TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት እንደገና ያልተዘጋጁ የጤና ስርዓቶችን ሊያሽመደምድ ይችላል " - ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም

አዲሱ ልውጥ የኮሮና ቫይረስ #አሚክሮን በዓለም ላይ ታይቶ በማይታወቅ ፍጥነት እየተሰራጨ ነው ሲል የዓለም ጤና ድርጅት አስጠነቀቀ።

እስካሁን አሚክሮን በ77 አገራት ውስጥ መኖሩ ተረጋግጧል።

ነገር ግን የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በሰጡት መግለጫ ፤ምናልባት እስካሁን ያልታወቁ በሌሎች አገራት ውስጥ ሊኖር ይችላል ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ልውጡን ዝርያ ለመጋፈጥ በቂ ስራ አለመሰራቱ እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ ፥ " በእርግጥ እስካሁን ድረስ ይህ ቫይረስ የጋረጠውን አደጋ አቅልለን እንደምንመለከተው ተረድተናል ። ምንም እንኳን ኦሚክሮን ብዙም የከፋ በሽታ ባያመጣም፤ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ብዛት እንደገና ያልተዘጋጁ የጤና ስርዓቶችን ሊያሽመደምድ ይችላል" ብለዋል።

ዶ/ር ቴድሮስ በመግለጫቸው ላይ አንዳንድ ሃገራት ለኦሚክሮን ምላሽ ለመስጠት የክትባት መርሃ ግብራቸውን ያጠናከሩ ሲሆን ከዚህም ጋር ተያይዞ ስለ ክትባት ኢ-ፍትሃዊነት ያላቸውን ስጋት በድጋሜ ማንፀባረቃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia