሜን ሸዋ የተለያዩ ከተሞች ሸዋሮቢት ፣ አጣየ ፣ ደብረሲና ወደቀደመው መደበኛ እንቅስቃሴ ለመመለስ እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
ፊንላንድ 4.1 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ አደርጋለሁ ብላለች።

ፊንላንድ በኢትዮጵያ 🇪🇹 ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ወገኖች ለህይወት አድን የሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ 4.1 ሚሊዮን ዩሮ ለዓለም የምግብ ፕሮግራም-ኢትዮጵያ እንደምትሰጥ አሳውቃለች።

ከዚህም ባለፈ ፊንላንድ በኢትዮጵያ የድርጅቱን የትምህርት ቤት የምግብ ፕሮግራም ለመደገፍ የ1 ሚሊዮን ዩሮ ድጋፍ እንደምትሰጥ ገልፃለች።

@tikvahethiopia
ጋዜጠኞቹ ታሰሩ።

የኢትዮጵየ ፌደራል ፖሊስ በህ/ተ/ም/ቤት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀው " ሸኔ " በዓለም አቀፍ ደረጃ አስተዋውቀዋል ያላቸውን የአሶሽየትድ ፕረስ ጋዜጠኞችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት ተጠርጣሪዎች፦
- አሚር አማን፣
- ቶማስ እንግዳ እና አዲሱ ሙሉነህ ናቸው።

@tikvahethiopia
#UNESCO #WHO

" ... ድርጅቶቹ ያለአድሎ ኃላፊነታቸውን ሊወጡና የህወሃት ቡድን የፈጸመውን ውድመት በይፋ ማውገዝ ይጠበቅባቸው ነበር " - አቶ ዮሴፍ ካሳዬ

ዛሬ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮሴፍ ካሳዬ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተጠሪ ከሆኑት ዶ/ር ዮሚኮ ዮኮዝኪ እና የዓለም ጤና ድርጅት ተጠሪ ዶ/ር በርማ ኤች. ሳምቦ ጋር ተወያይተዋል።

በወቅቱም አቶ ዮሴፍ ፥ የህወሓት የሽብር ቡድን የትግራይ ክልልን ጨምሮ በአፋር እና አማራ ክልሎች የባህላዊ ቅርሶች እና የጤና መሰረተ ልማቶች ላይ የፈጸመውን ውድመት ለማውገዝ ድርጅቶቹ ቸልተኝነት ማሳየታቸው ገልጸውላቸዋል።

አቶ ዮሴፍ ፥ " ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ንብረቶች ላይ የደረሰው ውድመት እና የንብረት ዘረፋ ከፍተኛ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው " ያሉ ሲሆን " የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጉዳዩን በቸልታ ማለፉ ህወሃት በተግባሩ እንዲገፋበት አበረታቶታል " ብለዋል።

ኢትዮጵያ እንደ ተመድ መስራች አባልነቷ ከሁሉም የተመድ ድርጅቶች ጋር የረጅም ጊዜ ግንኙነት እንዳላት አንስተው፣ ድርጅቶቹም ያለአድሎ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡና የህወሃት ቡድን የፈጸመውን ውድመት በይፋ ማውገዝ ይጠበቅባቸው እንደነበረ አጽንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

የስራ ኃላፊዎቹ በበኩላቸው ከዋና ዳይሬክተሩ ጋር ስላደረጉት ውይይት ምስጋናቸውን ገልፀው፣ ያላቸውን ኃላፊነት ግምት ውስጥ ባስገባ መልኩ የኢትዮጵያን ጉዳይ በአንክሮ ለመመልከት ቃል መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA : አሜሪካ በድሮን ጥቃት በካቡል ለገደለቻቸው ንፁሃን አፍጋነስታውያን ዘመዶች ካሳ እከፍላለሁ ብላለች። ከጥቂት ወራት በፊት ካቡል የአሜሪካ ጦር በድሮን ጥቃት ንፁሃንን መገድሉ፤ በኃላ እርምጃው በስህተት የተፈፀመ እንደሆነ መግለፁ ፤ ይቅርታም መጠየቁ አይዘነጋም። በወቅቱ አሜሪካ ጨቅላ ህፃናትን ጨምሮ አጠቃላይ 10 ሰዎችን ነበር የገደለችው። አሜሪካ ለገደለችው 10 ሰዎች ዘመዶች የገንዘብ ካሳ…
" አደጋውን ያደረሱት የሠራዊቱ አባላት አይቀጡም " - ፔንታገን

ባለፈው ነሃሴ ወር በአፍጋኒስታን በአሜሪካ ድሮን ለተገደሉ 10 ሰላማዊ ሰዎች የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር፣ ፔንታገን አደጋውን ያደረሱትን የሠራዊቱን አባላት እንደማይቀጣ አስታወቀ፡፡

ከዚህ ውሳኔ የተደረሰው የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን ከሁለት የበላይ አዛዦች የቀረበላቸውን አስተያየት ካጸደቁ በኋላ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የፔንታገን ቃል አቀባይ ጆርን ከርቢ ለቪኦኤ ለቀረበላቸው ጥያቄ እንደተናገሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ በጉዳይ ላይ ተጨማሪ የተጠያቂነት ምርመራ እንደማይፈቅዱ ማስታወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

ፔንታገን ገለልተኛ መርማሪ መድቦ ሁኔታውን ካጣራ በኋላ እኤአ ነሀሴ 29 የተፈጸመው አደጋ “አስዛኝ ስህተት ነው” ብሏል፡፡

“ የተፈጸመው ስህተት የተሳሳተ መረጃን አምኖ ከመቀበል እንጂ ከንዝህላልነት ወንጀል የተከሰተ ነው ብሎ እንደማያምንም ” ፔንታገን አስታውቋል፡፡

በወቅቱ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ከሀሚድ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ 13 አሜሪካውያንን ጨምሮ 170 የአፍጋን ሰዎችን በገደለበት ማግስት በተካሄደ የድሮን ጥቃት ሰባት ህጻናትን ጨምሮ 10 ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል፡፡ ~ ቪኦኤ

@tikvahethiopia
#UAE

ዩኤኢ የሪፐር ድሮኖች እንዲሁም የተዋጊ ጄቶችን ግዢ ልትተወው ነው ?

የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) ከ23 ቢሊዮን ዶላር በላይ በሆነ ገንዘብ አሜሪካን ሰራሽ ኤፍ-35 ተዋጊ ጄቶችን ፣ ሪፐር ድሮኖችንና ሌሎች እጅግ የዘመኑ ጥይቶችን ለመግዛት ያላትን ስምምነት ልትተወው መሆኑን ዎል ስትሪት ጆርናል ዛሬ ዘግቧል።

የባህረ ሰላጤዋ የአሜሪካ አጋር የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (UAE) የአሜሪካ የደህንነት መስፈርቶች በጣም ከባድ ናቸው የሚል ቅሬታ ማቅረቧን ስማቸው ያልተገለፀ የአሜሪካ ባለስልጣናትን ዋቢ በማድረግ ዎል ስትሪት ጆርናል አስነብቧል።

ጉዳዩን በተመለከተ የኤፍ-35 ኮንትራክተር ሎክሄድ ማርቲን ኮርፕ (LMT.N)፣ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያቤት እንዲሁም የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ወዲያው ምላሽ አልሰጡም።

ሮይተርስ ፥ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቴስ 50 ኤፍ-35 ጄቶች እና እስከ 18 ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) ለመግዛት ከአሜሪካ ጋር ስምምነት መፈራረማቸውን ጉዳዩን ከሚያውቁ ሰዎች በጥር ወር መስማቱን ገልጿል።

ለአሜሪካ በጣም ቅርብ ከሆኑ የመካከለኛው ምስራቅ አጋሮች አንዷ የሆነችው የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ (UAE) በሎክሄድ ማርቲን የተሰሩትን ኤፍ-35 የጦር ጄቶች ለመግዛት ፍላጎቷን ስትገልጽ ነበር ፤ በተለይ በ2020 ከእስራኤል ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መመስረቷ ኤፍ-35 የጦር ጄቶችን በእጇ እንድታስገባ እንደሚያግዛት ሲነገር ነበር።

እስራኤል በመካከለኛው ምስራቅ ብቸኛ የኤፍ- 35 የጦር ጄቶች ተጠቃሚ ናት።

@tikvahethiopia
" የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት ያደርገዋል የተባለው ስብሰባ የተቋሙን ገለልተኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ነው " - የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት በመጪው አርብ ያደርገዋል የተባለው ስብሰባ የተቋሙን ገለልተኝነት በጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለፀ፡፡

በምክር ቤቱ የተወከሉ በርካታ የአፍሪካ አገራት እያሉ በስብሰባው የሚካፈል አንዳችም የአፍሪካ አገር አለመኖሩ የውጭ ጣልቃ ገብነቱ በኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ላይ የተቃጣ መሆኑን ያሳያል ብሏል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ እንዳሉት እንደተባለው በትግራይ ውስጥ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቢፈፀም እንኳ መንግስት አለ የተባለውን ችግር በማጣራት እና የማስተካከያ እርምጃ በመውሰድ ላይ ባለበት ሁኔታ ስብሰባው መደረግ አልነበረበትም፡፡

ስብሰባው የተወሰኑ መንግስታትን ፍላጎት ለማስፈፀም የሚካሄድ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው ተቋሙም በነዚህ መንግስታት ተፅዕኖ ስር ወድቋል ነው ያሉት፡፡

አቶ ከበደ ዴሲሳ ፥ "የተመድ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤት አሸባሪው ህወሓት በአማራና በአፋር ክልሎች የፈፀማቸውን አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በዝምታ አልፏቸዋል " ብለዋል።

በተጨማሪም " የዓለም የጤና ድርጅት እና ዩኔስኮም በተጠቀሱት ክልሎች በርካታ የጤና ተቋማት እና ትምህርት ቤቶች እንዲሁም የዓለም መካነ ቅርሶች ሲወድሙ ድርጊቱን በማውገዝ ፈንታ በዝምታ ማለፍን መርጠዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የነዚህን ተቋማት መርህን ያልተከተለ አሰራር እና አቋም በጥብቅ ትቃወማለች ሲሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ከበደ ዴሲሳ መናገራቸውን ኢብኮ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት እንደገና ያልተዘጋጁ የጤና ስርዓቶችን ሊያሽመደምድ ይችላል " - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

አዲሱ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ #አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።

እስካሁን አሚክሮን በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል።

ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በሰጡት መግለጫ ፤ምናልባት እስካሁን ያልታወቁ በሌሎች አገራት ውስጥ ሊኖር ይችላል ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ልውጡን ዝርያ ለመጋፈጥ በቂ ስራ አለመሰራቱ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ " በእርግጥ እስካሁን ድረስ ይህ ቫይረስ የጋረጠውን አደጋ አቅልለን እንደምንመለከተው ተረድተናል ። ምንም እንኳን ኦሚክሮን ብዙም የከፋ በሽታ ባያመጣም፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት እንደገና ያልተዘጋጁ የጤና ስርዓቶችን ሊያሽመደምድ ይችላል" ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ በመግለጫቸው ላይ አንዳንድ ሃገራት ለኦሚክሮን ምላሽ ለመስጠት የክትባት መርሃ ግብራቸውን ያጠናከሩ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ ስለ ክትባት ኢ-ፍትሃዊነት ያላቸውን ስጋት በድጋሜ ማንፀባረቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Omicron

UK ከአዲሱ ኦሚክሮን የኮቪድ ተህዋሲ ዝርያ ጋር በተያያዘ በ11 የአፍሪካ አገራት ላይ ጥላ የነበረውን የጉዞ ዕቀባ አንስታለች።

የጉዞ እቀባ የተነሳላቸው ፦
- አንጎላ፣
- ቦትስዋና፣
- ኢስዋቲኒ፣
- ሌሴቶ፣
- ማላዊ፣
- ሞዛምቢክ፣
- ናሚቢያ፣
- ናይጄሪያ፣
- ደቡብ አፍሪካ፣
- ዛምቢያ እና ዚምባብዌ ናቸው፡፡

አገራቱ በUK የጎዞ ዕቀባ የተጣለባቸው ባለፈው ኅዳር ወር የኦሚክሮን ተህዋሲ ዝርያ ከዚሁ ደቡባዊ አፍሪካ አካባቢ መገኘቱን ተከትሎ ነበር፡፡

የUK የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ሳጂድ ጃቪድ ፥ ዕቀባውን ማንሳት ያስፈለገው ተህዋሲው አሁን በስፋት በሌሎች ቦታዎችም መሰራጨቱ ስለተረጋገጠ በነዚህ አገራት ላይ ጫና አድርጎ መቆየቱ ትርጉም ስለሌለው ነው ብለዋል።

ለወረርሽኝ ተጋላጭ አደገኛ አካባቢ በሚል ከተዘረዘሩ አገራት ወደ UK የሚገቡ ተጓዦች ለ10 ቀናት ራሳቸውን ለይተው መንግሥት ባዘጋጃቸው ሆቴሎች መቆየት ይኖባቸዋል፡፡

ወጪውን የሚችሉትም ተጓዦቹ እንደሚሆኑ የUK ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ ያስነበበው ቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia
#Omicron

ኦሚክሮን በ3 የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ውስጥ መገኘቱ ተረጋግጧል።

አዲሱ የኮሮና ቫይረስ ልውጥ ኦሚክሮን #ኬንያን ጨምሮ በ3 የምስራቅ አፍሪካ ሃገራት መገኘቱ ተረጋገጠ፡፡

ኬንያ ቫይረሱን መንገደኞች ናቸው ባለቻቸው ሶስት ሰዎች ላይ መገኘቱን ማረጋገጧን አስታውቃለች፡፡

ሩዋንዳም ስድስት ሰዎች በአዲሱ ቫይረስ መያዛቸውን ማረጋገጧን አስታውቃለች፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ከየትኛውም የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች የበለጠ ተዛማችነት አለው ያለለት ቫይረሱ በኡጋንዳ እንደተገኘ ሪፖርት ተደርጎ ነበር።

ምንጭ፦ አል ዓይን

@tikvahethiopia