የ12ኛ ክፍል ፈተና መሰጠት ተጀመረ።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከዛሬ ጥቅምት 29 ጀምሮ መሰጠት ተጀምሯል።

ፈተናው ኅዳር 02/2014 ዓ.ም ይጠናቀቃል።

በዛሬ ጥዋት የፈተና መርሃ ግብር መሰረት የእንግሊዘኛ ፈተና እየተሰጠ ይገኛል።

በጸጥታ ችግር ምክንያት በመጀመሪያው ዙር ፈተናው በማይሰጥባቸው አካባቢዎች ፈተናው በሁለተኛ ዙር ለመስጠት እቅድ ተይዟል።

በ131 የፈተና ጣቢያዎች በጠቅላላው 36 ሺህ 340 ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተናው በመጀመሪያ ዙር አይቀመጡም።

ዛሬ ለሀገር አቀፍ ፈተና የተቀመጡ ተማሪዎች በሙሉ መልካም ፈተና እንዲሆን እየተመኘን ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ከፈተናው ጋር ተያይዞ በማህበራዊ ሚዲያ ከሚሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች እንድትጠነቀቁ አደራ እንላለን።

ለሚመለከተው አካል ፦ ፈተናው ገና ከመጀመሩ ከፈተና ክፍል ውስጥ የተነሱ የፈተናውን ጥያቄ የያዙ ፎቶዎች በማህበራዊ ሚዲያ በተለይ ደግሞ ቴሌግራም ላይ እየተዘዋወረ መሆኑን መመልከት ችለናል።

ይህ ትውልድ ገዳይ አገደኛ ድርጊት ፌስቡክ ላይም እየተፈፀመ ነው፤ ድርጊቱ ለዓመታት የለፉ ተማሪዎች ድካም ከንቱ የሚያስቀር በመሆኑ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ይሰጠው (ሶሻል ሚዲያውን መዝጋት)

ለአክቲቪስቶች እና ማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ፦ ተማሪዎች የዓመታት ድካማቸው ከንቱ እንዲሆን ለማድረግ ፎቶዎችን እየለጠፋችሁ የምትገኙ አካላት በተለይ አክቲቪስት ነን ምትሉ ምንም የማያውቁ ተማሪዎችን ህይወት ከፖለቲካ ጋር በማገናኘት የግል አላማን ለማሳካት ሚደረግ ተግባር ፍፁም ስነምግባር የጎደለ ተግባር መሆኑን በመረዳት ከድርጊታችሁ ልትቆጠቡ ይገባል።

የፖለቲካ ጉዳይን ከተማሪዎች ህይወት ጋር በማገናኘት ትውልድ አትግደሉ።

አጠቃላይ የማህበራዊ ሚዲያ ጉዳይ እጅግ አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል።

#ቲክቫህ

@tikvahethiopia