TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#EMMPA

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማህበር ከሰሞኑ የተወሰኑ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች፦
- የተዛቡ፣
- ትክክለኛ የጋዜጠኝነት መርህን ያልተከተሉ፣
- የአገር ሉዓላዊነትና የህዝቦችን አንድነት አደጋ ውስጥ የሚጥሉ ብሎም የፖለቲካዊ ውግንና ያላቸውን ዘገባዎች ማሰራጨታቸውን አጥብቆ ኮነነ።

ማህበሩ የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳይ የሰሩትን ዘገባ አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

በዚህ መግለጫው ሰሞኑን አዲስ አበባን እና ዙሪያዋን በተመለከተ የተሰራጩ ዘገባዎችን ትክክለኛነትና ሚዛናዊነት ለማጣራት ጥረት ማድረጉን ገልጿል።

ለዘገባ ከተንቀሳቀሱና በየአካባቢው ከሚኖሩ አባሎቹ ብሎም ከነዋሪዎች ባገኘነው መረጃ መሰረት እስካሁን ድረስ አዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙት አካባቢዎች ሁሉ በተለመደው እንቅስቃሴያቸው ላይ ይገኛሉ ብሏል።

ማህበሩ ከሰሞኑ ዓለምአቀፍ ሚዲያዎች የተዛቡ እና ፖለቲካዊ ውግንና ያላቸውን ዘገባዎች ማሰራጨታቸውን አጥብቆ የኮነነ ሲሆን በእንደዚህ ያሉ ሙያዊ መርሆን ባልተከተሉ ዘገባዎች እየተሳተፉ ያሉ ጋዜጠኞች ጋዜጠኝነታቸውን በሙያዊ አስተምህሮው መሰረት እንዲፈፅሙ ጠይቋል።

በተጨማሪ መቀመጫቸውን በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ ዓለም ያደረጉና ስለኢትዮጵያ የሚዘግቡ የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ባለሙያዎች ከእንደዚህ አይነት አዘጋገብ እንዲወጡ አጥብቆ አሳስቧል።

የኢትዮጵያ መንግስትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላትም የየትኛውም መገናኛ ብዙኃን ዘጋቢዎች ተገቢውን መረጃ እንዲያገኙና በተለያዩ አካባቢዎች ተዘዋውረው እውነተኛ መረጃ ለህዝብ ማቅረብ እንዲችሉ አስፈላጊውን ትብብር ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስቧል።

የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃንም ፈጣን፣ ወቅታዊ፣ ትክክለኛና ሚዛናዊ መረጃዎችን እንዲያቀርቡ መክሯል።

*ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
ዕለታዊ የኮቪድ-19 ሪፖርት #Ethiopia

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 11 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 3,962 የላብራቶሪ ምርመራ 148 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 421 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#EHRC

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተለያዩ ከተሞች ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በመዋል ላይ የሚገኙ ሰዎች ሁኔታና የአያያዝ ሂደት ያሳስበኛል አለ።

ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀበት ከጥቅምት 23/2014 ዓ/ም ጀምሮ ሰዎች ከስራ ቦታቸው፣ ከመኖሪያ ቤታቸው እና ከመንገድ ላይ ጭምር በቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ የከተማዋ ፖሊስ ጣቢያዎች ተይዘው እንደሚገኙ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ምንም እንኳን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ "ከሽብር ቡድኖች ጋር ይተባበራሉ ተብለው ምክንያታዊ በሆነ መልኩ የተጠረጠሩ ሰዎችን" ይዞ የማቆየት ስልጣን ለህግ አስከባሪ አካላት ቢሰጥም ፣ኢሰመኮ አደረኩት ባለው ክትትል እንዳረጋገጠው እስሩ ማንነት/ብሄርን መሰረት ባደረገ መልኩ በሚመስል ሁኔታ መከናወኑን በአንዳንድ ፖሊስ ጣቢያዎች የቤተሰብ ጥየቃ፣ ልብስ እና ስንቅ ማቀበል መከልከሉ እና እስሩ ህፃናት ልጆች ያሏቸው እናቶች እና አረጋዊያንን ያካተተ መሆኑ በእጅጉ እንደሚያሳስበው ገልጿል።

ኢሰመኮ የህግ አስከባሪ አካላት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁንና መመሪያዎቹን በስራ ላይ ሲያውሉ እና ሲያሰፈፅሙ የህጋዊነት ፣ የጥብቅ አስፈላጊነትና ተመጣጣኝ እንዲሁም ከመድልዎ ነፃ መሆን የሚሉትን የሰብዓዊ መብት መርሆዎችን ባከበረ መልኩ ሊሆን ይገባል ብሏል።

የህግ አስከባሪ አካላት በማንኛውም ሁኔታ ሊገደቡ የማይችሉ ሰብዓዊ መብቶችን የማክበርና የማስከበር፣ ተግባራቶቻቸውም በከፍተኛ የሙያ ስነምግባር በመመራት የማከናወን ኃላፊነት አለባቸውም ሲል ገልጿል።

በተለይ አረጋውያን፣ የህፃናት ልጆች እናቶች እንዲሁም የህክምና ክትትል የሚያስፈልጋቸው ሰዎችን ጨምሮ ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎችን አያያዝ በተመለከተ ፈጣንና ልዩ የማጣራት አሰራር መዘርጋት እንደሚያስፈልግ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia
የ12ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ተጀመረ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው ኅዳር 02/2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

በዛሬ ጥዋት የፈተና መርሃ ግብር መሰረት የእንግሊዘኛ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተናው በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ፈተናው በሁለተኛ ዙር ለመስጠት እቅድ ተይዟል።

በ131 የፈተና ጣቢያዎች በጠቅላላው 36 ሺህ 340 ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተናው በመጀመሪያ ዙር አይቀመጡም።

ዛሬ ለሀገር አቀፍ ፈተና የተቀመጡ ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና እንዲሆን እየተመኘን ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ከፈተናው ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠነቀቁ አደራ እንላለን።

ለሚመለከተው አካል ፦ ፈተናው ገና ከመጀመሩ ከፈተና ክፍል ውስጥ የተነሱ የፈተናውን ጥያቄ የያዙ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ ደግሞ ቴሌግራም ላይ እየተዘዋወረ መሆኑን መመልከት ችለናል።

ይህ ትውልድ ገዳይ አገደኛ ድርጊት ፌስቡክ ላይም እየተፈፀመ ነው፤ ድርጊቱ ለዓመታት የለፉ ተማሪዎች ድካም ከንቱ የሚያስቀር በመሆኑ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው (ሶሻል ሚዲያውን መዝጋት)

ለአክቲቪስቶች እና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ፦ ተማሪዎች የዓመታት ድካማቸው ከንቱ እንዲሆን ለማድረግ ፎቶዎችን እየለጠፋችሁ የምትገኙ አካላት በተለይ አክቲቪስት ነን ምትሉ ምንም የማያውቁ ተማሪዎችን ህይወት ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት የግል አላማን ለማሳካት ሚደረግ ተግባር ፍፁም ስነምግባር የጎደለ ተግባር መሆኑን በመረዳት ከድርጊታችሁ ልትቆጠቡ ይገባል።

የፖለቲካ ጉዳይን ከተማሪዎች ህይወት ጋር በማገናኘት ትውልድ አትግደሉ።

አጠቃላይ የማህበራዊ ሚዲያ ጉዳይ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል።

#ቲክቫህ

@tikvahethiopia
የሸካ ዞን መቀመጫ ቴፒ እንዲሆን ተወሰነ።

ጥቅምት 27/2014 ዓ.ም የሸካ ዞን ም/ቤት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የዞኑ ዋና መቀመጫ #ቴፒ_ከተማ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወሰኔ አሳልፏል።

ምክር ቤቱ ቅዳሜ ባካሄደው 9ኛ የሥራ ዘመን 4ኛ ዙር 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ የአሠራር ቅልጥፍናና የአገልግሎት አሰጣጥን ለማሻሻል የዞኑን ዋና ከተማ ከነበረበት ማሻ ከተማ ወደ ቴፒ ከተማ ለማዛወር የቀረበውን የውሣኔ አጀንዳ በመወያየት የዞኑ ዋና ከተማ ቴፒ እንዲሆን በሙሉ ድምፅ ወስኗል።

ውሳኔው በተሻሻለው የደ/ብ/ብ/ህ/ክልል መንግስት ህገ መንግስት አንቀፅ 81 ንኡስ አንቀፅ 2 ላይ የዞን ምክር ቤቶች በዞኑ ውስጥ የበላይ የፖለቲካ ስልጣን ባለቤቶች ናቸው ተብሎ በተገለፀው መሠረት በጉዳዩ ላይ በመወያየት ካለው ህዝባዊ ጠቀሜታ እና ፋይዳ አንጻር የዞኑ ማዕከል አሁን ካለበት ማሻ ከተማ ወደ ቴፒ ከተማ እንዲዛወር በሙሉ ድምፅ ውሳኔ መተላለፉ ተገልጿል።

መረጃው የደረሰን ከሸካ ዞን ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የ12ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ተጀመረ። የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ መሰጠት ተጀምሯል። ፈተናው ኅዳር 02/2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል። በዛሬ ጥዋት የፈተና መርሃ ግብር መሰረት የእንግሊዘኛ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል። በጸጥታ ችግር ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተናው በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ፈተናው በሁለተኛ ዙር ለመስጠት እቅድ ተይዟል። በ131 የፈተና ጣቢያዎች በጠቅላላው 36…
#MoE

የትምህርት ሚኒስተር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እና የአ/አ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ኮከበ ጽበሀ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት በመገኝት የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና አጀማመር ተመለክተዋል።

የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከትግራይ ክልል እና የፀጥታ ችግር ካለባቸው የተለያዩ አካባቢዎች በስተቀር በሁሉም ክልል እና አካባቢዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል።

ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ ትምህርት ቴሌቪዥን (ጋዜጠኛ ነፃነት)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Mekelle የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሐፊ እና የአስቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ እርዳታ አስተባባሪ የሆኑት ማርቲን ግሪፊትስ እና በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ዛሬ የትግራይ ክልል መዲና መቐለ መግባታቸውን ሮይተርስ ከአንድ የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊ ምንጭ እና ጉዳዩን ከሚያውቅ አንድ ሰው መስማቱን ዘግቧል። በኢትዮጵያ የሚገኘው የUN…
#Olusegun_Obasanjo

ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መፍትሄ አፈላላጊው ሰው - ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ !

በአፍሪካ ህብረት (AU) የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ከተሾሙ በኃላ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲፈታና ሰላም እንዲወርድ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ።

ኦባሳንጆ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ሲያደርጉ ነበር፤ ከኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከሌሎች ኢትዮጵያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል።

ኦባሳንጆ በሰሜን ጦርነት ጉዳይ ከአሜሪካ እና አውሮፓ ከፍተኛ የመንግሥት ኃላፊዎችም ጋር ውይይት ሲያደርጉ ቆይተዋል።

የአፍሪካ ህብረት የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት እንዲፈታ በግጭቱ እየተሳተፉ ካሉ ኃይሎች ጋር እየተወያየ አንደሆነ መግለፁ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ መንግስት በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛው ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ ይዘውት የሚመጡትን የመፍትሔ ሐሳብ እየጠበቀ ነው።

ያንብቡ 👇
https://telegra.ph/Olusegun-Obasanjo-11-08
TIKVAH-ETHIOPIA
#Audio : ዛሬ አ/አ በነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ታዳሚው እነ CNN፣ አልጀዚራ፣ BBC ፣ ሮይተርስ በመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ላይ እጅግ ኃይለኛ ትችት እና ወቀሳን ሰንዝሯል። የሚዲያ ተቋማቱ እጃቸውን ከኢትዮጵያና ከህዝቧ ላይ እንዲሰበስቡ ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃዎችን እንዲሁም ውሸቶችን ለዓለም ህዝብ ከማሰራጨት እንዲታቀቡ ሰልፈኞች አሳስበዋል። ህወሓት /TPLF/ አሸባሪ ድርጅት ነው ያሉት…
#ETHIOPIA

ከሰሞኑን የተለያዩ የውጭ ሀገራት ሚዲያዎች ተናበው ሚሰሩ በሚመስል መልኩ ኢትዮጵያን የተመለከተ በርካታ ዘገባዎችን አውጥተዋል።

የሚዲያ ተቋማቱ ድርጊት ኢትዮጵያውያንን ክፉኛ አስቆጥቷል።

ለአብነት በአራት ቀናት ብቻ CNN፣ BBC ፣ አልጀዚራ ፣ ፍራንስ 24 ፣ አሶሼትድ ፕሬስ በድምሩ 72 ዜናዎችን በኢትዮጵያ ጉዳይ አውጥተዋል (ይህን ቁጥራዊ መረጃ ያጋራው የቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ የሚሰራው ጋዜጠኛ ሰለሞን ካሳ ነው)

ከ72ቱ ዜናዎች 21ዱን CNN ፣ 13ቱን BBC ፣ 11ዱን አልጀዚራ ፣ 19ኙን ፍራንስ 24 እና 8ቱን አሶሼትድ ፕሬስ ነው የሰሩት።

አብዛኛዎቹ ዜናዎች ኢትዮጵያ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ሀገሪቱን ለቀው እንዲወጡ ለማሸበር የተሞከረበት ነው ፤ ከዚህ ባለፈም ኢትዮጵያን ለመበትን የሀሰት ትርክት እና የስነልቦና ጫናና አለመረጋጋት በህዝቡ ዘንድ ለመፍጠር ረጅም መንገድ የተሄደበት መሆኑ አመላካች እንደሆነ ያሳያል።

የሚዲያዎቹ ድርጊት ከሙያዊ ስነምግባር ያፈነገጠና አድሏዊ የሆነ በሀገር ውስጥ ያለው ነዋሪ ምን መአት መጣ ብሎ እንዲጨነቅ እና እንዲሸበር ፣ አካባቢውን ቄየውን ለቆ እንዲሸሽ ለማድረግ የታለመበት ይመስል ነበር።

የሚዲያዎቹ ድርጊት ያስቆጣቸው ነዋሪዎች ትላንት አዲስ አበባ ከተማ በነበረ ሰልፍ ላይ ሆን ተብሎ ህዝብ ለማሸበር እና ለማስደንገጥ የሚያደርጉትን ድርጊት እንዲያቆሙ፤ እጃቸውን ከኢትዮጵያ ላይ እንዲሰበስቡ አሳስበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Olusegun_Obasanjo ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መፍትሄ አፈላላጊው ሰው - ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ ! በአፍሪካ ህብረት (AU) የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ከተሾሙ በኃላ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲፈታና ሰላም እንዲወርድ የተለያዩ ስራዎችን እየሰሩ ይገኛሉ። ኦባሳንጆ በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ አካላት ጋር ውይይት ሲያደርጉ ነበር፤ ከኢትዮጵያ ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም…
#OlusegunObasanjo

የአፍሪካ ህብረት የጸጥታው ምክር ቤት በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በህብረቱ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ ገለጻ እንደተደረገለት አል ዐይን በድረገፁ አስነብቧል።

ህብረቱ ዛሬ ጥቅምት 29 ቀን 2014 ዓ/ም አስቸኳይ ዝግ ስብሰባ አካሂዷል፡፡ ስብሰባው በበይነ መረብ የተካሄደ እንደነበር ተገልጿል።

በስብሰባው ላይ ፦

• የህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች፣ የሰላም እና ደህንነት ጉዳዮች ኮሚሽነር አምባሳደር ባንኮሌ አዲዎዬ፣

• የህብረቱ የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴገን ኦባሳንጆ፣

• በአፍሪካ ህብረት የግብጽ ቋሚ ተወካይ መሃመድ ጋድ እና በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ ተሳትፈዋል፡፡

ስብሰባው የተካሄደው በወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ለመምክርና የአፍሪካ ህብረት የምስራቅ አፍሪካ ተወካይ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴገን ኦባሳንጆን ገለጻ ለማድመጥ ነበር፡፡

በአፍሪካ ህብረት የኢትዮጵያ ተወካይ አምባሳደር ተስፋዬ ይልማ በተሳተፉበት በዚህ ስብሰባ ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ከመከረና የኦባሳንጆን ገለጻ ካደመጠ በኋላ ያለው ወይም ያስቀመጠው ቀጣይ አቅጣጫ እንዳለ የታወቀ ነገር የለም፡፡

ነገር ግን ም/ ቤቱ የተሰበሰበበትን ጉዳይ የተመለከተ መግለጫን እንደሚያወጣ መረጃ እንዳለው አል ዓይን ዘግቧል።

@tikvahethiopia
'' ፈተናውም በማንም፤ በምንም፤ በየትም አልተሰረቀም '' - ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

የትምህርት ሚኒስትሩ ር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ዛሬ መሰጠት የተጀመረው የ2013 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ቲክቫህ መግለጫውን ተከታትሏል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ በመግለጫቸው ከሞላ ጎደል ፈተናው በሰላማዊ መንገድ መከናወኑን ገልጸዋል። ''ፈተናውም በማንም በምንም በየትም አልተሰረቀም'' ሲሉ ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት 2 ተማሪዎች በኦሮሚያ ክልል 2 ተማሪዎች በደቡብ ክልል በስልካቸው ፎቶ አንስተው ''ኤሌክትሮኒክ ኩረጃ'' ሊፈጽሙ ሲሉ መያዛቸውን ጠቅሰዋል።

ተማሪዎቹ ፈተና ክፍል ከገቡ በኋላ ፈተናውን በፎቶ አንስተው ሲላላኩ መያዛቸው ነው የተጠቀሰው። ይህም ተማሪዎች ለፈተና ከገቡ በኋላ የተለቀቀ በመሆኑ ፈተናው ተሰርቋል ሊባል አይችልም ተብሏል።

ፈተናው በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ከፌደራል ጀምሮ እስከታች ባሉ የኮማንድ ፖስቱ አባላት ያደረጉት አስተዋጽኦ የተሻለ መሆኑን ጠቅሰዋል። በሚቀጥሉት ሦስት ቀናትም ትብብሩ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ተማሪዎች የሞባይል፣ የስማርት ሰዓትም ሆነ ሌሎች ዲጂታል ኤሌክትሪክ መሳሪያዎችን ይዞ መገኘት እንደማይፈቀድ አጽንኦት ተሰጥቶ ተገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#OlusegunObasanjo

በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ወደ አማራ ክልል አፋር ክልል ይጓዛሉ።

ኦባሳንጆ ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም።

ዛሬ ወደ ባህር ዳር እና ሰመራ በማቅናት ከክልሎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እያደረጉት ስላለው የሰላም ጥረት ይወያያሉ ተብሏል፤ እስካሁን ስለጉዟቸው ዝርዝር ነገር የለም።

በሌላ በኩል ኦባሳንጆ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት ለመፍታት በሚያደርጉት ጥረት ተልዕኳቸውን አልቀበልም ያለ አካል እንደሌለ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግስት ይሁን በትግራይ ክልል ያሉ አካላት እሳቸውን አልቀበልም ያለ እንደሌለ አሳውቀዋል።

ኦባሳንጆ ፥ "የአፍሪካ ሕብረት ሰላም ለማምጣት፣ ንግግርን ለማስጀመር እና ደኅንነትን ለማስጠበቅ ልዩ መልዕክተኛ መሰየሙን ሁሉም ወገን በበጎ ነው የተቀበሉት" ብለዋል።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ፥ "የጠየቅኩትን ትኩረት ሰጥተውኛል። በሚገባው ልክ አስተናግደውኛል" ሲሉ ስለተደረገላቸው መልካም አቀባበል ገልጸዋል።

ትግራይ ክልል ሲሄዱም ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ኤርፖርት ድረስ ሄደው እንደተቀበሏቸው ገልፀዋል።

ሁለቱም ወገኖች የአፍሪካ ሕብረት ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆን "አልተቀበሉንም የሚለው ሐሳብ ፍጹም ስህተት ነው" መሆኑን አሳውቀዋል።

አሁን ላይ የድርድሩ ሂደት ምን ላይ እንዳለና በቀጣይ የሚፈጠረውን ጉዳይ በተመለከተ ኦባሳንጆ ፤ "አሁን ገና የመጀመሪያው ምዕራፍ ላይ ነኝ። ድርድሩ ወዴት እንደሚሄድ የምናገርበት ጊዜ አይደለም" ብለዋል።

አሁን ያሉበት ደረጃ በተደራዳሪ ወገኖች ዘንድ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ምን እንደሆነ የመለየት እንደሆነም ለቢቢሲ ፎከስ ኦን አፍሪካ አስረድተዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#OlusegunObasanjo በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም እና ሰላም እንዲወርድ መፍትሄ እያፈላለጉ ያሉት ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ ዛሬ ወደ አማራ ክልል አፋር ክልል ይጓዛሉ። ኦባሳንጆ ከቀናት በፊት ወደ ትግራይ ክልል መቐለ ተጉዘው እንደነበር አይዘነጋም። ዛሬ ወደ ባህር ዳር እና ሰመራ በማቅናት ከክልሎቹ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር እያደረጉት ስላለው የሰላም ጥረት ይወያያሉ ተብሏል፤ እስካሁን ስለጉዟቸው…
#OlusegunObasanjo

ትናንት በወቅታዊ የአፍሪካ የጸጥታ ሁኔታዎች ላይ የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ስበስባ ተቀምጦ ነበር።

በዚህ ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦሊሴንጉን ኦባሳንጆ በኢትዮጵያ በመደረግ ላይ ስላሉ የሰላም ጥረቶች ገለጻ አድርገዋል፡፡

በገለጻቸውም በአዲስ አበባ ከጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ ከፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ እንዲሁም ከኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ጋር መነጋገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ውጥረቱን ለማርገብ እና ለቀጣይ ውይይቶች ምቹ መደላድልን ለመፍጠር የሚያስችል ፍሬያማ ንግግር ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት፡፡

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጋር ከተነጋገሩና ወደ ትግራይ እንዲያቀኑ ከተስማሙ በኋላ እሁድ ጥቅምት 28 ቀን 2014 ዓ/ም በመቐለ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካዔልን ጋር ተገናኝተው ውጥረቱን ለማርገብና አመርቂ መፍትሄዎችን ለመፈለግ የሚያስችል ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ እና በሰሜን ያሉ ሁሉም መሪዎች በመካከላቸው ያለው ችግር ፖለቲካዊ እንደሆነና በውይይት ሊፈታ የሚችል ፖለቲካዊ መፍትሄን እንደሚፈልግ በግለሰብ ደረጃ መስማማታቸውንም አስታውቀዋል፡፡

ችግሩ የከፋ ማህበረ ምጣኔ ሃብታዊ እና ሰብዓዊ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን በመጠቆም ዘላቂ እልባት ለመስጠት መፍጠን እንደሚያስፈልግ ኦባሳንጆ ተናግረዋል።

የጸጥታው ምክር ቤት ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁመው ወደ ውይይት እንዲመጡ፣ ያልተቆራረጠ የሰብዓዊ እርዳታዎች አቅርቦት እንዲኖር፣ የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ሁሉን አካታች ብሔራዊ ውይይት በአፋጣኝ እንዲደረግ ግፊት እንዲያደርግና ሁኔታዎችን በአንክሮ እንዲከታተል አሳስበዋል፡፡

Credit : አል ዓይን

@tikvahethiopoa